cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Show more
Advertising posts
14 033
Subscribers
+2324 hours
+1277 days
+72030 days
Posts Archive
Photo unavailableShow in Telegram
ፈጣሪ/ያህዌ ይጨፍራል? ... ብዙ የአይሁድ ድርሳናት/ታልሙድ/ እንደሚናገሩት ወደፊት ፈጣሪያቸው ከጠቢባን ጋር እንደሚጨፍር ያምናሉ። ከታች የተቀመጡ የአይሁድ ድረሳናት ፈጣሪ/ያህዌ እንደሚጨፍር በግልጽ የሚናገሩ ናቸው። ዶቭ ዌይስ በ "Pious Ireverence" መጽሀፉ ገጽ 150 ላይ የነዚህ ገለጻዎች ትርጉም ከዚህ የተለየ አለመሆኑን ገልጿል። ... ሱብሀነሏህ..!
Show all...
👍 25😱 9🤩 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢስራዕና ሚዕራጅ ወገድለ ቅዱስ ላሊበላ ንጻሮ ... ስለመጽሀፈ ሄኖክ በማነብበት ሰአት የገድለ ቅዱስ ላሊበላ ታሪክን አሰሰመልክቶ የሚገልጹ ጹሁፎች ስሜቴን ያዙት። ላሊበላ በ12ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ንጉስ ሲሆን ገድሉም የሚያወራው ስለሱ ነው። በገድለ ላሊበላ ገጽ 80 ላይ ላሊበላ በመልአኩ ገብርኤል አማካኝነት ወደ ሰባቱ ሰማያት ያደረገው ጉዞ ተገልጿል። የሚገርመው ይህ ብቻ አይደለም፣ በተመሳሳይ ሰአት ወደ ኢየሩሳሌምም የዚያኑ ወቅት በገብርኤል አማካኝነት ጉዞ አድርጓል። በሰማይ ስላገኛቸው አካላትም ገድሉ በዝርዝሩ ያወራል። ይሄ ታሪክ ከመጻፉ ከ500 አመት ገደማ በፊት በእስልምናው ታሪክ ውስጥ በነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ላይ የተፈጠረና የሚታወቅ ታሪክ ነው። "እስልምና ከኛ ወስዷል" የሚሉት ቀውሞች መሠል ታሪክ በዚህ መልኩ እነሱ ጋር ዘግይተው መጻፋቸውን የሚያውቁ አይመስልም። የኢስራዕና ሚዕራጅን ጉዞ ተአማኒነት ለማጣጣል ሲሞክሩም የላሊበላን ገድል ግን የሊቃውንቶቻቸው ማህደር ላይ እንዳለ እንኳን በቅጡ አያውቁም። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 60🤩 9 5
Photo unavailableShow in Telegram
ኢስራዕና ሚዕራጅ ወገድለ ቅዱስ ላሊበላ ንጻሮ ... ስለመጽሀፈ ሄኖክ በማነብበት ሰአት የገድለ ቅዱስ ላሊበላ ታሪክን አስመልክቶ የሚገልጹ ጹሁፎች ስሜቴን ያዙት። ላሊበላ በ12ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ንጉስ ሲሆን ገድሉም የሚያወራው ስለሱ ነው። በገድለ ላሊበላ ገጽ 80 ላይ ላሊበላ በመልአኩ ገብርኤል አማካኝነት ወደ ሰባቱ ሰማያት ያደረገው ጉዞ ተገልጿል። የሚገርመው ይህ ብቻ አይደለም፣ በተመሳሳይ ሰአት ወደ ኢየሩሳሌምም የዚያኑ ወቅት በገብርኤል አማካኝነት ጉዞ አድርጓል። በሰማይ ስላገኛቸው አካላትም ገድሉ በዝርዝሩ ያወራል። ... ይሄ ታሪክ ከመጻፉ ከ700 አመት ገደማ በፊት በእስልምናው ታሪክ ውስጥ በነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ላይ የተፈጠረና የሚታወቅ ታሪክ ነው። "እስልምና ከኛ ወስዷል" የሚሉት ቀውሞች መሠል ታሪክ በዚህ መልኩ እነሱ ጋር ዘግይተው መጻፋቸውን የሚያውቁ አይመስልም። የኢስራዕና ሚዕራጅን ጉዞ ተአማኒነት ለማጣጣል ሲሞክሩም የላሊበላን ገድል ግን የሊቃውንቶቻቸው ማህደር ላይ እንዳለ እንኳን በቅጡ አያውቁም።
Show all...
