cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Broadcasting corporation ®

Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media. https://telega.io/c/EBC_TV ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!! https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0

Show more
Advertising posts
11 232Subscribers
-1124 hours
-427 days
-18130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Ads time 👫 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ ! 🎁 አንድ ሰው ሲጋብዙ 3 ብር ይሰራሉ ። እስካሁን የጋበዙት ሰው መጠን: 0 ሰው 🔰 መጋበዣ ሊንክ : https://t.me/hulepay_official_bot?start=r0931284302 ✅ ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ ።
Show all...
የወጣትነት ገፅታን የተላበሰችው የ60 ዓመቷ አርጀንቲናዊት በቁንጅና ውድድር አሸነፈች *** የ60 ዓመቷ ጠበቃና ጋዜጠኛ አሌሃንድራ ማሪሳ ሮድሪጌዝ የሚስ ቦነስ አይረስ የውበት ውድድር አሸናፊ በመሆን ለቀጣዩ የሚስ አርጀንቲና የውበት ውድድር አልፋለች። የሚስ ዩኒቨርስ የቁንጅና ውድድር ከ65 ዓመታት በላይ በትግበራ ላይ የቆየውን የተወዳዳሪዎች የዕድሜ ገደብ ባለፈው ዓመት መገባደጃ ላይ ማንሳቱ ለአሌሃንድራ እና ለብዙዎች በር ከፍቷል። አሌሃንድራ ከብዙ ወጣት ቆነጃጂት ጋር ተወዳድራ የሚስ ቦነስ አይረስ ማዕረግን መያዟ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾች መነጋገሪያ አድርጓታል። የ2024ቷ የቦነስ አይረስ ቆንጆ፥ ውበት በዕድሜ አይገደብም ስትል ለብዙዎች ምሳሌ መሆን እንደምትፈልግ መግለጿንም ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል። በ60 ዓመቷ በ20ዎቹ እና በ30ዎቹ ዕድሜ ያለ ውበት የመላበሷ ምስጢር በሳምንት ለ3 ቀናት ስፖርት መስራት እና እያፈራረቁ መጾም መሆኑን አሌሃንድራ ትናገራለች። ውበት የሚያበቃበት ቀን የለውም የምትለው የ60 ዓመቷ አሌሃንድራ የ2024 የሚስ ዩኒቨርስ አርጀንቲና ዘውድን ለመጫን ቆርጣ መነሳቷንም ትገልጻለች።
Show all...
👍 2
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችንና በልማቱ የተነሱ ነዋሪዎችን ጎበኙ **** በጉብኝት መርኃ ግብሩ ላይ የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። የምክር ቤቱ አባላት በጉብኝታቸው በግንባታ ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፤ በኮሪደር ልማቱ ተነስተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ በሀና ፉሪ እንዲሁም በጉራራ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎችን ጭምር ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሪት ፋይዛ መሀመድ ለምክር ቤቱ አባላት እና ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ፥ ከተማዋን ለማዘመን በተጀመረው የኮሪደር ልማት የመንገድ፣ የመብራት፣ የአረንጓዴ ልማት እና ምቹ የእግረኛ መንገድ መሰረተ ልማቶች እተሰሩ ነው ብለዋል። ስራው በተያዘለት ጊዜና በጥራት እንዲከናወን ለማድረግ ምክር ቤታቸው የጀመረውን የክትትልና የድጋፍ ስራም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሪት ፋይዛ መሀመድ ተናግረዋል። በኮሪደር ልማቱ ለተነሱ ነዋሪዎች ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከውሃ፣ ከመብራትና ከመንገድ መሰረተ ልማቶችን ከማሟላት ባሻገር የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።
Show all...
