cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Show more
Advertising posts
13 206Subscribers
+124 hours
+477 days
+33630 days
Posts Archive
💫አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ 💫 🔅በ ክቡር ኮሌጅ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ እነሆ ለረመዳን ለተቸገሩ ወንድም እህቶች የወር አስቤዛ ለመሙላት እንቅስቃሴ እያረጉ ይገኛሉ በዚህም በተማሪ አቅም የተቻላቸውን እያበረከቱ ይገኛሉ በዚህ መልካም ተግባር ላይ አሻራውን ማሳረፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሙስሊም ለዚህ መልካም ሥራ በ አክብሮት እንጋብዘዋለን!🔅 🍇 አላህ ሁላችንም ለ ከይር ሥራ የምን ያድርገን🍇 ☄የ አንድ ቤተሰብ ሙሉ ፓኬጅ 4700 ብር ነው ☄ ፓኬጁም 🥄ዘይት 5 ሌትር 🥄ዱቄት 10 ኪሎ 🥄ሩዝ 10 ኪሎ 🥄ቴምር 5 ኪሎ ነው ::🙏 ንግድ ባንክ -1000608716665(ዩሱፍ : አብዱል ፈታህ : አብዱረሂም ) ለበለጠ መረጃ -+251991923566 - +251904600868 -+251911155794
Show all...
👍 12 4
ሁሉም ሰው ያስጨነቀውና እንዲሆንለት የሚመኘው ጉዳዮች አሉት። ከዱንያ ሀጃዎች በላይ ደግሞ የአኼራ ክጃሎታችን የላቀ ነው። ይህ ወር ትልቁ የፈረጃ ወር ነው፤ በዱዓ እንቃረብ። አሏህ ይቀበለን.! ረመዷን #1
Show all...
37👍 12
እንኳን ለተከበረው የረመዷን ወር በሰላም አደረሰን፤ ወሩን በአግባቡ ከሚጠቀሙበት ሰዎች አሏህ ያድርገን!
Show all...
66👍 21
"ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" ቁርአንን ጽፈውታልን?" በሚል ርዕስ ለአንድ ወር ሲሰጥ የነበረው የበይነመረብ ስልጠና ተጠናቋል። ቁርአንን እሳቸው ጽፈውታል በሚል የሚነሱ መከራከሪያዎችን መሠረታዊ በሆነ መልኩ የቃኘው ይህ ስልጠና በትላንትናው ዕለት የካቲት 28/2016 ተጠናቋል። ትምህርቱን ተከታትለው ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎችም የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። © ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል Picture - ሰርተፍኬቱን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የሚገኙ ናቸው።
Show all...
👏 43👍 13 12
እየመሸ ስለነበር ወደ ቤቴ ለመመለስ በጥድፊያ ላይ ነበርኩ፣ ድንገት መንገድ ላይ የተወሰኑ ፕሮቴስታንቶች ተሰባስበው ፓምፍሌት እየሰጡ ነበር። ሊሰጡኝ መፈለጋቸውን አስተውየ ከአንዳቸው ተቀበልኩና ጉዞየን ቀጠልኩ። አስር ሜትር አካባቢ እንደሄድኩ ሰዎች ሰብሰብ ብለው ያዳምጣሉ። ከፕሮቴስታንቶቹ መካከል ከአንዱ ጋር የሚወያይ ሙስሊም ነው። በጣም ብቸኩልም ቀረብ ብየ ቢያንስ 1 ደቂቃ ለማደመጥ ወሰንኩ። ፕሮቴስታንቱ በደህንነት ትምህርቱ ወቅት የሰማትን ቃል ደጋግሞ ያስተጋባል። ሙስሊሙ ልጅ መጠነኛም ቢሆን የንጽጽር ትምህርቶች እንደደረሱት በሚያስታውቅ መልኩ ለፕሮቴስታንቱ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ልጁን ግራ እንዳጋቡት ከፊቱ ያስታውቃል። አማራጭ ያጣው ፕሮቴስታንቱ ልጅ ዝምታን መርጦ ማዳመጥ ጀመረ። እሰብካለሁ ብሎ የወጣው ልጅ ተሰባኪ ሆነ፥ ውስጤን የማላቀው ደስታ እየተሰማኝ እኔም ጉዞየን ቀጠልኩ። እዚህ መንደር ስለሚሽነሪው አስጊ ስራዎች በዝርዝር ተነግሯል። ለቅሶ ደጋግመን አውርተናል፣ ሰምተናል። በዚህ ምክንያት ላለፉት አመታት ብዙው ሰው በእልህ ተሞልቶ የአቅሙን ተፍጨርጭሯል። አንዳንዶቻችን ተስፋ ቆርተን ትተነውም ይሆናል። ግን በብዙ አመታት ትግል ውስጥም ቢሆን የሆነ ቦታ ላይ ፍሬዎች መኖራቸው ግን ምንም ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው። አንዳንዱን ፍሬ አሏህ ፈቅዶልን ልናየው እንችላለን፣ አንዳንዱን ደግሞ ሳናየው ሞት ሊቀድመን ይችላል። ግን መቸም በአሏህ ላይ የምንተማመነውና የማንጠራጠረው ነገር ኢንሻአላህ ነገ ከዛሬ የተሻለ እንደሚሆን ነው..! ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
120👍 53🏆 11
ከሞትክ በኋላ ሰዎች በምን ያህል ፍጥነት እንደሚረሱህ ብታውቅ ኖሮ አሏህን እንጂ ማንንም ለማስደሰት አትኖርም ነበር። آه لو علمت السرعة التي ينساك الناس بها بعد موتك، فلن تعيش حياتك لإرضاء أحد سوى اللّٰه.
Show all...
👍 53😢 21😱 2
አንዳንድ ወገኖቻችን፦ “እስልምና ትክክለኛ ሀይማኖት ከሆነ እንዴት ሁሉም ነብያት አረቦች ሊሆኑ ቻሉ? እኛ፦ ከ124,000 ነብያት ውስጥ አረብ መሆናቸው የተነገረን 4 ብቻ ናቸውኮ (ሁድ፣ ሷልህ፣ ሹዐይብ፣ ሙሐመድ "ﷺ" ‎منهم أربعة من العرب: هود، وصالح، وشعيب، ونبيك يا أبا ذر). ይኸው ወገናችን፦ “ግን እኮ ሁሉም አረብኛ እንተናገሩ ነው በቁርአን ውስጥ በአረብኛ የተጠቀሰው” እኛ፦ ኧረ ተው! ቁርአን ውስጥኮ የጉንዳኗ 🐜 ንግግር ሳይቀር በአረብኛ ተጠቅሷል፣ ታዲያ ጉንዷኗ አረብ ናት ማለት ነው? 😒🤦🏻‍♂️ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ “..እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ..” (Qur’an 27:18). #ትርጉም ___ https://t.me/Yahyanuhe
Show all...
👍 50 9🤩 8🏆 2
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች - 31 https://vm.tiktok.com/ZMMYaxUPx/
Show all...
👍 16🎉 3
በወር ከመቶ ብር ጀምሮ በመነያት የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል በመሆን የዳዕዋው አካል ይሁኑ፦ https://bit.ly/4aGr93u በቴሌግራም በኩል ሊያገኙን ከፈለጉ፦ @Hidayaislamiccenter
Show all...