329 ሚሊየር ብር...! ለቦረና እና ደቡብ ኦሞ ዞን ብቻ ድጋፍ እንዲደረግ (የወንጌል ስራ እንዲሰራ) ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል የተሰኘ የሚሽነሪ ድርጅት የበጀተው ብር ነው..! ታዲያ ብሩ ለመላው ሀገረቱ አይደለም፤ ለሁለቱ ቦታዎች ብቻ ነው። ይህንን ስራ እንዲሰሩ ደግሞ የሚከተሉት የቸርች ተቋማት ታጭተዋል፦ ◾️የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ የልማት ኮሚሽን ◾️ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የልማት ኮሚሽን ◾️ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ የልማት ኮሚሽን ◾️ የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤ/ክ የልማት ድርጅት ◾️ የኢትዮጵያ መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ እርዳታና ልማት ማህበር ◾️ የብርሃን ወንጌል ቤ/ክ ልማት ድርጅት ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል የተሰኘው የሚሽነሪ ተቋም በ585 ቦታዎች ለ135,731 ህጻናት በቋሚነት የሚሰጠው እርዳታ እንዳለ ሁኖ ነው መሠል ፕሮጀክቶችን አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ በተጓዳኝ የሚሰራው። ይህ እንግዲህ የአንድ ተቋም ስራ ብቻ ነው፣ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት በርካታ ናቸው። የቦረና ሙስሊም አሏህ ይሁንህ..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
😢 59👍 17 2👏 1
ተወልጀ ያደግኩበት አካባቢ ያለው መስጅድ አያቴና አብረውት የነበሩ ሰዎች ከ50 አመት በፊት የተቀበሉት መስጅድ ነበር። ይህ መስጅድ ሲሰጣቸው ቦታው የቆሻሻ መጣያ ስለነበር ቦታውን ለማስተካከል እንደ አሁኑ ቴክኖሎጂ ጉዳዩን ቀላል አላደረገም ነበርና ህዝበ ሙስሊሙ በጉልበት ደክሟል። እነኛ አባቶች የቆሻሻው ሽታ እስኪጠፋ ታግሰው መስጅዱን መስጅድ አድርገው ለልጆቻቸው አስተላልፈዋል። ... ሁሌም መስጅዱ ጋ በሄድኩ በልጅነት አአምሮየ በተደጋጋሚ ጥያቄ ይሆንብኝ የነበረው ሀሳብ በሞላ ቦታ ለምን ይሆን የቆሻሻ ቦታን ያውም ለመስጅድ "ከፈለጋችሁ ያውላችሁ" ተብሎ ሊሰጣቸው ቻለ የሚለው ነበር። ወቅቱ አስቸጋሪ ከመሆኑ አንጻር መስጅድ ማግኘትም ትልቅ እድል ነበርና አባቶቻችን በደስታ ተቀብለው ቆሻሻውን አጽድተው የአሏህ ቤት አድርገውታል። በተቃራኒው ሀገሪቱ "የኛ ናት" ብለው የሚያምኑ ሰዎች መዝገንን ስለሆነ የሚያስቡት ጭቅጭቃቸው ስለነሱ መሰጠት አይደለም። ጥያቄያቸው ከፍ ያለ ነው፣ መሰጠት ለነሱ የሚያሞቃቸውም የሚያበርዳቸውም አይደለም። የነሱ ጥያቄ እንደ አለቃ " የቆሻሻ መጣያ ቦታስ ቢሆን ለምን ለእነ እገሌ ተሰጣቸው?" የሚል ነው። ... እኛ በደልን ሰምተነውም ኑረንበትም ትከሻችን ስለጎበጠ ከመታገልና ግብረ መልስ ከመስጠት በዘለለ ምናልባት እንደ ሀገር ባለቤት ለማሰብ ጊዜያችን ገና ሊሆን ይችላል። 40ሺ ካሬ ተሰጥቶን "ለምን ተሰጣቸው" ብለው የሚጠይቁት ግን ከፊቱ 450ሺ ካሬ ያጠሩ ባለእምነቶች ናቸው። ይህንን አይነት ታሪክ አባቶቻችን ሲያስረዱን በደሉ ብዙም ስላልራቀ ተረድተናቸዋል። ይህንን አይነት ጥያቄ በዚህ ዘመን በድፍረት ተጠይቀን ስንዋከብ እንደነበር ለኛ ልጆች ለማስረዳት ግን እንዴት እንደሚቻል አላውቅም። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 63 12😢 3👏 2
