cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus

ዳዕዋ ሰለፍያ በአርባ ምንጭ AMUጫሞ ካምፓስ ሃቅን ፍለጋ ከቁርዓንንና ከትክክለኛ ሃድስ በነዚያ ደጋግ ቀደምቶች ( በሰለፉነ–ሷሊሂን) አረዳድ ! "ከሃቅ በሗላ ጥሜት እንጅ ምን አለ! ? " ስለዚህ ሃቅን ብቻ ተከተል ! ማሳሰቢያ: –ለማንኛውም አስተያየትዎ ከታች ባለው ቦት ያስቀምጡልን ጀዛኩሙላህ ኸይር @JemalEndroAbuMeryem

Show more
Advertising posts
2 393
Subscribers
-224 hours
-87 days
-2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ምርጡ ውሃ! ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿خيرُ ماءٍ على وجهِ الأرضِ ماءُ زَمزمَ، فيهِ طعامُ الطُّعمِ، وشِفاءُ السُّقمِ،﴾ “በምድር ላይ ካሉት ውሃዎች ምርጡ የዘምዘም ውሃ ነው። በምግብነት ለተጠቀመው ምግብ ለበሽታ ለተጠቀመው ደግሞ መድኃኒት ነው።” 📚 ጠበራኒ ዘግበውታል አልባኒ በሶሂህ አትርጊብ ውስጥ ሀሰን ብለውታል፡ 1161 ✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ 📱፦ https://bit.ly/486xnrS 📱፦ https://bit.ly/41zEZkk 📱፦ https://bit.ly/4arMbTx 🖥፦ https://bit.ly/41tIUPv 📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አላህ  ኸይር  ጀዛችሁን  ይክፈላቹ  ኒቃብ  ወይም  ጅልባብ  ለመልበስ  ፈልገዉ  የተቸገሩ በዉስጥ  እየመጡ  የሚጠይቁ  እህቶች  ብዙ  ናቸዉ  ጅልባብ  ኒቃብ  ወይም  ገንዘብ  የሚሰጡ  ሰዎች  ግን  ትንሽ  ናቸዉ  አልተመጣጠነም  ገንዘብ  መስጠት  የማትችሉ  እህቶች  ትርፍ  ኒቃብ  እና  ጅልባቦቻችሁን  ለመስጠት  ፍቃደኛ  ብትሆኑ  ያላችሁበት  ድረስ  መተን  እንቀበላችሁአለን። የኢትዮጲያ  ንግድ  ባንክ ➛ 1000588690486 Hikma and/or Ahlam and/or Muhiba http://t.me/NikabJilbab
Show all...
👍 4
ርብርብ ለጋራ ግብ ~ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በዚህ የብዙ ሴቶች አለባበስ በተበላሸበት ዘመን ጂልባብ እና ኒቃብ መልበስ እየፈለጉ በችግር ምክንያት ያን ማድረግ ካቃታቸው እህቶች ጎን መቆም ድንቅ ስራ ነው። ችግሩን ለመቅረፍ የበኩላችንን እንወጣ ዘንድ ይመለከተኛል የሚልን በሙሉ አካታች የሆነ ሰፊ ሀሳብ ይዘንላችሁ መጥተናል። ይህም የጂልባብ እና የኒቃብ ባንክ መክፈት ነው። ስራዉን በሚሰሩ ወይም በሚመለከታቸዉ እህቶች ስም የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን   1. ገንዘብ በማሰባሰብ ኒቃብና ጅልባብ መግዛት፣ 2. ቅያሪ ኒቃብና ጅልባብ ኖሯቸዉ መስጠት ለሚፈልጉ እህቶች ያሉበት ሰፈር ድረስ ሄዶ በመቀበል ለተቸገሩ እህቶቻችን ማድረስ ናቸው። የድርሻችንን እንወጣ። በችግር ምክንያት መልበስ ላልቻሉ እህቶቻችን እንድረስላቸው። የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ➛ 1000588690486 Hikma and/or Ahlam and/or Muhiba ለየትኛውም ሀሳብ፣ አስተያየት፣ ጥቆማና ጥያቄ እነዚህን አማራጮች መጠቀም ትችላላቹ። እህቶች በዚህ👇 @AhluYeWereilua @nikab_new_wbetea  ወንድሞች በዚህ👇 @FuadBezu @red_one1212 ስልክ 0913666695          0903939033 የቴሌግራም  ቻናላችን👇 t.me/NikabJilbab የቴሌግራም  ግሩፓችን 👇 t.me/nikab_jilbab_group
