cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Show more
Advertising posts
13 182Subscribers
+624 hours
+717 days
+40430 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViewsSharesViews dynamics
01
የሸይኽ ሙሐመድ ዑስማን ማራኪ ቲላዋ ነው፣ አድምጡት https://t.me/Qurantilawas
1 0693Loading...
02
"ጎንደር ላይ 500 ሚሊየን ብር የሚፈጅ አውዳሚ ዩራኒየም ቦንብ ከሙስሊሞች ይዘናል" ብለው የጎንደሩን ጭፍጨፋ ሲያጋፍሩ ከነበሩ ቀጣፊ ግለሰቦች መካከል ነበሩ፥ ሊቀ ኅሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ..! በወቅቱ በፈጸሙት ግዙፍ ውሸት ምክንያት ሀፍረታቸውን ለመሸሸግ ሲኖዶሱ ከቦታው ዘወር አድርጎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አምጥቷቸው የነበረ ቢሆንም አሁን ጉዳዩ የተረሳሳ ሲመስል በአቡነ አብርሀም የድጋፍ ደብዳቤ አማካኝነት ወደ ማዕከላዊ ጎንደር የቀድሞ "ስራቸው" ተመልሰዋል። https://t.me/Yahyanuhe
1 7790Loading...
03
ማርያም በእቅፏ የነበረው ልጇ "ሰማያትና ምደርን ያስገኘው የአለማት ፈጣሪ" ነው ብላ ታምን ነበርን? ___ https://t.me/Yahyanuhe
2 64523Loading...
04
አንዳንድ ጉዳዮችን በዝርዝር ከመጻፍ አጠር አድርጎ በሜሜ ማቅረብ የተሻለ ሀሳቡን ሊያብራራ ይችላል..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
2 69413Loading...
05
በውጭ ሀገር ያሉ ሙስሊም ነበርን እያሉ የሚዋሹ ሰዎች ደግሞ ሲጠየቁ የሚመልሱት መልስ በሳቅ ድክም ነው የሚያደርገው። አንዱን በእንግሊዝኛ እየጠየቁት "እርግጠኛ ሙስሊም ከነበርክ ከየትኛው ጀመዓ ነበርክ?ከሳንቡሳ ወይንስ ከመንዲ ጀመዓ ነበርክ?እርግጠኛ ነን ከመንዲ ጀመዓ ነበርክ እነሱ ናቸው ከሀቅ ያፈነገጡት" ሲሉት እሱም ተቀብሎ "ኧረ በፍጹም እኔ ከሳንቡሳ ጀመዓ ነበርኩ" ብሎ የምሩን መለሰ፤ በእርግጥ እንደኔ የመንዲ ጀመዓ ይሻለው ነበር 🙌
4 76612Loading...
06
Media files
5 32112Loading...
07
በዛሬው እለት በግፍ የተገደሉት ሶስቱ የአንድ ሰው ልጅ ናቸው፣ የሀ*ማ*ሱ መሪ የእስማኤል ሀኒዓ ልጆች..!በተጨማሪም ሶስት የልጅ ልጆቹንም ገድለውበታል። ታዲያ ዜናውን ሲያረዱት የሚያሳየውን ምስል ለተመለከተ "ምን አይነት ፍጡራን ናቸው?" ያስብላል። እንዳቀረቀረ " ይህንን ክብር ላጎናጸፈን አሏህ ምስጋና ይገባው፣ ልጆቼ ከሌሎች የፍልስጤማውያን ልጆች የተለዩ አይደሉም። ጠላቶች ልጆቼን በመግደላቸው ሁኔታዎችን የሚቀያይሩ ከመሰላቸው ግን ተሳስተዋል" ... አሏህ የጽዮናውያንን መጥፊያ በዘመናችን ያሳየን..!
5 8307Loading...
08
ከዒድ ዕለት ጀምሮ ወደተውነው ወንጀል መመለስ ለሸይጧን "የእንኳን ደህና መጣህ" አቀባበል ከማድረግ የሚተናነስ አይደለም።
5 1034Loading...
09
نحو المجهول ،، الجزء الاول https://youtube.com/watch?v=B1p9w2FNMGk&si=3AO225-TMA_qFst9
950Loading...
10
እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን፣ አሏህ ዒባዳቸውን ከተቀበላቸው መካከል ያድርገን፥ ዒድ ሙባረክ
5 0084Loading...
11
የነብዩ "ﷺ" ልጅ ኢብራሒም በሞተበት ቀን የጸሀይ ግርዶሽ ተከስቶ ነበር። ሰዎቹ ክስተቱን ከሳቸው ልጅ መሞት ጋር በማገናኘት የሀዘን ምልክት አድርገው ወስደውት ነበር። ኃላ ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ሲሰሙ ግን መሳሳታቸው ገልጸው ገሰጿቸው። ጸሀይና ጨረቃ የአሏህ ﷻ ተአምራት/ምልክቶች መሆናቸውን የጸሀይ ግርዶሽም በአንድ ሰው ሞትም ሆነ ህይወት ምክንያት የሚፈጠር እንዳልሆነ አብራርተው ስህተታቸውን አረሙ። አንድ ሀሰተኛ ነብይ ቢሆን መሠል ወርቃማ እድልን ፈጽሞ አያሳልፍም ነበር። ክስተቱን ተመርኩዞ አይደለም በተቃራኒው ሊናገር ይቅርና ሀሳቡን በማጠናከር "ተመልከቱ በልጄ መሞት ሰማይ እንዴት እንዳዘነ" በሚል ለዚህ ሀሳብ መጀመሪያውኑ የቀረቡ ሰዎችን በተሻለ ለማሳመን እድሉን ይጠቀምበት ነበር። ግን ለእውነተኛ ነብይ ከእውነት በላይ ማስረጃም ጉዳይም የለውምና ይህንን የሚያደርጉበት ምክንያት ስልነበራቸው ፈጽሞ አላደረጉትም፣ ማድረግም አይጠበቅባቸውም ነበር..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
5 62813Loading...
