cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Harun Media - ሀሩን ሚዲያ

Advertising posts
17 073
Subscribers
+3024 hours
+1647 days
+1 16630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"የሁለት አመት ልጅ እያለሁ ነበር ወደ አዲስ አበባ የገባሁት" በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ አጋታ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ጢድ ጀፎረ በኡስታዝ አቡ ሀይደር የትውልድ ስፍራ ከትመናል። ... (ሃሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ፦ግንቦት 19/2016) ... ኡስታዝ አቡ ሀይደር ጉንችሬ ለዳዕዋ በመጣበት የትውልድ ስፍራውን የጎበኘ ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት ከረዥም አመታት በኋላ ወደ ተወለደባት ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ አጋታ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ጢድ መንደርን ጉብኝቷል።ከስፍራውም ሆኖ ለኡማው መልዕክት አስተላልፏል። .... ኡስታዙ እንዳለው የዚህ ስፍራ አብዛኛ ነዋሪ በስራ፣ በትምህርትና በተለያዩ ምክኒያቶች ወደ ከተማ ፈልሷል ለአብነትም የኔ ወላጆችም ቀያቸውን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ከገቡ ሰነባብቷል እንደምትመለከቱት ቤታችን ዝግ ነው ማንም አይኖርበትም በማለት አስረድቶናል። ... ይህ ደግሞ አካባቢው ለአክፍሮት ኃይላት እንዲጋለጥ ችሏል ለዝህ ደግሞ አህለል ከይር ወንድምና እህቶች በገጠራማው የሀገራችን ክፍል መስጂድና መስድረሳ መገንባትና እምዲሁም ኡስታዞችን በመቅጠር ኡማውን ልንታደገው ይገባል በማለት ጥሪውን አስተላልፏል። .... የመልካዓ ምድር አቀማመጧና ደጋማ የአየር ንብረቷ የአካባቢው ውብ ገጽታ በሊቅ ኢንጂነር የተቀየሱ እንጂ አርሶ አደሩ የመተረውና የቀየሰው ነው ብሎ ለማመን የሚያዳግተው የውስጥ ለውስጥ መንገዶቿ ስፍታና ዲዛይን ፣ የጊቢ አጥር ድርዳሮውና እኩል ክርክም ብሎ በእንጨት የተዘጉ የአጥር ግንባታዎች ፤በእንሰት ተክል ያጌጡ ጓሮዎች፣  የአውድማው ልምላሜ ፤የነዋሪዎቿ እንግዳ አክባሪነትና ትህትናቸው ፣ቢቻ ተፈጥሮ ምንም ሳትሰስት  ሁሉንም በረከት የተቸራትን የምዕራብ ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ አጋታ ቀበሌ ገበሬ ማህበር መንደር ልባችንን ማርኮ እያሸፈተው ነበር ከኡስታዝ ጋር ቆይታችንን አጠናቀን  የተለያየነው። ... ¤ሃሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ ከስፍራው ሆኖ ያጠናቀረው ዘገባ እንደደረሰን የምናቀርብላችሁ ይሆናል። ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
👍 20 5
ሃሩን ሚዲያ  ሀገራዊ  ምክክር  ኮሚሽኑን በማስመልከት ሰፊ  የግንዛቤ  ማስጨበጫ ዝግጅቶችን    በምክክር ኮሚሽኑ ያሉ ክፍተቶችን ሲያቀርብ እንደነበር ይታወቃል :: በትላትናው  እለትም ኮሚሽኑ በሚሰጠው   መግለጫ  ተገኝተን  ጥያቄ እንድናቀርብ ተደውሎ  በዛሬው  መግለጫ   ተገኝተናል :: ሃሩን ሚዲያ   በዛሬው  እለት ሀገራዊ  ምክክር  ኮሚሽኑ   ዛሬ  በሰጠው   መግለጫ   ላይ  በመገኘት   ሀገራዊ   ምክክር   ኮሚሽኑ   ጋር  በተያያዘ በሙስሊሙ   ላይ  እየተፈፀሙ  ያሉ  ጉድለቶችን አስመልክቶ  ጥያቄ  አቅርቧል :: ... የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ጨምሮ በስሩ ያሉት የክልል እና ከተማ አስተዳደር መጅሊሶች ከተሳፊ ልየታ ጋር እንዲሁም ከአጀንዳ ጋር በተያያዘ ያነሱትን ቅሬታ አስመልክቶ ከሀሩን ሚዲያ ጋዜጠኛ ከማል ኑርዬ ለኮሚሽኑ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ኮሚሽኑም በምላሹ ቅሬታዎች መቅረቡን አምኖ ነገር ግን የተሳታፊ ልየታ ምርጫ የሚደረገው በህዝብ እንጂ በኮሚሽኑ አይደለም ብሏል።በጎንደር ከተማ ኮሚሽኑ በሚሰጠው ስልጠና ላይ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ሙስሊሞች በተመለከተ "በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠኝን ተሳታፊ አስገብቻለሁ"የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።የፌዴራል መጅሊሱ ይካተቱልኝ ያላቸውን አጀንዳዎች በተመለከተ ከመጅሊሱ ጋር በመወያየት እንደሚመለከቷቸውም ተናግረዋል። ... ¤ሀሩን ሚዲያ በቦታው በመገኘት የተከታተለውን ሙሉ መግለጫ ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል! ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
