cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethiopian Broadcasting corporation ®

Ethiopian broadcasting corporation is a 24 working public media. https://telega.io/c/EBC_TV ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ ካላችሁ በዚህ ላኩልን እንቀበላለን!! https://t.me/+G7d4hSzJEhViMzQ0

Больше
Рекламные посты
11 168
Подписчики
-724 часа
-557 дней
-19330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🏆🏆 ሪያል ማድሪድ ሻምፒዮን ሆኗል 🏆🏆 የስፔን ላሊጋን በሰማንያ ሰባት ነጥቦች እየመራ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ የላሊጋው 2023/24 የውድድር አመት አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ሎስ ብላንኮዎቹ ባርሴሎና በጂሮና መሸነፉን ተከትሎ ከወዲሁ የሊጉ አሸናፊ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችለዋል። ሪያል ማድሪድ ሰላሳ ስድስተኛ የስፔን ላሊጋ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል። ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከሪያል ማድሪድ ጋር አስራ ሁለተኛ ዋንጫቸውን አሳክተዋል። @zlionsport @zlionsport
Показать все...
👏 2👍 1
ልጅ ያሬድ ተፈቷል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ክብር የሚነካ ቃላት ተናገሮ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበረው ልጅ ያሬድ በዛሬው ዕለት ተፈቷል።
Показать все...
የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምና ደህንነት በመጸለይና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን ይገባል - የሃይማኖት አባቶች ******** የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምና ደህንነት በመጸለይና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን ይገባል ሲሉ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያን ካውንስል ዋና ጸሃፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ በዓለ ትንሳኤ የእግዚአብሄር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል። በዓለ ትንሳኤውን ስናከብርም ለእግዚአብሄር ክብርና ለሰው ልጆች ደኀንነት በአንድነት በመቆም መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። በመሆኑም የትንሳኤ በአልን ስናከብር በፍቅር በመተሳሰብና በመተጋገዝ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል፤ በበኩላቸው የትንሣኤ በዓል የክርስቶስን መነሣት ያስተማረን የምሥራች መሆኑን ተናግረዋል። የትንሳኤ በዓል ሲከበር የችግሮች ሁሉ መውጫ ቁልፍ ሰላም ብቻ በመሆኑ በትንሣኤው ብርሃን ለሀገርና ለህዝብ የሰላም መሣሪያ በመሆንና ለሰላም በመፀለይ ሊሆን ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያን ካውንስል ዋና ጸሃፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ፤ ምዕመኑ የትንሳኤን በዓል ሲያከብር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል። በክርስቶስ ትንሳኤ ሁሉም በፍቅር ልብና በይቅርታ ለሰላምና አብሮነት በመጸለይ በዓሉን እንዲያከበርም መልክት አስተላልፈዋል።
Показать все...
ማን ያሸንፋልAnonymous voting
  • አርሰናል
  • አቻ
  • በርንማውዝ
0 votes
የጨዋታ አሰላለፍ ! 8:30 አርሰናል ከ በርንማውዝ @zlionsport @zlionsport
Показать все...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተገነቡ እና የታደሱ 907 ቤቶች ለነዋሪዎች አስተላለፉ ***** የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተገነቡ እና የታደሱ 907 ቤቶች ለነዋሪዎች አስተላልፈዋል። ሌሎች የአስዳደሩ አመራሮችም በቀሪ ክፍለ ከተሞች መርሃ ግብሩን አከናውነዋል። በከተማዋ ልበ ቅን ባለሃብቶች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት ባህል ከሆነ ውሎ ማደሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለነዋሪዎች ቁልፍ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዋል። ከተላላፉ ቤቶች መካከል በ31 ሚሊዮን ብር ወጪ በወጣቱ ባለሃብት ሙኒር ኸይረዲን የተገነቡ "ባለ ሁለት መኝታ" አስራ አንድ ቤቶች ይገኙበታል። ወጣቱ ባለሃብቱ የዛሬውን ጨምሮ 66 ቤቶችን በራሱ ወጪ ገንብቶ ለአቅመ ደካሞችና ለሀገር ባለውለታዎች በማስተላለፋቸው አመስግነዋል። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፋስት ኢንተርፕራይዝ ሶሳ ትሬዲንግ፤ ጀፋር ዩኒቲ ድርጅት፤ ሲሳይ በቀለ ሞል፤ ኢማሮሽ ኢንጂነሪንግ፣ አየለና ባጫ ተቋራጭ እንዲሁም ኢሳኮር የዲዛይን አማካሪ በ66 ሚሊዮን ብር ወጪ ለ44 ነዋሪዎቸ ገንብተው ማስረከባቸው ተገልጿል። በተጨማሪ በአራዳ ክ/ከተማ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመሆን ባለሀብቶችን በማስተባበር በ70 ሚሊዮን ብር ወጪ 25 ቤቶችን ገንብቷል። በአዲስ መልኩ ተገንብተው ለነዋሪዎች የተላለፉ ቤቶች በደቀቁ እና ለመኖሪያ በማይመች ሁኔታ የነበሩ ቤቶች እዚያው በነበሩበት ተገንብተው ለመኖሪያ ምቹ ሆነው መተላለፋቸው ተገልጿል። በጥላሁን ካሳ
Показать все...