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ምርጡ ውሃ! ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿خيرُ ماءٍ على وجهِ الأرضِ ماءُ زَمزمَ، فيهِ طعامُ الطُّعمِ، وشِفاءُ السُّقمِ،﴾ “በምድር ላይ ካሉት ውሃዎች ምርጡ የዘምዘም ውሃ ነው። በምግብነት ለተጠቀመው ምግብ ለበሽታ ለተጠቀመው ደግሞ መድኃኒት ነው።” 📚 ጠበራኒ ዘግበውታል አልባኒ በሶሂህ አትርጊብ ውስጥ ሀሰን ብለውታል፡ 1161 ✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ 📱፦ https://bit.ly/486xnrS 📱፦ https://bit.ly/41zEZkk 📱፦ https://bit.ly/4arMbTx 🖥፦ https://bit.ly/41tIUPv 📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته በሳኡድ አረቢያ ለምትገኙ እህት ወንድሞች በተለይ በመካ ና ጅዳ ለምትኖሩ በሙሉ የሩቂያ(ቁርዓን) ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ። ሩቂያ ማስደረግ እና የሩቂያ አገልግሎት ለምትፈልጉ በሙሉ ያሉበት ድረስ መተን ለማድረግ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።         ከእርሶ የሚጠበቀው ፦ 1.ካሉበት ሆነው በአስቀመጥንሎት ስልክ ይደውሉ 2.የሚገኙበት ቦታ ሎኬሽን በዋሳፕ ይላኩ              በመስመር _+966559318178              በዋሳፕ_+251932419090              በቴሌግራም_+251939912164 ⏺ አድራሻ: —መካ                  ✍አቡ ሃፍሷ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱሁ ይህ ወንድማችን ወሎ ቦረና ከላላ ወረዳ ልጓማ የምትባል አካባቢ ተወልዶ ያደገ ነዉ። ተጨማሪ ስልክ 09 14 36 37 98 ወይንም 09 31 82 91 83 ሼር እያደረጋችሁ።
Show all...
ነብዩን መላጨት
Show all...
👍 1
ጭፍራው ቅርቃር ውስጥ ገብቷል ~ ቅልጥ እንደ ቅቤ - ፍርስ እንደ ሸክላ ሁሉ ነገር እርቃን - እነ ሳይሞቅ ፈላ! ይሄ ሰካራም ጭፍራ ብዙ እንደማይራመድ በጣም እርግጠኛ ነበርኩ። በዚህ ፍጥነት ድንብርብሩ ሲወጣ፣ ጉዱ ሲዝረከረክ ማየት ግን የጠበቅኩት አልነበረም። ከሁለት ዓመት በፊት መሰለኝ ወራቤ ላይ አንድ ወንድም ዐብዱልሐሚድ ለተሞ አንድ መንሀጅ ላይ ሁለት አመት ታግሶ መቆየት አይችልም ጠብቁ ሲል ሰምቼው ነበር። ምናልባት የሆነ ያክል ተጋኖ ይሆን? አላውቅም። ንግግሩ ግን በውስጡ የሆነ እውነት አዝሏል። አሁን ላይ አንዳንድ ነገሮች ጫፋቸው እየዘለቀ ነው። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ይሄው እየጠራ መጣ። በየጊዜው እየወጡ ካሉ በርካታ የቪዲዮ እና የፎቶ ማስረጃዎች ውስጥ ለጊዜው አንድ ማሳያ ልጥቀስ፦ ጠሃ ኸዲር የዚህ የተንቀዠቀዠ ጭፍራ አጫፋሪ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ሶሻል ሚዲያ ላይ እየዘለቀ ሁለት ሶስት መስመር ስድብ መፃፍን ቁም ነገር ያደረገ በተግባር ግን በተለያየ ቦታ የተለያየ ፊት የሚጠቀም ሰው ነው። * ሳዑዲ ውስጥ ጤነኛ ያልሆኑ ሰዎች ዘንድ ቁጭ ብሎ ለአመታት ይማራል። እዚህ ደግሞ እነ እከሌ ከእነ እከሌ ጋር ተቀመጡ እያለ ፎቶ ይለጥፋል። የሳዑዲ ኤምባሲ ሲጋብዛቸው ራሱም ጭፍራዎቹም ከነዚያው ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር አንድ ላይ ይጣዳሉ። በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ፊት ማሳየትን ተክኖበታል። * መሻይኾች ዘንድ ሌላ ሰው ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ደግሞ ሌላ። * ሳዑዲ ውስጥ ሌላ ሰው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ። * እንደ ባህሩና ሑሴን ያሉ ተናካሽ ጓዶቹ ጋር ሲሆን ሌላ ነው። አቃቂር እያወጡ፣ ቅጥፈት እየለጠፉ የሚናከሱ አውሬዎች ናቸው። እያደናነቀ የሚያስተዋውቃቸው የሀረር አካባቢ ጭፍራዎቹ ደግሞ እሱ በሚስላቸው 'ሙስተዋ' ላይ አይደሉም። ያያያዝኩት ቪዲዮ ለዚህ አንድ ምስክር ነው። በቪዲዮው ላይ የጠሀ ጭፍራ የሆኑት (የነበሩት ብለው ይሻል ይሆን?) እነ ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ (ጭሮ?) ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር ተቀማምጠው የአንድነት መግለጫ ያወጡበት ጉባዔ ነው። ቪዲዮው ላይ ከሰፈረው ቃል ቀንጨብ ላድርግ፦ 1- የዶክተር ጀይላን ንግግር፦ "በሀረር ዑለማኦች መካከል ልዩነት እንደሌለ እንዲሁም በዑለማኦቹ መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላት በዑለማእ ስም የሚነግዱ እንደሆኑ፤ እኛ ሁላችንም አንድ እና የተሰማማን እንደሆንን፤ በመካከላችን ልዩነት እንደሌለ የሀረር እና የኢትዮጵያ መሻይኽ ጉባኤ ገልጿል።" 2- የኢልያስ ዐባስ ንግግር፦ "እኛ እንደ አሕመድ ሱኣላ እና እንደ ዶክተር ጀይላን ካሉ ታላላቅ ዑለማኦች ጋር ነን። ድሮም፣ አሁንም በመካከላችን ልዩነት የለም። እስከ ዘላለም ከነሱ አንለይም።" 3- የአሕመድ ሙሐመድ ንግግር:- "እኛ አሁን ከዑለማኦቻችን ጋር ነን። እነሱን ከሚሳደቡ አካላት ድሮም አሁንም የጠራን ነን። ፈፅሞ ከነሱ (እነሱን ከሚሳደቡ) ጋር አንሆንም።" ልብ በሉ! ጠሀ ኸዲር እነዚህን ሁለቱን ሰዎች (ማለትም ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ) ሞቅ አድርጎ ያወድሳል። ያሰራጭላቸዋልም፡፡ ለምሳሌ ያክል በቅርቡ እንዲህ ሲል ፅፏል:- أشد على أيديكم يا أبطال شرق هرر فضيلة الشيخ Sheek Iliyaas Abbaas وفضيلة الشيخ Shekh Ahmade Muhammed زادكم الله قوة إلى قوتكم فقد أقضت جهودكم المضاجع وألهبت المشاعر وأسهرت وهزت ولن يهنأ منهم أحد مهما كان بعدما التهبت الأحشاء واضطرمت! = እነዚህ የጠሀ ጀግኖች ግን፡ 1ኛ፦ ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር እንደሆኑ ድሮም፣ አሁንም በመካከላቸው ልዩነት እንደሌለ ገልፀዋል። እስከ ዘላለም ከነሱ እንደማይለዩም አስረግጠው ተናግረዋል። 2ኛ:- እነሱን (እነ ዶክተር ጀይላንን) ከሚሳደቡ አካላት ድሮም አሁንም የጠራን ነን። ፈፅሞ እነሱን ከሚሳደቡ ጋር አንሆንም ማለታቸውን ያዙ። እዚህ ላይ ቁጥር አንድ ተጠቃሹ ጠሀ ኸዲር ነው። አሞሌው አልሰራም። ከዚህ በኋላ ያለው ምርጫ ሁለት ነው። 