قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Open in Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
900
Subscribers
-124 hours
-177 days
+3530 days
Posts Archive
تحفة الأبطال شرح لامية الأفعال
تأليف : الشيخ محمد ولي
رحمه الله تعلى رحمة واسعة
اللهم يسِّر أمورنا، واشرح صدورنا، وبارك لنا في أرزاقنا وأوقاتنا، واصرف عنا كل همٍّ وغمٍّ وبلاء، واجعل لنا من كل ضيقٍ مخرجًا، ومن كل همٍّ فرجًا، ومن كل بلاءٍ عافية.
ربنا آتنا في الدنيا حسنة، وفي الآخرة حسنة، وقنا عذاب النار
👉 በሱና ላይ መፅናት ፍም እንደመጨበጥ ነው።
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿المُتَمسِّكُ بسُنَّتِي، عندَ اختلافِ أُمَّتِي كالقابضِ على الجمرِ﴾
“ህዝቦቼ በተለያዩ ግዜ፣ በሱናዬ ላይ ፀንቶ መቆየት ፍም እሳት እንደመጨበጥ ይሆናል።ሶሂህ አልጃሚ
وَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًٔا وَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ وَعَسَىٰٓ أَن تُحِبُّوا۟ شَيْـًٔا وَهُوَ شَرٌّ لَّكُمْ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
አንዳች ነገርን እርሱ ለናንተ የበለጠ ሲሆን የምትጠሉት መኾናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አንዳችንም ነገር እርሱ ለናንተ መጥፎ ሲሆን የምትወዱት መሆናችሁ ተረጋገጠ፡፡ አላህም (የሚሻላችሁን) ያውቃል ግን እናንተ አታውቁም፡፡
ሱረቱል በቀራ :216 ✍️
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉ቆስላችሁ ታውቃላችሁ!?
የልብህን ጥልቅ ስብራትና የጉዳትህን ስፋት በትክክል ሊረዳ የሚችለው የራስህ ልብ ብቻ ነው።
..... ከቁስልህ የምታገኘው መንፈሳዊ ንጽህና እና እውነተኛ የነፍስ ድህነት የሚገለጸው ያጋጠመህ ህመም ሙሉ በሙሉ ተፈውሶ ለአንተ ብቻ የሚታይ የውስጥ እውነት ሆኖ ሲበራልህ ነው።
.... ምክንያቱም ትልቁ ፈውስ በራስህ ህመም ቁስል ውስጥ አልፈህ የምታገኘው የራስህ ማንነት እውነት ድህነት ነውና ቆስሎ መቅረትን ለማንም አትመኙ ማንንም ማቁሰልም አትመኙ መዳን የማይቀር ሀቅ ነው።
የማይታይ ቢሉ ህመም የማይመስል፡
ሚስጥሩ የራቀ ጥልቅ የሆነ ቁስል፡
ክብደቱ ሀያል ነው ባይኖረውም ምስል፡
ያልታወቀ ቁስል መግል ያልፈሰሰው፡
ይማርህ እያለ ወዳጅ ያልዳበሰው፡
ዶክተር ካላከመው ተስፋ ካልፈወሰው፡
የህመሙን ስሜት ምን ነው የሚያስረሳው
ከወደቀበትስ ማነው የሚያነሳው..!?
ጥልቅ ላይ ነው ያለ ፍም አይሽርም ጠባሳው፡
.....ኑር....
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from N/a
ابن_باز_تزكية_الشيخين_محمد_أمان_الجامي_وربيع_المدخلي48k.m4a2.59 KB
Repost from የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ
ለተሚዮች
እነዚህ ቡድኖች የሚያራምዱት አካሄድ ለዳዕዋው አውዳሚ ነው። በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ ዑለማኦችን ሳይቀር በጅምላ በመፈረጅ እና በማጥላላት ይታወቃሉ።
ከሀገር ውጪ ያሉት ዑለማኦች:
የየመን መርከዞች እና የሀገሪቱ ዑለማኦች፣ እንዲሁም እንደ ሸይኽ አብዱረዛቅ በድር፣ ሸይኽ ሱለይማን አርሩሃይሊ፣ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ አርረይስ፣ ሸይኽ አብዱልመሊክ አርረመዷኒ እና ሌሎች ታላላቅ ዑለማኦች ሳይቀሩ ከእነዚህ ቡድኖች ወቀሳ እና ዘመቻ አላመለጡም።
በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ:
በሀገር ውስጥም የነሱን አስተሳሰብ የማይከተል እና አድናቂ ያልሆነ ማንኛውም ሰው፣ የዕውቀት ደረጃው ምንም ይሁን ምን "ሙብተዲዕ" ተብሎ ይፈረጃል። በየገጠሩ፣ የተውሂድ እና የሱና መሰረታዊ ነገሮችን በማስተማር ላይ ባሉ መስጂዶች እና መድረሳዎች በመሄድ፣ ስድብ እና የተብዲዕ ዘመቻ በመክፈት ብዙዎችን ከመስጂድ እንዲርቁ አድርገዋል። በስንት ትግል የተገነቡ የዳዕዋ ማዕከላትን እና ስብስቦችን በመበተን ለትልቅ የዳዕዋ ትርምስ ምክንያት ሆነዋል።
https://t.me/Menhaje_Selef/
በርታልኝ የኔ ጀግና ለአላህ ብየ እወድሀለሁ።አላህ ሙሉ አፍያህን ይስጥህ።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ወደ ፊት ብቻ!
~
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሁሉም አይነት ሰው አለ። ሞቅ ያለ ተሳትፎ ካለን በተለያዩ አካላት እንገመታለን። እንገመገማለን። እንተመናለን። በአቋም የሚመስለን እንዳለ ሁሉ የሚቃረነንም ብዙ ነውና ዋጋችንና ቦታችን ከሰው ሰው ይለያያል።
* ከፊሉ የምትፅፈው/ የምትናገረው ነገር አይጥመውም። ከፊሎቹ ጋር ደግሞ እውነታው ይለያል።
* ከፊሉ ቀድሞ በጥላቻ ስለተሞላ የኔ የሚለው ሰው ቢናገረው የሚደግፈውን ብትናገር እንኳ ሰበብ ፈልጎ ያብጠለጥልሃል።
* ከፊሉ ዘንድ ሚዛናዊ ነህ። ሌላው ዘንድ ደግሞ ፅንፈኛ፣ ፍርደ ገምድል ነህ።
* ከፊሉ ዘንድ አስተዋይና በሳል ነህ። ሌላው ዘንድ የሃገርና የወቅት ተጨባጭ ያልገባህ ጥሬ ነህ።
* ከፊሉ ዘንድ አዛኝ ነህ። ከፊሉ ዘንድ ጨካኝ ነህ።
* ከፊሉ ዘንድ እየበሰልክ ነው። ሌላው ዘንድ እየባሰብህ ነው።
* ከፊሉ ዘንድ ቡድንተኛ ነህ። ሌላው ዘንድ ውግንናህ ለሐቅ ብቻ ነው።
