HOP Ministry
Открыть в Telegram
HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
566
Подписчики
+524 часа
+257 дней
+5930 дней
Архив постов
566
ዛሬም ገና ያልያዝነው፣ ያወቅው ግን ደግሞ ተረድተን ያልጨረስነው እግዚአብሔር እንዳለ እናስተውል።
📖 Hear. Obey. Practice.
#HOPMinistry #HearObeyPractice
#DailyDevotional
t.me/hopministry10
566
በእድሜ መጎልመስ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤት ብዙ ጊዜ መቆየት አንድ ነገርን ሊያጠፋብን አይገባም። እርሱም፦ እግዚአብሔርን ለማወቅ መቃተት፣ መናፈቅ፣ መበርታትን። የሁልጊዜ ስራችን እርሱን ለማወቅ መበርታት ከሆነ በእግዚአብሔር ላይ ሳናድግ ዘወትር እንደ ልጆች፣ እንደ ህጻናት የቃሉን ወተት እንመኛለን። ዋል አደር እያልን ስንሄድም ገና እንዳልያዝነው እየገባን ዱካውን መከታተል እናበዛለን።
ዛሬም ገና ያልያዝነው፣ ያወቅው ግን ደግሞ ተረድተን ያልጨረስነው እግዚአብሔር እንዳለ እናስተውል። በዙሪያችን የሚሆነው ነገር፣ የሕይወት አዙሪት እየወጣ እየገባ፣ እየበላ እየጠጣ፣ እየተኛ እየተነሳ.... መደበኛ ኑሮው ላይ ብቻ ተጠምዶ የሚኖር #አማኝ፣ እግዚአብሔርን አዋቂ ነኝ ባይ ሰው ሊያደርገን የተጋ ነው። እኛ ግን በዚህ አዙሪት መሃል ቆም ብለን በየዕለቱ ልባችንን፣ አሳባችንን፣ ጊዜያችንን፣ ትኩረታችንን ልንሰጠው የሚገባ እግዚአብሔር እንዳለ ማሰብ፣ ማወቅም ይኖርብናል። እግዚአብሔር የየዕለት ነው፤ የሁሌ ነው፤ የዕለት እንጀራችን ነው። በሕይወት ለመሰንበታችን ወሳኙ መብል፣ መናም እርሱ ነው።
ሌላው በዚህ እርሱን የማወቅ ፍለጋ ውስጥ መታደስ አለ። ይህም ለሕይወታችን እንዲሁም ለሕይወት ትርጉማችን (ስንኖር ልናደርገው ለተገባን ዓላማችን) ነው። ከጊዜ ብዛት ዘንግተነው ሕይወት ጣዕም ካጣብን እንኳን፤ ወደ እርሱ ቀርበን የልባችንን ስናወጋው፣ የልቡንም ስንጠይቀው፦ በልብ በነፍሱ ያለውን አሳቡን ሹክ ይለናል፤ የልቡን መሻት እንደገና ያስረዳናል። እኛ ብቻ ልንፈልገው፣ ልናውቀው፣ ልንከተለው እንበርታ እንጂ እርሱ እንደ ወገግታ ተዘጋጅቶ እንደምናገኘው ቃሉ ዋስትናችን ነው።
“እንወቅ፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ እንደ ዝናብም ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ መጨረሻ ዝናብ ይመጣል።”
— ሆሴዕ 6፥3
1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥
²-³ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።
✍️ መክሊት አየለ
📆 October 2, 2025
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
566
#እኔ_እንደምፈልገው_ሳይሆን_አንተ_እንደምትፈልገው_ይሁን የሚለው ጸሎት እጅግ በጣም ቅልል ያለ፤ በምቹ ጊዜ፣ ጥቅማችን ባልጎደለ ሰዓት፣ የእኛ የምንለው ሁሉ ሳይነካ ብቻ የሚጸለይ ጸሎት ነው? ተግባሩስ እንደ ንግግሩ ቀላል ነው?
