HOP Ministry
Open in Telegram
HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
614
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+6830 days
Data loading in progress...
Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
October '26Oct '26
October '26
+17
in 1 channels
September '26
+82
in 1 channels
Get PRO
August '26
+83
in 1 channels
Get PRO
July '26
+459
in 3 channels
Get PRO
June '260
in 2 channels
Get PRO
May '26
+3
in 2 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 09 October | +1 | |||
| 08 October | +2 | |||
| 07 October | +3 | |||
| 06 October | 0 | |||
| 05 October | +1 | |||
| 04 October | +3 | |||
| 03 October | +2 | |||
| 02 October | +1 | |||
| 01 October | +4 |
Channel Posts
ከፊት ላለው፣ ለሚጠብቀኝ፣ እንዴት እንደሆነ ለማላውቀው መንገዴ እግዚአብሔር ዋስትናዬ ነው። የምሄድበትን መንገድ የሚያውቀውን አምላኬን አምነዋለሁ።
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 12, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
| 2 | #ከድካም_ሸሽቶ_ወደ_እግዚአብሔር_መሮጥ፡፡
ድካም እኛን አስሮ፣ ገንዘቡ አድርጎ ለማቆየት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች ዋና ዋናው በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ብቁ አለመሆናችንን ማሳየት፤ የዛልንበትን ነገር፣ ውድቀታችንን በልባችን ላይ ማግዘፍ፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የማይገባን መሆናችንን፣ እግዚአብሔርም በእኛ ደስ እንደማይሰኝ ማሳሰብ ነው፡፡
ለምሳሌ በእግዚአብሔር ፊት መጸለይ፣ ቃሉን ማጥናት፣ ፈቃዱን ማድረግ ሲገባን ፈቃድ፣ ጊዜ፣ ትኩረታችንን ለሌላ ነገር ሰጥተን ከእግዚአብሔር ፊት ስንጠፋ #ልባችን_እግዚአብሔርን_እንዲሰማ_ክፍት_ካላደረግነው በቅድሚያ ለማድረግ የሚቀናን ሁሉን አልፎ ወደ እግዚአብሔር መገስገስ ሳይሆን፣ በጀመርነው የስህተት መንገድ መቀጠል፣ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ አለመብቃታችንን እያሰብን ወደኋላ ማፈግፈግ ነው፡፡
በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እግዚአብሔር የሚወደው፣ የሚሻው በድካማችን ተሸማቀን ከፊቱ እንድንርቅ ሳይሆን ከድካማችን ሸሽተን ወደ እርሱ፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድንመለስ ነው፡፡
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የእረፍት ጥሪ ብርቱዎችን ወደ እርሱ ለማሮጥ የተነገረ ሳይሆን፤ ደካሞችን፣ ሸክም የከበደባቸውን ወደ አሳራፊው ለመሳብ፣ለማሳረፍ የተነገረ ነው፡፡
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" — ማቴዎስ 11:28
በእግዚአብሔር የጸጋ ዙፋን ፊት በእምነት የምንቀርበውም ያለ አንዳች ድካም የሆንን፣ በራሳችን የበቃን እና ጥንቅቅ ያልን ሰዎች መሆናችንን ለማሳየት ሳይሆን፤ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ምህረትን እንድንቀበል፣ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ነው፡፡
"እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።" — ዕብራውያን 4:16
ከድካም ጋር ስታገል፣ ስንፍናዬ፣ አለመብቃቴ፣ ስህተቴ ገዝፎ ሲታየኝ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ሳፍርና ስሸማቀቅ፣ ለመጸለይ፣ ቃሉን ለማጥናት አቅም ሳጣ እግዚአብሔር ለልቤ አንድ ነገር ሲናገር ተሰማኝ፡፡ ይህም፦ ለድካም፣ ለስንፍና፣ ለየትኛውም ስህተትና አለመብቃት መፍትሔውና መድኃኒቱ ከእግዚአብሔር መሸሽ፣ ወደኋላ ማፈግፈግ ሳይሆን አንዳሉ፣ የሆኑትን ሆኖ፣ በተሰበረ ልብ፣ በእምነት ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ ጸጋው ዙፋን መቅረብ ነው፡፡
ይሄ ሲገባኝ በእግዚአብሔር እግር ስር ለመውደቅ አቅም አገኘሁ፡፡ ለእግዚአብሔርም እንዲህ አልኩት፡- እግዚአብሔር ሆይ ከድካሜ ስሸሽ ወደ አንተ እሮጣለሁ፡፡ ድካም አቅም የሚያጣው፣ ድል የሚነሳው በአንተ ፊት ብቻ ነው፡፡ አቤቱ ድካሜን እይ፣ ሸክሜን ተመልከት፣ በጸጋህ ጉልበት ከላዬ አንሳው፣ እንደገና አድሰህ፣አጽንተህ አቁመኝ፡፡ ሳልዝል እንድከተልህ ጸጋህን አብዛልኝ አሜን!!
