cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ibn Awol

الحق يقال ولو كان مرا

Show more
Advertising posts
1 723
Subscribers
+924 hours
+317 days
+11730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የከሸፈው ኢብን ሙነወር ሰለፊዮችን በመረጃ መጋፈጥ ያቃተው የሙመይዓዎች ቀንደኛ ጠበቃ ኢብን ሙነወር ሰለፊዮች ላይ መቅጠፍን ቀጥሎበታል።ሚያነሳቸው ነጥቦች እዚህ ግቡ ባይባሉም ዝም ሲባሉ ጃሂሎች እንዳይሸወዱ ኣንድ ኣንድ ነጥቦች ለማየት ወደድኩ። 1ርእሱ"በለተሞ መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋቹህ" ይላል ↪️ኢሄ ሙሪዶቹን ለማስደሰት የሚጠቀመው ቃል ነው።እንጂማ ለተሞ የሚባል ቡድን ዬለም።ኣለ ካለ ሰለፊያን የተፃረሩበትን መሠረታዊ ነገሮችን ይጥቀስ።ምንም ኣይነት የተፃረሩት ነገር ከሌለ ግን ሰዎችን ያለ አግባብ ቅፅል ስም እየሰጡ ማነወር የቢደዓ ባለቤቶች አካሄድ ነው። ሌላው "የምርቃና ስብከት"ያልከው ሼኽ አብድል ሃሚድን አይደለም ወዳጆቻቸው ጣለቶቻቸውም ደዕዋቸው በቁርኣንና በሀዲስ የታጨቀ መሆኑን ያውቃሉ።ሌዬትኛውም አቋማቸው ሰዎች በቃን እስከሚሉ ድረስ መረጃ ያቀርባሉ ።ኢሄ ላንተ ምርቃና ከሆነ የመረቀንከው ኣንተ ነህ። 2ኛ"እነዚህ ሰዎች የመንሃጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣...ስለሆነ የመንሃጅ ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ"ይላል። ↪️ለዚህ"የመንሃጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ"ለሚለው ሙግትህ ኣንድ መረጃ እንኳን አለመጥቀስህ ለተከታዮችህ ያለህን ንቀት ያሳያል፣እንዴት ኣንድ መረጃ እንኳን አትጠቅስላቸውም?፣እነሱስ(ተከታዮቹ) እስከ መቼ ነው በዚህ አቅሉ በምቀኝነት በታወረ ሰውዬ ቅጥፈት ምትነዱት?፤ለምን መረጃ አትጠይቁትም?። ቀጠለና እንዲህ ኣለ"ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብን ባዝ፣አልባኒይ.....ኪታቦችና ድምፅ ቂጂዎች ተጠቀሙ"። ↪️ጥሩ ነው ነገር ግን እኛም እንጠይቅ እስቲ።እነዚህ የጠቀስካቸው ኡለሞች ዬቱ ጋር ነው መጀመሪያ የነበራቸው ጠንካራ አቋም የቀየሩት?፤ዬቱ ጋር ነው ጀርህና ተእዲል የኢጅቲሃድ መስኣላ ነው ያሉት?፤ዬቱ ጋር ነው ከኢኽዋን ጋር ኣንድ ሁኑ ያሉት?፤ዬቱ ጋር ነው ለመስጂድ ብላቹህ አቋማቹን ቀይሩ ያሉት?፤ዬቱ ጋር ነው የቢደዓ ባለቤቶችን ማወደስ ችግር ዬለውም ያሉት፤ዬቱ ጋር ነው ከቢደዓ ባለቤቶች የሚያስጠነቅቁ ሰዎችን ቡድንተኛ ያሉት?። ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች የሰለፎች አቋም ምን ነበር?