en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

Open in Telegram

📝በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ የሚሰጡ ደርሶች ፣ሙሃደራዎች እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
3 883
Subscribers
-424 hours
+1277 days
+62830 days
Posts Archive
🔷የኢኽዋንና የራፊዷ ጥምረት ሸይኽ ረቢዕ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "በአሁኑ ጊዜ ወጣቶች በኢኽዋን አል'ሙስሊሚን ተግባር ግራ ተጋብተዋል። እነርሱ የራፊዷዎችና የእነርሱ አጋሮች መጠቀሚያ ናቸው። እንደማስበው በኢኽዋን አል'ሙስሊሚን መካከል ሰርገው የገቡ ራፊዷዎች አሉ። እነዚህም በእነርሱ የሚከተሉ የዋሆችን ስሜት ይቀሰቅሳሉ። ይህ በየትኛውም አገር ሊገኝ ይችላል። ከራፊዷ ጋር ሲተሳሰሩ ታገኛለህ። በኢራቅ ፣ በሶሪያ ፣ በሊባኖስ ፣ በሱዳን ፣ በአፍሪካ  እና በምስራቅ ኤሽያ አገሮች ሰዎችን ለማበላሸት ፣ የራፊዷ አመለካከት ሰርጎ እንዲገባ ኢኽዋነል ሙስሊሚን መንገዶችን  ሲያመቻቹ ታገኛለህ።" شرح عقيدة السلف أصحاب الحديث ص/٤٧١ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

🚫አዲስ የተጀመረ የዐቂዳህ ትምህርት
➽ኹዝ ዐቂደተከ ሚነል ኪታቢ ወስ'ሱነቲ አስ'ሰሂሀ
➠ክፍል አንድ (01) 📝#የቴሌግራም Channeሉን #join በማለት  #ይቀላቀሉ➷➷➷➷➷ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

