cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሰለምቴዎች ቻናል

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

Show more
Advertising posts
2 878Subscribers
+524 hours
+327 days
+16430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡ «እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም #ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አልላችሁ፡፡ ለእናንተም በእርሷ ውስጥ #የምትፈልጉት ሁሉ አልላችሁ፡፡ @slmatawahi
Show all...
- "ቁርዓን ከአላህ ለመውረዱ ማስረጃ" - "ሰይጣን በክርስትና አስተምህሮ" - "የገድላት ቅሌት" ◍ ወንድም ሳላህ ◍ ወንድም አቡ ሳላህ ◍ እኅት ዛህራ
Show all...
ይገደል! በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ “ዘንብ” ذَنب ማለት “ኃጢአት” ማለት ነው፥ በሥነ-ኃጢአት ጥናት”hamartiology” ውስጥ “ኃጢአት” ማለት “አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ” ማለት ነው። ኃጢአት “ከባኢሩ አዝ-ዘንብ” كَبَائِر الْذَنب እና “ሶጋኢሩ አዝ-ዘንብ” صَغَائِر الْذَنب ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ፥ “ከባኢር” كَبَائِر ማለት “ዐብይ” “ታላቅ” ማለት ሲሆን “ሶጋኢር” صَغَائِر ማለት ደግሞ “ንዑስ” “ትንሽ” ማለት ነው። ከዐበይት ኃጢአቶች መካከል አንዱ ነፍስን ያለ ሕግ መግደል ነው፦ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53 ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏ “ቀትሉ አን-ነፍሥ” قَتْلُ النَّفْس የሚለው ቃል ይሰመርበት! አምላካችን አሏህ ነፍስን መግደል ሐራም አርጓል፦ 17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ “እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ ልብ አድርግ! “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው። "ሕግ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሐቅ" حَقِّ ሲሆን በሐቅ፣ በእውነት፣ በፍትሕ ነፍስ ሊገደል ይችላል። ለምሳሌ በባይብል የአምላክን ስም የሰደበ እንዲገደል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦ ዘሌዋውያን 24፥16 የእግዚአብሔርንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ "ይገደል"። "ይገደል" ብሎ ትእዛዝ የሰጠው ሙሴ ሳይሆን የሙሴ አምላክ እንደሆነ ዐውደ ንባቡ ላይ፦ "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው" የሚል ቃል አለ፦ ዘሌዋውያን 24፥1 "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው"። አንድ ሰው ከአንዱ አምላክ ውጪ ሌላ ማንነትን "እናምልክ" ብሎ ቢያስተምርህ ፈጽመህ "ግደለው" የሚል መመሪያ አለ፦ ዘዳግም 13፥6-9 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት "እናምልክ" ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥ አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ ነገር ግን ፈጽመህ "ግደለው"፤ እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። አስመላኪው ብቻ ሳይሆን ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትን የሚሠዋ ይገደላል፥ እንዲሁ የእስራኤልንም አምላክ የማይፈልግ ይገደል ዘንድ መሐላ አለ፦ ዘጸአት 22፥20 ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ "ይጥፋ"። ዘዳግም 17፥3 ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ ዘዳግም 17፥5 ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ። 2 ዜና 15፥13 የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ። የጥንቆላ አምልኮ ከአንድ አምላክ ውጪ ስለሆነ "ጠንቋዮች ፈጽመው ይገደሉ" የሚል ትእዛዝ አለ፦ ዘሌዋውያን 20፥27 ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው። በተጨማሪም አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ "ይገደል" ተብሏል፦ ዘጸአት 21፥17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ "ይገደል"። ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ተራክቦ ቢያደርግ "ይገደል" ተብሏል፦ ዘሌዋውያን 20፥15 ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ "ይገደል"፥ እንስሳይቱንም ግደሉአት። ግብረ ሰዶም የሚያደርጉ "ይገደሉ" ተብሏል፦ ዘሌዋውያን 20፥13 ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። ከላይ "ይገደል" ወይም "ይገደሉ" የሚለው ፈጣሪ እንደሆነ ልብ አድርግ! በአዲስ ኪዳንም ቢሆን እነዚህ ሕግጋት አልተሻሩም፦ ማቴዎስ 5፥17-18 እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ። ሰማይ እና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት አትሻርም። የፈጣሪን ሕግ የማይረባ እና ደካማ ብሎ በመንቀፍ "ተሽራለች" ያለው ጳውሎስ ነው፦ ዕብራውያን 7፥18 ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ "ተሽራለች"። የጳውሎስ ትክክለኛ ስሙ "ሳውል" ሲሆን በኃላ ላይ ለራሱ ያወጣው ስም "ጳውሎስ" ነው፥ "ጳውሎስ" ማለት ትርጉሙ "ታናሽ" ማለት ነው። እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም ተሽሯል ብሎ የሚያስተምር ሳውል በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ነው፦ ማቴዎስ 5፥19 እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ "ታናሽ" ይባላል። ስለዚህ የተቆላበት እያለ የተጋፈበትን መጠየቅ አግባብ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
👍 1
سوره النور🥀 🌠የብረሀን/ ምዕራፍ🏞 🌇 🕌በመድና፣የወረደ🕌 ራሀቱል፣ቀልብ❤️ @slmatawahi
Show all...
