cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Show more
Advertising posts
13 383
Subscribers
+1224 hours
+847 days
+31630 days
Posts Archive
አምላካችን አሏህ በመልእክተኛው ወሕይ ከማውረዱ በፊት ልክ አንድ ሕጻን የእናት ሁለት ጡቶችን መርጦ እንዲጠባ በኢልሃም"innate knowledge" እንደሚያሳውቀው ሁሉ አንድ ነገር ኸይር ወይም ሸር መሆኑን ሁለቱንም ለአንድ ሰው በውሳጣዌ ግንዛቤ ያሳውቃል፦ 90፥10 *ሁለት ”መንገዶችም” አልመራነውምን?"* وَهَدَيْنَٰهُ ٱلنَّجْدَيْنِ 76፥3 *"እኛ አመስጋኝ ወይም ከሐዲ ሲሆን ”መንገዱን መራነዉ”*። إِنَّا هَدَيْنَٰهُ ٱلسَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًۭا وَإِمَّا كَفُورًا "ማመስገን" እና "አመስጋኝ" የሚለው ቃል "ማመን" እና "አማኝ" ለሚል ቃል ተለዋዋጭ ሆኖ የገባ ነው፥ ሰዎች በነቢይ በኩል መልእክቱ ደርሷቸው አመስግነው አመስጋኝ ቢሆኑ አሏህ ይወድላቸዋል ይጨምርላቸዋል። በተቃራኒው ክደው ከሓዲ ቢሆኑ አላህ ከእነርሱ የተብቃቃ ነው፥ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም። ይቀጣቸዋል፥ ቅጣቱ ብርቱ ነው፦ 39፥7 *"ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፥ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑ እርሱን ይወድላችኋል"*፡፡ إِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمْ ۖ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ الْكُفْرَ ۖ وَإِن تَشْكُرُوا يَرْضَهُ لَكُمْ 14፥7 *ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም እቀጣችኋለሁ፥ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ አስታውሱ"*፡፡ وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ "መሺኣህ" مَشِئَة የሚለው ቃል "ሻአ" شَاءَ ማለትም "ፈቀደ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፈቃድ" ማለት ነው፥ ስለዚህ ሰው አምኖ ለሚሠራው መልካም ሥራ አሊያም ክዶ ለሚሠራው መጥፎ ሥራ ነጻ ፈቃድ አለው፦ 18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን! የሻም ሰው ይካድ!»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر 64፥2 *"እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከእናንተም ከሓዲ አለ፥ ከእናንተም አማኝ አለ፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው"*፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ فَمِنكُمْ كَافِرٌ وَمِنكُم مُّؤْمِنٌ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ "የሻም ሰው ይመን! የሻም ሰው ይካድ" የሚለው ሰው የማማረጥ ነጻ ፈቃድ እንዳለው አመላካች ነው፥ በተጨማሪም "የሻም" ለሚለው የገባው ቃል "ሻአ" شَاءَ ነው። በዓለማችን ላይ "ካፊር" እና "ሙእሚን" ያለው ሰው በፈቃዱ በመረጠው ምርጫው ነው፥ አሏህ የምንሠራውን ሁሉ ተመልክቶ በምንሠራው ሥራ ይጠይቀናል፦ 16፥93 *ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ*፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون 102፥8 ከዚያም *ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ*። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ “ነዒም” نَّعِيمِ ማለት “ጸጋ” ማለት ሲሆን ይህ የተሰጠን ጸጋ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ነጻ ፈቃድ"free will" ነው። ሰው በሚሠራው ሰናይ ሆነ እኩይ ሥራ ግብረገባዊ ተጠያቂነት"moral accountability" ያለው ፍጡር መሆኑ እነዚህ ሁለት አናቅጽ ፍንትው እና ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። አሏህ በሠራው እና በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም፥ ሁለት ምርጫ ያላቸው ፍጡራን ግን በሚሠሩት ሥራ ይጠየቃሉ፦ 21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ ሰዎች በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ይሠሩት የነበሩትን መልካም ነገር ይመነዳሉ፥ በተቃራኒው ይሠሩት የነበሩትን መጥፎ ነገር ይቀጣሉ፦ 18፥180 *"ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ"*፡፡ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ 6፥120 *"እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣሉ"*፡፡ نَّ الَّذِينَ يَكْسِبُونَ الْإِثْمَ سَيُجْزَوْنَ بِمَا كَانُوا يَقْتَرِفُونَ አሏህ በነጻ ፈቃዳቸው ካመኑት እና መልካም ከሠሩት ሙተቂን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ሁለት አማራጭ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 91፥8 *"አመጽዋን እና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት"*፡፡ فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا በቁርኣን "ነፍሥ" نَفْس ማለት “ራስነት”own self-hood” ማለት ሲሆን "ማንነት" ነው፥ አምላካችን አሏህ ለነፍሥ በኢህላም አመጽ ምን እንደሆነ እና አሏህ መፍራት ምን እንደሆነ አሳውቋታል፦ 91፥8 *"አመጽዋን እና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት"*፡፡ فَأَلْهَمَهَا فُجُورَهَا وَتَقْوَاهَا እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሳወቀ" ለሚለው የገባው ቃል "አልሀመ" أَلْهَمَ መሆኑን ልብ በል! "ኢልሃም" إِلْهَام የሚለው ቃል እራሱ "አልሀመ" أَلْهَمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ውሳጣዊ ግንዛቤ"intuition" ማለት ነው፦ ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 91፥8 *ኢብኑ ዐባሥ "አመጽዋን እና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት" የሚለውን ሲናገር፦ "ለእርሷ መልካም እና ክፉን ገልጾላታል"*። ሙጃሂድ፣ ቀታዳህ፣ ሶሓክ እና ሰውሪይ ተመሳሳይ ነገር ብለዋል፥ ሠዒድ ኢብኑ ጁበይር፦ "መልካም እና ክፉን ባሳወቃት" ብሏል"*። قال ابن عباس : ( فألهمها فجورها وتقواها ) بين لها الخير والشر . وكذا قال مجاهد ، وقتادة ، والضحاك ، والثوري . وقال سعيد بن جبير : ألهمها الخير والشر . "ፉጁር" فُجُور ማለት "አመጽ" ማለት ሲሆን ይህም አመጽ አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር ባለማድረግ እና የከለከለውን መጥፎ ነገር በማድረግ ማመጽ ነው፥ "ተቅዋ" تَقْوَا ማለት ደግሞ "አሏህን መፍራት" ማለት ሲሆን ይህም ፍርሃት አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር በማድረግ እና የከለከለውን መጥፎ ነገር ባለማድረግ መታዘዝ ነው። ከዚያም ሰው ዐቅሉ ሲያመዛዝን አሏህ ነቢይ ልኮ በወሕይ "ይህ መልካም ነው" "ይህ መጥፎ ነው" በማለት ቅኑን መንገድ ከጠማማው መንገድ ይገልጥልናል፦ 2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር በማድረግ እና የከለከለውን መጥፎ ነገር ባለማድረግ አሏህ የሚፈራው "ሙተቂን" مُتَّقِين ሲባል በተቃራኒው አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር ባለማድረግ እና የከለከለውን መጥፎ ነገር በማድረግ ያመጸው አመጸኛ "ፉጃር" فُجَّار ይባላል፦ 38፥28 *"በእውነቱ እነዚያን ያመኑትን እና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ "አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን?"* أَمْ نَجْعَلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَالْمُفْسِدِينَ فِي الْأَرْضِ أَمْ نَجْعَلُ الْمُتَّقِينَ كَالْفُجَّارِ “ዘንብ” ذَنب ማለት “ኃጢአት” ማለት ነው፥ “ኃጢአት” ማለት በሥነ-ኃጢአት ጥናት”hamartiology” አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ ነው። አምላካችን አሏህ ለሰው የሰጠው መልካም እና ክፋ የማሰብ፣ የመናገር፣ የማድረግ ነጻ ምርጫ በችሎታችን ልክ ነው፥ ያለ ችሎታችን ልክ አያስገድደንም፦ 23፥62 *ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም*፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا 2፥286 *አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም*፡፡ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا "ዉሥዕ" وُسْع ማለት "ዐቅም" "ችሎታ" ማለት ሲሆን አንድ ሰው አንድን ነገር የማድረግ እና ያለማድረግ ችሎታ ከአሏህ የተሰጠ ነጻ ፈቃድ ነው፥ ከተሰጠው በላይ ለማድረግ ላለማድረግ የተገደደ ሰው አይጠየቅም። “የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም” فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ተብሏልና፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 2123 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ በኡማዬ ላይ ስህተት፣ መርሳት እና የገተደዱበትን ነገር አንስቷል”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ وَضَعَ عَنْ أُمَّتِي الْخَطَأَ وَالنِّسْيَانَ وَمَا اسْتُكْرِهُوا عَلَيْهِ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48 ዓኢሻህ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል፥ እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ እና ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏ አሏህ ፍትሓዊ አምላክ ነው፥ ባለማወቅ ስህተትን ለሚሠሩ እና መልእክቱ ያልደረሳቸውን ሰዎች አይቀጣቸውም፦ 2፥286 *"ጌታችን ሆይ! ”ብንረሳ ወይም ብንስት አትቅጣን” በሉ*፡፡ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَ 33፥5 *በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም፥ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ኃጢአት አለባችሁ"*። አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا 17፥15 *መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም*፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የካቲት 16 ወይንም February 24 በዕለተ ቅዳሜ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ በጋዜጠኛ አብዱረሒም አህመድ (Abdurahim Ahmed) የቲክቶክ አካውንት በኩል ለሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሔዳል። ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በሚሽነሪ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ ተቋም ሲሆን ለቀጣይ ሁለት አመታት ያቀዳቸው 3 ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ ለማድረግ የፈንድሬይዚንግ ፕሮግራም በአሏህ ﷻ ፍቃድ ይካሔዳል። በዚህ የድጋፍ መርኅ ግብር ተገኝተው የዳዕዋው አካል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። 1000499318212 Hidaya Islamic Center አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212 የአብዱረሂም ቲክቶክ አካውንት ፎሎው ያድርጉ https://www.tiktok.com/@abdurahimahmed99?_t=8k2WeDvrYQI&_r=1
Show all...
👍 39
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #27 https://vm.tiktok.com/ZMM1DKVhw/
Show all...