12
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፊጥር በዓል ኢንሻአላህ ረቡዕ ይከበራል። ነገ ማክሰኞ የረመዷን የመጨረሻው ቀን ይሆናል።
3 7926Loading...
13
በተከበረው ወር ጾመኛ ሙስሊሞችን ከመስጅድ ሲወጡ ጠብቆ መግደል የአረመኔነት ጫፉ ነው..!ሙስሊሙ ከግድያ ጀምሮ እስመታገት በተወለደበት ቀየ እየደረሰበት ያለው በደል ተዘርዝሮ አያልቅም። ሟቾችን አሏህ ይዘንላችሁ፣ ያላችሁትንም አሏህ ይጠብቃችሁ..!
4 1669Loading...
14
ወዳጆች ሆይ! በመልካም ዱዓ አንረሳሳ
3 7201Loading...
15
ስለ "Halal Jobs" ይህ ፕላትፎርም የተከፈተው ሐላል የሆኑ የስራ ማስታወቂያዎችን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማድረስ ሲሆን፥ አዲስ ስራ ለሚፈልጉ፣ ስራ መቀየር ላሰቡና እንዲሁም ቀጣሪዎች የስራ ማስታወቂያቸውን በነፃ እንዲለቁበት በማሰብ የተዘጋጀ ፕላትፎርም ነው!። ጆይን ያድርጉት፣ ሼርም ያድርጉት https://t.me/HalalJobsEth
4 26113Loading...
16
"ኢየሱስ ተሰቅሎ አንዴ ድነናል፣ መጨረሻችንም ገነት መሆኑን እናውቃለን" የምትሉ ወንጌላውያን ክርስቲያኖች ለምን ቤተ ክርስቲያን እንደምትሄዱ አይገባኝም። እንደ አምነታችሁ ከሆነ ስራም አያስፈልጋችሁም፣ እኛንም በመስበክ መባተል አይጠበቅባችሁም..! ለምንስ ትደክማላችሁ?ግን እንዴው ለህሊናችሁ እንዲሆን ቁርአን እንዳለው በትክክል "የገነት ነን" የሚለውን ካረጋገጣችሁ እስኪ ከልባችሁ ሞትን ተመኙ..! አንዳችሁም እንደማትመኙት ውስጣችሁ ያውቀዋል። ለስራ የደከመ ሰነፍ ግለሰብ እንጅ አቅል ያለው ሰው እንዴት ይህንን ሀሳብ በህይወቱ ተቀብሎ እንደሚኖረው ሳስበው እራሱ ይገርመኛል።
2 96310Loading...
17
እውን ቁርአን እርስ በርሱ ይጋጫልን? ❐ ቀዳሚ ቃል ቁርአን ከአምላካችን አላህ (سبحانه وتعالى ) የተሰጠን መለኮታዊ መፅሀፍ በመሆኑ በውስጡ ምንም አይነት የእርስበርስ ግጭት እንደሌለበት እኛ ሙስሊሞች እናምናለን። አንድ "መለኮታዊ" የተሰኘ መፅሀፍ ውስጡ ከእርስ በርስ መጣረስ የፀዳ ሊሆን እንደሚገባ ሁሉም ሰው ይጠብቃል። የእርስ በርስ ግጭት ስንል ከሀሳብ ግጭት ጀምሮ የቁጥር፣ የጊዜ፣ የቦታ ወዘተ ግጭቶችን ያካትታል። መነሻ ላይ የተናገረውን መድረሻ ላይ በተቃራኒ ቃል የሚያፈርስ መፅሀፍ አይደለም የአምላክ ቃል ሊሆን ይቅርና የአስተዋሽ ደራሲ ውጤትም ሊሆን አይችልም። ከዚህ በመነሳት እኛ ሙስሊሞች መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ስንሰነዝር ቆይተናል። መፅሀፍ ቅዱስ አያሌ የእርስ በርስ ግጭቶችን በውስጡ አቅፎ የያዘ መፅሀፍ እንደሆነ የሚገልፁ የተለያዩ ድርሳናት በተለያዩ ቋንቋዎች ለዘመናት ሲቀርቡ ኑረዋል። ለሀገራችን አንባቢያን እንዲጠቅም በማሰብም ከዚህ በፊት "ስቲሮት" በሚል ርዕስ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የሚገኙ በቁጥር ከመቶ በላይ የሚሆኑ ግጭቶችን በማጠናቀር በአማርኛ ቋንቋ መጠነኛ መፅሀፍ አዘጋጅቼ ነበር ¹ ሌሎች ወንድሞችም በተመሳሳይ በራሳቸው መንገድ ከመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያገኟቸውን የእርስበርስ መጣረሶች በተለያዩ ጊዜያት አስነብበዋል፤ ጠይቀዋል። ነገር ግን እነዚህን መጣረሶች አስመልክቶ በክርስቲያኖች ዘንድ የተሰጡ ምላሾች እምብዛም የሚባሉ ናቸው። በዚህ ዘርፍ ምላሽ ለመስጠት የሞከሩ ጥቂት የክርስቲያን ፀሀፍትን ስራዎች ብንመለከት "ምላሽ" ተብለው የቀረቡ ሀሳቦች ከነ አካቴው ሊያስገርሟችሁ ሁሉ ይችላሉ። የአንዳንዶቹ መልስ "ቢጋጭ ምን ችግር አለው?" ወይንም "የቁጥርና መሠል ግጭት መኖሩ እምነታችን ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ የለውም" የሚሉ "ምላሾች" ነበሩ። ዳንኤል ተሾመ የተሰኘ የክርስቲያን ፀሀፊ "ይኸውና መልሴ" በሚል ርዕስ ምላሽ ለመስጠት በሞከረበት መጽሀፉ ላይ የመፅሀፍ ቅዱስ ስህተቶችን አስመልክቶ የሚከተለውን ይላል፦ " .