en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Open in Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
910
Subscribers
-324 hours
-157 days
+4830 days
Posts Archive
አሰላሙ ዐለይኩም ~ ባለፈው ሳይመቸኝ በመቅረቱ የተላለፈው ሰይድ ቁጥብን የሚመለከተው ፕሮግራም ዛሬ ምሽት 3፡00 ላይ ይኖራል። በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ :- የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

📢 መልካም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ​መርከዝ መናሩ-ሱና በኦንላይን (Online) የሚሰጣቸውን የቋሚ ኪታብና የተፍሲር ትምህርቶች ለመከታተል የሚፈልጉ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀምሯል። ​
📢 መልካም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ! ​መርከዝ መናሩ-ሱና በኦንላይን (Online) የሚሰጣቸውን የቋሚ ኪታብና የተፍሲር ትምህርቶች ለመከታተል የሚፈልጉ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀምሯል። ​ትምህርት ቤታችን በተፍሲር ዘርፍ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎቹን የትምህርት ማረጋገጫ (ሸሀዳ) በመስጠት ያስመረቀ ሲሆን፣ በአቂዳ ዘርፍ ደግሞ ላለፉት 4 ዓመታት ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎችን በአላህ ፈቃድ ከወር በኋላ የሚያስመርቅ ይሆናል። ​በመሆኑም በዚህ የታላቅ እውቀት ማዕድ ላይ ባሉ የተወሰኑ ክፍት ቦታዎች ቀድመው እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል። {​የመምህራን እና የትምህርት መርሃ-ግብር መረጃ} ➠​የተፍሲር ትምህርት፦ በሸይኽ አቡ አማር አወል ቢን አህመድ የሚሰጥ ➠​የዐቂዳ ትምህርት፦ በአቡ ዑበይዳ የሚሰጥ {​የትምህርት ቀናት፦} ከጁሙዓ ውጭ በየቀኑ (ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ እርማት ያካተተ ነው)    { ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች} ◈ ​ቁርኣንን በነዞር (በምልከታ) ቀድሞ ያጠናቀቀ/ች ◈ ​ጥሩ አደብና ኢስላማዊ ሥነ-ሥርዓት የተላበሰ/ች ◈ ​ያለፈቃድ ከትምህርት የመቅረት ልማድ የሌለው/ላት ◈ ​የግሩፑን ደንብና መመሪያ በጥብቅ የሚያከብር/ የምታከብር ◈ ​ትምህርቱን በየቀኑ ሙራጃዐ (ክለሳ) እያደረገ/ች በጥራት የሚከታተል/ የምትከታተል ​📲[ የምዝገባ አድራሻዎች] ●​ለቁርኣን ተፍሲር ትምህርት ለመመዝገብ፦ @Hawie71 ● ​ለዐቂዳ ትምህርት ለመመዝገብ፦ @Ferst6335 ​ማስታወሻ፦ ቦታዎቹ ሳይሞሉ ቀድመው ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ!

رب اجعلني مقيم الصلاة ومن ذريتي ربنا وتقبل دعاء . ربنا تقبل منا إنك أنت السميع العليم وتب علينا إنك أنت التواب الرحيم.

አንድ ከለተሞ መንጋዎች ቻናሉን ልክ ቴሌግራም በአሁን ሰዓት በራሱ ጊዜ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን በቻናሎች ላይ እንደሚለቀው እንዴት እንደሆነ ባላውቅም የልጁም ቻናል በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ቻናል ላይ እየተለቀቀ ነው።ለማንኛውም ሰዎቹ ቻናልህን በሙመይዓ ቻናል ላይ ሼር ተደርጎ አይተናል ብለው አስፈንጥረው ሙመይዕ ብለው እንዳይተኩሱበት ይጠንቀቅ።!

ሙስሊም መሪን በተመለከተ የሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊይ አቋም ቁርኣንና ሐዲሥ ላይ የተመሰረተ ነው። ኢኽዋኖችና የነሱ ፍልፍሎች እንደሚቀጥፉባቸው ሸሪዐ በማይፈቅደው መልኩ መሪዎችን በመታዘዝ ላይ የሚሰብኩ አልነበሩም። ከብዙ ንግግሮቻቸው ውስጥ አንድ ማስረጃ ላቅርብ፦ "እኛ፣ በአላህ እንምላለን፤ ሰይፎች በአንገታችን ላይ ቢደገኑ እንኳን፣ ውሸትን ወይም የተሳሳተ ነገርን መናገር ፈጽሞ የምንፈቅድ አይደለንም። የምንለው፦ “መሪዎችን አላህን መታዘዝ ባለበት ጉዳይ ላይ ታዘዝ፤ አላህን ማመፅ ባለበት ጉዳይ ግን አትታዘዛቸው” ነው። “መሪዎችን አላህን መታዘዝ ባለበት ነገር ታዘዙ፤ አላህን በማመፅ ባለበት ነገር ግን አትታዘዟቸው።” ይህ ኢስላማዊ መርህ ነው ወይስ እስላማዊ መርህ አይደለም? እኔ ይህንን እውነት ነው ለወጣቶች የማቀርበው፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነውን መብትና በላዩ ያለውን ግዴታ እንዲያውቅ ነው። እንዲሁም የነቢዩ ﷺ ትምህርት ያሰመሩበትን መንገድ፣ እንደነገርኳችሁ፣ በትክክል እንዲያውቁ እገልጻለሁ። እኛ የእውነትን ቃል በድፍረት እንናገራለን፤ በአላህ ጉዳይም የሚወቅሰንን ሰው ምንም አንፈራም፤ ይህም በገዢውም ሆነ በተገዢው ላይ ነው። ስለዚህ አላህ በማመፅ በሆነ ነገር ላይ ማንኛውንም ገዢ አትታዘዙ፤ አላህን በመታዘዝ ባሉበት ነገር ግን ታዘዟቸው። ይህ ግዴታ ነው።" = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