በአንድ ነገር ላይአቋም ከመያዝህ በፊት ጠንካራ ማስረጃ አጥብቀህ ያዝ!! ————— አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት አስተማማኝና ጠንካራ ማስረጃ ከያዘ፣ ዱኒያ ላይ ሰዎች ፊት፣ በአኼራም አላህ ፊት አይዋረድም። እውነተኛ የሆነ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙም በፊት ሆነ ከመናገሩ በፊት በቂ ማስረጃ መያዝ እንዳለበትና እርግጠኛ መሆን እንዳለበት ግልፅና ለማንም የማይሰወር ነገር  ነው። አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት ትክክለኛ የሆነን ማስረጃ ካልያዘ፣ የያዘው አቋምና አመለካከት ትክክል ሳይሆን ቀርቶ በሌሎች ሲተችበት ለጭንቀቱ ማምለጫ ሊሆነኝ ይችላል: ብሎ ያሰበውን ሁሉ እያመጣ ሲደረድር ይበልጥ ወደ ሌላ ጥፋት ያመራል። ለዚያም ነው፣ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዝ በፊት ትክክለኛ የሆነን ማስረጃ መያዝ የአህሉሱንናዎች መገለጫ ነው። በተቃራኒው ደግሞ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከያዙ በኋላ ማስረጃ መፈለግ የቢድዐ ሰዎች ባህሪና ልዩ መገለጫ ነው። ምናልባትም አንዳንዴ በራሳቸው ላይ ማስረጃ ሊሆንባቸው የሚችልን ማስረጃ ያለቦታው ሲያቀርቡት ይስተዋላል። አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ያለ በቂ ማስረጃ አስቀድሞ አቋም ከያዘ የምታመጣለትን ማስረጃ ሁሉ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ ሳይሆን ራሱ አስቀድሞ ለያዘው አቋም በሚመቸው መልኩ ብቻ መቀበል ነው የሚፈልገው። ይህ ደግሞ ወደ ጥመት የሚመራው በጣም ከባድ አደጋ ነው!!። ለዚያም ነው የሱንና ሰዎች በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዛቸው በፊት ትክክለኛውን ማስረጃ በደጋግ ቀደምቶቻቸው ግንዛቤ መሰረት ከቡድንተኝነትና ወገንተኝነት ገለልተኛ ሆነው ይፈልጋሉ፣ ከዚያም በኋላ አቋም ይዛሉ። የቢድዐ ሰዎች ደግሞ አስቀድመው አቋም ይዛሉ ከዚያም በኋላ ለያዟት አቋም ትሆነናለች ብለው ያሰቧትን ብዥታ ሁሉ እንደ ማስረጃ አንግበው ይንቀሳቀሳሉ። ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዳሉትም "ለቢድዐ ሰዎች ብዥታ እንጂ ማስረጃ የላቸውም።" ለዚያም ነው፣ አስቀድሞ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት ትክክለኛውን ማስረጃ ከመያዙ በፊት አቋም የያዘ ሰው፣ ቁርኣንና ሀዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤና አካሄድ መሰረት ይዘህለት ብትቀርብም ለራሱ አቋም በሚመቸው መልኩ ቀዶ ካልሰፋው የማይሆንለት። ከዚህም አልፎ አንዳንዴ የያዘውን አቋም ትክክል አለመሆኑን በማስረጃ ስታወግዝበት በቂ ማስረጃ ሲያጣ ከገባበት ማጥ ለማምለጥ ጉዳዩን በተዘዋዋሪም ይሁን በቀጥታ የግል የግጭት ጉዳይ ለማስመሰል ይኳትናል። ምናልባትም በማስረጃ የነቀፉትን ሰዎች ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ የግል ታሪካቸውን፣ (መቼም የሰው ልጅ ባህሪ ይለያያልና) በግል ባህሪያቸው… የመሳሰሉ ከዲን ነጥብ ውጪ ወይም ከተተቹበት አጀንዳ ውጪ የሆኑ ጉዳዮችን እያነሱ ሲወርፉ ማየትም ሊስተዋል ይችላል። ይህ ይበልጥ በቂ ማስረጃ ሳይኖራቸው አቋም መያዛቸውን የሚያሳብቅ ሲሆን! ምንም እንኳን የግል ፀብ ቢኖርም ባይኖርም ማንኛውም ገለልተኛ አካል ይህ ሰው አቋም የያዘበት ጉዳይ ሲነቀፍ ከተመለከተ ማየት ያለበት ሰውዬው አቋም የያዘበትን ማስረጃና ነቃፊው አካል የሚያቀርበውን ማስረጃ ክብደት ብቻና ብቻ ነው!። በመሆኑም አንድ ሱኒይ ነኝ የሚል ሰው የሚጠበቅበት፣ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት ተረጋግቶ ግራና ቀኙን በማየት ትክክለኛውን ማስረጃ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት አጥብቆ መያዝ ግድ ይለዋል!!። ✍🏻 ኢብን ሽፋ t.me/ibnshifa የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join አድርገው ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

➲የዚህ ዘመን ጂሓድ የሸሪዓ እውቀትን መፈለግ እነ ወደ አላህ መጣራት ስሆን ከዚህ ትልቅ ዒባዳና የትጥቅ መሳሪያ ወደ ኋላ ማለት አደጋው ከባድ እነ አስከፊ ነው❗️

🔷ለተማሪዎች ምክር ዶክተር ሸይኽ ሁሴን - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ከታዋቂነትና ከአመራር ውዴታ መራቅ ፤ ምክንያቱም እርሷ የሰለፍያን እንቅስቃሴ የከፋፈለችና ያፈራረሰች አስጸያፊ እና እጅግ የተወገዘች መጥፎ ባህሪ ነችና። ባለቤቶቿ አስተሳሰባቸው ደካማ እና ጤናማ ያልሆኑ ናቸው።" الرسالة : خمسون نصيحة لطلاب العلم   ص/41 https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