👍 2
●▯ውይይት ▯● ◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም 🅅🅂 ◍ አይሁዳዊው ወገናችን ጌዲዮን
Show all...
ሳጥናኤል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ "ሳጥናኤል" የሚለው የግዕዝ ቃል በዕብራይስጥ "አዛዝኤል" עֲזָאזֵל ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "አዛዝ" עֲזָא ማለት "ጥንካሬ" ማለት ሲሆን "ኤል" זֵל ማለት አምላክ ማለት ነው። በጥቅሉ "አዛዝኤል" ማለት "አምላክ ጥንካርዬ ነው" ማለት ነው፥ ይህ ስም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን የሚባል ጂን ከመሰይጠኑ በፊት የነበረው ስም እንደሆን በአፈ ታሪክ ይነገራል። ይህ ጋኔን በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ከሃያ አንዱ አጋንንት አንዱ ሆኖ ተገልጿል፦ ሄኖክ 3፥10 በአዛዝኤል ሥራ እና ትምህርት ምድር ሁሉ ጠፋች፥ የሰውን ሁሉ ኃጢአት በእርሱ ጻፍበት አለው። ሄኖክ 15፥7 "በአዛዝኤል" ይፈረድበታል፥ በወገኖችሁ ሁሉ እና በመላእክት ጌታ ስም ባላመኑ በሰራዊቱም ሁሉ ይፈረድባቸዋል። ሄኖክ 19፥10-12 የእነዚያ የአጋንንት ስማቸው እንደዚህ ነው፦አለቃቸው ስማዝያ፣ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፣ ሥስተኛውም አርሚን ነው፣ አራተኛውም ኮክብኤል ነው። አምስተኛውም ጡርኤል ነው፣ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፣ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፣ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፣ ዘጠነኛውም በራቃኤል ነው፣ አስረኛውም “አዛዝኤል” ነው፣ አስራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፣ አስራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው። አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ ለአዛዝኤል ይሆናል፦ ዘሌዋውያን 16፥8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ "ለአዛዝኤል"። וְנָתַן אַהֲרֹן עַל-שְׁנֵי הַשְּׂעִירִם, גֹּרָלוֹת–גּוֹרָל אֶחָד לַיהוָה, וְגוֹרָל אֶחָד לַעֲזָאזֵל. ዐማርኛው ላይ "ሚለቀቅ" ብሎ ቢያስቀምጠውም ዕብራይስጡ ግን እንቅጩን ፍርጥ አርጎ "አዛዝኤል" עֲזָאזֵל ብሎ አስቀምጦታል። ዐረቢኛውም ባይብል ሳያቅማማ "ዐዛዚል" عَزَازِيل ብሎታል፥ እንዲሁ በእንግሊሹ Good News Translation በትክክሉ "Azazel" ብሎታል። ከሥነ አምክኖ አንጻር እስቲ እዩት! አንዱ ለፈጣሪ ሁለተኛው ለሳጥናኤል ፍየል ይገበራል? "ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ" ተብሏል እኮ፦ ዘጸአት 22፥20 ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ። ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትና ምንነት መስዋዕት መሰዋት ይህንን ያክል ከባድ ወንጀል ከሆነ እንግዲያውስ ለሳጥናኤል የፍየል መስዋዕት ይቀርባል የሚለውን የብርዘት ውጤት ትታችሁ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ብቻ እንድትሰዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሙሥሊም መስዋዕቱ ለፈጠረው ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ብቻ ነው፦ 6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
አህሉል ቁርአን 📌 فَلَوْلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلْحُلْقُومَ (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡  📌 - القــارئ ؛ عبدالرحمن أبا الخيل ቃሪእ- ዓብዱረህማን አበልኸሊል
Show all...
አህሉል ቁርአን 📌 فَلَوْلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلْحُلْقُومَ (ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡  📌 - القــارئ ؛ عبدالرحمن أبا الخيل ቃሪእ- ዓብዱረህማን አበልኸሊል
Show all...