en
Feedback
HOP Ministry

HOP Ministry

Open in Telegram

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
452
Subscribers
+124 hours
+177 days
+6830 days
Posts Archive
መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹²⁹ ምስክርነትህ ሁሉ ድንቅ ነው፤ ስለዚህ ነፍሴ ትጠብቀዋለች። ¹³⁰ የቃልህ ትርጓሜ ያበራል፤ አላዋቂዎችንም አስተዋዮች ያደርጋል። ¹³¹ ትእዛዝህን ናፍቄአለሁና፣ አፌን ከፈትሁ፤ አለከለክሁም። ¹³² ስምህን ለሚወዱ ማድረግ ልማድህ እንደሆነ ሁሉ፣ ወደ እኔ ተመልሰህ፣ ምሕረት አድርግልኝ። ¹³³ አካሄዴን እንደ ቃልህ ቀና አድርግልኝ፤ ኀጢአትም በላዬ እንዲሠለጥን አትፍቀድ። ¹³⁴ ትእዛዝህን መጠበቅ እንድችል፣ ከሰዎች ጥቃት ታደገኝ። ¹³⁵ በባሪያህ ላይ ፊትህን አብራ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ። ¹³⁶ ሕግህ ባለመከበሩ፤ እንባዬ እንደ ውሃ ይፈሳል።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹²¹ ፍትሕና ጽድቅ ያለበትን ሠርቻለሁ፤ ለሚጨቍኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ። ¹²² ለባሪያህ በጎነት ዋስትና ሁን፤ እብሪተኛ እንዲጨቍነኝ አትፍቀድላቸው። ¹²³ ዐይኖቼ ማዳንህን፣ የጽድቅ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ። ¹²⁴ ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ መጠን አድርግ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ። ¹²⁵ እኔ ባሪያህ ነኝ፤ ምስክርነትህን ዐውቅ ዘንድ ማስተዋልን ስጠኝ። ¹²⁶ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕግህ እየተጣሰ ነውና፣ ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው። ¹²⁷ ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ ትእዛዛትህን ወደድሁ። ¹²⁸ መመሪያህ ሙሉ በሙሉ ልክ ነው አልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹³ መንታ ልብ ያላቸውን ጠላሁ፤ ሕግህን ግን ወደድሁ። ¹¹⁴ አንተ መጠጊያዬና ጋሻዬ ነህ፤ ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ። ¹¹⁵ የአምላኬን ትእዛዛት እጠብቅ ዘንድ፣ እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ ከእኔ ራቁ። ¹¹⁶ እንደ ቃልህ ደግፈኝ፤ እኔም ሕያው እሆናለሁ፤ ተስፋዬም መና ቀርቶ አልፈር። ¹¹⁷ ያለ ሥጋት እቀመጥ ዘንድ ደግፈህ ያዘኝ፤ ሥርዐትህንም ዘወትር እመለከታለሁ። ¹¹⁸ መሰሪነታቸው በከንቱ ነውና፣ ከሥርዐትህ ውጭ የሚሄዱትን ሁሉ ወዲያ አስወገድሃቸው። ¹¹⁹ የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ። ¹²⁰ ሥጋዬ አንተን በመፍራት ይንቀጠቀጣል፤ ፍርድህንም እፈራለሁ።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰⁵ ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው። ¹⁰⁶ የጽድቅ ሕግህን ለመጠበቅ፤ ምያለሁ፤ ይህንኑ አጸናለሁ። ¹⁰⁷ እጅግ ተቸግሬአለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቃልህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ። ¹⁰⁸ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈቅጄ ያቀረብሁትን የአፌን የምስጋና መሥዋዕት ተቀበል፤ ሕግህንም አስተምረኝ። ¹⁰⁹ ነፍሴ ዘወትር አደጋ ላይ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም። ¹¹⁰ ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ እኔ ግን መመሪያህን አልተላለፍሁም። ¹¹¹ ምስክርነትህ የዘላለም ውርሴ ናት፤ ልቤ በዚህ ሐሤት ያደርጋልና። ¹¹² ትእዛዝህን ለዘላለም፣ እስከ ወዲያኛው ለመፈጸም፣ ልቤን ወደዚያው አዘነበልሁ።

Yehywete Memeria.mp35.05 MB

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁹⁷ አቤቱ፤ ሕግህን ምንኛ ወደድሁ! ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ። ⁹⁸ ትእዛዛትህ ምንጊዜም ስለማይለዩኝ፣ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረጉኝ። ⁹⁹ ምስክርነትህን አሰላስላለሁና፣ ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የላቀ አስተዋይ ልብ አገኘሁ። ¹⁰⁰ መመሪያህን ተከትዬ እሄዳለሁና፣ ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋይ ሆንሁ። ¹⁰¹ ቃልህን እጠብቅ ዘንድ፣ እግሬን ከክፉ መንገድ ሁሉ ከለከልሁ። ¹⁰² አንተው ራስህ አስተምረኸኛልና፣ ከድንጋጌህ ዘወር አላልሁም። ¹⁰³ ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው! ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው። ¹⁰⁴ ከመመሪያህ ማስተዋልን አገኘሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።