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሄን ጸሎት የጸለየባት ወቅት ሁሉ ሊያበቃ ተቃርቦ፣ የሞት አፏፍ ላይ ቆሞ ነው። መከራን ሊቀበል እንደሆነ፣ ወደ ሞት እንደተቃረበ ያውቃል። #ቢቻል ይህ ጽዋ ከእርሱ ቢያልፍ ይሻል፤ ነገር ግን ብሎ ሲቀጥል ግን የአባቱን ፈቃድ መፈጸም የእርሱ ዋና ጉዳይ ነው።
የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ አባቱ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ የእርሱ ደስታው፣ ምግቡም ነው። እርሱን ተመችቶት፣ እርሱ የሚፈልገው ሆኖ፤ ነገር ግን አብ ደስ ባይሰኝ፣ አብ የሚፈልገው ባይሆን የወልድ ልብ አያርፍም።
የምሳሌያችን የእግዚአብሔር ወልድ ደስታና እረፍት ያለው፦ ፍላጎቱን ትቶ እግዚአብሔር አብ የሚፈልገውን በማድረግ ውስጥ ነበር። እያዘነ፣ እየተከዘ፣እየተጨነቀ፣ ነፍሱ እስከ ሞት ድረስ አዝና ቅድሚያ የሚሰጠው ለአባቱ ፈቃድ ነው። " #እኔ_እንደምፈልገው_ሳይሆን_አንተ_እንደምትፈልገው_ይሁን" የማይቀየር ጸሎቱ ነው።
እኛስ? አይደለም የሞት አፋፍ ላይ ቆመን በደህናው ጊዜ፣ አገር ሰላም በሆነበት ወቅት እንኳን ልባችን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ምን ያህል ይገዛል? እኛና የእኛ ወደ ኋላ ቀርተን እግዚአብሔርን፣ የእግዚአብሔርን ለማስቀደም ምን ያህል ታዛዦች ነን? #እኔ_ልቅደም፣ #የእኔ_ይቅደም ከማለት ይልቅ እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ እንደምትፈልገው ይሁን ብለን ሁሉን ለፈቃዱ ለመሰዋት ምን ያህል ቅርብ ነን?
ጌታ ይርዳን!! ጸጋ ይብዛልን!!
ማቴዎስ 26 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁹ ጥቂት ዕልፍ ብሎ በግንባሩ በመደፋት፣ “አባቴ ሆይ፤ ቢቻል ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ነገር ግን እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ እንደምትፈልገው ይሁን” ብሎ ጸለየ።
…
⁴² እንደ ገና ለሁለተኛ ጊዜ ሄዶ፣ “አባት ሆይ፤ ይህ ሳልጠጣው የማያልፍ ጽዋ ከሆነ፣ ፈቃድህ ይፈጸም” ብሎ ጸለየ።
…
⁴⁴ ትቶአቸውም እንደ ገና በመሄድ ለሦስተኛ ጊዜ ቀደም ብሎ የጸለየውን ጸሎት ደገመ።
✍️ መክሊት አየለ
📆 February 19, 2025
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
566
ቤተክርስቲያን የፍጹማን፣ ተሰርተው ያለቁ ሰዎች ጉባኤ ብትሆን ኖሮ እግዚአብሔር አገልጋዮችን ባልሾመና ባላበዛ ነበር። የሚሰራ፣ የሚታነጽ ብዙ ሕይወት ይጠብቀናል።
566
#በድካማችን_የሚራራልን_ሊቀካህናት_ኢየሱስ።
የሰው ድካም ብርቱ ነኝ ባዩን ሰው ራሱን ከደካማው ሰው ጋር አነጻጽሮ በራሱ እንዲኮራ፣ እንዲመካ፣ ደካማውን እንዲንቀው ሲያደርገው፤ በራሱ፣ ጻድቅ በመሆኑ፣ ኃጢአትን ባለማድረጉ ሊመካ የተገባውን በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠው ታላቁ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ግን ለደካማው በድካሙ ይራራለታል።
ሰው ሆኖ ከኃጢአት በቀር ሰው የሚያልፍበትን መንገድ፣ የሚደርስበትን ነገር ሁሉ ስላየው ይረዳዋል፣ ይረዳዋል ( ይረዳዋል፦ ሲጠብቅም፣ ሲላላም)።
የዚህን ሊቀ ካህናት ታላቅነት አስቤ በታላቅነቱ ስደነቅ ለደካማው የሚራራ ልቡ፣ የወደቁትን ለማንሳት ፈጥኖ የሚዘረጋው እጁ ደግሞ ሌላው ድንቅ የጥልቅና የፍጹም ፍቅሩ ማሳያ ሆነብኝ።
ክብር ለሊቀ ካህናችን ይሁን!!
#ይራራልናል!