የኢየሱስን ማንነት አስመልክቶ ከዚህ በፊት የነበረው የክርስቲያኖች የቆየ አቋም ◾️ "ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ" አሁን ከብዙ የቲክቶክ "ጉባኤዎች" በኃላም ቢሆን መስማማት ቸግሯቸው እየተወያዩበት ያለው ሀሳብ ◾️ "ኢየሱስ ፍጡርም ነው ፈጣሪም ነው" የሚቀጥለው መድረክ ምንም ይሁን ምን ቀጣይ የ"ሊቃውንቱ" አጀንዳ "ኢየሱስ ፍጡር ነው" የሚለው የኒቃያው ጉባኤ አጀንዳ ሊሆን እንደሚችል እንጠበቃለን። ሰው በመሠረታዊ አቋሙ ዙሪያ "መደራደር" ከጀመረ በዚያ በኩል የነበረው መሠረቱ የጸና አልነበረም ማለት ነው። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 53🔥 5
Photo unavailableShow in Telegram
እንደተለመደው የምተማመንባቸውን ሀላል ንግዶች ሲኖሩ በየመሀሉ ማስተዋቀቄን እቀጥላለሁ። በከሰል ንግድ ላይ ያላችሁና ብዛት መውሰድ የምትፈልጉ ስትኖሩ ወንድማችን ጋር መውሰድ ትችላላችሁ። አሁን ላይ ያለው ዋጋ ከሰል ትንሹ ከረጢት ዋጋ 190 ብር ሲሆን ብዛት ለሚወስድ አስተያየት ይኖረዋል። ቦታ፦ አያት አደባባይ 0921093031
Show all...
👍 42🥰 2🤷‍♂ 1
01:27
Video unavailableShow in Telegram
📌 ለማስታወስ .... የመጽሀፍ ቅዱስ ይዘትን በተመለከተ በቀናነት ጥያቄ የምናቀርብበት "የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች" የተሰኘው የጥያቄ ክፍላችን 19ኛ ጥያቄ ላይ ደርሷል። በዋናነት ቲክቶክ ላይ የሚለቀቅ ሲሆን ፕሮግራሙን መከታተል፣ መልስ መስጠት የምትፈልጉ ሁሉ እንድትከታተሉት ተጋብዛችኃል። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
18.93 MB
👍 33 5👏 4
አዎ! ኢየሱስ ፍጡር ነው! https://vm.tiktok.com/ZM6yt6PFJ/
Show all...
👍 22 3
01:09
Video unavailableShow in Telegram
እኛ ስንናገር ብዙም ሰሚ አልነበረም፣ የናንተው ሰዎች ሲናገሩ ካዳመጣችሁ ደግሞ ይኸው ስሟቸው...! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
21.48 MB
49👍 18🙉 4🙊 4
Photo unavailableShow in Telegram
የሚሽነሪውን እንቅስቃሴ በመመከት በኩል ከዚህ በፊት የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ የነበረው ማዕከላችን አሁን ደግሞ በዚህ ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። እነዚህ ስራዎች የሚፈልጓቸው የፋይናንስ ወጭዎች ደግሞ የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቁ ናቸው። በጥቂት ቀናት የማኪያቶ ወጫችን ብቻ አባል በመሆን ማዕከሉን ማስቀጠል እንችላለን። ... በአባልነት ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦ 📎 https://bit.ly/4aGr93u በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦ 📎 @Hidayaislamiccenter 1000499318212 Hidaya Islamic Center አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212
Show all...