♦️♦️♦️እህቴ ሆይ…አቤት ብለሽ ማንበብ እንደጀመርሽ ተስፋ አደርጋለሁ 📌መልካም የሆነን ባል ለረጅም ጊዜ ስትጠብቂ ቆይተሻልን? ብዙ ጊዜ በሌሊት እጆችሽን ወደ ሰማይ አንስተሽ፣ በእንባ ዓይኖችሽን ሞልተሽ፣ “ያ አላህ! የእኔ ተራ መቼ ነው? በሩን አንኳክቶ ወደ ሕይወቴ የሚገባው ሰው መቼ ነው?” ብለሽ ይሆናል። 📍ጓደኞችሽ አንድ በአንድ ሲዳሩ አይተሽ ይሆናል። አንቺ ግን አሁንም ትጠብቂያለሽ። 🔷ሰዎችም ልብሽን በሚያሳምሙ ቃላት፦ “መቼ ነው የምትዳሪው?” “ለምን እስካሁን ዘገየ?” ብለው ይጠይቁሽ ይሆናል። ነገር ግን እህቴ ሆይ፣ ማንም ሰው ሊያውቀው የማይችለውን አንድ እውነት አስታውሺ፦ አላህ አልረሳሽም! እንባሽን ያውቃል። የልብሽን ህመም ያውቃል። የምስጢር ዱዓሽን ይሰማል። ማንም ሰው የማያውቀውን ያንቺን ልብ ያውቃል። አንቺ ገና ያላወቅሽውን ሰው እንኳን አላህ ያውቀዋል። ስለዚህ የትዳርሽ መዘግየት እንዲሰብርሽ አትፍቀጂ። ይልቁንም ወደ አላህ የሚያቀርብሽ ይሁን። 📍ሌሊት ሰዎች በተኙበት ጊዜ ተነሺ። ሁሉም ዝም ባለበት ጊዜ ከአላህ ጋር ተነጋገሪ። እጆችሽን አንስተሽ እንዲህ በይ፦ “ያ አላህ! ማንኛውንም ወንድ አልፈልግም። አንተ ለእኔ የመረጥከውን ሰው እፈልጋለሁ። ያ አላህ! አንተን የሚፈራ፣ ሶላቱን የሚጠብቅ፣ ቁርአንን የሚወድ፣ በእኔ ላይ የሚራራ፣ የሚያከብረኝ እንጂ የማያዋርደኝ፣ ስሳሳት በርኅራኄ የሚመክረኝ፣ ስደክም የሚያግዘኝ፣ በአንተ መታዘዝ ላይ የሚረዳኝን ባል ስጠኝ።” ከዚያም የነበዩ ሙሳን عليه السلام ዱዓ አስታውሺ፦ ﴿رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنْزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ﴾ “ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ወደ እኔ ለምታወርደው ማንኛውም መልካም ነገር በጣም ተፈላጊ ነኝ።”                       እህቴ ሆይ… ምናልባት ዛሬ በመዘግየቱ ታለቅሺ ይሆናል፤ ነገ ግን ወደ ኋላ ተመልሰሽ፦ “ያ አላህ! ያኔ ያንን ሰው ለምን አልሰጠኸኝም ብዬ ነበር፤ አሁን ግን ለምን ከእሱ እንደጠበቅኸኝ ገባኝ። አልሐምዱሊላህ!” ትዪ ይሆናል። ምናልባት የምትፈልጊው ሰው አላህ ላንቺ የማይስማማ መሆኑን ያውቃል። ምናልባት እሱ የልብ ሰባሪሽ ይሆን ነበር። ምናልባት ዲንሽን ያዳክም ነበር። ምናልባት ልጆችሽ የማይገባቸውን ነገር እንዲያዩ ምክንያት ይሆን ነበር። አንቺ ግን አታውቂም፤ አላህ ያውቃል። ስለዚህ አንድ በር ሲዘጋ አታልቅሺ፤ ምናልባት ከኋላው ያለውን ጉዳት አላህ እያራቀልሽ ይሆናል።            አደራ አደራ ...... በትዳር መዘግየት ምክንያት የማይመችሽን ሰው አትቀበዪ። የትዳር ጉዳይ የአንድ ቀን ደስታ ብቻ አይደለም። ትዳር ዕድሜ ነው። ትዳር ቤተሰብ ነው። ትዳር ልጆች ናቸው። ትዳር ዲን ነው። ትዳር የወደፊት ሕይወት ነው። ስለዚህ ከገንዘብ፣ ከውበትና ከማዕረግ በፊት ዲንና መልካም ሥነ-ምግባር ተመልከቺ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فزوجوه» “ዲኑንና ሥነ-ምግባሩን የምትወዱት ሰው ወደናንተ ከመጣ አጋቡት።”                እህቴ ሆይ…እያነበብሽ ነዋ አላህ የጻፈልሽ ነገር በፍጹም አያመልጥሽም። ሰዎች ቢያግዱት ይመጣል። ሩቅ ቢሆን አላህ ያቀርበዋል። ጊዜው ቢዘገይ ጊዜው ሲደርስ ይመጣል። አላህ ያልጻፈልሽ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ቢሰበሰቡ ሊያገኙልሽ አይችሉም። ስለዚህ እንዲህ በይ፦ “ያ ረቢ! እኔ በአንተ እተማመናለሁ። ለእኔ ምረጥልኝ፤ እኔ ለራሴ የማላውቀውን አንተ ታውቃለህ። ለእኔ የሚሆነውን አንተ ምረጥ።” ከዚያም ልብሽን አሳርፊ። አትጨነቂ። አትቸኩዪ። ተስፋ አትቁረጪ። የአላህን ምሕረት አትጠራጠሪ። ምክንያቱም… እንባሽን ያየ አላህ አለ። ዱዓሽን የሰማ አላህ አለ። ልብሽን የሚያውቅ አላህ አለ። ዕጣሽንም በእጁ የያዘ አላህ አለ። በመጨረሻም አላህ ሆይ! በሙስሊም ሴቶች ልብ ውስጥ ያለውን፣ አንተ ብቻ የምታውቃቸውን ምኞቶች ፈጽምላቸው። አላህ ሆይ! ለእነርሱም ሳሊህ ባሎችን ስጣቸው፤ በዲናቸው ላይ የሚረዷቸውን፣ የሚያከብሯቸውን፣ የሚወዷቸውንና በእነርሱ ጉዳይ አንተን የሚፈሩትን ስጣቸው። አላህ ሆይ! የተሰበረ ልብ ካለ አጽናው። ብቸኛ ልብ ካለ አጽናናው። የሚጠብቅ ልብ ካለ በመልካም ነገር አስደስተው። አላህ ሆይ! ከእያንዳንዱ መጠበቅ እፎይታን፣ ከእያንዳንዱ ዱዓ መልስን፣ ከእያንዳንዱ ሐዘን ደስታን ስጣቸው። አላህ ሆይ! ባል የሌላት አንዲትም ሴት አትተው፤ ለእሷ የሚሆን ሳሊህ ባል ስጣት። የተሰበረ ልብ አትተው፤ ጽናትና ደስታ ስጠው። አላህ ሆይ! በኢማን፣ በፍቅር፣ በምሕረትና በሰላም የተሞሉ ቤቶችን ስጣቸው።                  አሚን ያ ረብ ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