👍 29 13
📌 ሪፖርት የመጽሀፍ ወቅፉን በተመለከተ ... ስቲሮት የተሰኘውን መጽሀፍ ለተለያዩ መርከዞች ለመስጠት የ190 ኮፒ መጽሀፍ የሚሸፍን ከተገኘ በሚል ያቀረብኩትን ጥያቄ አስመልክቶ ከአንድ ኮፒ አቅም ጀምሮ ሙሉውን እስከሸፈነ አንድ ወንድም ድረስ ደስ የሚል ተሳትፎ የነበረበት ነበር። በዚህም መሠረት የመጽሀፉ ሙሉው ብር ማለትም 19,000 ብር የተሟላ ሲሆን በዚህም መሠረት ለሚከተሉት ቦታዎች እስካሁን ተልከዋል፦ ◾️ አዲስ አበባ ለሚገኝና ከ90 በላይ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው ትምህርት ለሚወስዱበት አንድ መርከዝ ለሁሉም መድረስ ባይችልም በጋራ እንዲጠቀሙበት 50 ኮፒ ገደማ አድርሰናል ◾️ በተመሳሳይ አዲስ አበባ ለሚገኝና ከደቡብ የሀገራችን ክፍል ለመጡ ተማሪዎች ትምህርት ለሚሰጥ አንድ መርከዝ ቃል የገባንላቸው ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት በአሏህ ﷻ ፍቃድ እናደርስላቸዋለን። ◾️ ደቡብ ለሚገኙ የሀድያና የከንባታ ተወላጅ የእራሴ ተማሪዎች በአካል እንዲያደርሱ በተመሳሳይ ለነሱም ሰጥቻለሁ። ◾️ ሸይኹ ለሚፈልጉት መርከዝ እንዲሰጡ ተጨማሪ መጽሀፍትን በማከል በፈለጉት ሰአት ሲጠይቁኝ እንዲወስዱ አማካይ ቦታ አስቀምጨላቸዋለሁ። ◾️ ከአማራ ክልል ጥያቄ ካቀረቡ ሁለት መርከዞች መካከል አንደኛው መድረሳ የወሰዱ ሲሆን ከደቡብ ወሎ የጠየቁኝ ወንድሞች ያገኙብኝ አድራሻ ስለጠፋብኝ ማግኘት አልቻልኩም፥ በዚህ አጋጣሚ ይህንን ፖስት ስታዩት አናግሩኝ። ◾️ በግል ወቅፍ ካደረጉ በኃላ ለራሳቸውም ኮፒ ለፈለጉ ወንድሞች በስማቸው በማስቀመጥ እንዲወስዱ ተመቻችቷል። 📌 የገባው ብር ከመጽሀፉ ዋጋ በላይ ስለነበር ተጨማሪ መጽሀፍትን በመግዛት ከላይ ለተዘረዘሩ ቦታዎችም ልኬያለሁ። በዚህም መሠረት አጠቃላይ 400 መጽሀፍትን በግዥ የጨመርኩ ሲሆን ከስቲሮት በተጨማሪ እነዚህም አብረው ተልከዋል። 📌 ከተገዙ ተጨማሪ መጽሀፍት ውስጥ አሁንም ጠይቃችሁኝ ያልተላኩ በርካታ መጽሀፍ ስላሉ ወንድም ሙስጠፋን በዚህ ስልክ በመደወልና የመርከዛችሁን አድራሻ በማሳወቅ የተቀመጠላችሁን መጽሀፍ መውሰድ ትችላላችሁ፦ +251911265565 ◾️ በመጨረሻም በዚህ ኸይር ስራ ላይ የተባበራችሁ ሁሉ አሏህ መልካም ምንዳውን ይክፈላችሁ እያልኩ በኒያችሁ ልክ አሏህ እንዲመነዳችሁ ዱዓየ ነው። እኔን ማግኘት ከፈለጉ በቴሌግራም አድራሻየ በኩል ያገኙኛል፦ t.me/Yahyanuhe1
Show all...
👍 26
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #30 https://vm.tiktok.com/ZMMNHYYFD/
Show all...
👍 12
የወንድማችን የሸይኽ ሰዒድ አሊ ጀውሀርን ሙሉ የቁርአን ንባብ የያዘ አፕልኬሽን ይፋ ተደርጓል። አፑ ካልተሳሳትኩ ፍሪ ይመስለኛልና ዳውንሎድ በማድረግ አድምጡት፣ በግሌ ጭኘው የተወሰኑ ሱራውችን አዳምጫለሁ፣ ማሻአላህ ደስ የሚል ስራ ነው። አሏህ የኸይር ስራ ሚዛኑ ላይ ያድርግለት..! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hexlabs.quran
Show all...
👍 36🥰 8👏 2🔥 1
የመጽሀፍ ቅዱስ ግጭቶች #29 https://vm.tiktok.com/ZMMNdUfBy/
Show all...