ዕብራውያን 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ እንግዲህ ወደ ሰማያት ያረገ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።
¹⁵ በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም።
¹⁶ እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበልና በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፣ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
✍️ መክሊት አየለ
📆 March 23, 2025
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
566
“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”
— ዕብራውያን 12፥1-2
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
#LookingtoJesus
566
ብልኽ የኢየሱስ ተከታዮች፦ ተልከው የመጡበትን ዓላማ ሳይዘነጉ፣ አይናቸውን ጉዳያቸው ላይ እንደተከሉ፣ ትኩረታቸው በባዕዳን ሳይቀማና ሳይደበዝዝ ከግብ ይደርሳሉ።
566
#ጉዳዩ ኢየሱስ ብቻ የሆነ ሰው፤ ከእርሱ ሌላ ነገር ማየት፣ ማሰብ፣ መስማት፣ ማውራት ያቃተው እንዴት የታደለ ነው?!
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
t.me/hopministry10
566
" #አይኔን_ጉዳዬ_ላይ_ማድረግ! "
#ጉዳዩ ኢየሱስ ብቻ የሆነ ሰው፤ ከእርሱ ሌላ ነገር ማየት፣ ማሰብ፣ መስማት፣ ማውራት ያቃተው እንዴት የታደለ ነው?!
በዚህ ቢሉት በዚያ ልቡንና አሳቡን ከተከለበት ከአምላኩ ውልፍት የማይል፣ ብዙ ነገሮች አባብለው ከትኩረቱ ሊወስዱት ቢጥሩ እንኳን ዞሮ አይኑን ወደ ተከለበት መነሻው የሚመለስ፣ ከእግዚአብሔር ውጪ ርዕስ ያጣ ሰው እንዴት የታደለ ነው?!
ይሄንን እያሰላሰልኩ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፦ ልጆች እያለን ወላጆቻችን ሱቅ አልያም ሌላ ቦታ ሲልኩን ለመሄድ ከመውጣታችን በፊት የሚሰጠን አንድ ማስጠንቀቂያ ነበር፤ "የላኩሽ ቦታ እስክትደርሺ ድረስ በየመንገዱ እንዳትቆሚ፣ ማንም ቢያናግርሽ መልስ እንዳትሰጪ፣ ቆመሽ ወሬ እንዳታዪ፣ እንዳትጫወቺ.....ወደ ተላክሽበት ቦታ ቀጥ ብለሽ ሄደሽ በፍጥነት ተመለሺ" እነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉት ዛቻ የተቀላቀለባቸው ጥብቅ ማስጠንቀቂያዎች ዓላማቸው ከተላክንበት ስፍራ፣ ተልከን ከወጣንበት ጉዳይ ላይ አይናችንን ሳንነቅል፣ በሌላ በምንም ነገር ትኩረታችን ሳይወሰድ፣ ከቤት የወጣንበትን ዓላማ ዘንግተን በመንገድ ላይ እንዳንባዝንና እንዳንባክን ነው።
በዚህ ምሳሌ ውስጥ እኛን እና በዚህ ዘመን ያለንበትን ሁኔታ አስገብቼ ስገመግም አንዳንዴ እንዲሁም አብዛኛውን ጊዜ፣ አብዛኞቻችን አተኩረን ልናይ የተገባንን ነገር፣ ተልከን የወጣንበትን ዓላማ ዝንግት አድርገን፦ በየፌርማታው እየቆምን ሕይወት የሌለበትን፣ የማያሰነብተንን፣ የማያሳድገንን፣ የማይጠቅመንን ወሬ ማየት፤ በጠፊ በአላፊው ነገር መደነቅና መወሰድ፤ ጠልፎ በሚጥለን፣ አንቆ እንዳናፈራ በሚያደርገን፣ በመንገድ በሚያስቀረን የማይመች አካሄድ መጠመድ፤ ከግብ ሳይደርሱ እንደወጡ ለመቅረት መጣደፍ ስራችን ሆኗል።
ብልሆቹ ግን ተልከው የመጡበትን ዓላማ ሳይዘነጉ አይናቸውን ጉዳያቸው ላይ እንደተከሉ፣ ትኩረታቸው በባዕዳን ሳይቀማና ሳይደበዝዝ ከግብ ይደርሳሉ።
ጌታ እግዚአብሔር የልቦና አይኖቻችንን ያብራልን፤ ማተኮር የተገባን ነገር ላይ አይኖቻችንን ተክለን ዘመናችን እንዲጠቀለል ይርዳን!!