በአንፃሩ ደግሞ ቅዱሳን ሰዎች በጊዜና በቦታ ውስን ስለሆኑ፣ ሁሉንም አይነት እውቀት ለምሳሌም መልክዓ ምድራዊ፣ ሥነ ቋንቋዊ፣ የሥነ ጹሁፍ፣ ልዩ ልዩ መረጃዎች .. ወዘተ ስለማያውቁ (በከፊል ካልሆነ በቀር) በሥነ ጹሁፋቸው ውስጥ እንደ መረጃ ስሕተት፣ የጊዜ አቆጣጠር መዛባት፣ እንደ ታሪካዊ ቅንብር ያለ ጉድለት ሊኖር ግድ ነው" ² በሌላ ቦታ እነዚህን የስምና የአሀዝ ግጭቶች አስመልክቶ ፀሀፊው ሲናገርም እንዲህ ይላል፦ ".. ስለዚህ የቦታ፣ የስምና የአሃዛት ልዩነት መከሰቱ እንግዳ ነገር አይደለም፤ ጸሀፊዎቹ የተሰጣቸውን መለኮታዊ መልዕክት በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋና በሥነ ጹሁፍ በኩል ስለሚያስተላልፉ፣ በዚያም ዘመን መረጃዎችን እንደ ልብ የማግኘትም ሆነ ወዲያው የመዘገብ ሁኔታ ስለሌለ፣ እስኪዘገብም ድረስ በትውስታ መልኩ ወደ ቀጣዩ ትውልድ ስለሚተላለፍ፣ መዘገብ በሚጀመርበት ጊዜ የቦታ፣ የስምና የአሃዛት ልዩነት ሊፈጠር ይችላል" ³ በተመሳሳይ ዶ/ር ተስፋየ ሮበሌ "የትምህርተ ሥላሴ መሠረታውያን፥ መጽሀፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ምክንዮአዊ ትንታኔ" በተሰኘው መጽሀፉ ላይም እንዲህ ይላል፦ "..2ኛ ሳሙኤል 10፥18፤ 1ዜና 19፥18 ላይ በ700 እና በ7,000 መካከል ያለው ልዩነት፣ በጥንት ጊዜ ክፍሉ ሲገለበጥ የተፈጠረ ስሕተት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ዐይነቱ የግልበጣ ችግር በወል የሚስተዋለው በእንዲህ ዐይነቱ ሁኔታ ውስጥ ነው.." ⁴ ከዚህ ጋር ተያይዞ ጥቅል በሆነ መልኩ የመፅሀፍ ቅዱስን ይዘትና የፀሀፊዎችን ማንነት አስመልክቶ ያለውን ግራ መጋባት መምህር ያሬድ ሽፈራው "የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ" በተሰኘው መፅሀፉ የመጀመሪያው ቅጽ (ቅጽ ፩) ላይ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፦ "በዘመናችን አንድ መጽሀፍ የመጽሀፉን ርእስ፣ የጸሀፊውን ስም፣ የተጻፈበትን ቀን፣ የታተመበትን ማተሚያ ቤትና ሀገር እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መረጃዎችን ስለሚይዝ ስለመፅሀፉ ለመናገር ይቻላል። ሆኖም ቅዱሳን መፅሀፍት በተጻፉበት ወቅት ይህንን ዘመናዊውን የመረጃ አሰጣጥ መንገድ ተከትለው ስላልተፃፉ የተፃፉበትን ጊዜ በርግጠኝነት ለማወቅና በማን እንደተፃፉ ለመረዳት እጅግ አዳጋች ሊሆን ችሏል" ⁵ በዚህ ዘርፍ ጠቃሚ መልስ የሌላቸውና ተስፋ የቆረጡ አካላት የተሻለ መስሎ የታያቸው አካሄድ በተቃራኒው "ቁርአን ውስጥም ግጭት አለ" የሚል መከራከሪያ በማንሳት ጥያቄውን በአፀፋ ለመመለስ መሞከር ነው። በዚህም "መፅሀፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን ቁርአንም ይጋጫልና ብዙ አይገርምም" የሚልን መልዕክት በቀላሉ በማስተላለፍ መልስ የሰጡ የመምሰል ኢ-አመክኗያዊ ብልጠት ነው። የነሱን ለራሳቸው ትተን ያመጡትን ስሁት ንጻሮ/False comparision/ በራሳችን መንገድ እንመልሳለን። ይህንን አስመልክቶ "በእውኑ ቁርአን ይጋጫልን?" የሚለውን ጥያቄ አንስተን በጥልቀት ካየን መልሱ "በፍፁም" የሚል ነው። ይህንን አስመልክቶ ከምንም በፊት እራሱ ቁርአን ማስተማመኛውን እንዲህ ሲል ይሰጠናል፦ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 82) ሙሐመድ ፉዓድ አብዱልባቂ የዚህን የቁርአን መልዕክት አስመልክቶ የምንመረምርበት/የምናረጋግጥበት ሁለት መንገድ አለ ይላል። አንደኛው መንገድ ቁርአንን ሙሉ ለሙሉ በማጥናት የሚጋጩ አንቀፆች እንደሌሉ ማረጋገጥ ነው። ይህኛው መሠረታዊና የሚተገበር ቢሆንም ከሁለተኛው አንጻር ትንሽ አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ነው። ሁለተኛው አካሄድ ደግሞ እራሱ ይህንን የቁርአን አንቀፅ ብቻ በመመልከት ረቂቅ በሆነ መልኩ የምናረጋግጥበት ሌላኛው መንገድ ነው። ስለ ግጭት የሚያወራውን የቁርአን አንቀጽ በዚህ መልኩ መፃፍና አንድ አስገራሚ እውነታ መመልከት እንደምንችል ያብራራል፦ "ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ اخْتِلَافًا كَثِيرًا "ኢኽቲላፈን ከሲረን" ባገኙ ነበር፡፡" ወይንም "ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙ اخْتِلَافًا "ኢኽቲላፈን" ባገኙ ነበር፡፡" ቃላቶቹን መልሰን ስንሰድራቸው የሚከተለውን አረፍተ ነገር