cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Natnael Mekonnen

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Show more
Advertising posts
175 792Subscribers
-8824 hours
-5737 days
-2 29730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚመራው የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚመራው የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ተጠናክሮ መቀጠሉን ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ገልጿል። ፖሊስ በላከው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከጥር 29 እስከአሁን በቀጠለው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ሥር በዋሉ ተጠርጣሪዎች ላይ 2 ሺህ 7 መቶ 63 የምርመራ መዝገብ ማደራጀቱን አስታውቋል። ፖሊስ ቀደም ሲል በኦፕሬሽኑ የተገኙ ስኬቶችን በየጊዜው እየገመገመ ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ በገባው ቃል መሠረት ያካሄደውን የተቀናጀ ኦፕሬሽን ውጤት በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ፦ 1. በእገታ፣ በዘረፋ እና በተለያዩ የማጭበረበር ወንጀሎች የተሳተፉና የተለያዩ 16 የወንጀል ዓይነቶችን የፈፀሙ በአንድ ቡድን የተደራጁ 12 ተጠረጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን ጉዳዩን አስመልክቶ ፖሊስ የምርመራ ውጤቱን በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፦ 2. የወንጀል ተግባር ሲፈፀምባቸው የተያዙ 20 ተሸከርካሪዎችና ሁለት ሞተር ሳይክሎች፣ 3. 58 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ 509 መሰል ጥይቶች ጋር፡ 4. 67 የተለያዩ ሽጉጦች ከ 427 መሰል ጥይቶች፣ በርካታ የኤፍ ዋን ቦንብ (F1 bomb) ስብርባሪ እና ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎች፣ 5. የተሰረቁ 66 ላፕቶፕ፣ 28 ታብሌት፣ 2 ሺህ 9 መቶ 86 የተለያዩ የሞባይል ስልኮች፣ ለሕገ-ወጥ ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 103 ሲም ካርዶች፣ 6. የተሰረቁ በርካታ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ 7. የተለያዩ ኢንች ያላቸው 23 ቴሌቪዥኖች፣ የኤሌክትሪክ ገመዶች እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ 8. በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ሚሊየን ብር እና 3 ሺህ 5 መቶ የአሜሪካን ዶላርን ጨምሮ የ15 ሀገራት ልዩ ልዩ ገንዘቦች፣ 9. በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የከበሩ ማዕድናት፣ 10. 2 መቶ 8 ሚሊየን ብር ግምት ዋጋ ያላቸው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር የገቡ መድኃኒቶች፣ 11. ለወንጀል መንስኤ የሆኑ 2 ሺህ 4 የሺሻ እቃዎች እና የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆች በተካሄደው ኦፕሬሽን ተይዘው ታዛቢዎች በተገኙበት እንዲቃጠሉ ተደርጓል ብሏል መግለጫው። አሁን ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ መሆኑን የገለፀው ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ የተደራጁ ወንጀሎችን በተቀናጀ ኦፕሬሽን መቆጣጠር የሚያስችል ስምሪት ተጠናክሮ የቀጠለ እና በቀጣይም በሀገራችን የሚካሄዱ ሕዝባዊ፣ መንግስታዊ እና ሀይማኖታዊ ሁነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት አድርጎ የተጠናከረ ጥበቃ ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አረጋግጧል። ኅብረተሰቡም እንደተለመደው ሁሉ ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል። ንብረት የተወሰደባችሁ ግለሰቦች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ ፖሊስ መምሪያ ማስረጃ እያቀረባችሁ ንብረታችሁን እንድትወስዱ ፖሊስ በመግለጫው ያስታውቃል።
Show all...
☝️☝️☝️ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሠጠ መግለጫ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል፡፡
Show all...
Show all...
TikTok · Natnael Mekonnen

Check out Natnael Mekonnen’s video.

በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ለጥፋት ቡድኑ መሳሪያ ሲያቀብሉ የነበሩ ግለሠቦች በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ለጥፋት ቡድኑ መሳሪያ ሲያቀብሉ የነበሩ ግለሠቦች በሠራዊቱ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገለፁት የኮሩ ዘመቻ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ተስፋዬ አስማረ ሠራዊቱ ህዝብና መንግስት የሠጡትን  ተልዕኮዎች ውጤታማ በሆነ አግባብ በመፈፀም ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ከሠሞኑም ሠራዊቱ ከህዝብ ጋር በመተባበር እና መረጃን በመለዋወጥ ለጥፋት ሃይሎች መሳሪያና ተተኳሽ ሲያቀብሉ የነበሩ ፅንፈኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ገልፀዋል። መቶ አለቃ ጥበቡ ግርማ በበኩላቸው ለጠላት ስንቅ እና ትጥቅ የሚያቀብሉ ህዝብን የሚበጠብጡ በገንዘብ ተገዝተው ሃገራቸውን ለመሸጥ የሚሯሯጡ ከሃዲዎችን  በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ተናግረው ወደ ጠላት ሊገባ የነበረ ክላሽ ፣ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ፣የብሬን ጥይት፣ ካዝና ፣ ገንዘብ እና የተለያዩ የመንቀሳቀሻ መታወቂያዎች እንዲሁም የተቀረፁ የመኪና ቁልፎችን አብረው በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ገልፀዋል።
Show all...
የሆቴሎች ኮከብ ደረጃ ምዝና ውጤት ይፋ ተደረገ። የቱሪዝም ሚኒስቴር የዓለም ቱሪዝም ድርጅት ያስቀመጣቸውን አስገዳጅ መስፈርት ላሟሉ 31 ሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ ውጤታቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጏል:: በ2014 እና 2015 ዓ.ም ምዘና ከተደረገላቸው 64 ሆቴሎች መካከል ሰባቱ ባለ 4 ኮኮብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን ዘጠኝ ሆቴሎች ደግሞ የ3 ኮከብ ደረጃን አግኝተዋል:: እንዲሁም አምስት ሆቴሎች የ 2 ኮከብ እና ስምንት ሆቴሎች ባለ 1 ኮኮብነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን ሁለት ሆቴሎች ደግሞ ከደረጃ በታች ሆነዋል። እነዚህ ሆቴሎች በአዲስ አበባ ኦሮምያ ክልል ቢሾፍቱ እና አዳማ ከተሞች የሚገኙ ናቸው:: የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የደረጃ ምደባው ሆቴሎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ብቃት እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ፡፡በቅርበት ካሉ ተፎካካሪ ሀገራት ጋር ያላቸውን አቅም በማሳየት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ገልፀዋል::
Show all...
በኅብረተሰቡ ውስጥ የሴቶች ሚና ብዙ መልክና ገፅ ያለው ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በኅብረተሰቡ ውስጥ የሴቶች ሚና ብዙ መልክና ብዙ ገፅ ያለው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “በዛሬው ውይይት ከተለያየ የማኅበረሰብ ዳራ የተውጣጡ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ ሴቶችን ሀሳብ አዳምጫለሁ” ብለዋል፡፡ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሴቶች ሚና ብዙ መልክ እና ብዙ ገፅ ያለው መሆኑንም በመልዕክታቸው አመላክተዋል።
Show all...
Go to the archive of posts
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!