የሚርቅህ ብቻ ሳይሆን የተሻለ የሚቀርብህ ራሱ የበለጠ ሊጠላህ እና ንግግርህንም ዝምታህንም ያላሰብከውን ትርጉም እየሰጠ ሊያጣጥልህ ይችላል። ቢሆንም ታገስ። ሞራልህ ሳይጎዳ ወደፊት ገስግስ።
የተራራቁ አመልካከቶች በበዙበት፣ ከዒልምና ተርቢያ የራቀ ትውልድ እንደ አሸን በፈላበት፣ በሺርክና መልከ ብዙ ቢድዐዎች ላይ የተዘፈቀው ወገን በበዛበት፣ ይሄ ሁሉ ወፈ ሰማይ በነፃነት የሚናገርበት መድረክ አግኝቶ ከየትኛውም አካል ጉንተላ ሳያገኘኝ ሰላም እጓዛለሁ ማለት ዘበት ነው፣ አጉል ምኞት።
ስለዚህ ደዕዋ ላይ ያለኸው ወገኔ ሆይ! በደዕዋህ ላይ ትችትና ዘለፋ አያስደንብርህ። ቲፎዞና ጭብጨባም አያቅልጥህ። ሰዎች የሚሰጡህ ደረጃም አይድነቅህ። ሁሉም አላፊ ነው። ይልቅ አላህን ብቻ አስብ። በኢኽላስ ተጓዝ። በኢኽላስ ለካ! በኢኽላስ ቁረጥ። ጫጫታ ሳይበግርህ ወደፊት ብቻ። እልህ እንዳይሾፍርህም ሚዛንህን ጠብቅ። ዝቅ ብለህ ጀምር። ወርደህ ስራ። ተግተህ ጣር። መስመር ይዘህ፣ አላህን እያሰብክ እስከተጓዝክ ድረስ መንናቅ አያሳምምህ። ዝናም አያንጠባርህ። በየትኛውም ሁኔታ ከደዕዋ እንዳትርቅ። እንዳትርረታ።
* ያያያዝኩት ግጥም የኔ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ዛሬ ደርስ አይኖርም" ብዬ ስፅፍ ይጨንቀኛል። የሰዎች የመማር ፍላጎት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የምቸልስ ነው የሚመስለኝ። ግን ደግሞ አንዳንዴ ሁኔታዎች ያስገድዳሉ። በሑዘይፋ መስጂድ ከመግሪብ በኋላ የሚቀርበው የኪታቡ ተውሒድ ደርስ ላይ መገኘት እንደማልችል ለማስታወስ ፈልጌ ሲከብደኝ ነው ይህን ማለቴ። ዛሬም ነገም የኪታቡ ተውሒድ ደርስ አይኖርም። ከትልቅ ይቅርታ ጋር!
ከሩቅ የሚታደሙ ስለሚኖሩ በማሰራጨት አግዙኝ፣ ለምታውቋቸውም አድርሱልኝ። ባረከላሁ ፊኩም።
⭕️👉አሏህን የተገናኘ ሰው የቂያማ እለት (የውመል ቂያማ) ፦
ሸይኽን እያመለከ ❌
በቀብር ተበሩክ እያደረገ ከቀብር በረካን እየፈለገ❌
በተሚማ አንጠልጥሎ ተበሩክ እያደረገ❌
አሏህን የተገናኘ።
መልካም ስራ የለውም ፣ ሰባት ገዜ ሀጂ ቢያደርግ ፣ ብዙ የሆኑ የረመዷን ወሮችን ቢፃም፣በጣም ብዙ ሶላቶችን ቢሰግድ አይጠቅመውም።
አሏህ እንዲህ ብሏል፦
وَلَوْ أَشْرَكُوا۟ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡
ይሄ ሽርክ ለዚች አገር መከራ ነው
🎤 ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂር (ሀፊዘሁሏህ)
👉⭕️አወ ጀማ ንጉስን፣ ማምለክ ፣ገታን ማምለክ ፣ማይባርን ማምለክ ፣አርባ ጫማን ማምለክ፣የቦረናውን ሸይኽ ማምለክ ፣አናን ማምለክ ፣ዳናን ማምለክ ፣ቁጥብን ከማምለክ ሰይፉ ጨንገሬን ማምለክ፣ ጭሌን ማምለክ፣ ለዛፍ ማረድ፣ በየ ሾላው ስር ከማረድ፣በየ ወንዙ ዳር ከመገበር፣በየሜዳው ላይ ለባድገዝ ድንኳን ጥሎ ከማጫጫስ፣ለጅን መገበር፣ ማረድ፣ቃልማ እያሉ መስከረም መስከረም ጥቁር በግ ገነጣጥሎ ማጫጫስ፣ ነጭ ፍየል ገዝቶ ቃልማ ብሎ ሀገሩን ማዞር፣መቃም ወ~ዘ~ተ የዚች ሀገር በተለይ የወሎ ሙሲባ ማነቆ መከራ ችግር ነው