እናገኛለን፦ "ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን "ኢኽቲላፈን/" ባገኙ ነበር፡፡" ይህንን ያስተዋለ ጎበዝ ምክንያታዊ ሰው ቀጥታ የሚያደርገው ተግባር ልዩነትን ለመግለጽ የገባውን "ኢኽቲላፈን" የሚለውን ቃል ትርጉሙን ለጊዜው አቆይቶ ቃሉን ሌጣውን በሙሉ በአረብኛው ቁርአን ውስጥ መፈለግ ነው። ምክንያቱም ቁርአኑ ከአሏህ ባይሆን ኑሮ ብዙ ኢኽቲላፈን የሚለው ቃል ይገኝበት ነበር የሚል ውስጠ ትርጉምም ይወስዳልና። በዚህም በቀላሉ የቁርአን ባለቤት አንድን ቃል በ"መጠቀም" እና እንዲሁ በ"ማንሳት" መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ የተረዳ እንደሆነ ማወቅ ይችላል። ያ ብልህ ምክንያታዊ ሰውም ኢኽቲላፈን የሚለው ቃል ቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው ብዙ ጊዜ ሳይሆን አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ በቀላሉ ይረዳል ማለት ነው። ይህም ቁርአን ስለልዩነት የሚያወራውን አንድ ቃል ልዩነት እንደሌለ በገለጸበት ኹናቴ ቃሉንም የተጠቀመው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ይረዳል ⁶
2 6695Loading...
18
ስለዚህም ቁርአን ከአላህ ሌላ የነበረ ቢሆን ኖሮ በውስጡ ብዙ "ኢኽቲላፈን" ይገኝበት ነበር። ቁርአን ስለፅንሰ ሀሳብ እያወራ ቃል ሲጠቅስም መልዕክቶችን አዝሎ ነው። ምናልባት አንድ ሰው ይህንን ሲመለከት ድንገታዊ ግጥምጥሞሽ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ሊሰነዝር ይችላል። መልሱ ግን "አይደለም" የሚል ነው። ምክንያቱም እንዲህ አይነት አስደናቂ አንቀፆች በዚህ አንቀፅ ብቻ የተገደቡ አይደሉም። ቁርአንን ያጠና ሰው መሠል አንቀፆችን ያስተውላል..! አንድ እንጨምር፦ "ዋሂዳ وَحِيدًا" ወይንም "አንድ" የሚለው ቃል ቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው በሚከተለው አንቀፅ ላይ ነው። ذَرْنِي وَمَنْ خَلَقْتُ وَحِيدًا አንድ ኾኖ ከፈጠርኩት ሰው ጋር ተዎኝ (እኔ እበቃሃለሁ)፡፡ (አል ሙደሢር - 11) ይህ "አንድ" የሚለውን ቃል ትርጉም የሚይዘው "ዋሂዳ وَحِيدًا የተሰኘ ቃል በቁርአን ውስጥ ስንት ጊዜ የተጠቀሰ ይመስልዎታል? መልሱ ቀላል ነው፤ አንድ ጊዜ ብቻ..! መሠል የቁርአን መልዕክቶች ጥልቀት ባለው መልኩ ጥናት የሚያስፈልጋቸውና ከተራ ትርጉም በዘለለ የግል ጥረትንም የሚጠይቁ ናቸው። ቁርአን ተጋጭቷል በሚል በአላዋቂ ሚሽነሪዎች የሚቀርቡ ሀተታዎችን አስተውሎ ለተመለከተ ሰው አይደለም መሠል ጥናት ውስጥ ሊያልፉ ይቅርና የትርጉም አንቀፆችን እንኳን በአርምሞት እንዳልተመለከቷቸው ይረዳል። በአንድ መፅሀፍ ውስጥ "በለጠ ወደ አዲስ አበባ ሔደ" የሚል አረፍተ ነገርና በሌላ ቦታ ደግሞ "በለጠ ወደ ጎንደር ሔደ" የሚል ሌላ አረፍተ ነገር ቢያገኙ ለነዚህ ሰዎች ምናልባት ግጭት ተደርጎ ታይቷቸው ሊያስገርሟችሁ ይችላሉ። ለነሱ በለጠ አንዴ አዲስ አበባ ከሔደ ሌላ የትም ቦታ ሊሄድ የማይችል ሚስኪን ግለሰብ ነው። እነሆ ከዚህ በኃላ በሚቀርበው ተከታታይ ፁሁፍ እያንዳንዳቸውን ቁርአን ላይ የሚቀርቡ የግጭት ክሶች በአሏህ ፍቃድ ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል። በዚህ ዘርፍ እስካሁን ያለውን ጥያቄ በአላህ ፍቃድ በተቻለ መጠን በዚህ ተከታታይ ፁሁፍ ዘርዝረን የምናጠናቅቀው ይሆናል። ማጣቀሻዎች 1/ ስቲሮት፥ ከ100 በላይ የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች - የሕያ ኢብኑ ኑህ 2/ ዳንኤል ተሾመ - "ይኸውና መልሴ" ገጽ 10 3/ ዳንኤል ተሾመ - "ይኸውና መልሴ" ገጽ 84 4/ ዶ/ር ተስፋየ ሮበሌ - የትምህርተ ሥላሴ መሠረታውያን፥ መጽሀፍ ቅዱሳዊ፣ ታሪካዊና ምክንዮአዊ ትንታኔ ገጽ 142 5/ ያሬድ ሽፈራው ፤ የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪካዊ አመጣጥ ቅጽ ፩ ገፅ 7 6/ Muhammad Fu'ad Abd al-Baqi, Al-Muahjam al-Mufahris li al-Fadh al-Qur'anal-Karim, 1997, Dar al-Fikr, Beirut (Lebanon), p. 305.