👍 18
የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች #4 https://vm.tiktok.com/ZM6oHsoAW/
Show all...
👍 11
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #26 https://vm.tiktok.com/ZM6K5Eu6C/
Show all...
👍 19
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ለጉዳይ ስንንቀሳቀስ ከሚያስቸግሩን ነገሮች ውስጥ አንዱ መስጅድ ያለበትን ቦታ በቀላሉ አለማወቃችን ነው። ይህንን ችግር የሚፈታና በቀላሉ የትም አካባቢ ያሉ መስጅዶችን በቴሌግራም በኩል በቀላሉ የምታገኙበትን ቻናል ልጠቁማችሁ ... ያላችሁበትን አካባቢ ስሙን ብቻ ሰርች ማድረጊያው ላይ በመጻፍ ለናንተ ቅርብ የሆነውን መስጅድ ከነጎግል ማፕ አድራሻው የምታገኙበት የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በሀገራችን ያሉ መስጅዶችን በዝርዝር እየተጨመሩበት ይቀጥላል። ለአብነት ጀሞ አካባቢ ብትሆኑና አቅራቢያችሁ ያለ መስጅድ ብትፈልጉ በቀላሉ ሰርች ማድረጊያው ላይ "ጀሞ" ብላችሁ መጻፍ ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ። ከሚመጣላችሁ ዝርዝር ውስጥ ማፑን በመመልከት የሚቀርባችሁ ጋር መስገድ ትችላላችሁ። ክፍለ ሀገርም ቢሆን በተመሳሳይ ነው። ◾️ ከመስጅዶች በተጨማሪ የሙስሊም የቀብር ቦታዎችንም አካቷል። ሼር በማድረግ በናንተ ምክንያት ሶላታቸውን ሳይቸገሩ በሰገዱ ሰዎች ልክ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ...! https://t.me/ethiopianmosques
Show all...
👍 71 21👏 1
00:24
Video unavailableShow in Telegram
👏 36👍 19 7🤷 7
የላሜሕ እድሜ “ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ ሞተም።” — ዘፍጥረት 5፥31 ይህንን የሚለው የ1954ቱ ትርጉም ሲሆን በዚህ እትም የኖረበት ዘመን 747 እንደሆነ ተገልጿል። የአዲሱ መደበኛ እትምን ስንመለከት ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን፦ “ላሜሕ በአጠቃላይ 777 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።” — ዘፍጥረት 5፥31 (አዲሱ መ.ት) በዚህኛው ትርጉም ደግሞ የላሜሕ እድሜ 777 እንደነበር ተገልጿል። ልዩነቱ በሁለት ብቻ አያበቃም። ከዚህ በታች አንቀጹ ላይ ያሉ ተጨማሪ ልዩነቶችን በተጨማሪ ቋንቋዎች እንመልከት፦ 1/ በተለምዶ LXX ተብሎ የሚጠራው ሰብቱዋጀንት ወይንም የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም እድሜውን 753 አድርጎ የሚገልጸው ሲሆን ይህኛው ቁጥር ሌላ የተለየ ተጨማሪ ቁጥር ነው። የኢት/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ባሳተመችው የ2000 ትርጉም ላይ የሰብአ ሊቃናት ትርጉም 753 እንደሚል በህዳጉ አስቀምጣለች። 2/ በተለምዶ MT የሚባለው የማሶሬቲክ ወይንም የዕብራይስጡ ጹሁፍ ደግሞ 777 አድርጎ የሚገልጸው ሲሆን የአማርኛው አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተርጓሚዎችና አብዛኛው የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ይህንን መጠቀማቸውን መረዳት እንችላለን። 3/ የሳማሪታን አይሁዶች ተውራህ/ቶራ/ የሆነውና በምህጻረ ቃል ST ተብሎ የሚጠራው ትርጉም ደግሞ እድሜውን 653 አድርጎ ይገልጸዋል። 4/ አራተኛውና የመጨረሻው የትርጉም ገለጻ ደግሞ የ1954ቱ የአማርኛ ትርጉምን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተጠቀሙት 747 አመት የሚለው ትርጉም ሲሆን ከላይ ካሉት ትርጉሞች የተለየና አዲስ ቁጥር ነው። ◾️ ማጠቃለያ የላሜሕ እድሜን በተመለከተ አንድ ሰው መጽሀፍ ቅዱስን ተጠቅሞ እድሜውን መናገር ቢፈልግ በትክክል መናገር አይችልም። በክርስትናው እምነት ውስጥ የትርጉም ምንጭ ተደርገው የሚታመኑ ጥንታዊ ጹሁፎች እንኳን እድሜውን በተመለከተ እርግጠኛ ቁጥር የላቸውም። አንዳንድ ሰው "ቁጥር ስለሆነ ጠቃሚ ነገር የለውምና ቢለያይም ችግር የለውም" የሚል ሀሳብ ሊያነሳ ይችላል። እንደዛ ከሆነ መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥም መሠል ነገር መቀመጡ አስፈላጊ አይደለምና የመቆየቱ ነገር ላይ አብራችሁ አስቡበት። የማይጠቅም ስህተት "ቅዱስ" የሚባል መጽሀፍ ውስጥ አለ ብሎ መሟገት በፈጣሪ ክብር ላይ መዘባበት ነው።
Show all...