🔴 ልዩ የትምህርት ማስታወቂያ 📚 የአረብኛ ሰዋሰው ትምህርት 📖 مُتْنُ الْمُقَدِّمَةِ الْآجُرُّومِيَّةِ ✍️ የኪታቡ አዘጋጅ፦ الإِمَامُ النَّحْوِيُّ أَبُو عَبْدِ اللهِ مُحَمَّدُ بْنُ دَاوُدَ الصَّنْهَاجِيُّ، الشَّهِيرُ بِابْنِ آجُرُّومَ رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى ❇️ የአረብኛ ሰዋሰውን ከመሠረቱ እንማር! የአረብኛ ቋንቋን በትክክል ለመረዳት፣ የቁርኣንንና የሐዲስን አገላለጾች ለመገንዘብ እንዲሁም የዑለማዎችን መጻሕፍት በጥልቀት ለማንበብ የሚረዳውን የናሕው ኪታብ በሥርዓት እንማር። 📌 የትምህርቱ ጥቅሞች፦ ✅ የአረብኛ ሰዋሰውን (عِلْمُ النَّحْوِ) መሠረታዊ ደንቦች መማር። ✅ ቃላት በአረብኛ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ያላቸውን የሰዋሰው ሚናና የኢዕራብ ሁኔታ (الإِعْرَابُ) መረዳት። ✅ የቁርኣንን አንቀጾችና የነቢዩን ﷺ ሐዲሶች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት መቻል። ✅ የሐዲስ፣ የፊቅህና የሌሎች የኢስላማዊ ዕውቀት መጻሕፍትን ለማንበብና ለመገንዘብ ጠንካራ መሠረት መገንባት። ✅ በንባብና በንግግር ጊዜ የሰዋሰው ስህተቶችን ለመቀነስ መቻል። ✅ ለቀጣይ የአረብኛ ሰዋሰው ኪታቦች ጥናት ጠንካራ መሠረት መጣል። 🎙 ትምህርቱን የሚሰጠው፦ አቡ ኢልሓም ሙሐመድ ኑር (وفقه الله) 🗓 የትምህርት ቀን፦ ቅዳሜና እሁድ 🕰 ሰዓት፦ ከዒሻእ ሶላት በኋላ 📍 ቦታ፦ መድረሰቱል ሙሃጂሪን مدرسة المهاجرين – معهد علمي ودعوي 📢 ግብዣ ለሁሉም የዕውቀት ፈላጊዎች! የአረብኛ ቋንቋን በመሠረታዊ ደረጃ ለመማር የምትፈልጉ፣ የዲን ዕውቀታችሁን ለማሳደግ የምትጥሩና የዑለማዎችን መጻሕፍት በትክክል ለመረዳት የምትመኙ ሁሉ በዚህ ጠቃሚ ትምህርት እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን። 💎 ዕውቀትን በትጋት፣ በትዕግሥትና በተከታታይነት እንቅሰም! 📖 مَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللَّهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ "ዕውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጎዘ ሰው፣ አላህ በዚያ ምክንያት ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ ያቀልለታል።" 📚 ምንጭ፦ ሰሒሕ ሙስሊም https://t.me/sunah123

📌ምቀኝነትና ጥላቻ ሰዎች ከመንሃጃቸው እንዲወጡ ሰበብ ይሆናል። ወንድምህን በዒልሙ፣በዱኒያው መመቃኘት አደጋው ከባድ ነው። ከምትመቃኝ ለሱ የሰጠውን አላህን ለሱ ከሰጠው የተሻለ እንዲሰጥህ ጠይቀው፣አላህ እኮ አያልቅበትም። አላህ ለሱ እንደሰጠው እያመንክ መልሰህ ምትመቃኝ ከሆነ ጦርነትህ ከአላህ ጋር ነው። ተው አትመቃኝ በቃ። http://t.me/ibnawolllll http://t.me/ibnawolllll

"በእራሳቸው ጥፋት አንተን የሚወነጅሉ ሰዎች ምናልባት የመርሳት ችግር ላይ ወድቀው ይሆናል!!" አንድ የመርሳት ችግር የነበረበት ባል ነበር ይባላል።ይህ ባል ከዕለታት አንድ ቀን  ሚስቱን ሊያስደስት በማሰብ ስጦታ ገዝቶ ወደ ቤት ይመጣል።ባል ወደ ቤት እንደገባ ሚስቱን ጠርቶ የያዘውን ስጦታ ከኃላ በመደበቅ ዓይንሽን ጨፍኚ አላት።ምስኪኗም ሚስቱ ዓይኗን ትጨፍናለች። ይህም የመርሳት ችግር ያለበት ባል ወዲያውኑ ጨፍኚ ያላትን ረስቶ በቁጣ ድምፅ "እኔን ማየት ደብሮሽ ነው አይደል ዓይንሽን የጨፈንሽው?" በማለት ከቤት ያባርራታል።ከቤት እራሱ እንዳባረራትም ረስቶ "እቺ ሴትዬ ወዴት ዙረት ሄዳ ነው?" ብሎ እርሷን ፍለጋ ወጣ ይባላል። ልክ እንደዚሁም በየቦታው በእራሳቸው ሴራና ተንኮል ተጠላልፈው ሲወድቁ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በውሸትና በቅጥፈት ክስ እያለቃቀሱ እዛም እዚህም ድስኩራቸውን ሲደሰኩሩ ይስተዋላል።ይህም አካሄድ አላህ ዘንድ መጠላቱ የበረታ የሆነውን ለእራሳችሁ የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ የሚለው ላይ ይጥላል። (يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ (2) كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ (3)) አላህ ከዚህ  አይነት ችግር ሰላም ያድርገን። اللهم آمين ✍አቡ ሙዓዝ