👍 43 4🥰 1🙊 1
ሀብት ለበርካታ ኸይር ስራ መንገድ የሚከፍት ነገር መሆኑ ግልጽ ነው። ሰዎች ሀብታም እንዲሆኑ መስበክም መልካም ነገር ነው። ግን ደግሞ ለአኼራው በገንዘቡ መልካምን መስራት የሚተናነቀው ሰው እልፍ ብልጽግና በበሩ ቢያልፍ እንደ ሙስሊም ምን ይፈይድለታል?ይህንን ሰው መስጅድ ውስጥ ስለ ብልጽግና ብትነግረው አትጠቅመውም። ገንዘቡን መልካም ቦታ ማዋል እንዳለበት ቀድመህ የነገርከውን ሰው "ሚሊየነር ሁን" ብትለው ችግር የለውም። ቁሳዊነት ገኖ ሀላልና ሀራም ሳይመረጥ በሚግበሰበስበት ዘመን ሰውን መስጅድ ውስጥ ምን መምከር እንዳለብን መረዳት በዚህን ያክል ሲጠፋን ማየት ያሳዝናል። በዚህ ከቀጠልን "የብልጽግና ወንጌል" ሀዲስና ቁርአን እየተጠቀሰለት በየመስጅዱ መሰበኩ አይቀርም። ምዕመኑ የመጨረሻ ግቡ ዱንያ እስኪሆን ድረስ የማማለል ስራውም እንዲሁ መሳ ለመሳ ይሄዳል ማለት ነው። ስናጠፋ ማንንም ሳይፈሩ "ተው" የሚሉን ዑለሞችን ያምጣልን..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 66🥰 5🤷‍♂ 3👏 3
📚 የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች 📌 ክፍል 17 በቲክቶክ ቪዲዮ https://vm.tiktok.com/ZM6MFCqyU/ https://vm.tiktok.com/ZM6A5Y8DE/
Show all...
👍 20
ይህንን ፎርም የሞላችሁ ወንድምና እህቶች በዚህ ሊንክ መሠረት አፕልኬሽኑን ዳውንሎድ ማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ። ፎርሙን ያልሞላችሁ አፑን ለመጫን ብትሞክሩም ስለማይሰራላችሁ አትድከሙ። https://play.google.com/store/apps/details?id=dev.ridwan.hidaya
Show all...
👍 25🥰 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢየሱስ "መለኮታዊነትና" የዮሐንስ ወንጌል "ማስረጃ" “እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።”   — ዮሐንስ 13:13 (የሕያ ኢብኑ ኑህ) ◾️ መግቢያ የኢየሱስን መለኮታዊነት አስመልክቶ በክርስቲያን ሊቃውንት በኩል ለማስረጃነት ከሚያገለግሉ ጥቅሶች መካከል ከላይ የተጠቀሰው ዋነኛው ነው። በተለይም ለዘመናት "እየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ካለ እንደዛ ያለበትን ቦታ አሳዩን" ለሚለው የሙስሊሞች ጥያቄ ያገለግላል በሚል ከሚቀርቡ "ማስረጃዎች" ይጠቀሳል።  በዚህ ጽሁፍ ይህንን አንቀጽ በተመለከተ "እውን የኢየሱስን መለኮታዊነት ይገልፃልን?" በሚል መነሻ የተወሰኑ ሐሳቦችን በማስፈር ሙግቶቻቸውን በማስረጃ ለመፈተሽ እንሞክራለን https://hidayacomparative.org/?p=988
Show all...
👍 18🎉 1
Photo unavailableShow in Telegram
ስትወለዱ ሙስሊም መሆናችሁን እኮ በይፋ መቀበል እየከበዳችሁ ነውንጅ አንዳንዴ ሳታውቁት ትመሰክሩታላችሁ.! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 55🤩 25🙊 2
ሥላሴን በተመለከተ ወንድማችን ኡስታዝ ወሒድ በተከታታይ እየሰጠው የሚገኘውን ትምህርት ግን ተከታትላችሁታል?በተለይ ንጽጽር ላይ ላላችሁ ተማሪዎች በጣም ጠቃሚ ነውና በሚገባ ተከታተሉት። እስካሁን የተሰጡ ትምህርቶችን በዚህ የዩቲዩብ አድራሻው ታገኟቸዋላችሁ። https://youtube.com/@Wahidislamicapologist?si=gfQyoalKw-o6MLif
Show all...