👍 29
Photo unavailableShow in Telegram
👍 9🎉 1
“..ቁርዓን ታሪክንም ህግንም ይዟል። በታሪኮች እየተደመሙ ህጉን የሚዘነጉ ሰዎች መርሳት የሌለባቸው ነገር ታሪኩ የሚያወራው ህጉን ስለዘነጉ ሰዎች እንደነበር ነው.."
Show all...
👍 56 15🥰 5😢 3
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች #2 ቪዲዮ መመልከት ለሚሻላችሁ፣ በቴሌግራም በጹሁፍ የማቀርበው ትምህርት እንደሚከተለው በቪዲዮም ይዘጋጃልና መርጣችሁ መመልከት ትችላላችሁ። ይህኛው በመጽሀፍ ቅዱስ የጹሁፍ ልዩነቶች/Textual variant/ ዙሪያ እየተሰራ ያለ አዲስ ተከታታይ ጹሁፍ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ነው። የመጀመሪያውን ቲክቶክ ላይ ታገኙታላችሁ፣ ፕሮግራሙም የሚቀጥል ይሆናል። .. ለማታውቁ - የጹሁፍ ልዩነት/Textual Variant/ ማለት በመጽሀፍ ቅዱስ የመገልበጥ/Copy/፣ የመተርጎም/Translation/ ስራዎች ውስጥ የተፈጠሩ ልወጣዎችን/ብርዘቶችን/ የሚገልጽ ዘርፍ ሲሆን መጽሀፍ ቅዱስ በዚህ በኩል ያሉበት ክፍተቶች የትየለሌ ናቸው። ይህ ዘርፍ ቁርአን የነገረንን የመበረዝ ሂደት ፍንትው አድርጎ ከምንጩ የሚያሳይ በቂ አስረጅ ከመሆኑ ጋር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችን ይሆናል፣ ኢንሻላህ..! https://vm.tiktok.com/ZM6th8sxd/
Show all...
👍 38
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች #2 https://vm.tiktok.com/ZM6th8sxd/
Show all...
👍 13 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዛውያ ቲቪና ሀሩን ሚዲያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ዛሬ በይፋ አሳውቀዋል። ይህ የአንድነትን ጉልበት የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው። የሁለቱንም ሚዲያ ወንድሞች በቅርበት አውቃቸዋለሁ። ለዲን መልፋትና ቀናነትን የተሸለሙ ትጉህ ሰራተኞች ናቸው። አሏህ ﷻ ይገዛችሁ፣ የተሻለ ዲኑን በህብረት የምትኻድሙም ያድርጋችሁ።
Show all...
👏 91👍 24🎉 6🥰 3🍓 3
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #24 https://vm.tiktok.com/ZM6GqfSPy/
Show all...
👍 18
Photo unavailableShow in Telegram
ይህ መጽሀፍ ገበያ ላይ የለም አልቋል፣ ካለቀ በርካታ አመታትን አሳልፏል። የታተመ ሰሞን የተወሰኑ ኮፒዎች አንድ ወንድም ጋ እንዲያስቀምጥልኝ አድርጌ ነበሩ። በወቅቱ እንዲተባበረኝ አስቤ የነበረ ቢሆንም በአንድ ወቅት ገጠር ለተማሪዎች የተወሰነ ኮፒ በነጻ ከሰጠሁ በኃላ ግን የተረዳሁት ነገር መጽሀፉ ከመጽሀፍት ቤቶች ከመሸጥ በላይ በላይ ለመርከዝና ለዲን ተማሪዎች መሠጠት እንዳለበት ነበር። በዚህም ምክንያት የንጽጽር መጽሀፍ ሳይታገድ ጊዜ ጀምሮ መጽሀፍቶቹ ከገበያ ላይ ማለቃቸውን ባውቅም ወደ ገበያ አልወስድኳቸውም ነበር። ... ከሰሞኑ ሁላችንም የምናውቃቸው አንድ ትልቅ ሼይኻችን መጽሀፉን በተለያዩ መርከዞች የንጽጽር ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ለመስጠት ፈልገውት ሲጠይቁኝ መጽሀፉ እንዳለኝ ነገርኳቸው። ግን ሙሉ የግዥ ወጭው ሸይኹ ጋር መሆኑ ምቾት ነሳኝ። ከመጽሀፉ ጥቂትነት አንጻር (190 ፍሬ ብቻ ነው) ብንተባበር በቀላሉ መሸፈን እንደምንችልና ከሳቸው አልፎ ለሌሎችም ተማሪዎች መበተን እንደሚቻል አመንኩ። እናም መጽሀፍቱን በአነስተኛ ዋጋም ቢሆን የሚገዛላቸው ከተገኘ ለሸይኹም በነጻ እንዲሁም የንጽጽር ፍላጎት ላላቸው ለመርከዝ ተማሪዎች በኔ በኩል መስጠት እጀምራለሁ፣ የአንዱ መጽሀፍ ዋጋ 100 ብር ብቻ ነው። በፍላጎቱ 1ም 2ም መጽሀፍ ስፖንሰር የሚያደርግ ሰው ሲገኝ የኒያውን ያክል መጽሀፍ ለመርከዝ ተማሪዎች ይደርስለታል። ሚሴንጀር ያልሰራላችሁ በቴሌግራም ማናገር ትችላላችሁ፦ t.me/yahyanuhe1
Show all...