ነጃ መውጣት ከፈለግን ይህንን አጉል ኮተት እምነት ህዝባችን እንዲተወው መስራት አለብን በተለይ በገጠር ለእናት ለአባቶቻችን ማስተማር ለወገናችን ማሰብ ይኖርብናል።
ወንድም አቡ ሹራ አህመድ
https://t.me/Sobabilalmesjid/5064
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
🔺👉 ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂሪ (ሀፊዘሁሏህ)
‼️የሱዳኑ ኮኮብ✳️
የነብያት ወራሽ አሊም ነው ታታሪ፡
የሱዳኑ ጀግና ሙዘሚል ፈቂሪ ፡
ሱፍያን ገራፊ ልክ እንደረመጡ፡
ሺአ ፣ማቱሪድን፣ በሁጃ የቀጡ
አሉን ታላቅ አሊም ሱዳን ላይ ያጌጡ ፡
የምድሪቱ ኮኮብ የተውሒድ መምህር፡
የሱና ዘበኛ ለጥላቱ ነብር፡
ባጢል ኹራፋት መዶሻ ነው ብትር፡
ድምፁ ጎላ ይላል እውነትን ሲናገር፡
አይደራደርም አቂዳውን በብር፡
የሀገሩ ድምቀት የሱዳኑ ጀንበር፡
ስሙም ይማርካል ሸይኽ ሙዘሚል ፈቂር ፡
ሽርክ በበዛበት ከጫፍ እስከ ጠረፍ፡
ደሊሉን አንግቦ ባጢልን የሚገርፍ፡
ትውልድ የሚቀርፅ በተውሂድ በሱና፡
ገልጦ እያነበበ አስ ሱነቱ ጁና፡
ጠንቋይ በበዛበት በእምነቱ ነጋዴ፡
እውነትን ሰባኪ የጥላት ጎራደ፡
በሙቀት በረሀ ቀልጦ እየነደደ፡
ለጦኦት አምልኮ ያልተንሸረደደ፡
አለን ታላቅ አሊም በሀገር ጎረቤት፡
ደረሶች ያፈራ ያበቃ ለስኬት፡
ሀቅ የሚስከብሩ በሁጃ ተውበው፡
ባጢልን ኮርኳሚ ቁርአን አንብበው፡
ጀመአቸው በዝቶ ጥላትን አክስመው፡
ለድኑ የቆሙ አሉት ውድ ልጆች፡
አፍርቷል ደረሳም የማይንገቻገች፡
በዳእዋህ ላይ በርታ አሏህ ይጠብቅህ፡
ሁሌ እንወድሀለን ሀቅ ላይ እስካለህ፡
ምክርህን ለግሰን ያሸኸል አላማህ፡
ቁርአንን ሲያነብ ሽርክን እያብራራ፡
ሂዋር ላይ ታድሞ ማንንም ሳይፈራ፡
ተቀላቅሎበታል አምነቱ ከደሙ፡
ቢጠሩት አይሰማም ታክተው ካልደከሙ፡
አፉን እያስያዘው በሁጃ በደሊል፡
ማንንም ሳይፈራ ለማንም ሳይዋልል፡
እውቀትን ታጭቆ ፀንቶ የሚታገል፡
ኹራፋት ቢድአን ሰርጓጅ እንደመርከብ፡
ዳእዋው ፍሬ ላይ ነው የሱዳኑ ኮከብ፡
‼️ ‼️ ‼️ ‼️
ጥር /5/2/2017
አቡ ሹራ Ahmed ksssaya
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Sobabilalmesjid
Repost from قَنَـاۃُ أَبِي عُـثَـيـمِـيـن السَّلَفِـي
ስለ ሼይኽ ሙዘሚል ፈቂሪ حفظه الله
https://youtu.be/6uN4dFiYCDA?si=hgTMuzpxdfidJ-dg