📚الحد الفاصل بين الحق والباطل حوار مع الشيخ بكر أبي زيد رحمه الله في عقيدة سيد قطب وفكره “በእውነትና በሐሰት መካከል የሚለየው መስመር ስለ ሰይድ ቁጥብ አቋም በአቂዳውና በአስተሳሰቡ ላይ ከሸይኽ በክር አቡ ዘይድ (አላህ ይዘንላቸው) ጋር የተደረገ ውይይት” المؤلف : العلامة الإمام د.ربيع بن هادي بن عمير المدخلي رحمه الله https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

إلى المغرورين بالحوثيين! ​استمعوا إلى ما يقوله هؤلاء الحوثيون: ​"نحن في حرب مع أبي بكر وعمر وعائشة، ولن تضع هذه الحرب أوزارها حتى نسقط ما تبقى من احترام لأبي بكر وعمر وعائشة..." ​ثم يأتيك الحركي المغفل المسكين ليقول لك: هذه حرب سياسية وليست دينية! ​أفسبّ وطعن وتكفير أفاضل صحابة رسول الله ﷺ يُعدّ سياسة؟! ​أُفٍّ لسياستكم هذه! ​እነዚህ ሁቲዎች የሚሉትን አዳምጡ፦ ​"እኛ ከአቡ በክር፣ ከዑመር እና ከዓኢሻ ጋር በጦርነት ላይ ነን፤ ይህ ጦርነት ደግሞ ለአቡ በክር፣ ለዑመር እና ለዓኢሻ የሚደረገውን ቀሪ አክብሮት እስከምናስወግድ ድረስ አያበቃም..."

ሰይድ ቁጥብ ለዑስማን እና ለሰሐቦች ያለዉ እይታ ከራሱ ኪታብ ላይ انظر فتجد فيها أشياء كثيرة من أنفاس الشيعة والروافض https://t.me/durusuabihizam

👌በኢብኑ-መስዑዶች ላይ መናገር አቆማችሁ ብሎ ክስ የመሰረተው ቡድን እሱም #በሐጁሪዮች ላይ ረድ ማድረግ በማቆሙ ክስ እንዳይመሰረትበት ፈራለሁ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