👍 2
ቅዳሜ ስዑር *** የትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ከቀድሞው በተለየ መልኩ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል "ቅዳሜ ስዑር" ወይም የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች። የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው በመቃብር የዋለበት በመሆኑ እሱን በማሰብ ምእመናንም እንደ ሐዋርያት የትንሣኤውን ብርሃን ሳናይ እህል አንቀምስም በማለት በጾም ያሳልፉታል። ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ተላልፎ ከተሰጠበት ሐሙስ ሌሊት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም። ይመኩበት እና ተስፋ ያደርጉት የነበረው አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አሳልፈውታል። ከሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረትም ሐዋርያት በማዘን፣ በመጾም እና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናንም ከሐሙስ ማታ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ፤ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ። ይህ ማለት ክርስቶስ ወደ መቃብር በመውረዱ ከእህል ውሃ የማይጾምበት ሰንበት በጾም ተሻረች ለማለት እንጂ የቀዳሚትን ሰንበትነት የሚሽር እንዳልሆነ አባቶች ያስተምራሉ። ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቄጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ "ለምለም ቅዳሜ" ትባላለች። ቄጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል እያሰሙ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ (በመስቀሉ ሰላምን አደረገ) የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠ እና ትንሣኤውንም እንደገለጠ በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ። ምእመናኑም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ። ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፤ ይህም አይሁድ ክርስቶስን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው። የቄጠማው አመጣጥ እና ምሥጢርም ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው። ምድር በጥፋት ውኃ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሠረችው ቄጠማ እና የወይራ ዝንጣፊ ይዛ በመምጣት ነው። ምሳሌውም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ኃጢአት ጠፋ፤ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነፃነት ታወጀ ለማለት ነው። በሌላ አጠራር "ቅዱስ ቅዳሜ"ም ይባላል። ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ስለሆነ ነው። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፤ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ እንደተባለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታስተምራለች። በለሚ ታደሰ
Показать все...
👍 2