👍 37🥰 15 4
የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የንጽጽር ድረ ገጻችን ወንድማችን ኢዘዲን ከሰራው በተጨማሪ አሜሪካ በሚኖር በጎ ፈቃደኛ የሶፍትዌር ባለሙያ ወንድማችን አማካኝነት ውብ በሆነ መልኩ በአንድሮይድና በIOS ተሰርቶ ተጠናቋል። ፕለይስቶር ላይ 20 ሰው Test ማድረግ ስለሚያስፈልገው የአፕልኬሽኑ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ለመሆን በፎርሙ ኢሜላችሁን መላክና የመጀመሪያዎቹ 20 ተጠቃሚዎች መሆን ትችላላችሁ። ለሌሎቻችሁ ደግሞ ዘግይቶ የሚለቀቅ ይሆናል። ፎርሙን ለመሙላት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://forms.gle/ZSGogqLzQLanBpoBA
Show all...
👍 14 1
የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የንጽጽር ድረ ገጻችን ወንድማችን ኢዘዲን ከሰራው በተጨማሪ በበጎ ፈቃደኛ የሶፍትዌር ባለሙያ አማካኝነት ውብ በሆነ መልኩ በአንድሮይድና በአፕ ስቶር ተጠናቋል። ፕለይስቶር ላይ 20 ሰው Test ማድረግ ስለሚያስፈልገው የአፕልኬሽኑ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ለመሆን በፎርሙ ኢሜላችሁን መላክና የመጀመሪያዎቹ 20 ተጠቃሚዎች መሆን ትችላላችሁ። ለሌሎቻችሁ ዘግይቶ የሚለቀቅ ይሆናል። ፎርሙን ለመሙላት የሚከተለውን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://forms.gle/ZSGogqLzQLanBpoBA
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"...አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው.." ምላሽ -9 https://vm.tiktok.com/ZM6B1dYJW/
Show all...
👍 17 5
የቀድሞው የወንጌላውያን አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል ፕሬዝዳንት የነበረ ሰው "በመኖሪያ ቤቴ አቅራቢያ መስጂድ አይሰራም" በማለት ህጋዊ ካርታ እና የግንባታ ፍቃድ ያለውን መስጂድ ከንቲባ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ አሳግዶታል። የኮልፌ ቀራኒዮ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ሄደው ማብራሪያ ሲጠይቁ "የአከባቢው ማህበረሰብ ቦታው ላይ መስጂድ እንዳይሰራ ፒትሽን ፈርሞ ስላሰገባ ካርታውን አምክነን ተለዋጭ ቦታ እንሰጣቹኃለን" የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል ። አካባቢው ላይ ለተለዋጭ የሚሆን ምንም አይነት ክፍት ቦታ የለም። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ጉዳዩን ይዞ መከታተል ይኖርበታል። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 36😢 18🔥 3😱 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
"መኖሪያ ቤቴ አቅራቢያ ማንም ሰው መስጅድ አይሰራም" ብሎ ሙስሊሙን የሚያሰቃየው ባለስልጣን https://vm.tiktok.com/ZM6kbLprh/
Show all...
😢 40👍 8
ተቅዲር/እጣፈንታ/ በተድቢር/በእቅዶች ወይንም ጥንቃቄዎች/ ይስቃል ይባላል تقدیر به تدبیر میخندد እዚህ ዱንያ ላይ ለዘላለም እንደምንኖር በማሰብ ብዙ ጊዜ ታላላቅ እቅዶችን እናወጣለን፣ ነገር ግን የህይወታችን ዘመን በቅርቡ ፍጻሜው ተቃርቦ ሊሆን ይችላል። ወይንም ደግሞ አሏህ ﷻ ለእኛ ትልቅ እቅድ ሲኖረው እኛ ግን አንዳንድ ጊዜ በዝቅተኛ ተስፋዎች እየዋለልን ይሆናል። ◾️ የሰው ልጅ ደካማነት ከእጣፈንታው ጀርባ የተደበቀውን እንኳን አያውቅም። ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 41🥰 7 1
የኦሪት መጽሀፍት_Bass(1).mp327.37 MB
👍 19 5🥰 2
መስመር እየሳተ ነው..! https://vm.tiktok.com/ZM6hsWvyB/
Show all...