3 4577Loading...
19
Media files
2 3880Loading...
20
እስልምናን በመደዴ ባህሪ የሚሳደቡ ሰዎች ከማንም በላይ የሚያሳዝኑት እነሱ ናቸው። ውስጣቸው የሚንከባለለውን የሰላም እጦት ለማስታገስ ትኩረት ፍለጋ ስድብ ውስጥ ይኳትናሉ። የሚጠቅማቸው ስለሚመስላቸው እንጅ በሽታቸውን ከማባባስ የዘለለ ሚና የለውም። በእርግጥ ብዙዎቹ እራስን ለማጥፋት ሳይቀር ህሊናቸው ጋ የሚታገሉ ብኩኖች ናቸው። መሠል ነውረኛ ሰዎች ለሚናገሩት ጸያፍ ንግግር ተጠያቂ እንደማይሆኑና ሙስሊሙም ምንም እንደማያመጣ ስለተረዱት ልቅ አፋቸውን ከማላቀቅ መሳቀቅ አቁመዋል። .. እኛም የምናመቻምቸው ጉዳይ እየበዛ የመጣ ይመስላል። ከምንም በላይ የሚያሳዝነው ግን በአደባባይ የተነገረን ግልጽ ወንጀል እንኳን ከፌስቡክ ውግዘት በዘለለ መሬት ወርዶ በህግ የሚፋረድና የምንተማመንበት ተቋም አለመኖሩ ነው። መጅሊሱ የህግ ክፍል የለውም? መሠል ግልጽ የህግ ጥሰቶችን የሚጠይቅስ ስብስብ የለንም? በቅርቡ ልጅ ያሬድ የሚባል አንድ ግለሰብ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በይፋ በተናገረው ጸያፍ ንግግር ሳቢያ ቤተ ክርስቲያኗ ክስ መስርታ በህግ እንዲጠየቅ አድርጋለች። መሠል ተግባር ውስጥ የሚሳተፉና እስልምናን የሚሰድቡ ሰዎችስ በህግ የሚጠየቁበት የህግ ማዕቀፍ በመጅሊሱ በኩል አሁንም የለም?በበጎ ፈቃደኝነት መሠል ነውረኛ ሰዎችንስ ለሰሩት ተግባር ዋጋ እንዲከፍሉ የሚያደርግ የዲን ክብር የሚያስጨንቀው የህግ ባለሙያ ስብስብ የለንም?ከተግባሩ ባልተናነሰ ምንም እንደማናመጣ ታስቦ እየተፈጸመ ያለው የተግባሩ መደጋገም ውስጥ ያቆስላል..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
3 0324Loading...
21
የንጽጽር መጽሀፍት ሲታተሙ ያለውን መከራ በሒደቱ ውስጥ ያለፈ ሰው ያቀዋል። መጽሀፍቶቹ ኢምንት ትርፍ የሌላቸው አብዛኛዎቹ የታተሙበትን ዋጋ እንኳን ሳይመልሱ በኪሳራ የሚቀመጡ ናቸው። ያም ሆኖ ግን አንድ ትልቅ ትርፍ አላቸው፤ ይኸውም በመጽሀፍቶቹ ሳቢያ ብዙ ወገኖች ሒዳያን እንዲያገኙ ሰበብ ሁነዋል። በውጭ ሀገር የሚገኝ አንድ መስጅድ ውስጥ ኢትዮጵያዊ የሆነ ወገናችን ሸሀዳ ካስያዙት በኃላ ለምን እንደሰለመ ቀርበው ሲጠይቁት በአማርኛ የተጻፉ የንጽጽር መጽሀፍትን አንብቦ መሆኑን ነግሯቸዋል። አጋጣሚ ያናገሩት ሰዎች ጋ እንተዋወቅ ነበርና በደስታ ነበር የነገሩኝ..! ከዚህ በላይ ትርፍ የለም ሀቂቃ። ይህንን ትልቅ የሒዳያ ስጦታ አሏህ ሰበብ ካደረገን ዘንዳ ሌላው ዱንያዊ ኪሳራ ምንስ ሲባል ያስከፋል? .. ይህች ወገናችን በንጽጽር መጽሀፍት ሳቢያ ሙስሊም እንደነበረች ገልፃ አሁን ግን መመለሷን ትገልፃለች። ከንግግሯ የነበረባትን ጫና በቀላሉ ነበር የተረዳሁት። በዚህ አጋጣሚ የንጽጽር መጽሀፍት ምን ያህል ጠቃሚና ህዝቡ ዘንድ ተደራሽ እንደሆኑ ትልቅ ጥቆማ የሰጠ ነበር። አሏህ ﷻ ይመልስሽ ዘንድ ዱዓየ ነው። ስትሰልሚ የደረሰብሽን መከራ በልምድ እረዳዋለሁና ፈጽሞ በንግግርሽ ከሚበሳጩት አይደለሁም። ኢንሻአላህ አንድ ቀን ብርታቱን ሲለግስሽ በቁርጠኝነት መመለስሽ አይቀርም። .. በዚህ አጋጣሚ የንጽጽር ስራዎችን በዋናነት ለመስራት የተቋቋመውን ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመሆን ደግፉ እላለሁ። በማኪያቶ ዋጋ በሚደረግ ድጋፍ የብዙ ኸይር ስራዎች ተካፋይ መሆን ይችላሉ። ማዕከሉ በንጽጽሩ ዙሪያ ከሚያዘጋጀው መጽሀፍት በተጨማሪ ተከታታይ ትምህርቶችን በኦዲዮ፣ በቪዲዮና በድረ ገጽ አማካኝነት ይሰጣል። የንጽጽር ስልጠናዎችን በመላው ኢትዮጵያ በኦንላይንም በአካልም በመስጠት ላይ ይገኛል። በቅርቡ አሏህ ﷻ ፍቃዱ ከሆነ ከዚህ ዘርፍ ጋር በጥልቀት ስራ የሚሰራ የጥናት ማዕከልና የማስተማሪያ ተቋም ለማቋቋም እንቅስቃሴ ላይ ነው። ____ https://bit.ly/4aGr93u በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦ @Hidayaislamiccenter 1000499318212 Hidaya Islamic Center አጭር የንግድ ባንክ ቁጥር - 8212