👍 7 2
ቤቲንግ ወይንም ቁማር ከከተማው አልፎ በገጠሩ በኩልም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኝ የኡማችን አንዱ ጠንቅ ሁኗል። አንዳንድ የክፍለ ሀገር ከተሞች ላይ ስያሜውን ለክርክር እንዲመች ቁማርን "ቀመር" በሚል አግባቢ ቃል እየሰየሙ እንደሚጠቀሙት አንዳንድ ወንድሞች ነግረውናል። በዚህ በኩል ሰፊ ስራ ከኡለሞችና ከዱዓቶች ይጠበቃል። በዚህ ትውልድ ገዳይ ተግባር ውስጥ የሚሳተፉ ወንድሞችንም መምከርና ማስተማር የሁላችንም ሀላፊነት ነው።
Show all...
👍 69 20
ከሒዳያ መስራቾች መካከል የሆነው የወንድማችን ሙስጠፋ ሙደሲር የቲክቶክ አካውንት ነው። ለላይቭ ትምህርቶች በቪዲዮ ለመግባት 1,000 ሰው ስለሚያስፈልገው ፎሎው በማድረግ 1,000 እንሙላለት። ጠቃሚ ቪዲዮዎችንም በሒደት መልቀቅ ስለሚጀምር ከቪዲዮዎቹ እንጠቀማለን፦ https://www.tiktok.com/@mudesirmustefa?_t=8kCQr9JdDqX&_r=1
Show all...
👍 30 2
ከሒዳያ መስራቾች መካከል የሆነው የወንድማችን ሙስጠፋ ሙደሲር የቲክቶክ አካውንት ነው። ለላይቭ ትምህርቶች በቪዲዮ ለመግባት 1,000 ሰው ስለሚያስፈልገው ፎሎው በማድረግ 1,000 እንሙላለት። ጠቃሚ ቪዲዮዎችንም በሒደት መልቀቅ ስለሚጀምር ከቪዲዮዎቹ እንጠቀማለን፦ https://www.tiktok.com/@mudesirmustefa?_t=8kCQr9JdDqX&_r=1
Show all...
ቦረናን እንደ ሀድያ “True generosity comes without strings attached” ቦረና ተርቧል፣ ድጋፍም ይሻል። ከምንም በላይ የተቸገረ ወገንን ለመርዳት መንቀሳቀስ መልካምና የሚበረታታ ተግባር ነው። እርዳታን ፖለቲካዊ ማድረግ እንደሚወገዘው ሁሉ ግን በራበው ሰው ላይም "ወንጌል መስራት" ሰሚ ባይኖረውም ሊወገዝ ይገባል። ፕሮፌሰር ጆን ማርክ "Models of muslim evangalizing" በሚለው ፔፐሩ ከሚገልጻቸው የማክፈሪያ መንገዶች አንዱ "Institutional Model" ሲል የሚጠራው መንገድ አንዱ ነው። የሞዴሉ አተገባበር በአጭሩ እንደሚከተለው ነው፦ ሰውን እንዲሁ "ወንጌልን ተቀበል" እያሉ መወትወት ያን ያህል ፍሬ አያስገኝም። ታዲያ ምን ይሻላል?የተሻለው አካሔድ ሙስሊም በሚበዛባቸው አካባቢ የተለያዩ ተቋማትን በመገንባት ለነዚህ አገልግሎቶች የሚመጣውን ሙስሊም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ማክፈር የሚል ነው። ለዚህም የእርዳታ ድርጅት፣ ሆስፒታል፣ የትምህርት ተቋማት ወዘተ ተመራጭ ማዕከላት ናቸው። ... የመሠረተ ክርስቶስ ቸርች ለቦረና ወገኖቻችን ድጋፍ ማድረጓን በግሌ ልቃወመው የምችለው አይደለም። ለቦረና ህዝብ ሙስሊሙ ወገናቸው በተሻለ ሊያደርገው የሚገባውን ቀድመው ማድረግ ችለዋል። ግን ደግሞ ካለፈ ተሞክሯችን እንደምናውቀው ከነዚህ እርዳታዎች ጀርባ ያሉ የእጅ ጥምዘዛዎችንም መከታተልና በትክክልም እርዳታዎች "እርዳታ ብቻ" መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን። ይህ በህጉም ይከለከላል፣ የተራበን ሰው ለማብላት ሌላ ሞቲቭ ይዞ መሄድ አይፈቀድም። የእርዳታ ድርጅቶች የሀይማኖት ጫናን መሠረት እንዲያደርጉ ፈጽሞ አይፈቀድም። ◾️ ለኛ፦ ሁሌም መሠል ነገራትን መናገር ለተናጋሪው ብቻ ሳይሆን ለሰሚውም እንደሚያሰለች እገምታለሁ። ግን አሁንም አረፈደም ከሚል ቀና ግምት መናገሩና መወያየቱ ከተቻለም የአቅምን አበርክቶ ህዝባችንን ከዱንያም ከኤኼራም ፈተና ማዳን የሁላችንም ኃላፊነት ነው። በተለይ በተቋም በኩል ያላችሁ ሰዎች ብዙ ኃላፊነት እንናንተው ጋር መውደቁ አይቀርም። ልብ በሉ፦ አንዳንድ ኩፍሮች በበደል ስር አድርገው ዱንያችንን ሊያበላሹ ይችላሉ፣ አንዳንድ ኩፍሮች ደግሞ ዱንያችንን ሰጥተው አኼራችንን ሊያሳጡን ይችላሉ። የአኼራው የከፋና አደገኛ ነው። ◾️ ሰጭዎችም ይህንን አባባል አትዘንጉት፦ "True generosity comes without strings attached, freely given from the heart with no expectation of reciprocity or ulterior motives." ቁርዓን ሰውን ስለሚያበሉ ደጋጎች በሚገርም መልኩ ይነግረናል። ስራቸው ሁሉ ጌታቸው ዘንድ ምንዳን ከማግኘት እንጅ በምትኩ ምስጋናም ሆነ የተለየ ክፍያን ፈልገው አይደለም፦ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا «የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡ [ አል-ደህር - 9 ]
Show all...
👍 57 10🔥 1
አንድ እዚህ መንደር የሚታወቅና በብዙ ሰው ዘንድ "የሚከበር" ጸሀፊ አለ፣ እምነቱ ፕሮቴስታንት ቢሆንም ስለእምነቱ አብዝቶ የሚጽፍ ሰው ግን አይደለም። ግለሰቡ የአንድ የማቀው ፋብሪካ ባለቤት ከመሆኑም በተጨማሪ በተለያዩ ሜንስትሪም ሚዲያዎች ማህበረሰብን ስለማረቅ በሚያስተጋባቸው ሀሳቦቹ ብዙው ሰው (ሙስሊሙን ጨምሮ) እንደበጎ አሳቢ አይቶ ያደንቀዋል። ሌላም ግን የማይታወቅ ማንነት አለው። ቁርአንና ነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" የሚሰደቡባቸው የፕሮቴስታንት ሰባኪ ፖስቶች ላይም ያለምንም መሸማቀቅ Love teact ሲሰጥ ታገኙታላችሁ። መጀመሪያ አካባቢ ካለው ማንነት አንጻር በስህተት ያደረገው መስሎኝ ኡዝር ሰጥቸው አውቃለሁ። ሲደጋገም ግን እራሱ ፈልጎት እንደሆነ ገባኝ። አስፈላጊ አይደለም ብየ ስላመንኩ እንጅ ሜንሽን ባደርገው ብዙ ሰው ባለማመን እንደሚከራከረኝ አቃለሁ። ይህ እንግዲህ በአደባባይ ያየነው እውነታ ነው፣ ከጀርባ ያለውን ደግሞ አሏህ ያውቃል። ለማንኛውም የሚሽነሪውን ቡድን ደብል ፌስ ማሳያ ነውና ትምህርት ውሰዱበት..!
Show all...
👍 56
Show all...