#በማረፍ_ማትረፍ_መትረፍ! በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከሚገጥሙ ፈተናዎች የተነሳ ችግረኛው (መፍትሄ ፈላጊው) ፍቱን መድኃኒት፣ መፍትሄ ፍለጋ የማይዞርበት፣ የመፍትሄ መገኛ ከመሰለው የማይቆምበት ፌርማታ አይኖርም። ይህንን ሁሉ ነገር አድርጎ ሲያበቃ የዞረው ዙረት፣ የፈለገው ፍለጋ ከመፍትሄው ጋር ካላገናኘው ተስፋ በቆረጠ ልብ #ያልዞርኹበት_የለም ሲል እልኽ አስጨራሽ፤ ነገር ግን ፍሬአልባ ጥረቱን ይመሰክራል። መንፈሳዊ ተሃድሶን፣ የሕይወት ለውጥን ለማምጣት የምንዞርበት ብዙ ስፍራ ቢኖረን የዞርንበት ሁሉ ወደ መድኃኒታችን ላያስጠጋን ይችላል። #አንድ_ነገር ግን ብቸኛና ፍቱን መድኃኒት፣ ከዙረት የሚገላግል የመሰሪያና የፈውስ ቦታ ነው። ዓለም በመዞርና፣ እግር እስኪቀጥን መድኃኒትና መፍትሄ ፍለጋ በመሄድ መፍትሄ ይገኛል ብላ ስታስተምር፤ እግዚአብሔር ግን በመመለስና በማረፍ መዳን እንዳለ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል እንደሚሆንልን፣ እንደምንበረታ ይነግረናል። ታዲያ የእኛ የአሁናዊ ሁኔታ እውነት ለማረፍ የተመቸ፣ ጸጥታን የወደደ፣ ለመመለስ የቆረጠ፣ ይሄ ሁሉ ይቅርና ለመዳን እንኳ መመለስ፣ ማረፍ፣ ጸጥታ፣ መታመን ቁልፍ እንደሆነ ያውቃል፣ ያምናል? አይመስለኝም! የበላን ሌላ ቦታ የምናከው ሌላ፤ መዳኛችን የተሰወረበት ስፍራና ለፍለጋ ስንዞር የምንውልበት ስፍራ ለየቅል፤ ሕመማችን ሌላ፣ መድኃኒት ብለን የምናግበሰብሰው ነገር ሌላ! ስንዞር የዋልንበት ስፍራ ሳይሆን፤ በማስተዋል ዘወር ብለን ብናየው፣ ወደ እርሱ መለስ ብንል፣ ብናርፍ፣ ጸጥ ብለን ልንሰማው ብንወድ፣ ብንታመነው፦ የቅርብ ሆኖ፣ እንደ ወገግታም ተገልጦ የምናገኘው እግዚአብሔር ዛሬም #የሚያስተውል፣ #እግዚአብሔርን_የሚፈልግ_መኖሩን_ለማየት_ከሰማይ_ወደ_ሰው_ልጆች_ይመለከታል። ወደ እርሱ ለመመለስ፣ እርሱን ለመመልከት፣ ለማረፍ፣ ጸጥ ለማለት፣በእርሱ ለመታመን፣ ለመዳን ዝግጁ ነን? ከሆንን ያን ጊዜ እውነተኛ ፈውስ ይሆንልናል፣ ኃይል ገንዘባችን ይሆናል፤ እንበረታለን። መመለስ፣ ማረፍ፣ ጸጥ ማለት፣ መታመን፣ መዳን፣መበርታት ይሁንልን!! ጸጋ ይብዛልን!!