2 8181Loading...
22
Media files
2 7505Loading...
23
ከአመታት በፊት ጀምሮ በተደጋጋሚ ከሚነሱ ጥያቄዎች ውስጥ "..ቁርአን አይሁዶች ኢየሱስን አልሰቀሉትም አለን እንጅ ኢየሱስ ከነ አካቴው አልተሰቀለም አላለም.." የሚለው መከራከሪያ አንዱ ነው። በዚህ ቪዲዮ ክሌሙን ፈትሸናል፣ ማብራሪያም ተሰጥቶበታል። ይመልከቱት፣ ሼርም ያድርጉት..! https://vm.tiktok.com/ZMMmNoBTm/
4 1449Loading...
24
“አይሁድም መልሰው፦ እኛ ሕግ አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና አሉት።” — ዮሐንስ 19፥7 በዚህ ጥቅስ መሰረት ኢየሱስ ሊሰቀል ሲል ጲላጦስ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም ብሎ ራሱን ነፃ ያወጣል ፣ አይሁዶች ግን ህግ አለን እንደህጋችን መሰረት ሊሞት ይገባዋል ራሱን የእግዝአብሔር ልጅ አድርጓልና ብለው ይመልሳሉ። ጥያቄ: —የትኛው የብሉይ ኪዳን ህግ ነው የእግዝአብሔር ልጅ መባል የሚያስገድለው? https://t.me/Abuyusra3
3 8627Loading...
25
መጀመሪያ ስናየው ቁርአን ነበር የመሠለን፣ ግን ቁርአን ሳይሆን የሶማልኛ መጽሀፍ ቅዱስ ነበር። "መስቀል ሳናደርግ መጽሀፍ ቅዱስ አናትምም" የሚል መከራከርያ እዚህ ሰፈር ሲዘዋወር ነበርና መጽሀፉን ስናይ መገረማችን አልቀረም። የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማኅበር ከሰሞኑ በስካይላይት ሆቴል አንድ ዐውደ ርዕይ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከወንድሜ አቡ ዩስራ ጋር በመገኘት ለመሳተፍ ችለን ነበር። በፕሮግራሙ ላይ የማኅበሩ አባል የሆኑት ሶስቱ እምነቶች በህብረት ተሳትፈውበታል። የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም ስራና ታሪካዊ ሒደቱን በስፋት ለማስቃኘት ሞክረዋል። ክርስቲያናዊ መጽሀፍትንም በማካተት የፈለገ ሰው እንዲሸምት አመቻችተዋል። ከምንም በላይ ለመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም የሰጡት ቦታ የሚያስደንቅ ነው። ለአብነት መጽሀፍ ቅዱስን በኦሮምኛ ብቻ አልተረጎሙትም። በየአካባቢው ዘይቤ ሳይቀር ተተርጉሟል። የአርሲ ኦሮምኛ ትርጉም፣ የቦረና ኦሮምኛ ትርጉም፣ የምስራቅ ኦሮምኛ ትርጉም፣ የምዕራብ ኦሮምኛ ትርጉም በሚል ለእያንዳንዱ አካባቢ በዘየው ተተርጉሞለታል። ጥቂት ክርስቲያን ያለባቸው እንደ ጉሙዝ ማኅበረሰቦች ሳይቀር የደቡብና የሰሜኑን ለዛ በጠበቀ መልኩ ሁለት አይነት ትርጉም ተዘጋጅቶላቸዋል። በዚህ ብቻ አያበቃም ጭራሽ ክርስቲያን የለባቸውም ተብሎ የሚታመኑ የሶማሌ፣ አፋር፣ ሀላባ ወዘተ አካባቢዎችም መጽሀፍ ቅዱስ በቋንቋቸው ተተርጉሞ ተሰራጭቷል። ማዳመጥ ይቸግራቸዋል ተብለው ለሚታመኑ የገጠር አካባቢዎች ድግሞ የድምጽ ንባቦች /Audiobook/ ተዘጋጅቶ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ በሶላርና ማንዋል ቻርጅ በሚደረጉ ማዳመጫ ማሽኖች ጋር በገጠሩ ተበትኗል። ላለፉት አርባ አመታት በሚሽን ስራው ከሰሯቸው መጠነ ሰፊ ስራዎች አንጻር ህዝባችን እንዴውም አልከፈረም ብሎ መናገር ይቀላል። ሙስሊሙ ዛሬ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራቸው የዳዕዋ ሜካኒዝሞች እነሱ የዛሬ አርባ አመትና አምሳ አመት የተጠቀሟቸውና የሰሩባቸው ናቸው። ቀረብ ብለን የተወሰኑትን ለቀጣይ ስላቀዷቸውና እየሰሩባቸው ስላሉ "የወንጌል ስርጭት መንገዶችም" ጠይቀናቸዋል። ያሰቡትን እየሰሩት ያሉትንም በቀናነት አብራርተዋል። ትላንት ዛሬ ባይሆንም ሰዎቹ ግን አኼራችንን ለመቀማት ለሰከንድም የሚያርፉ አይመስሉምና አብዝቶ መስራት ግን ያስፈልጋል። ___ https://t.me/Yahyanuhe
4 81814Loading...