👍 16🏆 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሰለምቴው ወንድማችንን እናሳክመው ... ወንድማችን እስልምናን ከተቀበለ በኃላ በደረሰበት መደብደብ ምክንያት ለበርካታ ጊዜያት ህመም አልተለየውም። አሁንም ህመሙ እያገረሸ ስቃይ ውስጥ ጥሎታል። ህመሙን በቋሚነት እንዲታከምና ወንድማችንም ከጭንቅ እንዲገላገል የተቻለንን ድጋፍ እናድርግለት። በራሱ አካውንት የተከፈቱ የባንክ ቁጥሮች ከዚህ በታች ተቀምጠዋል፦ ሰልማን ካሳ ሞላ አቢሲኒያ ባንክ 18950828 ሰልማን ካሳ ንግድ ባንክ 1000186476933
Show all...
😢 64👍 35👏 3 2
"ጠላትህን ውደድ" እንዲሁም "የሚረግሟችሁን መርቁ" ወዘተ የሚል መጽሀፍ አንብበው ይጠቅሱልንና መዝሙር ሲያወጡ ግን "ድብን ይበል ጠላቴ" ሲሉ "ይቀኙታል" መጽሀፉ ጋር እራሱ እልፍ ጊዜ ነውኮ የምትተላፉት..!
Show all...
🤩 49👍 7😱 2👏 1🏆 1
በጊዜ መላ ሊፈለግለት የሚገባ ተደጋጋሚ ችግር https://vm.tiktok.com/ZM6rdqNaN/
Show all...
👍 18
የህግ አስከባሪዎች የህግ ጥሰት 📌 Live ተከታተሉ ... https://vm.tiktok.com/ZM6M9HUXG/
Show all...
👍 17
📚 የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች 📌 ክፍል 14 በቲክቶክ ቪዲዮ https://vm.tiktok.com/ZM6MFCqyU/
Show all...
👍 13 2🎉 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከዚህ ቀደም ይህ መጽሀፍ አስፈልጎኝ የምታገኙልኝና ብሩን ልኬላችሁ ገዝታችሁ የምትልኩልኝ ካላችሁ ብየ ጠይቄ ነበር። አንድ እህት ከምትኖርበት ሀገር ገዝታ ዛሬ ላከችልኝ፣ ለመክፈል ብለምንም "በፍጹም" አለች። ዛሬ መጽሀፉ እጄ ሲገባ ስቀበል ምስጋናየን ላደርስ ብፈልግም ለምስጋና አልሰራችውምና ላገኛት አልቻልኩም። በዚሁ አንችንም ያረሰልኝን ወንድምሽንም አመስግኛለሁ፤ አሏህ መልካም ምንዳዋን ይክፈላችሁ። ___ © የሕያ ኢብኑ ኑህ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 70 23👏 4
የቲክቶክ ሰው ስድብ ብቻ ሳይሆን አስቂኝ መልስም ያውቅበታል። ከሰሞኑ ስለመጽሀፍ ቅዱስ ግጭት በሰራሁት ቪዲዮ ላይ "ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ስሞታል ወይንስ አልሳመውም?" ብየ ሁለት የሚቃረኑ አንቀጾችን ጠቅሸ ጠይቄ ነበር። አንዱ ክርስቲያን ሲመልስም፦ "ዋናው ነገር አሳልፎ መስጠቱ ነው" ሲል በቀላሉ "ለመመለስ" ሞክሯል። ቢስመውም ባይስመውም ያው ስለሆነ ቢጋጭም ትርጉም የለውምና "አትጨነቅ" እያለኝ ነው። ዋናው ነገር "አሳልፎ መስጠቱ ነው" እያለ ነው። እርግጥ ከግጭቱ አውድ ከወጣን የልጁ ሀሳብ ነጥብ አለው። ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ሰጥቶ ባያስገርፍና ባያሰቅለው የክርስቲያኖች የመዳን እጣፈንታ ጥያቄ ውስጥ ይገባ ነበር። ክርስቲያኖች ለመዳን ኢየሱስ መሰቀል አለበት ብለው ካመኑ ይሁዳ ባለውለታቸው ነው። ይሁዳ በዚህ ተግባሩ ብቻ የገነት ሊሆን ይገባል። እርግጥ በስቅለቱ ውለታ ቆጥረው ባያስገቡት እራሱ ኢየሱስ ለሱም ሀጥያት ከሞተ ገነት መግባት ይኖርበታል። ይሁዳ ገነት ከገባ ደግሞ ከሱ የባሰ ግፍ ያልሰራ አንድ ሰው ለመዳኑ ሊጠራጠር አይገባም። ይገባል ከተባለም በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ። የክርስትና መሠረተ አእማዶች "እንዲህ ብንባል ምን እንላለን?" በሚል መጠበብ ውስጥ የተፈጠሩ ስለሆኑ በየቦታው እያፈሰሱ የሚደፈኑ ቀዳዳዎች በርካታ ናቸው። t.me/yahyanuhe