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 11, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 324 |
| 3 | ፀሎቴ__Tselote_Prayer(128k).m4a | 87 |
| 4 | #ጸሎቴ፦
እግዚአብሔር ሆይ ብዙዎች አሁን ታይተው ወዲያው እንደ ጤዛ በሚጠፉበት በዚህ ዘመን፤ በምድር ብሰነብት ለአንተ እንዳድር፣ እንድኖር እርዳኝ!!
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 10, 2026 | 597 |
| 5 | #የፈለግነውን_ነገር_በማጣት_ውስጥ_የእግዚአብሔር_ጥበቃ_አለ።
#የፈለግነውን_ነገር_ባለማግኘት_ውስጥ_ለሚያስፈልገን_ነገር_በእግዚአብሔር_ተጠብቆ_መቆየት_አለ።
በሕይወታችን ውስጥ ፈልገን ስላጣነው ነገር፣ ከእግዚአብሔር ለምነን ስላልተቀበልነው ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።
ምክንያቱም እግዚአብሔር የለመነውን ነገር ለእኛ ባለመስጠቱ ውስጥ እኛን ከጥፋት እየጠበቀን ነው።
የለመነውን ነገር በመከልከል ለሚያስፈልገን ነገር ጠብቆ፣ ሸሽጎ ለሚያቆየን አምላክ ክብር ይሁን!!
#የእግዚአብሔር_ፈቃድ
#የእግዚአብሔር_ጊዜ
#የእግዚአብሔር_ጥበቃ
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 10, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 686 |
| 6 | "ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ። መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።"
— ኢሳያስ 40:27-31 (አማርኛ 1954) | 811 |
| 7 | Track_14_Erasih_Asitemarekegn_እራስህ_አስተማርከኝ_Aster_Abebe_Vol_2128k.m4a | 196 |
| 8 | " #ጉዳይ_የለኝም_ከአንተ_የሚያጎድለኝ፤
#ቁምነገሬ_ነህ_ሌላ_ምን_አለኝ። "
#በየዕለቱ_ከእግዚአብሔር_ጋር
#እግዚአብሔርን_ማስቀደም
#እግዚአብሔርን_መፈለግ
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
https://t.me/hopministry10 | 1 197 |
| 9 | የእግዚአብሔር እጅ ይታመናል። "ምን ይፈጠር ይሆን?" ብለን እስካንሰጋ ድረስ ሁሉን ለታማኝ እጁ ጥለን፣ ራሳችንንም በማይጥል እጁ ላይ አሳርፈን እርፍ! እንላለን።
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 5, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 1 116 |
| 10 | ለመናገር፣ ለመምከር፣ ለመገሰጽ፣ ለማስተማር፣ ልብን ለማቅናት ያልደከመው እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ቃሉ እያለን፤ ለመስማት፣ በእግሮቹ ሥር ለመቀመጥ የዛልን እኛ፣ ይህን የተሰጠንን ዕድል እንዴት አባከንን?!