1ኛው ምርጫ፦ ወይ እንደ ግለቱ እያዩ ሲያሻቸው "እኛ ድሮም ጀምሮ መንሀጅ ገብቶናል፣ ለ 20፣ ለ30 አመታት ሰለፊያን (የነሱን ቨርዥን) ስናስተምር ነው የኖርነው፣ ከኢኽዋን የጠራን ነን፣ ..." እያሉ መሞገት፤ ሲላቸው ደግሞ ከነዚያው ኢኽዋን ከሚሏቸው ሰዎች "ድሮም አሁንም አንድ ነን፣ ዘላለም አንለያይም" እያሉ የጋራ መግለጫ እያወጡ መቀጠል ነው። በተለያየ መመዘኛ እየመዘኑ፣ የተለያየ ፊት እያሳዩ መሄድ ለጠሀ ከባድ አይመስለኝም። ይሄ ግን የሰለፊ መገለጫ አይደለም። ሸይኽ ሙቅቢል እንዲህ ይላሉ፦ فالحزبي مستعد أن يكون له خمسة أوجه. والنبي ﷺ يقول: إن من شر الناس ذا الوجهين الذي يأتي هـولاء بوجه وهؤلاء بوجه. أما السني فإنه متمسك بدينه سواء رضي فلان أو لم يرضَ بخلاف الحزبيين. "ቡድንተኛ ሰው አምስት ፊት ሊኖረው ዝግጁ ነው። ነብዩ ﷺ 'ከክፉ ሰዎች ውስጥ የሆነው ባለ ሁለት ፊት ነው። ያ እነዚያ ዘንድ በአንድ ፊት፣ ሌሎቹን ደግሞ በሌላ ፊት የሚቀርበው።' ሱኒይ የሆነ ሰው ግን እከሌ ቢወድም ሆነ ቢጠላ ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ነው። ከቡድንተኞች በተለየ።" [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 290] 2ኛው ምርጫ፦ ከነዚህ ሲያወድሳቸው ከነበሩ አካላት መለያየቱን ማወጅ ነው። ሰውየው ተቃራኒ ነገሮችን የማስተናገድ ልምድ ቢኖረውም ይሄኛው ግን ለመሸፈን የሚመች አይደለም። "ግመል ሰርቆ አጎንብሶ" አይሆንም። ስለዚህ መለያየትን ከማወጅ ውጭ ምርጫ አይኖርም። ካ'ህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ይበታተናል ጅብ የጮኸ 'ለት! - የነዚህ ሰዎች ጉድ ይሄ ብቻ አይደለም። አለ ገና! ستُبْدي لكَ الأيّامُ ما كنتَ جاهلاً - ويأتِيكَ بالأخبارِ مَن لم تُزَوِّدِ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👍 1
Repost from N/a
ጥቂት ምክሮች ለኔና ለአምሳያዎቼ እውቀት ፈላጊዎች ቁ: 1⃣1⃣ ➡️ ወገንተኝነትን ራቅ! ወንድሜ ለሃቅ እንጂ ለግለሰብ ወገንተኛ መሆን ከእኛ አይጠበቅም። ይህ ለብዙዎች ሀቅን ለመሸሽ እና ቢዳዓ ላይ ለመውደቅ ምክንያት መሆኑን ዑለሞች ያወሳሉ።  ለሸይኽ፣ ለኡስታዝ፣ ለዳዒ ወዘተ ወገንተኛ መሆን የጃሂልዮች መንገድ አንዲሁ የቢዳዓ ባልተቤቶች መገለጫ ነው። ስለዚህም ወገንተኝነታችን ለአላህ ኪታብ እና ለመልእክተኛው ንግግር ሊሆን ግድ ነው። እንዳንዶች አነርሱ ዘንድ ካልቀራህ፣ የእነርሱን ሸይኽ ካላወደስክ፣ የእነርሱን አቋም "ሁሉ" ካላንፀባረቅ ምን ጠንካራ ብትሆን የሱና ሰው አድርገው አይቆጥሩህም። ይህ የተክፊርዮች አካሄድ ከመሆን የሚድን አይደለም። ታድያ ወንድሜ የሱና ሰዎች በርካቶች ሊሆኑ ይችላሉ። እኛ በምናውቀው ቦታ ብቻ ስላልተገኙ፣ እኛ የምንቀራውን ኪታብ ስላልቀሩ፣ እኛ የምንለውን ሁሉ ስላላሉ ከሱና ይወጣሉ ማለት አይደለም። በሃቅ ላይ የፀና የሆነ ሁሉ፤ ብናውቀውም ባናውቀውም የሃቅ ሰው ከመሆን የሚከለክላው ነገር እንደሌለ ልናውቅ  ይገባል። እንዲሁም ዛሬ ተንሰራፍቶ የምናየው የብሄር፣ የዘር፣የጎሳ ወገንተኝነት እኛ ዘንድ ቦታ ሊኖረው አይገባም። ውዴታችን ለሀቅ እና ለሀቅ ባልተቤቶች ብቻ ሊሆን ይገባል። ✍ አቡ ሁዘይፋህ [ H.M ] https://t.me/Menhaje_Selef
Show all...