፤ሰለፎቻችን እኮ አይደለም ከቢደዓ ባለቤቶች ሊተባበሩ የቢደዓ ባለቤቶችን ሲያዩ መንገድ ይቀይሩ ነበር፣ከነሱ ኣንድትን የቁርኣን አንቀፅ እንኳን ላለመስማት ጆሮዎቻቸውን ይይዙ ነበር፣ሙብተዲዕን ያወደሰ አካል እስልምናን በማፍረስ ላይ ተባብሮዋል ይሉ ነበር...አረ ስንቱ ይጠቀሳል፣ታዲያ ለተከታዮች ዬትኛውን የሰለፎች አካሄድ እንዲያዩ ነው ምትመክረው?። ሌላው ኡለሞችን ስትጠቅስ ምነው እነ ሼኽ ረቢዕን፣ሼኽ ኡበይድን፣ሼኽ ሙሀመድ ብን ሃዲን....ረሳሃቸው?፤ወይስ ከነሱም እያስጠነቀክ ነው?፤እውነታው ግን የነሱ ኪታቦችና ደርሶች የናንተን ቁስል ስለሚነካኩ ነው። 3ኛ"ደእዋቹህ አካባቢያቹህን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን....። ↪️ኣዎ ልክ ነህ ደእዋዉ አካባቢውን ያማከለ መምሰል ኣለበት፣አካባቢው ላይ ሺርክ ካለ ስለ ሺርክ ይወራል፣ሙመይዓ ካለ ስለሙመይዓ ይወራል፣አረ ሙመይኣዎች አካባቢው ላይ ባይኖሩም ይወራል።ኣንተም የፈለከው ስለ ሙመይኣዎች አታውሩ ለማለት ነው።ሲጀመር ሙመይዓዎች የሌሉበትን አካባቢ መጥቀስ ከባድ ነው፤ዬሉም እንኳን ቢባል ሰዎች ፊትናቸውን ቀድመው እንዲያቁና እንዲጠነቀቁ ቀድሞ ማስጠንቀቁ ተገቢ ነው፤ኢሄ ሚያሳየው በመንሃጅ ላይ ያለህ አቋም ምን ያህል እንደወረደ ነው።ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ከደጃል ያስጠነቀቁት እኮ ደጃል ገና ሳይመጣ ነው፣ከኸዋሪጆችም ያን ሁሉ ያስጠነቀቁት እነሱ ገና ሳይመጡ ነበር። "ከሁሉም አትላተሙ"ላልከው ደሞ ↪️ሀቅ የያዘ ሰው ከባጢል ጋር መላተሙ ማይቀር ጉዳይ ነው፤ኢሄ የአላህ ሱና ነው።የአላህ መልእክተኛም"ከኔ ኡማ ኣንዲት ቡድን ኣለች እስከ ቂያማ ድረስ ሀቅ ላይ ከመሆን አትወገድም፣የተዋትና ያዋረዳት አይጎዳትም"ብለዋል። ኣንተ የፈለከው ግን መንሃጅ ብታቁም አትስሩበት ነው፣ልክ እንደእኛ አውቀናል በሉ ግን አትስሩበት፣ዝም ብላቹህ ሰለፊዮችን አዛ አድርጉ ነው ለማለት የፈለከው። "እነሱን ተከትላቹህ ደዕዋቹህ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋለ ይመልሳቹሃል"ላልከው ↪️የሰለፊያ ደእዋ ካማረባት ቦሃለ ወደ ኋለ ለመመለስ የሞከረው ማነው?፤እንደዛ የመርከዙ ሰዎች እያልክ እየሰደብክ ጆሮዎቻችንን ካደኖቀርክ ቦሃላ መልሰህ ጠበቃ የሆንከው ኣንተ አይደለህም እንዴ?፤እነዚን ሰዎች ሲቀበሉም ሲሰጡም አናምናቸውም ካልክ ቦሃላ ጓደኛህ ከነዚህ ሰዎች ጋር ኣንድ ከምሆን አሞራ ይብላኝ ካለ ቦሃላ መልሶ እኛ ልጅ ነን እነሱ በእድሜ የበሰሉ ናቸው ብሎ ወደ ኋላ የሸሸው ማነው?።ችግሩ ሙሪዶችህ ኢሄንን እንኳን አያስታውሱህም። 4ኛ"ከለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጊዶቻቹሁን ያሳጣቹሃል" ↪️እንዲህ ነው መውረድ፣እንዲህ ነው መቅለጥ።