🚫ለሰለፊያ ደዕዋህ የሚከፈለው ዋጋ 👉ዘመን የማይሽረውን ሙሉውንና ውቡን እስልምና እነ  ረሱል ﷺ ለሷሃበዎች ያስተማሩትን  ፊንትው ያለውን ሱና ተዐቢዮች ከሷሀዎች የተገነዘቡትን የጸዳውን ሚንሓጅ ለመስራትና ለማንፀባረቅ የሚፈልግ ሙስሊም ትልቅ ዋጋ መክፈል ያስፈልጋል ። በተለይ ለሰዎች ደዕዋህ አደርጋለሁ የሚል አካል ትልቅ ዋጋ መክፈል አለበት  ራሱን ወደ ደዕዋው ካስጠጋ ብዙ ፈተናዎችና ችግሮች ሊደርሱበት ይችላሉና በዚህ ሰዐት ለደእዋው ከመጨነቅ አንፃር የሚደርሱበትን አዛዎችንና ችግሮችን በመቻል ደእዋውን ማስቀጠል አለበት  ጭንቁ ሀሳቡ ሚንሓጁ እነ ደዕዋው ትክክል መሆኑ ላይ እንጂ ሌላ ነገር ላይ መሆን የለበትም ። ➜የሰለፊያ ደዕዋህ  የማያስጨንቃቸው አካለት በምቀኝነትና በኩራት ብዙ ችግሮችን ልያደርሱበት ይችላል በዚህ ሰዐት በትግእስት ክብሩንና ጥቅሙን ችላ በማለት  ለደእዋው ትልቅ ዋጋ በመክፈል ማስቀጠል አለበት ። ደዕዋውን ልያፈርሱት ከሚንቀሳቀሱ ወጠምሻዎች አካባቢ የሚደረገውንና የሚሰማውን አይቶ ደዕዋውን ማቋረጥ  ቆሻሻ ዓለማቸውን ሊያሳካላቸው አይገባም። ➜ለዚህ ትልቅ ምሳሌ የሚሆን የረሱል ﷺ ሐዲስ ልጥቀስ ፦ 👈عن أبي هريرة رضي الله عنه : أنه سمع رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: كانت امرأتان معهما ابناهما، جاء الذئب فذهب بابن إحداهما، فقالت لصاحبتها: إنما ذهب بابنك، وقالت الأخرى: إنما ذهب بابنك، فتحاكما إلى داود صلى الله عليه وسلم فقضى به للكبرى، فخرجتا على سليمان بن داود صلى الله عليه وسلم فأخبرتاه، فقال: ائتوني بالسكين أَشُقُّهُ بينهما، فقالت الصغرى: لا تفعل! رحمك الله، هو ابنها، فقضى به للصغرى.   رواه البخاري ومسلم
◊አቡ ሑራይራ ረዲየአላሁ ዐንሁ ረሱል ﷺ እንዲህ ስሉ  ሰማቸው ፦ ከበኒ እስራኤሎች ውስጥ ህፃን ልጆቻቸውን የያዙ ሁለት እናቶች ነበሩ ተኩላ መጣና የአንዳቸውን ህፃን ይዞባቸው ይሄዳል በዚህ ሰዐት አንደኛዋ ተኩላው የወሰደው ያንቺን ህፃን ነው አለቻት ሁለተኛዋም አይ ተኩላው የወሰደው ያንቺን ህፃን ነው አለቻት ነቢዩ ዳውድ ዐለይሂ ሰላም ጋ በመሄድ ተፋረዱ ነቢይ ዳውድም  ዐለይሂ ሰላም ለታለቋ እናት ህፃኑ ያንቺ ነው በማለት  ፈረዱላት ከዚያም እንደገና ወደ ነቢዩ ሱለይማን ቢን ዳውድ ዐለይሂማ  ሰላም ጋ በመሄድ ተፋረዱ ነቢዩ ሱለይማንም ዐለይሂ ሰላም ብለዋ አምጡልኝ ህፃኑን በመሰንጠቅ ሁለት ቦታ አደርግላቸዋለሁ አለ ይህኔ አነስ የምትለዋ እናት አላህ ይዘንልህ አታድርገው ልጇ ነው ትውሰደው አለች ነቢዩላሂ ሱለይማንም ለትንሿ እናት ፈርደው ህፃኑ ያንቺ ነው ውሰጂው በማለት ፈረዱላት ።
➲ከዚህ ሐዲስ የምንማረው ቁምነገር ፦
➽ተለቅ የምትለዋ እናት የኔውን ህፃን ተኩላ ከበላው አይቀር የሷም መኖር የለበትምና ይታረድ በማለት ዝም ብላ ነበር ከተኩላው የተረፈው ህፃን እናት ግን የሚያሳስባት ህፃኗ ከሷ ጋር ማደጉ ሳይሆን የትም ሆኖ በሕይወት መኖሩ ስለሆነ ተወው አትሰንጥቀው የሷ ልጅ ነው በማለት አሳልፋ ሰጠቻት !
◉ከርዕሴ ጋር የሚገናኘው የሰለፊያው ደእዋህ የሚያሳስበው አካል ይህ ደእዋህ በማኑም እጅ ይመራ ደስ ይለዋል እንጂ እኔ ከልመራሁት ገደል ይግባ አይልም ! በሚያሳዝን ሁኔታ ዘሬ ለይ እኔ የላመሰልኩት ወጥ አይጣፍጥም በማለት ለሰለፊዮች ፊትና የሆኑ አካላት በሽ መሆናቸው ነው አላህ ይምራቸው !!! ➼የሰለፊያ ደእዋህ አሳስቦኛል የምትለው ወንድሜ ሆይ እውነት የሚያሳስብህ ከሆነ ማኑም ያራምደው ማኑም ያካሄደው ከቻልክ ከጎኑ በመሆን ደግፍው ጡንቻ ሁንለት ከልቻልክ በጥረቱና በሸፈነው ክፍተት ተደሰት አላህ ዘንድ አጅር ተገኝበታለህ ። ➲ስለዚህ እኛ ለአንዳንድ ወሮበላዎችና ወጠምሻዎች ቅጥፈትና ውንጀለ ብለን ከደዕዋው ለአንድ ሰከንድ ወደ ኋላ አንልም እንዲሁም ለቅጥፈታቸውና ባዶ ውንጀላው ከዚህ በፊትም መልስ አልሰጠንም ከዚህም በኋላ አንሰጥም። ◉ይህንንም የመረጥነው ከጥቅማችንና ክብራችን በላይ የደዕዋህ ሰለፊያ ነገር ስለሚያሳስበን ነው እንጂ ፈርተናቸው ወይም ጥፋቱ ኖሮብን አምነን ተቀብለን አይደለም ከሁሉም በፊት ቅድሚያ ለደዕዋህ ሰለፊያ መስለሃ ብለን እንጂ! ደዕዋው የሚፈልገውንና ለደዕዋው የሚከፈለውን ዋጋ ጠንቅቀን እናውቃለን !
🤲አላህ ሁላችንንም ለደእዋው አስፈላጊውን ሁሉ ዋጋ በመክፈል ለተሻለው ደዕዋህ ጥቅምና አብሮነት ይግጠመን አላሁማ ✍አሚን!
✍ከተወነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለጠፈ 📝#የቴሌግራም Channeሉን #join በማለት  #ይቀላቀሉ➷➷➷➷➷ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