Show all...
👍 82 12🏆 4🥰 1😱 1
📚 የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች 📌 ክፍል 14 በቲክቶክ ቪዲዮ https://vm.tiktok.com/ZM66eUkdc/
Show all...
👍 16
Photo unavailableShow in Telegram
የምስራች ... ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ከኡስታዝ አቡ ሐይደር ጋር በመተባበር እየሰጠ ያለው የሙቃረና ስልጠና 2ኛ ዙር ምዝገባ እነሆ ተጀምሯል። በባለፈው ዙር ለመሰልጠን እድሉን ያላገኛችሁ ሰዎች በዚህ ዙር በመመዝገብ ትምህርቱን በአካል ተገኝታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ። በዚህ ስልጠና ሴቶችንም ለማካተት ስለተሞከረ ፍላጎት ያላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። ለመመዝገብ በዚህ የቴሌግራም አድራሻ መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ፦ T.me/yahyanuhe1
Show all...
35👍 15🔥 3🥰 1🤩 1
“እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ #ጥቁር ነኝ ነገር ግን #ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።”   — መኃልየ. 1፥5 መጽሀፍ ቅዱስ የጥቁርነትን Default አስቀያሚነት አድርጎ ያቀርበዋል። ሰለሞን በዚህ አውድም መሠረት ጥቁርም ብሆን (ጥቁርነት አስቀያሚነት ስለሆነ) እኔ ግን ለየት እላለሁ አስቀያሚ አይደለሁም ማለት ነው። አንድ ሰው "ኢትዮጵያዊ ብሆንም ግን ቆንጆ ነኝ" ካለ በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አስቀያሚዎች ናቸው ማለት ነው። ከአስቀያሚዎች ጎራ ቢገኝም በውበት ረገድ ራሱን እየነጠለ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህንን አንቀጽ እየጠቀሱ "ጥቁርነት ውብነት ነው" እያሉ የሚጃጃሉብን ሰዎች አንቀጹን እንኳን ስረ መሰረቱን እንዳልተረዱት የሚያሳይ ነው። እርግጥ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ባርነትን አስመልክቶ ያለው ትምህርት ያልተሽሞነሞነና ፊትለፊት በመናገር የሚታወቅ ስለሆነ መሠል አንቀጾችን በጥንቃቄ ማጥናት ላያስፈልግ ይችላል። ___ © የሕያ ኢብኑ ኑህ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 37 2
“እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ #ጥቁር ነኝ ነገር ግን #ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።” — መኃልየ. 1፥5 መጽሀፍ ቅዱስ የጥቁርነትን Default አስቀያሚነት አድርጎ ያቀርበዋል። ሰለሞን በዚህ አውድም መሠረት ጥቁርም ብሆን
Show all...