cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Show more
Advertising posts
123 291Subscribers
+1724 hours
+1947 days
+1 52730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የኮሪደር ልማት ስራው ለነዋሪዎች መልካም እድል የፈጠረ ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ************** አዲስ አበባን ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራችን ለነዋሪዎቻችን መልካም እድል የፈጠረ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲያካሂድ የነበረውን የ2016 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቋል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፈተናዎች ባሻገር አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለነዋሪዎችዋ ምቹ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል ብለዋል፡፡ በቀሪ ወራት ለላቅ ውጤታማ ስራ የሚያተጉ እንዲሁም የነዋሪዎች ቅሬታ ምንጭ የሆኑትን ቀልጣፋና ከተማዋን የሚመጥን የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ወራት የተከናወኑት የሰው ተኮር ስራዎች የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ ያበሱ መሆናቸውን ከንቲባዋ ጠቅሰዋል፡፡ የመሬት ዲጂታላይዜሽን እና የገቢ አሰባሰብ ስራዎችም ውጤት ካገኘንባቸው ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡
Show all...
ተጠባቂው የቶተንሃም እና አርሰናል ጨዋታ በአርሰናል 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቀቀ ************* በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በተጠባቂው ሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሃምን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በጨዋታው የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ቡካዮ ሳካ፣ ሀቨርተስ እና ሆይቤር በራሱ ግብ ላይ ሲያስቆጥሩ ቶተንሃምን ከሽንፈት ያልታደጉትን ግቦች ክርስቲያን ሮሜሮ እና ሰን ሁንግ ሚን አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም አርሰናል 80 ነጥቦችን በመያዝ በፕሪሚየር ሊጉ ደረጃ ሰንጠረዡ 1ኛ ላይ ሲቀመጥ ማንቺስተር ሲቲ ደግሞ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ76 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል፡፡
Show all...
👍 45 9👎 7👏 1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ ************ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ+ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሸገር እንዲሁም በተለያዩ የመዲናዋ የልማት ስራዎች ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ፕሮጀክቶቹን ወርዶ በመምራት ከተማዋን እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን አውስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካውያን መዲና የሆነችው አዲስ አበባን ውብ፣ ፅዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ራዕያቸው አካል የሆነ “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” የሚል አዲስ ንቅናቄ ማስጀመራቸውንም ጠቅሰዋል። ይህ አዲስ ሃሳብ ክብርን ጠብቆ በመፀዳዳት ጤናማ አካባቢን ለመፍጠር እና የከተማ ውበትን ለመጨመር የሚያስችል ነው ብለዋል። መላው የከተማዋ አመራር እና ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጀመሩት በዚህ ታላቅ ተግባር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
Show all...
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካቶች የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እየተቀላቀሉ ነው ***************** የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይፋ አድርጓል። ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ ጽ/ቤቱ በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካቶች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ። ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና!
Show all...
በመጪው ክረምት በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል-ኢጋድhttps://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02rwGfE3QQV9Q3SJx35HZTcnugZTGuJqLiWEgpYbmWJcYfnkifV3mtCLS4q17JW1u8l
Show all...
Ethiopian Broadcasting Corporation

በመጪው ክረምት በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል-ኢጋድ ************************************ በኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አስታወቀ፡፡ እ.አ.አ...

👍 21 4👎 2👏 2
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀhttps://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0xUTZXJykFcUypucFGNzm1m3kPYyfcMxLavkMVCxNNRS1RHDFrZ3Z5curnruYcDtSl
Show all...
Ethiopian Broadcasting Corporation

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ ********************* የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ...

👍 24 11
1 ሺህ 262 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ********************* በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 262 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02gssTidFSySvhUBNCi52qvK1S3NMFthvBmGG3a9FYCVKmabdKuqhhzD6eEnUkHy7Dl
Show all...
Ethiopian Broadcasting Corporation

1 ሺህ 262 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ********************* በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 262 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዛሬው ዕለት...

👍 15👏 5 3
ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የነበራቸውን ህልም እውን ለማድረግ ለተቋቋመው ፋውንዴሽን ድጋፍ ሊደረግ ይገባል-አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ******************* ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ የነበራቸውን ህልም እውን ለማድረግ ለተቋቋመው ፋውንዴሽን ሁሉም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ አቅርበዋል።https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0UjFKtzxcj8nFnGZaQZArUvZbWWKxv7UcWWFZrZZUbPaCi4ZVPaUkrcng82UHaFPGl
Show all...
Ethiopian Broadcasting Corporation

ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የነበራቸውን ህልም እውን ለማድረግ ለተቋቋመው ፋውንዴሽን ድጋፍ ሊደረግ ይገባል-አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ******************* ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጥ የነበራቸውን ህልም እውን ለማድረግ ለተቋቋመው ፋውንዴሽን ሁሉም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ...

👍 25 4
እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለፀ ************ እስካሁን ድረስ 11 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ብልጫ አለው ተብሏል። በባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ላይ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የተቻለው 5 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ እንደነበር የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ የግብርናው ዘርፍ የዘጠኝ ወራት አፈፃፅምን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ የግዥ ሂደት ቀድሞ በመጀመሩ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። በዚህም ለበጋ መስኖ እና ለበልግ የሚያስፈልገው የአፈር ማዳበሪያ ግብዓት ቀደም ብሎ መሰራጨቱን ገልፀዋል። አሁን ላይ ደግሞ ወደ መኸር ዝግጅት እየተገባ በመሆኑ ክልሎች የደረሳቸውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ከወዲሁ ማሰራጨት እንዳለባቸው ተጠቅሷል። ለ2016/17 የምርት ዘመን23 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ 19.4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ መፈፅሙም ተጠቁሟል። በይመር አደም
Show all...