ሠለፊዮች ሰውን አልበታተኑም!! ——— ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ አን-ነጅሚይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ሰለፊዮች በመበታተንና በጭቅጭቅ የመጡ ናቸው ብሎ የሞገተ ሰው በእርግጥም ዋሽቷል። አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ፊት የሚጠየቅባት የሆነችን ከባድ ቅጥፈትን ቀጥፏል!። ወላሂ በመበታተን ላይ አልመጡም እነዚያ ቢድዐን (በዲን ላይ አዲስ ፈጠራን) ያመጡት ሂዝቢዮች (ቡድንተኞች) ቢሆኑ እንጂ፣ እነሱ ናቸው ለልዩነት ምክንያት የሆኑት። ይህ ከመሆኑም ጋር ግን ተናጋሪዎቻቸው አልያም ፀሀፊዎቻቸው ሠለፊዮችን በበታታኝነት ይወርፋሉ። ይህ አካል በሚከተለው አባባል ላይ ወድቋል:- (በራሷ ጉድፍ ወርፋኝ እራሷን ልክ እንደ ፍፁም ጨዋ አድርጋ ወጣች) እንደሚባለው ነው። ይህ እውነታን መከርበት ነው። ይህን ቃል የተናገረው ማን እንደሆነ አላህ ይጠይቀዋል።” [አልፈታዋ አልጀሊየህ ዐን መንሀጅ አድደዕዊየህ ገፅ 22] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