👍 22👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ! ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 19/2016) ... ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ... ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ፈርመውታል። ... በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤል ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ... ስምምነቱ ወደ ኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ሕጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል። ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
👍 15 1
"የተሳፊ ልየታ ያደረግነው በህዝብ ምርጫ እንጂ በኮሚሹኑ ስልጣን አይደለም አለ"የሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 19/2016፣አዲስአበባ) ... የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስአበባ ከተማ የክልሎች ምክክር ምዕራፍ ሊጀመር እንደሆነ ዛሬ ግንቦት 19/2016 ዓል በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል። ... የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የከተማ አስተዳደር  ክልላዊ የምክክር ምዕራፍ በአዲስአበባ ከተማ ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓል ሊጀምር ነው ።በዚህ ሂደት የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ  ተሳታፊዎችን ፣የሃይማኖት ተቋማት ፣ሲቪክ ማህበራት እና የመንግስት አካላት፣የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት ተወካዮችየሚመካከሩበት የአጀንዳ ግብዓታቸውን የሚያዘጋጁበትና በሀገራዊ ጉባኤው የሚወክሏቸውን ተሳታፊዎች የሚመርጡበት ወቅት እንደሆነ ተገልጿል ። ... ቀደም ሲል ኮሚሽኑ በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በክልላዊ የምክክር ምዕራፍ ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከየህብረተሰብ ክፍሉ ያስመረጠ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ የምክክር ሂደቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይነት ያለው የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት በሂደቱ ትርጉም ያለው ተሳታፊነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 27 በሚቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ከ2 ሺህ 500 በለይ የማሕበረሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ተጠቅሷል። ... የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ጨምሮ በስሩ ያሉት የክልል እና ከተማ አስተዳደር መጅሊሶች ከተሳፊ ልየታ ጋር በተያያዘ ከሀሩን ሚዲያ ጋዜጠኛ ከማል ኑርዬ ለኮሚሽኑ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ኮሚሽኑም በምላሹ ቅሬታዎች መቅረቡን አምኖ ነገር ግን የተሳታፊ ልየታ ምርጫ የሚደረገው በህዝብ እንጂ በኮሚሽኑ አይደለም ብሏል።በጎንደር ከተማ ኮሚሽኑ በሚሰጠው ስልጠና ላይ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ሙስሊሞች በተመለከተ "በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠኝን ተሳታፊ አስገብቻለሁ"የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።የፌዴራል መጅሊሱ ይካተቱልኝ ያላቸውን አጀንዳዎች በተመለከተ ከመጅሊሱ ጋር በመወያየት እንደሚመለከቷቸውም ተናግረዋል። ... ¤ሀሩን ሚዲያ በቦታው በመገኘት የተከታተለውን ሙሉ መግለጫ ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል! ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
👍 25 3🥰 2
የኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሙያዎች ማህበር ከቄራ መስጂድ ጋር በመተባበሩ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን ገለፀ! ... (ሀሩን ሚዲያ፦ግንቦት 18/2016) ... የኢትዮጵያ ሙስሊም ጤና ባለሙያዎች ማህበር ከቄራ መስጂድ ጋር በመተባበሩ የህክምና አገልግሎት በዛሬው ዕለት መስጠቱን የገለፀ ሲሆን ህክምናውም የአይን፣ የውስጥ ደዌ እና የህፃናት ህክምና ላይ ያተኮረ ሲሆን በዚህ ህክምና ከ100 በላይ ታካሚዎች ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል። ... እንደነዚህ አይነት ህክምናዎች ከቄራ መስጂድ በተጨማሪ በተለያዩ መስጂዶች፤የበጎ አድራጎት ተቋማት ላይ እና ክልሎች ላይ እንደሚቀጥል የማህበሩ መስራቾች አስታውቀዋል። ... በዚህ ስራ ላይ የማህበሩን ጥሪ አክብረው ለተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች እና እድሉን ያመቻቻቹ ላስተባበሩ የቄራ መስጂድ ጀማዎች ማህበሩ ምስጋናውን አቅርቧል። ... ©ሀሩን ሚዲያ
Show all...
👍 49 9
Go to the archive of posts