የማለዳ መልእክት (49) ~ ልጆቻችን አካዳሚ ትምህርት መማራቸው እና በዚህ ላይ መጎበዛቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። በዚህ ላይ ማገዝና ሞራል መስጠትም ተገቢ ነው። ይሄ የሚሆነው በዲናዊ ትምህርት ሂሳብ ከሆነ ግን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው። * ልጆቻችን ሶላት ይሰግዳሉ ወይ? ቁርኣን እና ሌሎችም ኢስላማዊ ትምህርቶችን ይማራሉ ወይ? በዚህ በኩል ከሌሉ በአካደሚ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ትርጉም የለውም። እንዲያውም ሊጎዳቸው ይችላል። ዲናቸውን ካላወቁ በየትምህርት ዓይነቶቹ ውስጥ የተሰነቀሩ ብልሹ አስተሳበቦችን ሳያመዛዝኑ ይውጣሉ። የዲንን ዋጋ እና የአለማመንን አደጋ በቅጡ ስለማይለዩ እንደዋዛ ከኢስላም ሊወጡ ይችላሉ። ስማቸው የሙስሊም የሆኑ ግን ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን በየዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሉ። የአካደሚ ትምህርት ደረጃቸው የሚያላብሳቸው ትእቢት ስላለ ምክር ለመስማትም ዝግጁ አይደሉም። (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስማቸው የሙስሊም የሆኑ፣ ግን ከነ ጭራሹ እስልምና ውስጥ የሌሉ፣ ሰው ግን ሙስሊም አድርጎ የሚያስባቸው ሁለት ዶክተሮችን አውቃለሁ።) * በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ልጆችን ማበረታታትና መሸለም ጥሩ ሆኖ ሳለ መነጋገሪያ ያደርግንበት መንገድ ግን በጣም የተጋነነ ነው። ቁርኣን ሒፍዝ የጨረሱ፣ በተለያዩ ሃገራት ለአመታት ተንከራተው ጥሩ የዒልም ደረጃ ላይ የደረሱ ደረሶችን ግን ዞሮም የሚያያቸው የለም። ከስር እየመጡ ላሉት ተተኪዎች ምንድነው እያስተላለፍን ያለነው? ይህንን የተራራቀ አቀራረባችንን እያዩ ለዲናቸው ትኩረት ይሰጣሉ ወይ? * የዲን ትምህርት ለምን የትርፍ ጊዜ ትምህርት ይሆናል? ክረምት ብቻ፣ ቅዳሜና እሁድ ብቻ፣ ... እየሆነ ነው። ለአካደሚው ግን ሁለ ነገራችንን እየሰጠን ነው። በግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለን እናስተምራለን። መጥፎ ነገር የማያዩበት የተሻለ ድባብ ያለበት ግቢ መምረጣችን ይሁን። ለቁርአን ትምህርት ግን የዚያን ግማሽ እንኳን ከፍለን ማስተማር አንፈልግም። ለአካደሚ ትምህርቱ ተጨማሪ ከፍለን አስጠኚ እናደርጋለን። ለቁርኣንና ኪታብ ትምህርቶች ግን የረባ ቦታም የለንም። እነዚህ ነገሮች ከጊዜያዊ ትኩረታችን መራራቅ ባለፈ በልጆቹ አእምሮ ላይ እያስቀመጥነው ያለው ነገር ይበልጥ አደገኛ ነው፡፡ የዲን ትምህርት መማር ያን ያህል አንገብጋቢ እንዳልሆነ በተግባር እያሰርፅንባቸው ነው። በዚህ ላይ ሶላት አለመስገድ ሲጨመርበት፣ ክፍተታቸው የበዙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ከሆነ፣ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አፍላ እድሜ ላይ ሲደርሱ ለመግለፅ የሚሰቀጥጥ ኪሳራ ይደርሳል። ስለዚህ ሳይቃጠል በቅጠል። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 05/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