42👍 27🍓 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሰባዎቹ ሽማግሌዎች ትንቢት “ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመና ወርዶ ተናገረው፤ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አሳደረባቸው፤ መንፈሱ ባደረባቸውም ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን #አልደገሙትም።” — ዘኍልቁ 11፥25 (አዲሱ መ.ት) “እግዚአብሔር በደመናው ወረደ፥ ተናገረውም፥ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አደረገ፤ መንፈሱም በላያቸው ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን #አልተናገሩም።” — ዘኍልቁ 11፥25 በአማርኛው ሁለቱም እትሞች ላይ ሰባዎቹ ሽማግሌዎች መንፈሱ በላያቸው ላይ ባደረ ጊዜ ትንቢት መናገራቸውን ከዚያ በኃላ ግን አለመናገራቸውን ይገልጻል። ይህ ትርጉም ግን ከሌሎች ቋንቋ ትርጉሞች ጋር ይለያያል። ለአብነት የእንግሊዝኛውን የንጉስ ጀምስ ቅጅ ብንመለከት ሰባዎቹ ሽማግሌዎች ከዚያ በኃላ አለመናገራቸውን ሳይሆን ከዚያ በኃላ መናገር አለማቆማቸውን/መናገራቸውን/ የሚገልጽ ነው። “And the LORD came down in a cloud, and spake unto him, and took of the spirit that was upon him, and gave it unto the seventy elders: and it came to pass, that, when the spirit rested upon them, they prophesied, and #did #not #cease.” — Numbers 11:25 (KJV) ለዚህም ይመስላል የአዲሱ መደበኛ ትርጉም በህዳግ ማስታወሻው ላይ "ከዚያ በኃላ ትንቢት መናገራቸውን አላቆሙም የሚሉ አሉ" ሲል የገለጸው። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 17
Photo unavailableShow in Telegram
አንዳንድ ነገሮች ሲያስደንቁኝ ዝም ከምል ማን እንደሚማርበት አላውቅምና ላካፍላችሁ፦ ከዛሬ አንድ ወር ገደማ በፊት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትልቅ ሚሲዮናውያን/Missionary/ የማዘጋጀት ስልጠና ነበር። ይህ ስልጠና ከሌሎች ስልጠናዎች ትንሽ ለየት ያለ ነበር። ከዚህ በፊት የነበሩ ሚሽነሪዎች ሰልጥነው ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚላኩ ነበሩ። አሁን ግን ዘመኑን ያማከለ ሌላ ስልጠና ነበር ቤተ ክርስቲያኗ ለ125 ሰልጣኞች ያዘጋጀችው። ይኸውም ሰልጣኞቹ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ተምረው ስራቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ በመስራት "ወንጌልን እንዲያገለግሉ" ነው የሰለጠኑት። ይህንን ሲሰሩም የሚያስፈልጓቸው ቴክኖሎጂዎች ተገዝተው በነጻ ተሰጥተዋቸዋል። የሚያስፈልጋቸው ስልጠናም በቸርቿ በኩል ቀርቦላቸው ሰልጥነዋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ሰልጥነውም ተመርቀዋል። የቤተ ክርስቲያኒቷ ፕሬዝዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በማጠናቀቂያ መርሀ ግብራቸው ላይ እንዲህ ብሏቸዋል፦ "ወደ አለም ሂዱ የሚለውን ትዕዛዝ በአካል መንቀሳቀስ ሳይጠበቅ በእጃችን ባለ መሳሪያ መስራት ይቻላልና፣ ይህንን ለመስራት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላችኃለው" الْكَلِمَةُ الْحِكْمَةُ ضَالَّةُ الْمُؤْمِنِ فَحَيْثُ وَجَدَهَا فَهُوَ أَحَقُّ بِهَا ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 55😱 9🥰 8
Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ የኦንላይን ኮርስ ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታልን?/A Critical Review of the authorship theories/ "ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታል" በሚል ሙስሊም ባልሆኑ ወገኖች የሚነሱ መላምቶችን የሚዳስስና የሚሞግት አዲስና በይዘትም አጭር የሆነ ኮርስ ሲሆን ፍላጎት ያለው ሰው መመዝገብና ኮርሱን መውሰድ ይችላል። በኮርሱ የሚዳሰሱ መላምቶች፦ 1/ ቁሳዊ ከበርቴነትን ለማግኘት ጽፈውታል/Material gain as motive 2/ ለስልጣንና ለክብር ሲሉ ጽፈውታል/Desire for power and glory/ 3/ ከአይሁድና ከክርስትና ምንጮች ተጠቅመው ጽፈውታል/From Jews and Christian sources/ 4/ ራዕይ የታያቸው መስሏቸው ሀሳባቸውን አቀናጅተው ጽፈወታል/The religious illusion theory/ 5/ የቁርአንና የመጽሀፍ ቅዱስ መሠረታዊ ልዩነት/Major difference between the bible and the qur'an/ እነዚህን አስመልክቶ ማብራሪያዎችና ትንተናዎች የሚቀርቡበት ሲሆን በትምህርቱ መጨረሻ የሚሰጠውን ፈተና ተከታትለው ለሚወስዱ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል። ስልጠናውን ለመከታተል፦ https://t.me/+cZu3KlAbhWYyODE8
Show all...