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዚህ ጋር የሚያያዝ አንድ አስቂኝ አጋጣሚ እንዲህ ይነግሩናል፡- “የሆነ ሰው ልጁን ‘ነክተል’ ብሎ ይሰይመዋል፡፡ ‘ምነው?’ ሲባል ‘አይ ይሄ የዩሱፍ ወንድም ስም ነው’ በማለት ( ﻓﺄﺭﺳﻞ ﻣﻌﻨﺎ ﺃﺧﺎﻧﺎ ﻧﻜﺘﻞ ) ብሎ ማስረጃ ያጣቅሳል፡፡” አንቀፁዋ ውስጥ የተጠቀሰው “ነክተል” የሚለው ቃል መልእክት ግን “ይሰፈርልናል” ማለት ነው፡፡ አስቂኝ!! ይሄ እውነት ተከስቶ ከሆነ ቁርኣን ላይ ስለተገኘ ብቻ መልእክቱን በውል ሳይለዩ መሰየም ሰያሚንም ተሰያሚንም የነቁ እለት የሚያሳፍር ጥራዝ-ነጠቅ አካሄድ ነው፡፡
14. የሚወጣው ስም በቤተዘመዱ ወይም በአቅራቢያው ካሉ ዘንድ ከመብዛቱ የተነሳ እስከሚያምታታ ባይደርስ ጥሩ እንደሆነ ኢብኑልዑሠይሚን ይገልፃሉ፡፡ አንዳንዱ ስም ድግግሞሹ ከመብዛቱ የተነሳ እስከ አራት እስከ አምስተኛ አያት ካልተጠቀሰ አንዱን ከሌላው ለመለየት የሚያስቸግርበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ ይሄ “ሐራም ነው” ባይባልም ባይደረግ ይመረጣል፡፡
ባጭሩ የዚህ ፅሁፍ አላማ የተከለከሉ ስሞችን መዘርዘር አይደለም፡፡ ይልቁንም የማይፈቀዱ ስሞችን የምንለይባቸውን መርሆዎች ማሳየት፣ ስንሰይም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ መጠቆም፣ የራሳችንም ይሁን “የኛ” የምንለው ሰው ስም ላይ ፍተሻ እንድናደርግ ማስታወስ እና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በጊዜ እርማት እንድናደርግ ማመላከት ነው፡፡ ይስተዋል! የክልከላ ዝርዝሮቹ በዝተው ከታዩን መለስ ብለን እናጢናቸው፡፡ አብዛሃኛዎቹ ገደቦች ለማንም የማይሰወሩ ሲሆኑ ሲያጋጥሙንም “ግን ለምን?” ብለን የምንደነቅባቸው ናቸው፡፡ በዚያ ላይ የሚወደዱና የሚፈቀዱ ስሞች ሞልተው የተትረፈረፉ ናቸው፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት፡-
1. ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ዐዝዘ ወጀል ዘንድ ከስሞቻችሁ ሁሉ ተወዳጁ ዐብዱላህ እና ዐብዱርረሕማን ነው፡፡” [ሙስሊም]
2. በመቀጠልም ለአላህ ባርያ መሆንን የሚገልፁ ስሞች ተወዳጅ እንደሆኑ ዑለማዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ለምሳሌ ‘ዐብዱልመሊክ’፣ ‘ዐብዱልዐዚዝ’፣… በማለት ለአላህ ባርነትን በሚገልፁ ስሞች መጥራት፡፡ ባይሆን ያስጠጋነው በተጨባጭ ወደ አላህ መልካም ስሞች መሆኑን እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ያለ ተጨባጭ ማስረጃ የትኛውንም ስም “የአላህ ስም ነው” ማለት አይፈቀድምና፡፡ ከዚህም በመነሳት አንዳንዶች “ዐብዱ ምናምን” ብለው ነገር ግን ትርጉም ወደሌለው ነገር ወይም የአላህ ስም ለመሆኑ ግልፅ ማስረጃ ወዳልመጣበት ስያሜ የሚያስጠጉ አሉ፡፡ ይሄ ችግር በሀገራችንም ይስተዋላል፡፡ “ዐብዱልካፍ” የሚለውን እንደምሳሌ ውሰዱ፡፡