❝ድንግል ስላልሆንኩ ትዳርን እፈራለሁ ላለች እህት የተላከ መልእክት!❞ ~ ውድ እህቴ ሆይ! ሰው ነሽና ተሳስተሻል፤ አማኝ ነሽና ተፀፅተሽ ወደ ጌታሽ ሮጠሻል። አላህ ደግሞ ተውበት አድራጊዎችንና ወደ እርሱ የሚመለሱትን እጅግ ይወዳል። ታዲያ ይቅር ባዩ ጌታሽ በራሕመቱ የሸፈነልሽን ስህተት ይዘሽ፣ ዛሬም ድረስ ራስሽን የምትወቅሺውና የሐላሉን የትዳር በር በራስሽ ላይ የምትቆልፊው እስከ መቼ ነው? እውነተኛው ንፅህና የተውበት እንባ ያጠበው የልብ ንፅህና ነው። ረሱል (ﷺ) «ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው ልክ ምንም ወንጀል እንዳልነበረው ነው» ብለውናል። ሸይጣን ሁለት ጊዜ ያጠቃሻል፦ 1.  በመጀመሪያው ወቅት ወደ ወንጀል እንድትገቢ አታሎሻል፤ 2. ዛሬ ደግሞ «አንቺ ድንግል አይደለሽም፣ ስለዚህ ለትዳር ብቁ አይደለሽም፣ ነገ ትዋረጃለሽ» እያለ በተስፋ መቁረጥ እና በብቸኝነት ወጥመድ ውስጥ እንድትኖሪ ይፈልጋል። ● ጥያቄ 1፡ «ቢክራ ሳልሆን እንዴት አገባለሁ? ለማግባት ብቁ ነኝ?» - ምላሽ፡- አዎን፣ ሙሉ በሙሉ ብቁ ነሽ! ትዳር በኢስላም ለድንግሎች ብቻ የተፈቀደ ሸቀጥ አይደለም። የነቢያችን ﷺ ሚስቶች ከእናት አዒሻህ በስተቀር ሁላቸውም ቀደም ሲል ያገቡ (ቢክራ ያልነበሩ) ናቸው። በሸሪዓው ሚዛን የሴት ልጅ ትልቁ ክብር የሚለካው በዲኗ፣ በስነ-ምግባሯና አላህን በመፍራቷ እንጂ በአንድ የአካል ሽፋን ብቻ አይደለም። ● ጥያቄ 2፡ «ለሚጠይቀኝ ሰው ያለፈውን ህይወቴን መንገር አለብኝ?»   - ምላሽ፡- ፈጽሞ የለብሽም! ኢስላም ያለፈን ወንጀል መዘርዘርን ያወግዛል። አላህ በምህረቱ የሸፈነልሽን ነውር ለሰው መግለጥ «ሙጃሀራህ» (ወንጀልን ይፋ ማድረግ) ስለሚሆን ይከለከላል። ማንም ሰው መርማሪ ፖሊስ ሆኖ የቀደሞ ህይወትሽን ሊመረምር አይፈቀድለትም፤ አንቺም የመናገር ምንም ዓይነት ሸሪዓዊ ግዴታ የለብሽም። ● ጥያቄ 3፡ «ወንዱ 'ቢክራ መሆን አለባት' ብሎ በግልፅ ቢያስቀምጥስ?»   - ምላሽ፡- አንድ ወንድ ድንግልናን ጥብቅ መስፈርት አድርጎ ካስቀመጠ፣ መዋሸት አያስፈልግሽም፤ በዚያው ልክ ደግሞ «እኔ እኮ  እንዲህ ሆኜ ነው ያጣሁት…» ብለሽ ራስሽን አትግለጪ። አጭሩ መልስ፦ «እኔና አንተ በመስፈርት አንጣጣምም፤ አላህ የተሻለውን ይስጥህ» በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጊው። ● ጥያቄ 4፡ «ወንዱ ስለ ድንግልና ምንም ካላነሳስ?»   - ምላሽ፡- ወንዱ ስለ ቢክራ ምንም ካላነሳና ትኩረቱ ስነ-ምግባርሽ፣ ዲንሽና አብሮ መኖር ላይ ከሆነ፤ ጉዳዩን ፈጽሞ ማንሳት  አያስፈልግሽም። ጥያቄውን በደስታ ተቀብለሽ ወደ ኒካህና ወደ ትዳርሽ መሻገር ሙሉ በሙሉ ይፈቀድልሻል። ስለዚህ ይህንን ጉዳይ ለጓደኛ፣ ለቤተሰብም ሆነ ለማንም ሰው አትናገሪ። በአንቺና በአላህ መካከል የቀረ ሚስጥር ይሁን። ከአሁን በኋላ የሚመጡትን የትዳር ጥያቄዎች «ቢክራ ስላልሆንኩኝ» በሚል ሰበብ ብቻ ውድቅ አታድርጊ። ወንዱ ቅድመ-ሁኔታ እስካላደረገው ድረስ፣ እንደማንኛውም ሴት ኢስቲኻራህ አድርገሽ ተቀበይ። «ያ አላህ! በምህረትህ ሸፍነኸኛልና በትዳሬም ውስጥ ነውሬን ሸፍንልኝ፤ የሚያከብረኝንና ወደ አንተ የሚያቀርበኝን ሷሊሕ ባል ወፍቀኝ» በማለት ዘወትር ዱዓ አድርጊ። አብሽሪ! --- t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