29👍 22
00:33
Video unavailableShow in Telegram
በጋዛ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በቃል መግለጽ አይቻልም ሲሉ የአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእንባ ጋር እየታገሉ ገልጸውታል 💔 ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 75😢 48 2
Photo unavailableShow in Telegram
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #22 https://vm.tiktok.com/ZM6gWUqT5/
Show all...
👍 20
አንድ ሰው ታመመ ሲባል በተለይም የድጋፍ ጥሪ በተፖሰተበት ቦታ እየመጣችሁ "ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ ይቀበል፣ ይፈወሳል" እያላችሁ ኮሜንት የምታደርጉ ጴንጤዎች የአእምሯችሁን የመቀንጨር ልክ እንድናየው ባታደርጉን ምናለበት..?! ስንቱን በህመም የሞተ ጴንጤ የማናውቅ ለምን እንደሚመስላችሁ አላውቅም። የፈውስ ድራማችሁን በተመለከተ እንኳን እኛን የራሳችሁንም ሰው ማሳመን ካቆመ ቆይቷልና አደራችሁን በየኮሜንቱ አትዘባበቱብን። ይልቅ እጅ መዘርጋት የወንጌላችሁ ቃል ነውና ለታመመው እርዱ፤ እሱ ከከበዳችሁ ደግሞ ዝምበሉ። ከሞንታርቦ የተረፈ ጆሯችንን እንዳናሳርፍ እዚህም እየመጣችሁ እጅ እጅ በሚል አስቀያሚ "ሰበካችሁ አይናችንን ደግሞ አታሳምሙት..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 105 18🤩 13👏 7
Photo unavailableShow in Telegram
የዛውያ ቲቪ መስራችና የምንጊዜም የማዕከሉ አበረታች የሆነው ወንድማችን ሙሳ ኑረዲን 1,200 ብር ድጋፍ አድርጓል። አሏህ ይቀበልህ..! ... 1000499318212 Hidaya Islamic Center አጭር ቁጥር - 8212 በሚከተሉት መገኛዎች ተቀላቅለውን ስራዎቻችንን ሊደግፉ ይችላሉ፦ በቴሌግራም፦ https://t.me/+5kfHxCCm0RRkYmI0 በዋትስአፕ https://chat.whatsapp.com/LPgG6cIEA181mtu3AO6tvW
Show all...
20👍 14🙊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሀገራችን የመጀመሪያ በሚባል መልኩ የተለያዩ ንጽጽር ነክ ስልጠናዎችን ለማካሔድ ስርአተ ትምህርትና እቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ። የሚሽነሪውን እንቅስቃሴ በመግታት ደረጃ የራሳቸው አሻራ ያላቸውን እነዚህን ፕርጀክቶች ለማሳለጥ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል። እርሶም የዚህ መልካም ስራ ተቋዳሽ ይኾኑ ዘንድ ተጋብዘዋል። በሚከተሉት መገኛዎች ተቀላቅለውን ስራዎቻችንን ሊደግፉ ይችላሉ፦ በቴሌግራም፦ https://t.me/+5kfHxCCm0RRkYmI0 በዋትስአፕ https://chat.whatsapp.com/LPgG6cIEA181mtu3AO6tvW
Show all...
22👍 8🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሚያስቅ ሁኔታ የትላንቱንም ፖስቴ ፌስቡክ ሰርዞታል 😄 ከቴሌግራም በተጨማሪ ቲክቶክ ቴክስት መጀመሩ ጠቀመን እንጅ በብስጭት ያስረጀን ነበር። በነዚህ በኩል ተወዳጁኝ፤ ለሌላውም ሰው ሼር አድርጉልኝ፣ በተለይም በፌስቡክ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@yahyaibnunuhe?_t=8j9pFCIutT4&_r=1 ቴሌግራም፦ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 28🥰 9 1🤩 1
አንዱ ወንጌላዊ ሰባኪ "እስራኤልን መደገፍ እንዳለብኝ ጌታ ተናግሮኛል" ሲል ሰማሁት። በወንጌላውያን ዘንድ "ጌታ ተናገረኝ" እንደሚለው ቃል መጫወቻ የሆነ ብሂል ያለ አይመስለኝም። ይህንን ፖስት ለመፖሰት እራሱ የነሱ ወገን ብሆን "ጌታ እንድፖስት ተናግሮኝ ነው" ማለት እችላለሁ። የወደቀብህን እስክርቢቶ ማንሳት እንዳለብህ ውስጥህ ቢነግርህም ጌታ እንደተናገረህ ማሳበብ ግን ትችላለህ።የውስጥህን መሻት ሁሉ በጌታ እያሳበብክ መፈጸምም፣ ማስፈጸምም ትችላለህ። ምሳ እንኳን ሲርብህ "ጌታ ብላ ብሎ ተናግሮኛል" ልትል ትችላለህ፣ በእውነታው ግን የተናገረህ ሆድህ እንጅ ጌታ አይደለም። እና አንድ ወንጌላዊ ጌታ ተናግሮኛል ሲል በቀላሉ "እንዲህ ማድረግ ፈልጌያለሁ" ብሎ እንደተናገረ ተረዱት...! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 77🤩 28 4🥰 4👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሰዎች ያልፋሉ፣ ሲያልፉም - ይነስም ይብዛም፣ ይመርም ይክፋም አሻራቸውን ትተው ነው የሚያልፉት። አሏህ መልካም ዱካ ትተው ከሚያልፉት ያድርገን...! وَاجْعَل لِّي لِسَانَ صِدْقٍ فِي الْآخِرِينَ (ሱረቱ አልሹዐራ - 84) በኋለኞቹም ሕዝቦች ውስጥ ለእኔ መልካም ዝናን አድርግልኝ፡፡
Show all...