የጁምዓ ኹጥባ(ምክር)
هَوَانُ الدُّنْيا وَفَضْلُ ركعَتَيْ الفَجْرِ የዱንያ ቀላልነት ፣ የፈጅር ሱና ያላቸው ደረጃ
በሼይኽ ዩሱፍ አህመድ (ሀፊዘሁሏህ) ጥቅምት 06 29 - 2019 ባህርዳር ሰለፍያ መስጂድ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq

ከታች ካሉ ዝርዝሮች የተመቻቹን ንኩ👇👇👇👇

♦️الرد الجديد
كشف افتراء خضر كمسي المميع الشهير على إمام الجرح والتعديل ربيع بن هادي أنه لا يبدع بكر أبو زيد .
✍للشيخ الدكتور حسين السلطي حفظه الله تعالى وجزاه الله خيرا https://t.me/HussinAssilty

🛜የሶሂህ አል'ቡኻሪ ደርስ ተጀመረ 🎙للشيخ الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله https://t.me/HussinAssilty?livestream

♦️الرد الجديد
كشف افتراء خضر كمسي المميع الشهير على إمام الجرح والتعديل ربيع بن هادي أنه لا يبدع بكر أبو زيد .
✍للشيخ الدكتور حسين السلطي حفظه الله تعالى وجزاه الله خيرا https://t.me/HussinAssilty

👉በሱመያ መድረሳ የሚሰጠው ደርስ ትውስታ ነገ ዕለተ ጁመዐህ ከፈጅር ሰላት በኃላ ጀምሮ እስከ ረፋዱ 3:30 ድረስ በሱመያ መድረሳ በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ የሚሰጠው ደርስ በቦታው ይጠብቃችሃል በግዜ ይገኙ ። https://t.me/ibnbaz1212

👉የደርስ ለውጥ ማስታወቂያ በሐጢባ መድረሳ በጁሙዓ ቀን ከ8:30 እስከ መግሪብ የሚሰጠው የፈዋኢድ ደርስ ለግዜው እየተሰጠ ባለው "50 ምክሮች ለጡላበልዒልም" ለዛሬ የተቀየረ ስለሆነ ከወዲሁ "50 ምክሮች ለጡላበልዒልም" ኪታባችሁን ይዛችሁ በግዜው እንድትገኙ እናሳውቃለንተ። https://t.me/ibnbaz1212