👍 2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ******** እንኳን ለ2016 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ መከራና ሞት፤ ግፍና ሙስናን፤ ሲዖልና መቃብርን አሸንፎ የተነሣበትን የትንሣኤ በዓል በየዓመቱ እናከብራለን። ከበዓሉ በፊት የሕማማትን ሰሞን እናሳልፋለን። ሰሞነ ሕማማቱ ፈተናን፣ ስቃይን፣ ክህደትን፣ አሳልፎ መስጠትን፣ የክፉዎችን ኅብረት፣ የምናስብበት ነው። ሐሰት ያሸነፈች፣ እውነት የተሸነፈች መስላ የታየችበት ነው። ብዙዎች መሥዋዕትነትን ፈርተው የሸሹበት ነው። አንዳንዶችን የሚያልፍ ጎርፍ ወሰዳቸው፤ አንዳንዶችን የሚሰክን ማዕበል ነጠቃቸው። ጥቂቶች ከሕማማቱ አልፈው ትንሣኤውን ለመመልከት ቻሉ። የከተማው ጩኸት እና የሐሰቱ ወሬ እንኳን በሩቅ የነበሩትን፣ ቅርብ የነበሩትንም አሸንፏቸዋል። የሆሳዕና ዕለት ደግፈው የወጡት ከሦስት ቀን በኋላ ሊቃወሙ ሲወጡ ምንም አልመሰላቸውም። ድጋፋቸውም ተቃውሟቸውም ሁለቱም የጥቅም እንጂ የመርሕ አልነበረም። ሁለቱም ከእውነታው የተጣሉ ነበሩ። ሕማማት የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተባብረውበታል። በሌላ ጊዜ ለሞት የሚፈላለጉ አካላት እውነትን ለመስቀል ሲሉ ግን ተባብረው ቆመዋል። ሰዎቹ ያልተረዱት አንድ እውነታ ነበር። ከሕማማቱ ይልቅ ትንሣኤው ይበልጣል፤ ይረዝማልም። ሕማማቱ አምስት ቀን ሲሆን ትንሣኤው ግን አስር እጥፍ ይሆናል። የአምስት ቀን ፈተና የሃምሳ ቀን ዋጋ አለው። በርግጥ የሕማማቱን ሽብርና ዋይታ፣ መከራና እንግልት ለተመለከተ ትንሣኤ የሚመጣ አይመስለውም። ትንሣኤው ግን የታመነና የተረጋገጠ ነው። የበለጠ ማረጋገጥ የሚቻለውም ጸንቶ እንደ ዮሐንስ በመቆም ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በፈተና ውስጥ እያለፈች ነው። በፈተና ውስጥ የቆመች ሀገር ግን አይደለችም። በፈተና ውስጥ እያለፈች ያለች እንጂ። ወቅቱ ለኢትዮጵያ የሕማማት ሰሞን ይሆን ይሆናል። አራት ነገሮች ግን እውነት ናቸው። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕማማት አጭር መሆኑ፤ ሁለተኛው አጭር ቢሆንም ከባድ መሆኑ፤ ሦስተኛው ኢትዮጵያ ሕማማቱን ለማለፍ የሚያስችል ኃይል ያላት መሆኑ፤ አራተኛው ከአጭሩ ሕማማት በኋላ ረዥሙ የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚመጣ መሆኑ ነው። የተነሣነው ኢትዮጵያ እንደምትፈተን ዐውቀንም፤ አምነንም ነው። ለዘመናት የኖሩ ስብራቶችንና ብልሽቶችን ልናክም ስንነሣ መንገዱ አልጋ በአልጋ አይሆንም። ከችግሩ ማትረፍ የለመዱ አካላት ዝም አይሉም፤ ኢትዮጵያ በማሽን እንደሚረዳ ሕመምተኛ ሆና በሞትና በሕይወት መካከል እንድትኖር የሚፈልጉ ኃይሎች ዐርፈው አይቀመጡም። ግን ሕማማቱን እኛ ካልተቀበልንላት ለኢትዮጵያ ማን ይቀበልላታል:: የመከራውን ቀንበር ካልተሸከምንላት የሀገር ልጅነቱ የቱ ጋ ነው:: “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው እንጀራዋን በልተው ተረከዛቸውን አነሡባት። የሕማማቱ ወቅት አጭር ቢሆንም ከባድ መሆኑን እናውቃለን። የኮሶ መድኃኒት እንዲያሽር ከተፈለገ በአንድ ጊዜ በከባዱ መወሰድ አለበት። በትንሽ በትንሹ ከተወሰደ አያሽርም። የኢትዮጵያም ሕማማት እንደዚሁ ነው። በፊስካል ፖሊሲ፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ነጻነትን በማስተዳደር፣ በክልል አደረጃጀት፣ በሲቪል ሰርቪስ፣ በጋራ ትርክት ግንባታ፣ ወዘተ. የተረከብናቸው ውዝፍ ዕዳዎች ብዙ ናቸው። ወገባችንን አሥረን፣ እጅጌያችንን ሰብስበን መራራውን የኮሶ መድኃኒት ውጠን፣ እነዚህን ችግሮች ካልፈታናቸው ቆመው አይጠብቁንም። በፈጣኑ ዓለም ውስጥ ቀስ ብለን ልንሄድ አንችልም። ተጠንቅቀን ግን ፈጥነን፤ አስበን ግን ዋጋ ከፍለን መጓዝ አለብን። ይሄ ነው ሕማማቱን የሚያሳጥረው። ኢትዮጵያ ሕማማቱን ለማለፍ የሚያስችል ኃይል አላት። ከዚህ በፊትም ብዙ አልፋለች፣ አሳልፋለች። የማይተዋት አምላክ አላት። የሚወዳት፣ የሚያስብላት ብቻ ሳይሆን የሚሞትላትም አመራር አላት። ዓላማ አይቶ ዋጋ የሚከፍል ሕዝብ አላት። አንጡራ ሀብት አላት። ይሄ የፈጣሪ፣ የአመራሩ፣ የሕዝቡ እና የአንጡራ ሀብቷ አራት ማዕዘናዊ ዐቅም፣ ሕማማቱን ማሳጠርና ማስቻል ብቻ ሳይሆን ቀጥሎ የሚመጣውን ፋሲካ ረዥም እንዲሆን ያደርገዋል። ብርቱውን ይዘናል - እንበረታለን፤ ኃይል በሚሰጠው እንታመናለን። ንጽሕናንና ለሀገር ያለንን በጎ ራእይ መሠረት አድገን ቆርጠን እንሠራለን። የጥብርያዶስ ሞቅታም ሆነ የፕራይቶሪዮን ግቢ ጩኸት ከመንገዳችን አያቆሙንም። የሆሳዕና ድጋፍም ሆነ የዕለተ ዓርብ ተቃውሞ መንገዳችንን አያስቀይሩንም። የኢትዮጵያን እውነት ብቻ ተከትለን እንገሠግሣለን። በዚህም ሕማማቱን አሳጥረን የኢትዮጵያን የትንሣኤ ጊዜ እናረዝመዋለን። በድጋሜ መልካም የትንሣኤ በዓል! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ሚያዚያ፣ 2016 ዓ.ም
Показать все...
👍 6