26
Media files
4 12514Loading...
27
Media files
4 18414Loading...
28
Media files
300Loading...
29
"ከሰዎች መካከል አሉ፣ ይጾማሉ ግን ከጾማቸው ረሀብን እንጅ አያተርፉም" ሱነን ኢብን ማጃህ 1690
4 1325Loading...
30
Media files
4 22512Loading...
31
ቀልድ አይደለም..! እስልምናን የሚተች አንድ የቴሌግራም ቻናል ነው ብለው ወንድሞች ልከውልኝ ሳየው ያገኘሁት ነው። ቁርአን ከአማርኛ ቋንቋ የተዋሳቸው ቃላት አሉ በሚል ሲያቀርብ የተጠቀመው ነው። ሁለቱ ቃላት ማለትም "ፈርስና ፈረስን" በቅጡ መለየት አልቻለም። አፕልኬሽኑ እንኳን ቢያሳሳት ሰው ኮንቴክስት አይቶ እንዴት መረዳት ይሳነዋል? እስልምናን ሲተቹ የምትመለከቷቸው አብዛኛዎቹ ተሳዳቢዎች እውቀት ላይ እንዲህ መናኛ ናቸው። የአማርኛ ቋንቋ በመሠረቱ ለአረብኛ ቃላት ምንጭ መሆን የሚችል አይደለም። እድሜውም ለዚያ አያበቃውም። ባየ ይማም "የአማርኛ ሰዋሰው" በተሰኘ መጽሀፉ መቅድም ላይ አማርኛ ቋንቋ ከተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትን በመዋስ የተፈጠረ ድብልቅ ቋንቋ እንደሆነ ይገልጻል። ፈረስ የሚለው ቃልም እንዲሁ የተውሶ ቃል መሆኑን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፦ "አማርኛ የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገር በነበረ ዘማችና አዝማች የተፈጠረ የሠራዊት ቋንቋ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ መሠረታዊ መድበለ ቃላቱ ባብዛኛው ሴማዊ ሲሆኑ፣ በመጠኑ ደግሞ ኩሻዊ ናቸው፡፡ ለዚህ እንደውሻ፣ ካራ፣ ውሃ፣ ሸኮና፣ አኮሌ፣ አሬራ፣ ኮርቻ፣ ቀብድ፣ #ፈረስ፣ ዱላ፣ ወዘተ. ያሉት ቃላት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል" ባየ ይማም "የአማርኛ ሰዋሰው" መቅድም የአማርኛ ቋንቋ በመሠረቱ ልሳነንጉስ የሆነው በ1272 በአጼ ይኩኖ አምላክ ነበር። ከዚያ በፊት ይታወቅም ይነገር የነበረውም ቋንቋ ግዕዝ ሲሆን አማርኛም ድብልቅ ቋንቋ ሁኖ መነገር ሲጀምር ነገስታቱ ከዛግዌ ለተረከቡት ሰለሞናዊ ስርአት ይፋዊ መነጋገሪያ አደረጉት። እውነታው ይህ ነው፣ ትንሽም ቢሆን ማስተዋልና ማንበብ የታከለበት ሰው መሠል ስህተት ውስጥ አይወድቅም። ___ https://t.me/Yahyanuhe
3 5035Loading...