✍️ መክሊት አየለ
📆 February 25, 2025
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional
566
" #ከእግዚአብሔር_ጋር_ያለ_ሰው_ድፍረት"
በጨለማ አግኝተኸኝ ለጨለማው ስላልተውኸኝ፣ ታካች ነፍሴን ስላበረታኽ፣ በሕይወት መንገድ ስለመራኸኝ፣ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ስለሆንኸኝ ከልቤ አመሰግናለሁ።
ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ሰው ድፍረት ወደ ራሱ፣ ወደ ሰዎች፣ ወደ ቁስ አያመለክትም፤ ነገር ግን
ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ሰው ድፍረት ይህ ነው፦
“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ?”
— መዝሙር 27፥1 (አዲሱ መ.ት)
ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ሰው ድፍረት፦ በጨለማው ላይ ብርሃኑን እግዚአብሔርን እያበራ፣ የሕይወት ዐምባውን ታምኖ፣ በብርሃን፣ በሕይወት ይኖራል።
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዴት ድንቅ ነው?! "ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ሰው ድፍረት" ብሎ ወደ ሰው ልጆች ኃይል ወይም በሰው አይን መመኪያ ወደ ተባሉ ቁሶች አይጠቁምም፤ ይልቁንም የሁሉ ምንጭ፣ የሁሉ ፈጣሪ የሆነውን እግዚአብሔርን፦
“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ?”
— መዝሙር 27፥1 (አዲሱ መ.ት)
ሲል አድምቆ ያሳየናል።
ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ሰው ድፍረት ልባችንን ይሙላው፣ ይክበበን፤ ሞገስ፣ ትምክህትም ይሁነን!!
✍️ መክሊት አየለ
📆 June 8, 2026
#HOPMinistry #DailyDevotional
#TheLORDismylight #TheLORDismysalvation
566
#ምድር_ትሞቃለች_ግን_የዘላለም_ቤት_አትሆንም!
ሰማይን የሰነቀ፣ መዝገቡን በዚያ የሰወረ ልብ ያለው ሰው ምን ፈዝዞ ከምድሩ ነገር ጋር ቢዛመድ አንድ ቀን ማብቂያ እንዳለው፣ የተሻለ ተስፋ እንዳለው ያውቃል፣ ያስባል።
እግዜሩ በዚህ ዘመን የዘላለም አጀንዳውን ለጠፋው የሰው ልጅ ለመግለጥ፣ ሹክ ለማለት አንደበት ሊሆኑት በብርሃን ያሉትን፣ የዳኑትን ልጆቹን ይጠቀማል፤ ይጠብቃል። መልዕክተኛ ብሎ፣ አድርጎም ሾሟቸዋልና አንደበታቸው የሰማዩን ዜና እንዲያበስር፣ ሕይወታቸውም እርሱን እንዲሰብክ፣ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ እንዲሆን ይጠብቃል።
ዛሬ በጌታ ፊት ሆኜ ስለፈቃዱ ለመጸለይ፣ የመንፈስ ቅዱስንም አሳብ ለማድመጥ ስሞክር ሕይወቴ ውስጥ ያለ ትልቅ ክፍተት ታየኝ። ራሴን ሳይ፦ ምድር የተመቸኝ፣ የሞቀኝም እንመስላለኹ። የእግዚአብሔር መንግሥት ጉዳይ፣ የነፍሳት መዳን ብዙም ልቤ ላይ ከብዶ ሲከነክነኝ አላይም።
በፊት በፊት በቀን ውሎዬ ድንገት ምን እንደነካኝ ሳላውቅ ኢየሱስ የሞተላቸው ብዙዎች ገና በጨለማ እንዳሉ አስብና ማልቀስ እፈልጋለሁ፤ አንዳንዴም እንደ ሰው ልማድ ወንጌል ለመመስከር "ይሄ ትክክለኛው ቦታ አይደለም" የሚባል ስፍራ እንኳ ቢሆን የእሳት ፍም የተጨመረበት ይመስል ልቤ ስለሚቃጠል፣ ተንፍሺ እያለ የሚተናነቀኝ አንዳች ነገር ስላለ፤ ጨከን ብዬ ኢየሱስ ይወድሃል/ ይወድሻል ለማለት ድፍረቱ ነበረኝ።