የጭንቅ መገላገያ ድንቅ ታሪክ በኢራቅ ባግዳድ "ከርኽ" በሚባለው አካባቢ የሚኖር፣ በሱናው (በሃይማኖታዊ ትጋቱ) የሚታወቅ አንድ ዓጣር (ሽቶ ሻጭ) ነበር። ይህ ሰው 600 (ስድስት መቶ) ዲናር ዕዳ ይከማችበታል። ዕዳው ሲበዛበት ሱቁን ዘግቶ፣ ከስራው ተቋርጦ፣ ቤቱ ውስጥ ተቀመጠ። ለብዙ ሌሊቶችም ወደ አላህ በመጸለይ፣ በመንከባለልና በዱዓ (ልመና) አሳለፈ። ከእለታት በአንዱ ሌሊት ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በሕልሙ አያቸው። እርሳቸውም፦ "ወደ ወዚሩ ዓሊ ኢብን ዒሳ ሂድ፤ እሱ 400 (አራት መቶ) ዲናር እንዲሰጥህ አዝዤዋለሁ" አሉት። ሰውየው ሲነጋ ወደ ወዚሩ ደጃፍ ሄደ። እዚያ ግን የሚያውቀው ሰው አልነበረም፤ እንዲያስገባው የሚጠይቅለት እስኪያገኝ ድረስ ለረጅም ሰዓት ተቀመጠ። በመጨረሻም ተስፋ ቆርጦ ሊመለስ ሲል ለበሩ ጠባቂ (ሀጂብ) እንዲህ አለው፦ "ለወዚሩ እንዲህ በልልኝ፤ እኔ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በሕልሜ ያየሁ ሰው ነኝ፣ ያየሁትንም ልነግራቸው እፈልጋለሁ።" ጠባቂውም ደነገጠና፦ "ያ ህልም የታየህ አንተ ነህ? ወዚሩ እኮ አንተን እንዲፈልጉ ብዙ መልእክተኞችን ሲያሰማራ ነበር!" አለው። ወዲያውኑ ወደ ወዚሩ አስገቡት። ወዚሩም ስለ ሁኔታው፣ ስለ ስሙና ስለ መኖሪያው ጠየቀውና እንዲህ አለው፦ "እኔም ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በሕልሜ አይቻቸው 400 ዲናር እንድሰጥህ አዘውኝ ነበር። ሲነጋ ግን አንተን የት እንደማገኝህ አላወቅኩም ነበር። እስካሁንም መልእክተኞችን ስልክ ነበርና ወደ እኔ ስለመጣህ አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ።" ከዚህ በኋላ ወዚሩ 1,000 (አንድ ሺህ) ዲናር እንዲመጣ አዘዘና ለሰውየው እንዲህ አለው፦ "ይህ 400 ዲናር የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ ስለሆነ ውሰድ፤ የቀረው 600 ዲናር ደግሞ ከእኔ የተሰጠህ ስጦታ ነው።" ሽቶ ሻጩ ግን፦ "በአላህ እምላለሁ! ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ካዘዙኝ በላይ አልጨምርም፤ ምክንያቱም በረከቱን የምፈልገው እርሳቸው ባዘዙት መጠን ላይ ነው።" በማለት 600 ዲናሩን ለመቀበል እምቢ አለ። ወዚሩም፦ "ይህ እኮ ነው እውነተኛ እምነትና እርግጠኝነት (ሲድቅ ወል የቂን)!" ብሎ አደነቀው። ሰውየው 400 ዲናሩን ይዞ ወጣ። ለባለዕዳዎቹም ሄዶ ገንዘቡን ሲያቀርብላቸው፦ "እኛ ለሦስት ዓመት እንታገስሃለን፣ በዚህ ወርቅ ሱቅህን ክፈትና ስራህን ቀጥል" አሉት። እርሱ ግን የዕዳውን አንድ ሦስተኛ (200 ዲናር) ከፈላቸው። በቀረው 200 ዲናር ሱቁን ከፈተ። አመቱ ሳይዞርም 1,000 ዲናር አተረፈ። ኢብኑ ከሲር "አል-ቢዳያ ወን-ኒሃያ"  መጽሐፋቸው (ቅጽ 11፣ ገጽ 245) https://t.me/rebizidniielma

🥀ናፍቆት እንደ ባሕር ማዕበል ነው… ዝም ይላል እንጂ አይጠፋም። አንዳንድ ጊዜ በዝምታ ውስጥ ይደበቃል፤ አንዳንድ ጊዜ ግን ድንገት ተነስቶ የተረጋጋውን ልባችንን ያናውጠዋል። የምንወዳቸው ሰዎች ከዓይናችን ሊርቁ ይችላሉ፤ ከልባችን ግን መራቅ አይችሉም። ድምፃቸውን ለመስማት ቀናት ሊያልፉ ይችላሉ፤ ትዝታቸው ግን በሐሳባችን ውስጥ ደጋግሞ ይመጣል። አንድ ቦታ፣ አንድ ቃል፣ አንድ ሁኔታ፣ አንድ የቀድሞ ትዝታ… ብቻ ይበቃል፤ ያኔ ለረጅም ጊዜ ዝም ያለው ናፍቆት እንደገና ይቀሰቅሰዋል። እንደ ባሕር ማዕበል… ይመጣል፣ ያናውጣል፣ እንባን ያመጣል፤ ከዚያም ይረጋጋል። ግን በልባችን ጥልቀት ውስጥ የተቀመጠው ናፍቆት አይጠፋም። አንዳንድ ጊዜ በሰዎች መካከል ተቀምጠን እንኳን ብቻችንን እንሆናለን፤ ምክንያቱም ሰውነታችን ከሰዎች ጋር ቢሆንም፣ ልባችን ግን ከምንናፍቃቸው ሰዎች ጋር ይሄዳል። “መቼ እንገናኝ ይሆን?” “መቼ ይሆን ይህ ርቀት የሚያበቃው?” “ዛሬ እንደምናስባቸው እነሱም ያስቡን ይሆን?” “ይህ መጠበቅ መቼ ወደ ደስታ ይቀየራል?” ብለን በውስጣችን እንጠይቃለን። ምናልባት አንድ ቀን የዛሬው ርቀት ያበቃ ይሆናል። የተለያዩ ልቦችም እንደገና ይገናኛሉ። ያኔ የዛሬውን እንባ እያስታወስን እንስቃለን፤ የዛሬውን መጠበቅም በምስጋና እናስታውሰዋለን። ምናልባትም ግን እንደፈለግነው ሳይሆን አላህ እንደወሰነልን ይሆናል። ያኔ ልባችን መማር ያለበት አንድ ነገር አለ፦ የምንፈልገው ሁሉ የእኛ እንዲሆን አይደለም፤ ለእኛ የተጻፈው ግን በእርግጥ ይደርሰናል። ስለዚህ እንናፍቅ… ግን ተስፋ አንቁረጥ። እንጠብቅ… ግን ልባችንን በጭንቀት አንሙላው። እንውደድ… ግን ልባችንን ለአላህ እናስረክብ። 🌹 ናፍቆት እንደ ባሕር ማዕበል ነው… ዝም ይላል እንጂ አይጠፋም። አንዳንድ ቀን ማዕበሉ ይበረታል፤ አንዳንድ ቀን ይረጋጋል፤ እኛ ግን በሁሉም ሁኔታ የልባችንን ሰላም ከአላህ እንፈልግ። ምክንያቱም ከምንናፍቃቸው ሰዎች መገኘት የሚያሳርፈን ቢሆንም፣ የልባችንን እውነተኛ ማረፊያ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነውና። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