👍 66 1
ጸረ-ፍልስጤማዊ ሰባኪዎች በአረብያን ምድር..! ... https://vm.tiktok.com/ZM6QxoVMG/
Show all...
👍 12
ዱንያ መልኳ ብዙ ነው፤ አፍጋኖች እንደሚሉት "ካገኘን ዶሮ እንበላለን፣ ካጣን ዶሮዋ የምትጥለውን እንበላለን፣ እሱንም ካጣን ዶሮዋ የምትበላውን እንበላለን" ይላሉ። በአሏህ ያላቸው መተማመን ከፍ ያለ ስለሆነ ነው መሠል ዶሮዋ የምትበላውን ጥራጥሬ ያሳጣናል ብለው ስላላሰቡ አባባሉን አልቀጠሉትም። የቀልብ ክብረት አያሰጣን..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 86 7🥰 5
00:48
Video unavailableShow in Telegram
Nothing disgusts me more than hearing about justice from the West.
Show all...
44👍 16🥰 4
Photo unavailableShow in Telegram
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በንጽጽር ትምህርት ዙሪያ የሚያገለግል አፕልኬሽን ለአንድሮይድና አይፎን ተጠቃሚዎች ማዘጋጀቱ ተገለጸ ... ሀሩን ሚዲያ፥ ጥር 4/2016 ... በሚሽነሪው እንቅስቃሴ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ የሚገኘው ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በንጽጽር ትምህርት ዙሪያ የሚያገለግል አፕልኬሽን ለአንድሮይድና አይፎን ተጠቃሚዎች ማዘጋጀቱን በትላንትናው እለት ማዕከሉ አስታውቋል። ... አፕልኬሽኑ እስካሁን የተሰሩ የንጽጽር ስራዎችን ቀጥታ ከይፋዊ ድረ ገጻቸው በመውሰድ ተጠቃሚዎች ያለኢንተርኔት /ኦፍላይን/ እንዲያነቡ የሚያስችል ነው። አፕልኬሽኑን ማንኛውም ሰው ከፕለይስቶርና ከአፕ ስቶር ዳውንሎድ ማድረግ መጠቀም እንደሚችል የማዕከሉ መስራቾች ገልጸዋል። ... For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.ridwan.hidaya For Iphone: https://apps.apple.com/us/app/hidaya-comparative/id6474642955 የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን ከፈለጉ፦ https://bit.ly/4aGr93u በቴሌግራም በኩል ሊያገኞቸው ከፈለጉ ደግሞ፦ @Hidayaislamiccenter ተቋሙን መደገፍ ሲፈልጉም፦ 1000499318212 Hidaya Islamic Center አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212 ... © ሀሩን ሚዲያ ___ በቴሌግራም፥ https://t.me/harunmedia በዩቲዩብ ፥ http://bit.ly/3MXs17j
Show all...
👍 26
Photo unavailableShow in Telegram
በስተመጨረሻም በጥራት የተሰራው ኦፍላይን አፕልኬሽን ተጠናቆ ይኸው ወደናንተ ደርሷል። አፕልኬሽኑ ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎችም ለአይፎን ተጠቃሚዎችም የተሰራ ነው። በንጽጽር ዙሪያ የተጻፉ ጹሁፎችን በዚህ ድረ ገጽ በፈለጉት ሰአት ያለ ኢንተርኔት ገብተው ማንበብ ይችላሉ። አዳዲስ ጹሁፎችም በአሏህ ﷻ ፍቃድ በተከታታይ ይጨመሩበታል። አፑን ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ፣ ለሰውም ሼር ያድርጉት፦ 📌 ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.ridwan.hidaya 📌 ለአይፎን ተጠቃሚዎች https://apps.apple.com/us/app/hidaya-comparative/id6474642955
Show all...
👍 42 5
Photo unavailableShow in Telegram
ማርያምን "የአብ ሙሽራ" ብሎ መጥራት ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?ጸሀፊው ምንስ መልዕክት በአአምሮው አስቦ ነው ይህንን ጹሁፍ የጻፈው? ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 20 2🙉 2
አነጋጋሪው የቲቢ ጆሽዋ ዶክመንትሪና አስቀያሚ ህይወቱ ... https://vm.tiktok.com/ZM6uwNWS2/
Show all...
😢 13👍 5
የረሳሁት የገዛ ሴት ልጁ ሳይቀር በሚደፍራቸው ሴቶች ስቃይ ሳቢያ በድፍረት ስተለናገረችው የመከራ መአትን አውርዶባታል። የሚያሳዝነው ይህችም ሴት የተወለደችው ከህጋዊ ሚስቱ ሳይሆን በዚና ነው።
Show all...