32
ሸይጧን በረመዷን ታስሯል ካላችሁ ለምን ኃጥያት ላይ ትወድቃላችሁ?ሸይጧን ከታሰረ እንዴት ወንጀል አልጠፋም? ጥሩ ጥያቄ ነው፣ እስኪ በአጭሩ እንደሚከተለው እናብራራው፥ የሰውን ልጅ ወደ መጥፎ ተግባራት የሚመሩት ሁለት አካላት ናቸው። እነሱም፦ 1- የሰይጣን ጉትጎታ (شَرِّ الشَّيْطَانِ) 2- የነፍስ ጉትጎታ (شَرِّ نَفْسِي) ናቸው። የሰው ልጅ ከሸይጧን ጉትጎታ በተጨማሪ የነፍስያው ጉትጎታም ሀራም ተግባራት ላይ ይጥሉታል። ስለዚህም ሸይጧን መታሰሩ ብቻ የሰው ልጅ መጥፎ ከመስራት አያቅቡትም፣ ነፍሱንም ጭምር መግራት ካልቻለ በቀር..!በመሠረቱ የሸይጧን ጉትጎታም ደካማ ተብሎ በቁርአን ተጠቅሷል። ነፍስ በዚህ በኩል የምትፈጥረው ጉትጎታ ቀላል አይደለም። ለዚህ ምንድን ማስረጃው ከተባለ የሚከተሉት የቁርአን አንቀጾችና ሀዲሳት ይጠቀሳሉ፦ ◾️ ማስረጃዎች፡- 1- ቁርኣን እንዲህ ይላል፦ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي "...ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡.." (ቁርኣን 12፡53)። 2- ቁርኣንም ደግሞ እንዲህ ይላል፦ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَّيْبِينَ "ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡" (ቁርኣን 50፡16)። 3- ነቢዩ "ﷺ" ይህንን ዱዓ አስተምረውናል፦ أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ "ከነፍሴ ክፋት ከሰይጣንም ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ" ["አቡ ዳውድ"፣ 5067 - صحيح]። 4- ነቢዩ "ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ "ሙጃሂድ (ታጋይ ማለት) ነፍሱን የሚታገል ነው።" ["ቲርሚዚ", 1621 - صحيح]. 5- ቁርኣንም እንዲህ ይላል። وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَى "በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፥ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ (ቁርአን 79፡40-41)። ወሏሁ አዕለም..! © አቡ ሐይሰም (Yahya) ___ https://t.me/Yahyanuhe
3 33017Loading...
የሸይኽ ሙሐመድ ዑስማን ማራኪ ቲላዋ ነው፣ አድምጡት https://t.me/Qurantilawas
Show all...
🥰 17👍 6
"ጎንደር ላይ 500 ሚሊየን ብር የሚፈጅ አውዳሚ ዩራኒየም ቦንብ ከሙስሊሞች ይዘናል" ብለው የጎንደሩን ጭፍጨፋ ሲያጋፍሩ ከነበሩ ቀጣፊ ግለሰቦች መካከል ነበሩ፥ ሊቀ ኅሩያን አባ ዮሴፍ ደስታ..! በወቅቱ በፈጸሙት ግዙፍ ውሸት ምክንያት ሀፍረታቸውን ለመሸሸግ ሲኖዶሱ ከቦታው ዘወር አድርጎ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አምጥቷቸው የነበረ ቢሆንም አሁን ጉዳዩ የተረሳሳ ሲመስል በአቡነ አብርሀም የድጋፍ ደብዳቤ አማካኝነት ወደ ማዕከላዊ ጎንደር የቀድሞ "ስራቸው" ተመልሰዋል። https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
ማርያም በእቅፏ የነበረው ልጇ "ሰማያትና ምደርን ያስገኘው የአለማት ፈጣሪ" ነው ብላ ታምን ነበርን? ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 45😢 11🤷‍♂ 2 2🙉 2
አንዳንድ ጉዳዮችን በዝርዝር ከመጻፍ አጠር አድርጎ በሜሜ ማቅረብ የተሻለ ሀሳቡን ሊያብራራ ይችላል..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 118🤩 7🙉 5😱 2🙊 1
በውጭ ሀገር ያሉ ሙስሊም ነበርን እያሉ የሚዋሹ ሰዎች ደግሞ ሲጠየቁ የሚመልሱት መልስ በሳቅ ድክም ነው የሚያደርገው። አንዱን በእንግሊዝኛ እየጠየቁት "እርግጠኛ ሙስሊም ከነበርክ ከየትኛው ጀመዓ ነበርክ?ከሳንቡሳ ወይንስ ከመንዲ ጀመዓ ነበርክ?እርግጠኛ ነን ከመንዲ ጀመዓ ነበርክ እነሱ ናቸው ከሀቅ ያፈነገጡት" ሲሉት እሱም ተቀብሎ "ኧረ በፍጹም እኔ ከሳንቡሳ ጀመዓ ነበርኩ" ብሎ የምሩን መለሰ፤ በእርግጥ እንደኔ የመንዲ ጀመዓ ይሻለው ነበር 🙌
Show all...
🤩 120👍 30🙊 24🙉 15🍓 3🥰 2😱 2 1🔥 1
67👍 33🎉 2🤷‍♂ 1😢 1
በዛሬው እለት በግፍ የተገደሉት ሶስቱ የአንድ ሰው ልጅ ናቸው፣ የሀ*ማ*ሱ መሪ የእስማኤል ሀኒዓ ልጆች..!በተጨማሪም ሶስት የልጅ ልጆቹንም ገድለውበታል። ታዲያ ዜናውን ሲያረዱት የሚያሳየውን ምስል ለተመለከተ "ምን አይነት ፍጡራን ናቸው?" ያስብላል። እንዳቀረቀረ " ይህንን ክብር ላጎናጸፈን አሏህ ምስጋና ይገባው፣ ልጆቼ ከሌሎች የፍልስጤማውያን ልጆች የተለዩ አይደሉም። ጠላቶች ልጆቼን በመግደላቸው ሁኔታዎችን የሚቀያይሩ ከመሰላቸው ግን ተሳስተዋል" ... አሏህ የጽዮናውያንን መጥፊያ በዘመናችን ያሳየን..!
Show all...
😢 167👍 36🤩 3😱 2
ከዒድ ዕለት ጀምሮ ወደተውነው ወንጀል መመለስ ለሸይጧን "የእንኳን ደህና መጣህ" አቀባበል ከማድረግ የሚተናነስ አይደለም።
Show all...
👍 81 16😢 1
نحو المجهول ،، الجزء الاول https://youtube.com/watch?v=B1p9w2FNMGk&si=3AO225-TMA_qFst9
Show all...

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን፣ አሏህ ዒባዳቸውን ከተቀበላቸው መካከል ያድርገን፥ ዒድ ሙባረክ
Show all...
80👍 12🔥 4