cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

This is FBC's official Telegram channel. For more updates please visit www.fanabc.com

Show more
Advertising posts
182 636Subscribers
+10924 hours
+9637 days
+3 78730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺህ 460 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም÷ የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ለ2ኛ ዙር የሚሰጠውን ይቅርታ ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 431 ወንድ እና ለ29 ሴት ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል ብለዋል፡፡… https://www.fanabc.com/archives/242990
Show all...
👍 17 3👏 1😱 1
በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸነፈች አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ ባለው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸንፋለች፡፡ በ60 ኪሎግራም የደቡብ አፍሪካ አቻዋን የገጠመችው ቦክሰኛዋ በውድድሩ ሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ባሰረፈችው ቡጢ በዳኛ ውሳኔ አማካኝነት በበቃኝ ማሸነፍ ችላለች። ማሸነፏን ተከትሎም ቦከሰኛዋ ወደ ቀጣይ ዙር… https://www.fanabc.com/archives/242940
Show all...
👍 15🥰 1
በአዲስ አበባ 140 የኤሌክትሪክ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተከናወነ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃዉ ለሚገኙ ተቋማት የሚያገለግሉ 140 የኤሌክትሪክ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች (ሚኒባስ) ርክክብ አከናወነ። 86 ተሽከርካሪዎች ለ11ዱ ክፍለከተሞች ቀሪዎቹ 54 ተሽከርካሪዎች ደግሞ ለማዕከል ተቋማት የተሰጡ ናቸው ተብሏል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎቹን ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ለህዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት ተሽከርካሪዎችን መግዛት ያስፈለገበት… https://www.fanabc.com/archives/242973
Show all...
👍 15 1👏 1
የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው – አቶ ፈቃዱ ተሰማ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተከናወነ የሚገኘው የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ገለፁ፡፡ በአቶ ፈቃዱ ተሰማ የተመራ ልዑክ በሰሜን ሸዋ ዞን ቅምቢቲ እና አቢቹኛኣ ወረዳዎች በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡ በዚህ ወቅትም አቶ ፈቃዱ… https://www.fanabc.com/archives/242974
Show all...
👍 7👏 2
የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው – አቶ ፈቃዱ ተሰማ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተከናወነ የሚገኘው የስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሥራ ውጤታማ እያደረገ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ገለፁ፡፡ በአቶ ፈቃዱ ተሰማ የተመራ ልዑክ በሰሜን ሸዋ ዞን ቅምቢቲ እና አቢቹኛኣ ወረዳዎች በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡ በዚህ ወቅትም አቶ ፈቃዱ… https://www.fanabc.com/archives/242974
Show all...
አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዋን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም÷የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት፣ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ዙሪያ መክረዋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ÷የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ አጋርነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ… https://www.fanabc.com/archives/242970
Show all...
👍 18 3👏 1
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይን ጎበኙ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሣይንስ ሙዝየም የተከፈተውን የስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በተጨማሪም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ተገኝተል። መጋቢት 30 በጀመረው እና እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ ከ900 የሚልቁ ስታርት አፖች ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩ እና ወደገበያ የመቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ ስታርት አፖችም ሥራዎቻቸውን ለዕይታ አብቅተዋል። በይስማው አደራው
Show all...
👍 18 10😁 3👏 1
የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ትሰራለች- ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ከወዳጅ አገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። በሰላም ዕጦት ውስጥ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥም አበክራ እንደምትሰራም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም… https://www.fanabc.com/archives/242957
Show all...
👍 21😁 15 1👏 1🤔 1
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ለተሽከርካሪ መገጣጠሚያና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ እና ማምረቻ ኢንዱስትሪ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጡ። ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረው የመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘመኑ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑንም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ለሀገርና ለተቋሙ የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ኢንዱስትሪው በአዲስ መልኩ ከተደራጀ በኋላ በተሰሩት ስራዎች ከኪሳራ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን አመላክተዋል፡፡
Show all...
👍 26 10👏 3
ከ2011 ዓ.ም ማህደር ለትውስታ
Show all...
👍 7😁 1