👍 9
👍 25 6👏 1
ምልጃ የሌለበት ቀን በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ "ምልጃ" ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፥ እነርሱም፦ ፨አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣ ፨ሁለተኛው የሚማልደው አማላጅ እና ፨ሦስተኛ የሚማለድለት ተመላጅ ናቸው። አሏህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፥ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱት አማላጆች ደግሞ መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው፦ 2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ 21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ "ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም" የሚለው ይሰመርበት! ዐውደ ንባቡ ስለ መላእክት እያወራ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የሚማለድላቸው ተመላጆች ደግሞ አሏህ ዘንድ ቃል ኪዳን የያዙት አማንያን ናቸው፦ 34፥23 ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ 19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا 20፥109 በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا "በዚያ ቀን" የሚለው የፍርዱ ቀን ሲሆን በዚያን ቀን አሏህ የፈቀደላቸው መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለምዕመናን ያማልዳሉ። ነገር ግን ለኩፋሮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፦ 40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع 2፥254 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ውስጥ ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ከሰጠናችሁ ነገር ለግሱ፡፡ ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنفِقُوا مِمَّا رَزَقْنَاكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا بَيْعٌ فِيهِ وَلَا خُلَّةٌ وَلَا شَفَاعَةٌ ۗ وَالْكَافِرُونَ هُمُ الظَّالِمُونَ "ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን" የፍርዱ ቀን ሲሆን ቤዛ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለው ለኩፋሮች ስለሆነ ዐውዱ ላይ "ከሓዲዎችም በዳዮቹ እነርሱ ናቸው" በማለት ይናገራል። ያ የፍርዱ ቀን እነርሱም ከአሏህ እርዳታ የማይረዱበትን እና ምልጃን የማይቀበሉባት ቀን ነው፦ 2፥48 ነፍስም ከነፍስ ምንንም የማትመነዳበትን፣ ከእርሷም ምልጃን የማይቀበሉባትን፣ ከእርሷም ቤዛ የማይያዝበትን፣ እነርሱም የማይረዱበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡ وَاتَّقُوا يَوْمًا لَّا تَجْزِي نَفْسٌ عَن نَّفْسٍ شَيْئًا وَلَا يُقْبَلُ مِنْهَا شَفَاعَةٌ وَلَا يُؤْخَذُ مِنْهَا عَدْلٌ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ "የማይቀበሉ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በግስ መደብ የተጠቀሱት እና "እነርሱ" ተብሎ በሦስተኛ መደብ በስም መደብ የተጠቀሱት በዳዮቹ ከሓዲዎች እንጂ ምእመናንን አይጨምርም፥ በፍርዱ ቀን አሏህ የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሙእሚን ቢኾን እንጅ ለከሓዲ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም። ኩፋሮች የትንሳኤ ቀን፦ "በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ? ተብለው ሲጠየቁ፦ "ከሰጋጆቹ አልነበርንም፣ ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፣ ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፣ በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን" ይላሉ። የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፦ 74፥48 የአማላጆችም ምልጃ አትጠቅማቸውም፡፡ فَمَا تَنفَعُهُمْ شَفَاعَةُ الشَّافِعِينَ "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" የተባለው አሁንም ለኩፋሮች እንጂ ለሙእሚን በፍጹም አይደለም። "ሑላህ" خُلَّة ማለት "ወዳጅነት" ማለት ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ማለት ደግሞ "ወዳጅ" ማለት ነው፥ በዚያ ቀን ኩፋሮች አንዱ ለሌላው ጠላት ነው፦ 43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ "ወዳጆች" ለሚለው የገባው ቃል "አኺላእ" أَخِلَّاء ሲሆን "ኻሊል" خَلِيل ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ" የሚለው ይሰመርበት! አሏህን ፈሪዎች ምእመናንማ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይወዳጃሉ፡፡ የእነዚያም ወዳጅነት አማረ፦ 4፥69 አላህን እና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَـٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَـٰئِكَ رَفِيقًا ስለዚህ "ምልጃም የሌለበት ቀን" የተባለው "ወዳጅነትም የሌለበት ቀን" በተባለበት ዐውድ ከሆነ እና ለምእመናን ምልጃ ሆነ ወዳጅነት ካላቸው ምልጃ እና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ለኩፋሮች ነው፥ የፍርዱ ቀን ለኩፋሮች ቤዛ የሌለበት ቀን ነው። ሙጅሪም ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፥ ቅሉ ግን ለእነርሱ ቤዛ የሌለበት ቀን ስለሆነ ከእሳት ቅጣት አይቤዥም፦ 70፥11 ዘመዶቻቸውን ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ ነፍሱን በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ يُبَصَّرُونَهُمْ ۚ يَوَدُّ الْمُجْرِمُ لَوْ يَفْتَدِي مِنْ عَذَابِ يَوْمِئِذٍ بِبَنِيهِ
Show all...