😢 34😱 11👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ምን ጉድ ነው? ... በክርስቲያኑ አለም ስመ ጥር ሰባኪ (በነሱ አጠራር ነብይ) የነበረውን ቲቢ ጆሽዋን አስመልክቶ The cult of TB Joshua በሚል ቢቢሲ ያዘጋጀውን ሶስት ክፍል ዶክመንትሪ አየሁት። ለተከታታይ አመታት ደቀመዛሙርት አድርጎ ሲደፍራቸው የነበሩ፣ በእንዝህላልነቱ ያለምንም ርህራሄ ለሞት አሳልፎ የሰጣቸው ከ80 በላይ አማኞች፣ አካላዊ ጥቃትና መከራ ሲፈጽምባቸው የነበሩ የራሱ አገልጋዮች በተመሳሳይ ድምጸት እያንዳንዱን ክስተት እያነሱ ተናዘዋል። ... ግለሰቡ በአደባባይና በድብቅ የነበሩትን ሁለት ፍጹም ተቃራኒ ህይወቶች እየነቀሱ አጋልጠዋል። ፈውስ ተብለው የሚቀርቡ ጉዳዮች ምን ያክል የተቀናበሩ ነጭ ውሸቶች እንደነበሩም ዋናዎቹ እራሳቸው ተዋናዮች ዘርዝረዋል። ከጅን መጥራት የዘለለ ፈጽሞ መንፈሳዊነት ስብእናው እንዳልነበር በብዙ ማሳያዎች ጠቅሰዋል። ከምንም በላይ ግን ከተለያየ አለም በሱ ዝና ተማርከው ቤተ ክርስቲያኗን ለማገልገል ሂደው የሱ የወሲብ ባሪያ የነበሩ ሴቶች ህይወታቸው እንዴት የባከነና የመከራ እንደነበር ሲናገሩ መስማት ልብ ይሰብራል። ... እርግጥ ቲቢ ጆሽዋ ከመሞቱም በፊት ቢሆን እነዚህ ተግባራቶቹ በራሳቸው በክርስቲያኖቹ አልፎ አልፎ ይጋለጡ የነበረ ቢሆንም የቻለውን እየዛተ፣ አሻፈረኝ ያለውን ደግሞ እስከመግደል ሙከራ ሳይቀር እየሄደ ዝም ለማሰኘት ሞክሯል። ይህንን ሰው ትልቅ አርአያ አድርገው የሚንቀሳቀሱ የሀገራችን ሀሰተኛ ነብያት ከዚህ ሰው በወረሱት አርአያነት በየገስት ሀውሶቻቸው ምን እንደሚያደርጉ አሏህ ይወቅ...! ከአመታት በፊት በነዚህ ሰዎች ጾታዊ ጥቃትና ብዝበዛ የደረሰባቸው ሰዎች ሚዲያ ላይ ወጥተው ሲናዘዙ በሀገራችንም አስተውለናል። በቆራጥነት ለአደባባይ የሚወጡት ምንጊዜም ጥቂቶች ናቸው፣ በየጓዳቸው መከራን የተሸከሙትን ደግሞ ቤቱ ይቁጠራቸው።
Show all...
👍 47😢 15
Photo unavailableShow in Telegram
የህንድ ሙስሊሞችን በማሰቃየት የሚታወቀው የገዥው ፓርቲ አባልና አመራር በሳዑዲ አረብያ ጉብኝቷ መዲናን መጎብኘቷን ገልጻለች። ሙሽሪኮች ያውም ጸረ ሙስሊሞች በይፋ መዲና የሚገቡበትን ዘመን...! ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
Show all...
😢 90👍 3 1
ከ90,000 በላይ ፎሎወር ያለው የፌስቡክ ፔጅ በቅርብ ጊዜ በነበሩ ፖስቶቼ ምክንያት በነበሩ ተደጋጋሚ እገዳዎች ፔጁን መጠቀም አልቻልኩም። ለዚህም ሲባል ይህንን አዲስ የፌስቡክ ፔጅ ከፍቻለሁ። በጹሁፎቼ እንዲሁም በትምህርቶቼ ሰዎች ይጠቀማሉ ብለው ካመኑ ሼር በማድረግ ያሰራጩት። https://www.facebook.com/ethiomuslim24?mibextid=ZbWKwL
Show all...
👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ሸይኻችንን አሏህ ይዘንላቸው፣ የሀገራችን ዓሊሞች ነገር አሁንም በዚህ ደረጃ በእዳና በመከራ ውስጥ መሆን ልብ ይሰብራል። ለዚህ ዑማ ከዓሊም በላይ ምን አለውና? አሏህ ገንዘብ የሰጣችሁ ሰዎች ገንዘቡን በመሠል ዚያራዎች ለአኼራችሁ ስሩበት። በየአካባቢያችን በርካታ ችግር ውስጥ ያሉ ኢማሞች ይኖራሉ። ችግራቸውን በሀያት እያሉ እንሸፍንላቸው፣ እንዘይራቸው። አሏህ እሳቸውንም ከደጋጎቹ ይቀስቅሳቸው፣ ያሉትንም ይጠብቅልን!
Show all...
👍 59😢 45