እኛ አስካሁን ምናቀው ከነ ኤገሌ ጋር አቲሂዱ ቢደዓ ውስጥ ትወድቃላቹህ፣ከነ ኤገሌ ጋር አቲሂዱ ሽርክ ውስጥ ትወድቃላቹህ ነበር።ተመልከት ኢሄ የኢኽዋን አህያ ምን እንደሚል።በተዘዋዋሪ እኮ መስጊድ እንድታገኙ ከኢኽዋንና ከሱፊያ ጋር ኣንድ ሁኑ፣ለመጅሊስ እውቅና ስጡ እያለ ነው።እንጊዲህ እስካሁን ሰለፊዮች የራሰቸው መስጊድ እንዳይኖራቸው ሲደረግ የነበረው በእንደዚህ አይነት ሴራ ነው።ሰለፊዮች ከነዚህ ሰዎች ከተለያዩ ቦሃላ ግን በየ ቦታው የራሳቸውን መስጊድ ሰርተዋል። ቀጠለና"ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫቹሃል"ይላል ↪️አዎ ወንድሜ ያ ማህበረሰብ ችግር ካለበት ችግሩ ሲነገረው መከፋቱ ማይቀር ነው።ያ ማህበረሰብ ግን ችግር ከሌለበትና ሀቅን ከተቀበለ እንደ ሰለፊዮች ሚወደው ዬለም።ለዚህ ምስክርነት ከፈለክ ኣንተ ጠበቃ የሆንከላቸውን የመርከዙን ሰዎች በየ ቦታው ምን እንደሚያደርጉና ማህበረሰቡ የሰለፊያ ኡስታዞችን እንዴት እንደሚወድ ጠይቃቸው።እነ አህመድ ኣደም ኩተሬ አካባቢ ላይ በሰለፊዮቸ ላይ ሚሰሩትን ደባ እነ ማህበረሰቡ ምን እንደሚያደርግ ደውለህ አረጋግጥ። 5ኛ"የአካባቢያቹሁን መስለሃ ራሳቹህ ወስኑ።በሩቅ ያለ ሰው ያላቹሁበትን ተጨባጭ ላያቅ ይችላል"ይላል ↪️ከዚህ በፊት የኛ ኡለሞች እያሉት የነበረው እኮ ኢሄን ነበር፣እናንተ ናቹህ ስለ ኢብን መስኡዶችም ስለ ሼኽ አብድልሃሚድም ምንም ማያቀውን ባሙሳን አምጥታቹህ ከነበራቹሁበት ጠንካራ አቋም አንሸራቶ ለዚህ ያበቃቹህ።ሌሎችንም አምጥታቹህ ስታጨማልቁ ነበር።እናም በዚህ ምክርህ እራስህ ብትሰራበት ኖሮ ለሙመይዓዎች ጠበቃ አትሆንም ነበር። ቀጠለና"እነዚህን ሰዎች አታማክሩ ላራሳቸውም አይሆኑም"ይላል ↪️ ሲጀመር አማክረን ያለህ ኣንድም ሰው ዬለም።እየተባልክ ያለው ለሙብተዲዕ ጠበቃ አትሁን፣ወደነበርክበት አቋም ተመለስ ነው። ↪️"ለረሠሳቸውም አልሆኑም"ያልከው ግልፅ ውሸት ነው፣ኡለሞቻችን ደእዋውን እየመሩት ያለው መጅሊስን ወይም ሂዝቢዮችን አማክረው አይደለም። ቀጥሎ የጠቀሳቸው ተራ ክሶችና አሉባልታ ናቸው።የሙሪዶቹን ልብ ከማሞቅ ያለፈ ነገር ዬለውም።ኣንድም የጠቀሰው መረጃ ዬለም።በሱ ጊዜዬን አላጠፋም። ስድስተኛው ክስም መሠረተ ቢስና እራሱ እንኳን ከዚህ በፊት ከፃፈው የሚፃረር ነው።ኢዚሁ ቻናሌ ላይ ከላይ ኢብን ሙነወር የድሮ አቋሙ የሚል ፁሁፍ ኣለ አንብቡት። ሌላው በአህሉል ቢደዓ ላይ መማርና ከአህሉል ቢደዓ አብሮ መስራት የሚሉትን ነጥቦች ለመደበላለቅ ሞክሮዋል።ኢሄ እንደዚህ ኣይነቱ አካሄድ ቡዙ ግዜ ርእስ ለመመስቀየር የሚያደርገው ጥረት ነው።እስካሁን ኡለሞቻችን ማንንም በአህሉል ቢደዓ ነው የተማረው ብለው ከሱና አላስወጡም።እሱ ግን አሁንም እየከሰሰን ነውt.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll
Show all...