⭕️የጓደኝነት ረቂቅ ሚስጥር!!⭕️ ---------------------------------- «ወንድማለም በምን ሁኔታ ላይ ሆነህ ይሆን⁉️ ሰሞኑን በጣም ናፈቅከኝ ስልክ አታነሳም በምን ላግኝህ ሁሌም እወድሀለሁ አሏህ ይጠብቅህ ኮከቤ!!» ♦️«ማድረግ የምችለው ዱዐዕ ነው አስታውስሀለሁ..አሏህ ወደ ደዕዋው እንድመልስህ እፀልያለሁ» 👉ጓደኝነት ማለት፦ከአሏህ የሚሰጥ ግሩም ገፀ-በረከት ነው ይህ መልካም ትስስር ከዱንያ እስከ አኸይራ የሚሻገር ረቂቅ ጥምረት ሲሆን ብዙወቻችን አልተረዳነውም። 👉ጓደኝነት ብዙ አይነት ነው። ❶ንፁህን የሆነ ጓደኝነት ልክ እንደ አየር ያስፈልግሀል። ❷►ልክ እንደ ምግብ አንዳንዴ በደስታ በፍቅር የምትመገበው እና አንዳንዴ ደግሞ ባይጥምም ለረሀብ ማስታገሻ የምትጠቀመው አለ። ❸►እንደ መዳኒትም እየመረረህ እየጎመዘዘህ ግን መዳኒት ነውና ህመሙን ምሬቱን ችለህ ጨክነህ የምትውጠው ጓደኛ አለ። ❹እንደ አስካሪ መጠጥ የሆነም ጓደኛ አለ ሁሌ የሚንገዳገድ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ግን ጥቅምም ያለው ግን ጉዳቱ ፅዩፍ የሆነ ጓደኛ አለ። ⭕️► ከየትኞቹ እንደሆንክ ጓደኛህን በግልፅ ጠይቀው እሽ⁉️ ⭕️►በሸዕባን 22 /1446 ھ በወንድም ኑረዲን ቻናል የተደረገ ወሳኝ ማስታወሻ ይደመጥና ይሰራጭ ሐያ....!! 🎙በወንድሜ አቡ-ረይስ ሀፊዞሁሏህ http://t.me/nuredinal_arebi http://t.me/nuredinal_arebi

Repost from ፈዋኢድ
መሠረታዊ የሐዲስ ዕውቀት እንዲኖረንና ወደ ሙሐዲስነት የሚወስደንን ጉዞ በትክክል ለመጀመር በሁለት ዋና ደረጃዎች ማለፍ ያስፈልጋል። የመጀመሪያው ደረጃ፦ الجانب التأصيلي أو النظري በዚህ ደረጃ የሙስጠላሕ እና መሰል ኪታቦችን በቅደም ተከተል ረጅም አመታት ልምድ ካለው ሸይኽ ጋር መማር ይመከራል ልክ ሸይኽ አቡል ሀሰን አራዚሂይ ያሉት ላይ። ከሚቀሩ ኪታቦች መካከልም፦ البيقونية ወይም طرفة الطرف نخبة الفكر الموقظة للذهبي اختصار علوم الحديث نزهة النظر ألفية العراقي ወይም ألفية السيوطي المتكلمون في الرجال للحافظ السخاوي ضوابط الجرح والتعديل ا ሁለተኛው ደረጃ፦ الجانب التطبيقي አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን የሙስጠላሕ እና መሰል ፈኖች በደንብ ቢማር እንኳን ይህ ብቻ ሙሐዲስ አያደርገውም። የተማረውን ዕውቀት በተደጋጋሚ በተግባር ማዋልና ረጅም ጊዜ ልምምድ ማድረግ ያስፈልጋል ልክ ተጅዊድ ኪታብ በመቅራት ብቻ ሙጅዊድ እንዳማይሆነው ። በተለይም በተኽሪጅ፣ በሪጃል፣ በጃርሕና ተዕዲል እንዲሁም በعلم العلل የቀድሞ የሐዲስ ሊቃውንት የጻፏቸውን መዛግብት በተደጋጋሚ ማንበብና ማጥናት እጅግ ወሳኝ ነው። ይህም በጊዜ ሂደት የሐዲስ ምርመራ ችሎታን እና ملكة ያዳብራል። ከዚህ አንጻር المفتاح في البحث والتخريج የተሰኘውን የሸይኽ አል-ሙሐዲስ አቡል ሐሰን አልራዚሒ ምርጥ ኪታብ መቅራት ይመከራል። ሸይኹ ራሳቸው አስተምረውታል https://t.me/AliAlrazihi/12539። የተኽሪጅ መሠረታዊ መንገድ ከተረዳ በኋላ በተግባር ላይ እያዋለ በብዛት መለማመድ ይገባዋል። አንዳንድ መሻይኾች እስከ 20,000 ሐዲሶችን ተኽሪጅ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይጠቅሳሉ። ይህ ቁጥር ራሱ ዓላማ አይደለም፤ ዋናው ነገር ብዙ ጊዜ በመለማመድ የሐዲስ بحث ክህሎትን ማዳበር ነው። በመጨረሻም የዚህ ሁሉ ጉዞ ዋና ቁልፎች፦ ኢኽላስ + ዱዓ + ትዕግሥት + ረጅም ጊዜ የሚቆይ ልምምድ። የሙሐዲስነት ጉዞ በአንድ ወይም በሁለት መጻሕፍት የሚጠናቀቅ ጉዞ አይደለም፤ ዕውቀት፣ ተግባር፣ ልምምድና ትዕግሥት የሚጠይቅ ረጅም ጉዞ ነው። اللهم أكثر المحدثين الأكابر إنك على كل شيء قدير وبالإجابة جدبر