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማፍራት እየተሰራ ነው ******** በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ ታዳጊዎችን ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በመጪው ክረምት የስልጠና መርሐ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀምሯል፡፡ ስልጠናው ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ያላቸውን ግንዛቤ እንደሚያሳድግ የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ተናግረዋል፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና ቴክኖሎጂ ዕድገት መለኪያ ዘርፍ መሆኑን አስገንዝብል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የምርምር እና ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) በበኩላቸው ስልጠናውን በክልሎች ለማስፋት መታቀዱን አመላክተዋል፡፡ የቴክኖሎጂ አማካሪው ሰለሞን ሙሉጌታ በበኩላቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ የሚሰጥ ስልጠና ታዳጊዎች የዓለምን አዝማሚያ እና ዝንባሌ በቅጡ እንዲረዱ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ በመጪው ክረምት ለ2 ተከታታይ ወራት በሚሰጠው ስልጠና ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 07 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል።
Show all...
ለ82 ቀናት የዓለማችንን ረጅሙን ምርጫ የምታካሂደው ሀገር- ሕንድ ******** በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከዓለማችን ግማሽ ያክሉን የህዝብ ብዛት የያዙ 10 ሀገራት ምርጫ ያካሂዳሉ። ባንግላዴሽ፣ ብራዚል፣ ህንድ፣ አሜሪካ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ እና ሜክሲኮ ዴሞክራሲያቸውን በምርጫ ያሳያሉ። አንዳንዶቹ ምርጫቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ሂደቱን ጀምረውታል። በእነዚህ ምርጫዎች ከ2 ቢልዮን በላይ የሚሆኑ መራጮች ድምጽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። ሕንድ ረጅሙን እና ዴሞክራሲያዊ የተባለውን ምርጫ እያካሄደች ትገኛለች። ሀገሪቱ በአውሮፓውያኑ 1947 ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነጻነቷን ካገኘች በኋላ የመጀመሪያውን ምርጫ ያካሄደችው ከ1951 እስከ 1952 ሲሆን፣ የዘንድሮ ምርጫ ለአሥራ ስምንተኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል። በ1.4 ቢሊዮን ሕዝብ የዓለምን አንደኝነት ከቻይና የተረከበችው ህንድ ከ2 ሺህ 500 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሯትም አስሩ ብቻ ሎክ ሳባ የተባለውን ምክር ቤት 86 በመቶ መቀመጫዎችን ይይዛሉ። የሕንድ ብሔራዊ ኮንግረስ (INC)፣ ጃናታ ዳል (People’s Party)፣ ባራቲያ ጃናታ ፓርቲ (Indian People's Party)፣ የሕንድ ብሔራዊ ኮንግረስ (R)፣ ጃናታ ፓርቲ (People's Party) የተባሉ አምስት ፓርቲዎች በምርጫው ዋነኛ ተፎካካሪዎች ሲሆኑ፣ በታሪክ ምርጫውን በማሸነፍ ብዙ ጊዜ በመምራት የሕንድ ብሔራዊ ኮንግረስን (INC) የሚያክል ፓርቲ የለም። በማተማ ጋንዲ ተመሥርቶ የነጻነት ንቅናቄውን የመራው እና በህዝቡ ከፍተኛ ተቀባይነት የነበረው ይህ ፓርቲ ዘጠኝ ጊዜ በማሸነፍ ሀገሪቱን መርቷል። ላለፉት ሁለት ተከታታይ ምርጫዎች ግን አሁን ሀገሪቱን እየመራ ባለው ጃናታ ዳል (Indian People’s Party) ተሸንፏል።የሕንድ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተፎካካሪ የሆነው የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ፓርቲ ባራቲያ ጃናታ ፓርቲ (Indian People's Party) አምስት ጊዜ፣ ቀሪዎቹ ሦስት ፓርቲዎች አንዳንድ ጊዜ በማሸነፍ ህንድን መርተዋል።
Show all...