ዛፎች አለቁና ቁጥቋጦች ተሰለፉ! ~ ኢኽዋን ዋሸ ዋሸ ስልጣን ወንበር ላይ ቀጭ ሲል ዚም ሙመይዓ ዋሸ ዋሻ ወንበር ላይ ቁጭ ሲል ዝም አሁንስ ሰለፊዮች ላይ ማን ይዋሽ? መልሱ ኢብኑ አእወር ~ ሸይኽ አብዱል ሐሚድ መጅሊስ ውስጥ ገባ ብሎ ይዘምር የነበረው መንጋ አሁንስ እና የቅጥፈት ቀፎ  የኢኽዋን ዲልዲይ ኢብን ሙነወር እና የሚጋልባቸው መንጋዎች ምን ይላሉ? የሚናገሩት ለአሏህ ከሆነ የሚቀጥለው አማረጭ ግድ ነው ። 1,ኛ ነፍሲያን ጥሎ የተናገርኩት እና የፀፋኩት ያልተረጋገጠ ወሬ ሰምቼ ነበር አሏህ ይቅር ይበለኝ ብሎ ሸይኹን ይቅርታ መጠየቅ ነው ። ይሄንን ቢሞት የሚያረገው አይመስልም እሱ ልክ በሸህ ላይ ብቻ ዋሽ ቅጠፍ በሆነ ባልሆነ መረጃ ሰውን ለማስበርገግ ታገል ጀነት ትገባል የተባለ ይመስላል ። 2, ኛ እሱ ዝም ስላለ ነበር የተናገርኩት የማምናቸው ወንድሞችም ፅፈው አግንቻለው ነው ¡  የራሷን አበሳ በሰው አብሳ : እንደሚባለው አለባባሶ መፈርጠጥ ነው ይሄም አያዋጣህም የምያምንህም የለም ። 3,ኛ አማራጭ ባልሰማ ባላየ መቼም በዚህ ውሸት እና ቅጥፈት አራጋቢነቱ እንደማይያዝ ሆኖ መቀጠል ነው የተለመደውም ይሄ ነው ብዙ ግዜም ተመልስኩ የሚል ነገር የለም በራሱ ላይ አደጋ ካላወቀ በስተቀር ~ መልዕክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ وَمَنْ خَاصَمَ فِي بَاطِلٍ وَهُوَ يَعْلَمُهُ لَمْ يَزَلْ فِي سَخَطِ اللَّهِ حَتَّى يَنْزِعَ عَنْهُ، وَمَنْ قَالَ فِي مُؤْمِنٍ مَا لَيْسَ فِيهِ أَسْكَنَهُ اللَّهُ رَدْغَةَ الْخَبَالِ حَتَّى يَخْرُجَ مِمَّا قَالَ ". በውሸት አውቆ የተሟገተ ከተሟገተበት ነግር እሰከ ሚወጣ ድረስ ከአሏህ ቁጣ አይለይም በሙዕሚን ላይ ያሌለበትን የተናገረ የጀሀነም ሰዎች እዥ መሰብሰቢያ ውስጥ አሏህ ያኖረዋል ከተናገረው ነገር እሰከ ሚወጣ ድረስ አሉ ። ሀዲሱ ወይስ አይመለከተውም እንዲያውም በመላ ፈስ ዳልቻ ነው አሉ ። በመላ ብቻ የሚደነፋው ኢብን ሙነወር ጉድ አያበቃም ። ያገኘውን ሁሉ ለውሸቱ እና ለሚሟግትላቸው አካሎች ሲል መለቃቀም እና እንደ እብድ ውሻ አዲስ አባባ የመን ከየመን ሰዑዲ ከስልጤ ወደ ጉራጌ ከጀመዓ ወደ ግለሰብ መናከስ የተለመደ ነው ። *~ 4, ኛ አይ ጥያቄ ባያቀርብ ወይም በውስጥ ባይገናኝ ስሙን አሳፍሩትም ነበር የሚል ክስ መምዘዝ ለውሸትህ መልስ ባይሆንም ለድንቅርናህ እና ለጭፍን ጥላቻህ ምልክት ነው ። ከዚህ በፊት እና ኣደም ካሚል ኡለማ ባይሆኑም እነ ሳዳትንም ጠርተናል ሲል ከዚህ ተመሳሳይ ንግግር ሲናገር ለፖለተካ ነው ብንኖርም ባንኖርም ሊጠቀሙበት ነው ሲል በያን ሰጥቶ ነበር ከሰለፊዮችም አንድም ሰዳትን ለምን ጠሩት የሚል ክስ ያቀረበም አልነበረም ሴራቸውንም ስለምናውቅ ። በዛ ክስ በራሱ ግን ሸይኽ አብዱልሐሚድን ዛሬ መክሰስ ምን ይሉታል እናንተስ በዚህ ጎዳይ እንደፍያል ሜ, ከማለት ቆም ብሎ ማሰብ አይሻላችሁም ለነገሩ ካህያ የዋለች መጋጥ ያምራታል ዝም ብሎ መጋጥ ነው  ! የፈለከውን ብታደርግ ያው አንተ ነህ ምንም ብታፈገፍጊ ከግድግዳ አታልፊም ! الولد للفراش وللعاهر الحجر! https://t.me/abuabdurahmen
Show all...