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸⁹ እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃልህ በሰማይ፣ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። ⁹⁰ ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ሁሉ ይኖራል፤ ምድርን መሠረትሃት፤ እርሷም ጸንታ ትኖራለች። ⁹¹ ሁሉም አገልጋይህ ነውና፣ በሕግህ መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ ጸንተው ይኖራሉ። ⁹² ሕግህ ደስታዬ ባይሆን ኖሮ፣ በመከራዬ ወቅት በጠፋሁ ነበር። ⁹³ በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና፣ ትእዛዝህን ከቶ አልረሳም። ⁹⁴ እኔ የአንተ ነኝ፤ እባክህ አድነኝ፤ ሕግህንም ፈልጌአለሁና። ⁹⁵ ክፉዎች ሊያጠፉኝ አድብተዋል፤ እኔ ግን ምስክርነትህን አሰላስላለሁ። ⁹⁶ ለፍጹምነት ሁሉ ዳርቻ እንዳለው አየሁ፤ ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁸¹ ነፍሴ ማዳንህን እጅግ ናፈቀች፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ። ⁸² “መቼ ታጽናናኛለህ?” እያልሁ፣ ዐይኖቼ ቃልህን በመጠባበቅ ደከሙ። ⁸³ ጢስ የጠጣ የወይን አቍማዳ ብመስልም፣ ሥርዐትህን አልረሳሁም። ⁸⁴ የባሪያህ ዕድሜ ስንት ቢሆን ነው? ታዲያ፣ በሚያሳድዱኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ይሆን? ⁸⁵ በሕግህ መሠረት የማይሄዱ፣ እብሪተኞች ማጥመጃ ጒድጓድ ቈፈሩልኝ። ⁸⁶ ትእዛዛትህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው፤ ሰዎች ያለ ምክንያት አሳደውኛልና ርዳኝ። ⁸⁷ ከምድር ላይ ሊያስወግዱኝ ጥቂት ቀራቸው፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም። ⁸⁸ እንደ ምሕረትህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ፤ እኔም የአፍህን ምስክርነት እጠብቃለሁ።

_ቃልህ_KALIH_by_Gospel_singer_Yoseph_Bekele,_Yigerem_Wondwosen_,_Tinsae.m4a7.50 MB

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷³ እጆችህ ሠሩኝ፤ አበጃጁኝም፤ ትእዛዛትህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ። ⁷⁴ ቃልህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይበላቸው። ⁷⁵ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍርድህ የጽድቅ ፍርድ፣ ያስጨነቅኸኝም በታማኝነት እንደሆነ ዐወቅሁ። ⁷⁶ ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት፣ ምሕረትህ ለመጽናናት ትሁነኝ። ⁷⁷ ሕግህ ደስታዬ ነውና፣ በሕይወት እኖር ዘንድ ቸርነትህ ትምጣልኝ። ⁷⁸ እብሪተኞች ያለ ምክንያት በደል አድርሰውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አሰላስላለሁ። ⁷⁹ አንተን የሚፈሩህ፣ ምስክርነትህንም የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ። ⁸⁰ እኔ እንዳላፍር፤ ልቤ በሥርዐትህ ፍጹም ይሁን።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁷ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ቃልህን ለመታዘዝ ቈርጫለሁ። ⁵⁸ በፍጹም ልቤ ፊትህን ፈለግሁ፤ እንደ ቃልህ ቸርነትህን አሳየኝ። ✨ SELAH ✨
መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁷ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ቃልህን ለመታዘዝ ቈርጫለሁ። ⁵⁸ በፍጹም ልቤ ፊትህን ፈለግሁ፤ እንደ ቃልህ ቸርነትህን አሳየኝ። ✨ SELAH ✨ A Week of Reading, Meditation, Prayer & Obedience Through God’s Word Join us and invite others to grow together in God’s Word. 📍 Facebook Page: https://www.facebook.com/hopministry10 📍 Telegram Channel: https://t.me/hopministry10

4_5854770414269501786.mp34.90 MB

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶⁵ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቃልህ፣ ለአገልጋይህ በጎ ውለሃል። ⁶⁶ በትእዛዛትህ አምናለሁና፣ በጎ ማስተዋልንና ዕውቀትን አስተምረኝ። ⁶⁷ እንዲያው ሳይቸግረኝ መንገድ ስቼ ሄድሁ፤ አሁን ግን ቃልህን እጠብቃለሁ። ⁶⁸ አንተ መልካም ነህ፤ የምታደርገው መልካም ነው፤ እንግዲህ ሥርዐትህን አስተምረኝ። ⁶⁹ እብሪተኞች ስሜን በሐሰት አጠፉ፤ እኔ ግን ትእዛዝህን በፍጹም ልብ እጠብቃለሁ። ⁷⁰ ልባቸው የሠባና የደነደነ ነው፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል። ⁷¹ ሥርዐትህን እማር ዘንድ፣ በመከራ ውስጥ ማለፌ መልካም ሆነልኝ። ⁷² ከአእላፋት ብርና ወርቅ ይልቅ፣ ከአፍህ የሚወጣው ሕግ ይሻለኛል።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵⁷ እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ቃልህን ለመታዘዝ ቈርጫለሁ። ⁵⁸ በፍጹም ልቤ ፊትህን ፈለግሁ፤ እንደ ቃልህ ቸርነትህን አሳየኝ። ⁵⁹ መንገዴን ቃኘሁ፤ አካሄዴንም ወደ ምስክርህ አቀናሁ። ⁶⁰ ትእዛዝህን ለመጠበቅ፣ ቸኰልሁ፤ አልዘገየሁምም። ⁶¹ የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም። ⁶² ስለ ጻድቅ ሥርዐትህ፣ በእኩለ ሌሊት ላመሰግንህ እነሣለሁ። ⁶³ እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፣ ሥርዐትህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ። ⁶⁴ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምድር በምሕረትህ ተሞላች፤ ሥርዐትህን አስተምረኝ።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁹ ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ዐስብ፤ በዚያ ተስፋ ሰጥተኸዋልና። ⁵⁰ ቃልህ ሕያው ያደርገኛልና፣ ይህች በመከራዬ መጽናኛዬ ናት። ⁵¹ እብሪተኞች እጅግ ተሣለቁብኝ፤ እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አልልም። ⁵² እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥንት የነበረውን ድንጋጌህን ዐሰብሁ፤ በዚህም ተጽናናሁ። ⁵³ ሕግህን ከተዉ ክፉዎች የተነሣ፣ ቍጣ ወረረኝ። ⁵⁴ በእንግድነቴ አገር፣ ሥርዐትህ መዝሙሬ ናት። ⁵⁵ እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን በሌሊት ዐስባለሁ፤ ሕግህንም እጠብቃለሁ። ⁵⁶ ሥርዐትህን እከተላለሁ፤ ይህችም ተግባሬ ሆነች።