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 3, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 1 085 |
| 11 | Emailing NEXT STEP DISCIPLESHIP - Central Press Version.pdf | 331 |
| 12 | እንደ-ብልኋ-ሴት.m4a | 328 |
| 13 | #ትንሿ_የብርሃን_ጭላንጭል
ትንሿ የብርሃን ጭላንጭል ብርሃንዋን በሚያዳፍን ከባቢ መሃል፣ ብልጭታዋን በሚያጠፋ ነፋስና ውሽንፍር መሃል ከተገኘች ምንም ያህል ታግላ ለጥቂት ጊዜ እያበራች ለመቆየት ብትጥርም የባሰው፣ የበረታው ነገር መጥቶ ኃይሏን ባዳከመው ጊዜ እልም ብላ መጥፋቷ፣ በጽልመት መዋጧ አይቀርም።
የዛሬው ማለዳዬ ላይ ወደ አዕምሮዬ የመጣ፣ ደግሞ አሁን ወደ መኝታዬ ልሄድ ስልም አሳቤ ላይ ውል ያለው ነገር ይህ ነው፦ መንፈሳዊ ግለትን ስለመጠበቅ፣ እየነደዱ ስለማብራት፣ ብርሃንን እያደመቁ ስለመሄድ ያለን ምልከታ እንዴት ነው? ለነገሩስ ምን ያህል ትኩረት እንሰጣለን?
ይሄን ሳስብ ወደ አዕምሮዬ የመጣው አሳብና የሳልኩት ምስል፦ በጽሑፌ መግቢያ ላይ ያለችው ላለመጥፋት፣ ብርሃኗን አስጠብቆ ለማቆየት፣ እንዲሁም እያደመቁ ለመቀጠል የምትታገለው ትንሿ የብርሃን ጭላንጭል ናት።
መንፈሳዊነታችንን በዚህ ምሳሌ መሰልኹት። እንደሚታወቀው መንፈሳዊነታችን እድገት፣ መሰራት፣ መታነጽ፣ ክርስቶስን እየመሰሉ ወደ ፍጽም ሙላቱ መገስገስ ያለበት ሕይወት ነው።
ታዲያ ለም መሬት፣ የሚያስፈልገውን አቅርቦት ሁሉ ያገኘ ተክል ለመፋፋትና፣ ለልምላሜ የቀረበ እንደሆነ ሁሉ አሁን የምንኖርበት ዓለም፣ በዙሪያችን ያለው ነገር መንፈሳዊነታች እንዲፋፋ፣ እየለመለመ እንዲሄድ የሚያደርግ ሳይሆን የሚያከስም፣ የሚያደርቅ፣ ጥቂቷን የብርሃን ጭላንጭላችንን እንኳ እልም አድርጎ ለማጥፋት የበረታ ነው።
በዓለም ያለው ፈተና እና ተግዳሮት እንዳለ ሆኖ፤ የብርሃናችን ጭላንጭል መጥፋት፣ የመንፈሳዊ ሕይወታችን መድረቅ ሁነኛው ባለ ድርሻ እኛው ነን ብዬ አስባለሁ። ምክያቱም አዋዋላችንን በማስተዋል አንመርጥም፣ አናስተካክልም። መንፈሳዊነታችንን ከሚያፋፋው ነገር ይልቅ ለሚያደርቅ፣ ለሚያጠወልገን ነገር ወደን እንገኛለን፤ የብርሃን ጭላንጭላችንን ሊያጠፋብን ለተዘጋጀ ነገር ደጃችንን ከፍተን እንቀመጣለን፤ እያሳሳቀ ሊወስደን የመጣውን ወንዝ ልንዋኝበት ይቃጣናል።
ብቻ ልዘርዝር ካልኩ የእኔ ተግዳሮቴና ድካሜ ብዙ ነው፤ 1, 2, 3......ብዬም አልጨርሰውም፤ የእናንተም እንደዛው ይሆናል የሚል ግምት አለኝ፤ እንዘርዝረውና የጋራ የሆነውን እንለይ ካልን አንድ፣ ሁለት ተመሳሳይ ነገርም አናጣም።
ሆኖም ለራሴ ካልኩት እና ከምለው ነገር ለእናንተም የምለው ነገር ቢኖር የመንፈሳዊነት ጭላንጭል ብርሃናችንን ሊያጠፋብን ከበረታ ነገር ጋር አንወዳጅ፣ ራሳችንን እንጠብቅ፤ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ከሚያፋፋው እና ብርሃናችንን ከሚያደምቀው ነገር ጋር እንወዳጅ። ጸጋ ይብዛልን!!