ከሀሳብ ዓለም ሲመለሱ... አልፎ አልፎ በሃሳብ ባህር ጠልቀን፣ ከዚህ ዓለም ጫጫታ ርቀን ስንሰምጥ እንቆያለን። በምናባችን ውስጥ የተለያዩ ሐጃዎች ይመላለሳሉ። በዙሪያችን ባለው ጭርታና ጸጥታ ውስጥ ሆነን የህይወትን ውጣ ውረድ ስናስተውል፣ ነፍሳችን የት እንዳለች እንረዳለን። በዚህ ሰዓት ህሊናችን ተመልሶ ሲነቃ፦ «ጌታዬ እኮ አላህ ነው!» በማለት ልባችን በሰላም ይመራል። ከዚያም ጭንቀታችን ተገፎ፣ ተስፋችን ታድሶ፦ «ጌታዬ! ምስጋና ለአንተ የተገባ ነው!» እያልን አንገታችንን ቀና እናደርጋለን። 🤲 በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እኛን የሚጠብቀን፣ የሚያስተናብረን እና የሚንከባከበን ጌታችን ምስጋና ይገባው። በጭንቀት ሰዓት መተማመኛችን፣ በብቸኝነት ሰዓት መጠጊያችን እሱ ብቻ ነውና አልሀምዱሊላህ! አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

📌ጥሩ የሚነበብ መፅሀፍ ልጠቁማችሁ..!! ━━━━━━።◈።━━━━━━━ 📚 የኪታቡ ስም፦ 🌿 "قصص الزاهدين والزاهدات" (የዱንያን ብልጭልጭ የናቁና ችላ ያሉ ደጋግ የአላህ ወንድና ሴት ባሮች ታሪክ) ✍🏻 አዘጋጅ፦ ሸይኽ ማህሙድ አል-ሚስሪ ሐፊዘሁላህ ታሪክና ቂሳዎች በሰው ልጆች ነፍስ ውስጥ እጅግ ጥልቅና ዘላቂ የሆነ ተፅዕኖ አላቸው። ታሪክም እንደየ አይነቱ ይለያያልና... በዚህ መፅሀፍ ውስጥ የምናገኘው በተለምዶ የታሪክ መፅሀፍ ተብለው በሚዘጋጁ ድርሳናት ላይ እንደምናገኘው አይነት እከሌ የሚባለው ሰው በዚህ ቀን እና ቦታ ላይ ተወልዶ እንደዚህ ሆነ፤ ከዚያም እንደዚህ ሰራ፤ በስተመጨረሻም እከሌ በሚባለው ቀን ሞተ እያለ የሚያትት አይደለም! ይልቅ ሌትና ቀናቸውን ለጌታቸው ፍቅር ስለተዋደቁ፣ የዱንያን ጊዜያዊ ክብርና ስልጣን እርግፍ አድርገው በመተው ከአላህ  ጋር ብቻ በዒባዳ ስለከረሙ ደጋግ ቀደምቶች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ስላሳለፏቸው እጅግ ሳቢና አጓጊ የሆኑ አጋጣሚዎች፣ ሁላችንም ልንላበሳቸው ስለሚገቡ ታላላቅ ስብዕናዎች፣ እንዲሁም ሕይወትን የሚቀይሩ ወርቃማ ትምህርቶችና ምክሮችን የያዘ መፅሀፍ ነው። ጠቅለል ስናደርገው በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ከቁስ እና ከስሜት ባርነት ነፃ ወጥተን፣ የዛለች ነፍሳችንን እንዴት በዒባዳና በዚክር መፈወስ እንደምንችል አቅጣጫ የሚሰጠን ኮምፖስ ነውና ጊዜ ሳታባክኑ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ መክተባ ሄዳችሁ ብትሸምቱት ስል ወንድማዊ ግብዣዬ ነው😊!! ፒዲኤፉን በዚህ ታገኙታላችሁ!👇🏻 https://t.me/Abuhatim7/2528 ✨@Abuhatim7

📕قصص الزاهدين والزاهدات ✍🏻الشيخ - محمود المصري ✨@Abuhatim7

Repost from Temari News
#የጥሪ_ማስታወቂያ #DebreMarkosUniversity ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤ ✔ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 18 – 19/2019 ዓ.ም 📚ለትምህርት መፅሐፍት 💻
#የጥሪ_ማስታወቂያ #DebreMarkosUniversity ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤ ✔ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 18 – 19/2019 ዓ.ም 📚ለትምህርት መፅሐፍት 💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes 📣ለትምህርታዊ መረጃዎች 💻 @TemariNews 💻 @TemariNews