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁷ እኔ እወደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል። ⁴⁸ እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።
መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁷ እኔ እወደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል። ⁴⁸ እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።

#ጸሎት እግዚአብሔር ሆይ ይህ ሞኝነት በሚመስል መንገድ እያደረግን ያለነው ነገር በውሎአችን ውስጥ ከቃልህ ጋር የተደጋገመ ንክኪ እንዲኖረን እያደረገን፣ ቃልህን ደጋግመን እንድንመለከተው፣ እንድናሰላስለው እየረዳን ስላለ እናመሰግንሃለን። እናምናለን ይሄ ጊዜ በትእዛዛትህ መንገድ እንድንሮጥ ልባችንን የምታሰፋበት ጊዜ ነው። በዚህ ፍለጋ ውስጥ የአንዳንዶቻችን የፈረሰ መሠውያ እየታደሰ ነው። ቃልህን በእጅና በአፋችን ብቻ ሳይሆን፤ በልባችን የምንይዝበት፣ የምንሰውርበት ጊዜ ይሁንልን። ሸማ ሰሪ ጥጡን በወደደው መንገድ ፈትሎ፣ አንዱን ክር ከሌላው ጋር እንደፈቀደው አጋምዶ አልባሳቱን ይሰራል፤ ውበት ያላብሰዋል። እግዚአብሔር ሆይ አንተም እንዲሁ ፈጣሪያችን፣ ሰሪያችን ነህና ሕያው፣ የሚሰራ በሆነው ቃልህ ሕይወታችንን እንደገና ፈትለህ ስራው፣ እንደወደድኽ አበጃጀን። ከልዑል አምላክ ማዕድ፣ ገበታ ያለመከልከል መቁረስ እንዴት መታደል ነው?! የተከበሩ የምንላቸው ሰዎች እንኳ በማዕዳቸው ማን መታደም እንዳለበት መስፈርት ያወጣሉ፤ የተመረጡ ለሚሏቸው ሰዎች ስፍራ፣ የክብር ወንበር ያዘጋጃሉ። እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሰው አይን የማይገቡ፣ የተናቁ የሚመስሉትን ሳትንቅ፤ የተሰበረና የተዋረደውን መንፈስ በማዕድኽ ዙሪያ የምትሰበስብ፣ የተራቡና በመንፈስ ድሆች የሆኑትን ከሕይወት ቃል፣ ከሕይወት እንጀራ የምታጠግብ ቸር አባት ነህና ስምህ ይባረክ። አቤቱ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ የፊትህ ብርሃን በላያችን ያብራ፣ የቃልህ ፍቺ፣ ትርጓሜ አስተዋዮች ያድርገን፣ በትእዛዛትህ መንገድ እንድንሮጥ ልባችን ይስፋ!! አሜን!!

ቃልህ___Kalih(128k).m4a4.75 MB

መዝሙር 119 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴¹ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ወደ እኔ ይምጣ፤ ማዳንህም እንደ ቃልህ ይላክልኝ። ⁴² በቃልህ ታምኛለሁና፣ ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ። ⁴³ ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ። ⁴⁴ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ። ⁴⁵ ሥርዐትህን እሻለሁና፣ እንደ ልቤ ወዲያ ወዲህ እመላለሳለሁ። ⁴⁶ ምስክርነትህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ፤ ይህን በማድረግም ዕፍረት አይሰማኝም። ⁴⁷ እኔ እወደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል። ⁴⁸ እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።