✍️ መክሊት አየለ
📆 September 30, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 1 433 |
| 14 | #ከመጽሐፍት_ገጾች
አንድ መጽሐፍ እያነበብኩ፣ ጸሐፊው የኃጢአት ደመወዝ ስለሆነው ሞት እና ኃጢአት ስለሚወልደው ሞት ካብራራበት መንገድ አንዱ በጣም አስደነቀኝ። እንዲህ ይላል፦
“The wage for sin, or what we have earned, is death. This death isn’t just the end of life after we grow old. Death comes in several forms for the person who doesn’t belong to God. First, sin produces a death of freedom so that we become enslaved.”
“Sin produces a death of freedom so that we become enslaved.”
በዚህ ዓረፍተ ነገር ውስጥ በነጻነት ውስጥ ሞት፣ እንዲሁም ከነጻነት በስተጀርባ ባርነት እንዳለ ማስተዋል እንችላለን። እንደ ሰው አስተሳሰብ ግን ማን ነጻነት ሞትን፣ ነጻነትም ባርነትን ይወልዳል ብሎ ያስባል?
ይህን ሀሳብ በአግባቡ እንድንረዳው፣ ጸሐፊው ቀጥሎ ያለውን ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ጋር ያቀርባል፦
“Sin traps us and becomes a ruthless master over our lives.”
“የኃጢአት ባሪያዎች ሳላችሁ ከጽድቅ ነፃ ነበራችሁና።”
— ሮሜ 6፥20 (አማርኛ 1954)
“For when you were slaves of sin, you were free in regard to righteousness.”
— Romans 6:20 (ESV)
ኃጢአት በሚሰጠው ነጻነት ውስጥ ፈቅደን በተመላለስን እና ወደን ለኃጢአት በተገዛን መጠን፣ ከጽድቅ ነፃ ሆነን፣ በባርነትም ሆነ በሞት ውስጥ እንኖራለን።
በተቃራኒው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚሰጠው ነጻነት ውስጥ ፈቅደን በተመላለስን እና ወደን ለእርሱ በተገዛን መጠን፣ ለኃጢአት ሞተን፣ ከኃጢአትና ከሞት በላይ ሆነን፣ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆነን መኖር እንችላለን።
#HOPMinistry
#HearObeyPractice
#DailyDevotional
#ከመጽሐፍት_ገጾች
#የመጽሐፍ_ንባብ
#የእግዚአብሔር_ቃል
#ሮሜ6
#FreedomInChrist
#FreedomFromSin
#ChristianReflection | 1 417 |
| 15 | ጸሎቴ፦
ጌታ ኢየሱስ አንተን አስቀድሜ ከኋላህ መዝመት፣ አንተን አስቀድሜ ከኋላህ መክተት አስተምረኝ። ስከተልህ መንገድህን አልስትም፤ በወደድኹት ከመትመም እጠበቃለሁ።
✍️ መክሊት አየለ
📆 September 29, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 1 289 |
| 16 | #ጸሎቴ፦
እግዚአብሔር ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ የተሰጠ ልብ ፍጠርልኝ። ልቤን ለወደድኹት ከማዋል ጠብቀኝ። ልቤ አንተ፣ የምትወደውም የነገሰበት ልብ ይኹንልኝ። ሳስደስትህ ዘመኔ ይጠቅለል።
✍️ መክሊት አየለ
📆 September 28, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 1 517 |
| 17 | Pastor_Tesfaye_Gabiso_ፓስተር_ተስፋዬ_ጋቢሶ_መህረቱ_አያልቅምና_Protestant_Mezmuer.m4a | 317 |
| 18 | ያላለቀ ፍቅር፣ ያላለቀ ምህረት፣ ያላለቀ የእግዚአብሔር ርህራሄ ተሸክሞ ዘመናትን አሻግሮናል። ደግሞም የማያልቅ ርህራሄ ያለው ቸሩ አምላካችን ዛሬን፣ ነገንም ሊሸከመን፣ ሊያሻግረን የታመነ ነው።
✍️ መክሊት አየለ
📆 September 27, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional | 1 777 |
| 19 | #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
https://t.me/hopministry10 | 1 918 |
| 20 | የሚስጨንቀንን ነገር፣ ሸክማችንን ሁሉ ገለል አድርጎ፣ እርግፍ አድርጎ ትቶ፦ ቅድሚያ ለእግዚአብሔር መስጠት፣ በእግዚአብሔር ፊት መሆን ይቻላል።
https://t.me/hopministry10 | 2 256 |