ምእመናን ግን በጀነት ስላሉ ከዚያ ቀን ስቃይ ተቤዥተዋል። ከእነዚያ ከካዱት ግን ቤዛ አይወሰድም፥ ለእነዚያም ለበደሉት ከሐድያን በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፦ 57፥15 «ዛሬም ከእናንተ ቤዛ አይወስድም፥ ከእነዚያ ከካዱትም አይወሰድም፡፡ መኖሪያችሁ እሳት ናት፥ እርሷ ተገቢያችሁ ናት፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» ይሏቸዋል፡፡ فَالْيَوْمَ لَا يُؤْخَذُ مِنكُمْ فِدْيَةٌ وَلَا مِنَ الَّذِينَ كَفَرُوا ۚ مَأْوَاكُمُ النَّارُ ۖ هِيَ مَوْلَاكُمْ ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ 39፥47 ለእነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላውም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሣኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተቤዡበት ነበር፡፡ وَلَوْ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُ مَعَهُ لَافْتَدَوْا بِهِ مِن سُوءِ الْعَذَابِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ይህቺ የካፊር ነፍስ ከነፍስ ምንንም ቤዛ የማይያዝበትን ቀን ተጠንቀቁ! እንግዲህ ቤዛ፣ ምልጃ፣ ወዳጅነት የሌለበት ቀን የተባለው ከዐውድ እና አጠቃላይ ከቁርኣን መልእክት አንጻር ለከሓዲ በዳዮች ብቻ ነው። የፍርዱ ቀን ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ምልጃ ያረጋል፥ የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ሰው ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 402 አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው የአሏህ ነቢይም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሁሉም ነቢይ ለኡመቱ ወደ አላህ ጸሎት ያረጋል፥ በትንሳኤ ቀን የእኔ ጸሎት ለኡመቴ ምልጃ ነው*። عَنْ قَتَادَةَ، حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لِكُلِّ نَبِيٍّ دَعْوَةٌ دَعَاهَا لأُمَّتِهِ وَإِنِّي اخْتَبَأْتُ دَعْوَتِي شَفَاعَةً لأُمَّتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏”‏ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41 አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏ ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ (ሱረቱ ቃፍ - 16) ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡ @slmatawahi
Show all...
ኢስላምና ሙስሊሞችን ለምን ይነካካሉ? | ኡስታዝ አህመድ አደም | ሀዲስ | Ustaz ahmed adem | hadis ሸገር ሲቲ Sheger @QesesTube
Show all...
●▯ውይይት ▯● "ዕብራውያን 1፥10" ◍ ኡስታዝ ወሒድ 🆅🆂 ◍ ወገናችን ክብረት
Show all...
#አማናን መጠበቅ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “አንድ ሰው ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሆነ ወሬ ከነገረህ አማና (ሚስጥር) ነው ማለት ነው።” 📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 1959
Show all...
“ወንድምህ በፈጸመው ወንጀል ላይ ነቀፋ እየሰነዘርክ መዘባበትህ፣ እርሱ ከፈጸመው ወንጀል የበለጠ ነው” ኢብኑል ቀይም አልጀውዚ መዳሪጅ አል'ሳሊኪን 1/178
Show all...
👍 35 14
ቲላዋ 💌 🍃ራሀቱል ቀልብ 🍃 •┈┈• ❀ 🍃🌸🍃 ❀ •┈┈• @slmatawahi
Show all...
#የምህረትና በንስሃ ወደ አላህ የመመለስ ትሩፋት! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ!  እናንተ ሀጢያት የማትፈፅሙ ቢሆን ኖሮ አላህ ያጠፋችሁ ነበር። ከዛ ሀጢያት የሚፈፅሙ ህዝቦችን ያመጣና በሀጢያታቸው ምክንያት አላህን ምህረት ይጠይቁታል እሱም ይምራቸዋል።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2749
Show all...
●▯ውይይት ▯● "ግድያ በእስልምና በክርስትና" ◍ ወንድም ሳላህ ◍ ወንድም ራስታ 🅥🅢 ◍ ክርስቲያን ወገኖች
Show all...
ዝምታን እንማር ! | ኡስታዝ አህመድ አደም | ሀዲስ በአማርኛ | Ustaz ahmed adem | Hadis Amharic @QesesTube @seifuonebs
Show all...