"የገቢና የወጪ ንግድ ላይ  የውጭ ባለሀብቶች እንዲሳተፉ መፈቀዱ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ያሻሽለዋል"-የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አረጋ ሹመቴ (ዶ/ር) "መመሪያው የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ከባለቤትነት ድርሻ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል"-የሕግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ *** የውጭ ባለሀብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢና ወጪ ንግድ ላይ በጅምላ እና በችርቻሮ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡ ኢትዮጵያ በምጣኔ ሀብት ታሪኳ የውጭ ኢንቨስተሮችን በተወሰኑ የስራ ዘርፍ ብቻ እንዲሰሩ ፍቃድ ትሰጥ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚህም  ከዓለም ብሎም ከብዙ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ኢኮኖሚዋ ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ነው ማለት የሚያስችል ቢሆንም፤ የተወሰኑ የሚባሉ ማሻሻያዎች ሲደረጉም ነበር፡፡ ከ2002 ዓ.ም በፊት የነበረው የኢንቨስትመንት ደንብ የውጭ ኩባንያዎች ሊሠሩበት የሚችሉትን ዘርፍ የሚጠቅስ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በተሻሻለው ደንብ የቢዝነስ ሀሳቦችን በመዘርዘር ከተጠቀሱት ውጪ ባሉት መስኮች የመሰማራት መብትን የሚሰጥ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ይህን አካሄድ በምትከተልበት በአሁኑ ወቅት፤ የውጭ ኩባንያዎች በገቢ እና ወጪ እንዲሁም በጅምላና ችርቻሮ ንግድ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል የሕግ ማሻሻያ በማድረግ መመሪያው መውጣቱን ይፋ አድርጋለች፡፡ ይህም ለኢትዮጵያውያን ብቻ ይፈቀዱ የነበሩ ዘርፎች ላይ የውጪ ባለሀብቶችን በማሳተፍ እና ገበያውን ክፍት በማድረግ የሀገሪቱ የግብይት ሥርዓትን በማስተካከል በወጪ ንግድ ዘርፍ ያላትን ተወዳዳሪነት ይጨምራል የሚል ግምት ተሰጥቶታል፡፡ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ አረጋ ሹመቴ፤ ይህንን ለውጥ በማድረግ የውጭ ኩባንያዎች በመንግስት ተይዘው ከነበሩ የአገልግሎት መስጠት ጀምሮ ወደ ንግዱ መስክ እንዲገቡ መፈቀዱ  የራሱ ጠቀሜታም ጉዳትም አለው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር በዋናነት የውጭ ባለሀብቶች በአምራች ዘርፍ፣ በግንባታ እና በሰፋፊ እርሻ ላይ እንዲሁም በሆቴል ዘርፍ ብዙም በማይባል ደረጃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይፈቀድላቸው እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡
Show all...
31ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የወጪ ንግድ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ለኢንደስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፣ በወጪ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች በማበረታታት ረገድ የታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ እና የዘርፉን ተዋንያን የሚያበረታታ ሥርዓት በመዘርጋት ተወዳዳሪነት ማላቅ ይቻል ዘንድ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም ረቂቅ ማሻሻያ አዋጁ ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጣውን ወጪ በከፊል መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የጤና ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በስራ ላይ ያለው የጤና ፖሊሲ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ፖሊሲው በጸደቀበት ወቅት ከነበረው ጠቅላላ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ፣ እየተከሰቱ ያሉ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት፣ በሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና ዙሪያ የሚከሰቱ ለውጦች፤ዘርፉ ጥራት እና ፍትሀዊነት ያለው አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ችግሮች የሚስተዋሉበት በመሆኑ እንዲሁም ከሀገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጋር የሚጣጣም የጤና ፖሊሲ እንዲኖረን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 4. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው በግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በስራ ላይ የነበረው የግብርና ፖሊሲ ከአዳጊ የምርትና ምርታማነት ፍላጎት ጋር አብሮ መጓዝ የቻለ ባለመሆኑ፤ ለግብርናው ዘርፍ እድገት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን መለወጥ አስፈላጊ በመሆኑ እንዲሁም ሀገራችን ከምትከተለው ብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ ስርአት ጋር የሚጣጣም ፖሊሲ ማስፈለጉ ታምኖበታል፡፡ ስለሆነም የግብርና ዘርፍን ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የበለጠ የሚያስተሳስር፣ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና በዘላቂነት መጠቀም የሚያስችል፤ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በገጠር መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የሚያግዝ ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
Show all...
🕊 3😁 2