♦️ አደብን ከእውቀት ማስቀደም ◊አላህ በተለያዩ የቁርኣን አንቀጾች እውቀትን የሚሰጠው አደብ ላላቸው ሙስሊሞች መሆኑን ተናግሯል ። የአላህ መልክተኛ ረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በትልቅ ስነምግባር ባለቤትነት ነው የተገለፁት ።ከማይጠቅም እውቀትና ከመጥፎ ስነምግባር በአላህ ይጠበቁ ነበር ። የጥሩ ስነምግባር ባለቤት የሆነ ሰው ለይል የሚሰግድና ቀን የሚፆም የሆነን ሰው ደረጃ በጥሩ ስነምግባሩ ብቻ እንደሚያገኝ ተናግረዋል ። ሰለፎቻችንም እውቀት አደብ እንደሚቀድም አስተምረዋል አደብን መማር እውቀትን ከመማር ቅድሚያ እንዲሰጠው የተለያዩ ምሳሌዎችን በመደርደር መክረዋል ። ◉አደብ የሌላው አዋቂ ከጃሒሎች አይሻልም ጀሒል ከሚያስከትለው ፊትና የባሰ ፊትና ያስከትላል። ➠አደብ ያለው ጃሒል ከስርዓት አልባው አዋቂ ነኝ ባይ አነብናቢ አላህም ጋ ሰዎችም ጋ በብዙ መልኩ የተሻለና የተወደደ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።
➦ከዐብደላህ ኢብኑ ሙባረክ ረሂመሁላሁ እንዲህ ብሏል ይባላል ፦
"الأدبُ يسترُ قليلَ العلمِ، والعلمُ لا يسترُ قليلَ الأدبِ، وفقدُهما عَراء، وجمعُهما ثَراء".
ስነምግባር ወይም አደብ ጥቂት እውቀትን ይሸፍናል እውቀት ግን ጥቂት የስነምግባር ጉድለትን አይሸፍንም። ሁለቱንም ማጣት መራቆት  ሲሆን ሁለቱንም መሰብሰብ ግን የላቀ ሀብት ነው።
➽የጨዋነትና  የጥሩ ስነምግባር ባለቤት የሆነ ሰው ለሰዎች የሚተናነስ መልካም ተግባቢነትን የተሰጠ ሰው እውቀቱ ትንሽ ብትሆንም ሁሉም ሰዎች ያከብሩታል የእውቀት ማነሱን መልካም ስነምግባሩ ይሸፍነዋል ። እውቀትን ሸምድዶ ብዙ የእውቀት ፈኖችን  ሰብስቦ የያዘ ቢሆን እንኳን ምግባረ ብልሹ ፣ ውሸታም ፣አጭበርባሪ ፣ሁለት ፊትና ምላስ ያለው ፣ ኩራተኛ፣ በሰዎች የሚያባላ እነ ልበ ደንዳና ከሆነ እውቀቱ ምንም አይጠቅመውም ሰዎችም ከሱ እውቀት ምንም አይጠቀሙም ። የስነምግባሩ ማነስ የእውቀት ደረጃውን በማርከስ በሰዎች አይን የቀለለ እነ ማላገጫ ይሆናል ። ➼አደብንና እውቀትን በማጣመር እንዋብ እንክበር ሁለቱንም በማጣት አንርከስ ! 📝#የቴሌግራም Channeሉን #join በማለት  #ይቀላቀሉ➷➷➷➷➷ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