3. በመቀጠል በታላላቅ የአላህ ነብያት ስሞች መሰየም ተመራጭ ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ዛሬ ሌሊት ልጅ ተወለደልኝ፡፡ በአባቴ ስምም ‘ኢብራሂም’ ብየ ሰየምኩት” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም] “ዩሱፍ” ብለው የሰየሙበትም አለ፡፡ [ሶሒሑልአደቢልሙፍረድ፡ 642] “በስሜ ተሰየሙ” ማለታቸውም የሚታወቅ ነው፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] ቁርኣን ውስጥ የብዙ ነብያት ስሞች እንዳሉ ይታወስ፡፡
4. ከዚያም በደጋጎችና በሙስሊም ዑለማዎች ስሞች መሰየም ይወደዳል፡፡ “እነሱ (ጥንታውያኑ የሁዶች) በነብዮቻቸውና ከነሱ በፊት በነበሩ ደጋጎች ስም ይሰይሙ ነበር” ብለዋል ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡ [ሙስሊም] በዚህ ረገድ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሐቦችና የመልካም ቀደምቶቻችን ስሞች ጥሩ መነሻ ይሆናሉ፡፡ ከልጆችም ልቦና ውስጥ የነዚህን ደጋጎች ታሪክ ለማወቅ፣ አልፎም ፈለጋቸውን ለመከተል መነሳሳትን ከውስጣቸው ይጭራል፡፡
5. ከዚያም ስርኣቱን በጠበቀ መልኩ እውነተኛ እና በተጨባጭ ገላጭ የሆነ ስም ይከተላል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከስም ሁሉ እውነተኛው (ተሰያሚውን የሚገልፀው) ‘ሀማም’ እና ‘ሓሪሥ’ ነው” ብለዋል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 1040] “ሀማም” ማለት “ሀሳብ የሚያበዛ” ማለት ሲሆን “ሓሪሥ” ማለት ደግሞ “አራሽ”፣ “ገበሬ” ማለት ነው፡፡ እነዚህ ስሞች ብዙሃኑን ህዝብ በተጨባጭ ይገልፁታል፡፡ ከዚህ በመነሳት ተጨባጭ መልእክት ያላቸው ስሞችን መጠቀም ይቻላል ማለት ነው፡፡
ስሞቻችን በተቻለ ዐረብኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ይህን ስል ትንሽ ትልቁን በዘር መነፅር የሚመለከቱ አጉል ፀጉር ሰንጣቂዎችን አስተያየት ከቁብም መቁጠር አያስፈልግም፡፡ እነ እስክንድር፣ እነ ዳንኤል፣ እነ ሄለን፣ እነ ዮሴፍ፣ ዮሐንስ፣ ራሄል፣ ወዘተ ኢትዮጵያዊ መነሻ ያላቸው ስሞች አይደሉም፡፡ በቁም የሚያንቀላፋ ፉዞ ሳያስተውል ቢያስተጋባም አንዳንዶች ዘንድ ዐረብኛ ስሞችን መቃወም አላማው ሌላ ነው፡፡ መቼስ ዐረብኛ ቋንቋ ከእምነታችን ጋር ያለውን ጥብቅ ትስስር ወዳጅ ቀርቶ ጠላት አይዘነጋውም፡፡ ስለዚህ አደፍርስ፣ ተምትሜ፣ አልጋነሽ፣ ጃኖ፣ ፈጌሳ፣ አምዴግባ፣ ቶሎሳ፣ ጫልቱ፣ ኢናሂና፣ ጉደሌ፣ ሸርሞሎ፣ ቢፍቱ፣ … እያልን ልጆቻችንን አንሰይም፡፡ አላህ ያውቃል! ይህን የምለው ለየትኛውም ቋንቋ ጥላቻን አንግቤ አይደለም፡፡ ወሰላም፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 2/2008)
https://t.me/IbnuMunewor