የስራ ሁኔታዬ የተለያዩ ሰዎችን፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ የተለያየ ሁኔታና ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎችን አገናኝቶኝ ስለሚያውቅ ምነው እነዚህ ሁሉ ሰዎች ጌታ ኢየሱስን ቢያውቁት ብዬ አስባለሁ፤ ደግሞ የመናገር፣ የማስተማር፣ የማሰልጠን እድሉን ሳገኝ የዕለቱ አበይት ርዕሰ ጉዳይ ሌላ ቢሆን እንኳን በዚህም በዚያም ብዬ፣ ነገሩን ጠምዝዤ የሕይወትን ትርጉም እንዲያስቡ፣ ራሳቸውንና ያሉበትን ሁኔታ እንዲመረምሩ፣ ዓላማ እንዲኖራቸው ለማድረግና የእግዚአብሔር መንግሥት፣ የዘላለም ሕይወት የሚባል ነገር እንዳለ ጠቆም አድርጌ ለማለፍ ሞክራለሁ።
አሁን ግን የምገባ፣ የምወጣ፣ የምሰራ፣ የምማር፣ በስራ ገበታዬ፣ በቀን ውሎዬ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የምገናኝ ብሆንም ያ የጠፉትን ለመፈለግ የተከፈተው አይኔ፣ የነፍሳት መዳን ጉዳይ ረሃቡ የሆነው ልቤ በእኔ ውስጥ ኮስሷል። ምድር ሞቃኝ ተደላድዬ ለመኖር ብዙ እቅድ አቅዳለሁ።
ከዚህ ሁሉ ብክነት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቆም! እንድል ስለረዳኝ አመሰግነዋለሁ። እኔማ በፊቱ መንበርከኬና ልሰማው መጠጋቴ ሕይወቴን ስራው፣ ቀይረኝ ከሚለው ራስ ተኮር ጸሎቴ እልፍ ያለ አልነበረም። እርሱ ከልብ ለሚሹት መገኘት፣ ለመሰራት ፈቅደው የተጠጉትን ማበጃጀት መች ተስኖት፤ ባልጠይቀውም ላይተወኝ፣ ሊሰራኝ የታመነ ነው።
ነገር ግን የኔን ነገር ገታ አደረገና፤ ስለ ዘመኑ ማለቅ፣ ስለ ብዙዎች አሁንም በጨለማና በእስራት ውስጥ መኖር እንዳስብ አደረገኝ። ሳላስብ ማልቀስ ጀመርኹ፤ ከልቤ የተወሰደው ስለ ሌሎች የነበረ ሸክሜ ትዝ አለኝ፤ በዙሪያዬ፣ ደግሞም በመላው ዓለም ብዙ ያልዳኑ ሰዎች እንዳሉ እንዳስብ አደረገኝ።
የእግዚአብሔር አምሳል የሆነውን የክርስቶስ፣ የክብሩን ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ፣ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን ሰዎች ልቡና እንዳሳወረ ሁሉ የእኛ ልቡናም በጠፊ በአላፊው ፍቅር ተነድፎ፣ ምድር ሞቅ ብላን፣ ሁሌ የምንኖርባት እስኪመስለን ድረስ ተደላድለን እንድንቀመጥ፣ ወንጌላችን የተከደነ እንዲሆን አዚም ያደረገብን ነገር እንዳለ አሰብኹ።
ይኼንን ጽሁፍ ስጽፍ፦ የሚያነቡትን ሰዎች ሁሉ እኔን ያነቃ መንፈስ ቅዱስ እንዲያነቃቸው፣ እኔን እንደሞገተ እና ቆም ብዬ እንዳስብ እንዳደረገኝ ሁሉ ልባቸውን እንዲሞግት በማሰብ ነው።
በመጨረሻም በርዕሱ ላይ እንዳልኹት ደግሜ፦ #ምድር_ትሞቃለች_ግን_የዘላለም_ቤት_አትሆንም! እላለሁ። በተለይ ለእኛ ለአማኞች ምድር የጥቂት ጊዜ የስራ ቦታ፣ የአገልግሎት መስካችን ነች። ለመከሩ ከሚያስፈልጉት ሰራተኞች መካከል አንዱ ነን።
በአንድ ወይም በሌላ መንገድ፣ በእኛ ሁኔታ የሚሰበክ ወንጌል፣ የሚገለጥና የሚታይ ኢየሱስ፣ የሚድኑ እልፍ ሰዎች አሉና ጌታ እግዚአብሔር እንደገና የመንግሥቱን አሳብ በልባችን ይሙላ፣ ለሥራው የታጠቁ ያድርገን፣ ልባችን፣ አንደበታችን፣ እጃችን ለመንግሥቱ ወንጌል ሁነኛ መሳሪያ ይሁን እላለሁ።
ጸጋ ይብዛልን፤ መንፈስ ቅዱስ ያግዘን!!
✍️ መክሊት አየለ
📆 June 8, 2026
#HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional #Gospel #JesusSaves