"ስትጣላ ለእርቅ የሚሆን ትንሽ ቦታ አስቀር፣ በኃላ ለእርቅ  እንዳያስቸግር" ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተበራከተ የመጣው በሰለፍዬች መሀከል አለመግባባትን የሚያሰፍኑ ሴራዎችን ብሎም የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች በውስጥ መስመር ስውር በሆነ አደረጃጀት እየረጩ ያሉ ሰዎች አሉ።ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች ለየትኛው አቋም መረጃን ማስቀደም ግዴታ መሆኑ ከእናንተ የተሰወረ ጉዳይ አይደለም ምክንያቱም መንሃጀ ሰለፍ መሰረቱም መረጃ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለየትኛው በሰለፍይ ወንድምና እህቶች ላይ ለሚናፈሱ ፕሮፖጋንዳዎች ማስረጃን በመጠየቅ የፊትና አቀጣጣይ ከመሆነ መቆጠብ ይገባናል። እንደሚታወቀው ሰለፍዬች በሙብተዲዕዎች ላይ እንኳን አቋም የያዙት ለወደፊትም የሚይዙት በቂ ማስረጃ ላይ ተመርኩዘው እንደሆነ ሁለት ሰለፍዮች የማይጋጩበት ጉዳይ ነው።ስለሆነም በሰለፍይ ወንድሞች ላይ የሚደረግ ፍረጃዎች ሲገጥሙን ይበልጥ ጠንቃቃዎች በመሆን አላስፈላጊ አቋም ከመያዝ በፊት ነገሩን በማስረጃ ማጥራት አስፈላጊ ነው።ሰለፍዬች ከሃቅ ጋር ያላቸው ትስስር እጅግ የላቀ በመሆኑ ለሃቅ ብለው ማንንም ይተዋሉ ነገር ግን ለማንም ብለው ሃቅን አይተውም።ይህም ከሃቅ ጋር ያላቸው የላቀ ትስስር የተረጋገጠላቸው በሚከተሉት ሶስት የማያወላውል ጠንካራ አቋማቸው ነው: አንደኛ በበቂ ማስረጃ እንጂ በማንም ላይ አቋም ከመያዝ ይቆጠባሉ።ለዛም ነው ማንኛውም አካል ለሚያመጣላቸው ነገር አቋም ለመያዝ ማስረጃን አምጣ ብለው የሚይዙት። "قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ" (سورة البقرة آية 111) ሁለተኛ በቂና ተገቢ የሆነ ማስረጃን ከያዙ በኃላ ማስረጃው በሚያስፈርደው መሰረት ከሃቀኛው ጎን ይሰለፋሉ። "يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ" (سورة التوبة آية 119) ሶስተኛ በማስረጃ ላይ ተመስርተው በያዙት አቋም የወቃሽን ወቀሳ አይፈሩም። "وَلَا يَخَافُونَ لَوْمَةَ لَائِمٍ" (سورة المائدة آية 54) ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ መርሆች በአላህ እርዳታና ተውፊቅ ሰለፍዬች በየትኛውም ጉዳይ ላይ ለሚወስዱት እርምጃ ስኬታማ መውቂፍን እንዲይዙ አድርጓቸዋል። በማስረጃ ላይ ተመስርተው ለያዙት አቋም የትኛውም ፕሮፓጋንዳም ይሁን ውስጣዊ የተንኮልና የሴራ አደረጃጀት ከመውቂፋቸው አይነቀንቃቸውም።ይህም የሆነበት ምክንያት የአላህ እርዳታ ሃቅን ከያዙት ጋር መሆኑን በፅኑ ስለሚያምኑ ልባቸውን በዛ ላይ በመቋጠር ብርቱ ተወኩልን ስለሚጎናፀፉ ነው። ስለዚህም ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች ከላይ በጠቀስኩት መሰረት ሰለፍይነታችንን የሚጥስ ቂላወቃለ የሆኑ አሉባልታዎች ላይ አቋም በመያዝ በመጀመሪያ ነፍሳችንን እንዳንበድል ሲቀጥል ያለአግባብ ማስረጃ አልባ በሆነ አሉባልታ አቋም የምንይዝባቸው ሰለፍይ ወንድምና እህትን እንዳንበድል ከወዲሁ ለማስታወስ እወዳለሁ። ማወቅ የሚገባን ነገር ሰለፍያ የምትረዳው በፍትህና በተቅዋ ላይ በተመሰረተ እንቅስቃሴ እንጂ ግፈኛ በሆነች ፍርድ እና በሴራና በተንኮል ውስጣዊ አደረጃጀት አይደለም።በተለይም በየቦታው እየተስተዋለ የመጣው የሰለፍዬችን ደርስ የመበተን፣ የማጨናገፍ በውስጥ መስመር የማስጠንቀቅ ነገራቶች ላይ ቆም ብለን ልናስብ እና አላህን መፍራት ይኖርብናል።አላህን አንፈራም ከተባለ ግን መጨረሻው ያማረ ሳይሆን ኪሳራን ነው የሚያስከትለው እና ለህይወታችን ዋጋ እንስጥ። የእራሳችን አላስፈላጊ አካሄድ የግዜ ጉዳይ እንጂ እራሳችንን ጠልፎ እንደሚጥለን መዘንጋት የለብንም ምክንያቱም ይህ የአላህ ህግ ነውና: "اسْتِكْبَارًا فِي الْأَرْضِ وَمَكْرَ السَّيِّئِ ۚ وَلَا يَحِيقُ الْمَكْرُ السَّيِّئُ إِلَّا بِأَهْلِهِ" (سورة فاطر آية 43) የሀገራችን ሰዎች የሚሉት ነገር አለ: "ስትጣላ ለእርቅ የሚሆን ትንሽ ቦታ አስቀር፣ በኃላ ለእርቅ እንዳያስቸግር" ✍አቡ ሙዓዝ