የኢብን ሙነወር ኑዛዜ ለጊዜው ብዙ ማለት አልፈለኩም።ለቸከቸከው ፁሁፍ ለእያንኣንድ በዝርዝር መመለስ ይቻላል።ነገር ግን አሁን የፈለኩት የሙሪዶቹ ደስታ ላይ ውሃ መቸለስ ነው። ኢብን ሙነወር በፃፈው ፁሁፍ ከመደሰታቹህ በፊት ኣንድ ጥያቄ ጠይቁት። ጥያቄውም፦ ዛሬ ያስጠነቀካቸው ሰዎች ከመንሃጅ አሰለፍ የጣሱት(የኻለፍት) መሰረታዊ ነገር ምንድነው? እነሱ የጣሱት መሰረታዊ ነገር ካለ እየጣቀስክ ብትነግረን ብላቹህ ጠይቁት። ከሌለ ግን ሀገራችን ላይ ኢሄ ሁሉ ሙብተዲዕ እያለ ኣንተ ሌት ተቀን ስለ እነሱ ምታወራው ለምንድነው? የዛሬውን ፁሁፍን ሳነብ ኣንድ ህፃን ልጅ በጉልበቶኞች ከተመታ ቦሃለ እንደሚያለቅስና እንደሚሳደበው አይነት ነው የመሰለኝ።ኢሄ ህፃን ከነዚህ ጉልበተኞች የሚታገልበት አቅም ዬለውም፣ያለው አማራጭ በነሱ ከተመታ ቦሃላ እያለቀሰ መሄዳቸውን አይቶ መሳደብ ነው። ኢብን ሙነወርም ከመሻይኾች ጋር የሚጋፈጥበት ኣንድ ማስረጃ ዬለውም።ያለው አማራጭ ሙሪዶቹን ለማሳመን ኡለሞችን መሳደብና በነሱ ላይ መቅጠፍ ነው። ሙሪዱም ጥያቄ አይጠይቅም።በዚህ ጉዳይ የሰለፎች አቋም ምንድነው ብሎ የጠየቀ ሙሪድ እስካሁን አላዬንም። በነገራችን ላይ ሰሞኑን የኢብን ሙነወር የድሮ አቋሙ ብዬ በለቀኳት ፁሁፍ መልስ ለመስጠት ሞክሮዋል።እንደውም ፁሁፉን የፃፈው በሷ ተናዶ ነው መሰለኝ። t.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll
Show all...
Ibn Awol

الحق يقال ولو كان مرا

02:27
Video unavailableShow in Telegram
👆 ድንቅ መልስ 📌 ሼህ ሱለይማን አሩሀይሊ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ ፡ ኣንድ ኣንድ ሰዎችከቢዳዓ ባለቤቶች ጋር ይቀማመጣሉ ሲከለከሉ ደሞ አላህ ሀቅ እና ባጢልን ምለይበት አእምሮ ሰቶኛል ጥሩጥሩውን እይዛለው መጥፎውን እተዋለው ይላሉ እርሶስ ምን ይላሉ ተባሉ 🦿ሼሁም እንዲህ ብለው መለሱ ፡ አላህ አእምሮ ቢሰጥህ ኖሮ ከነሱ ጋር ባልተቀመጥክ ነበር ኢሄ በጊዜያችን ያለ ትልቅ የሆነ ሸር ነው ወላሂ እኔ ምርጥ የሱና ሰዎች የነበሩ በዚህ ጉዳይ ተሳሁል ውስጥ ገብተው ከቢዳዓ ባለቤቶች ጋር ተቀማምጠው ሙሉ በሙል ተገልብጠዋል. ....ሙሉውን ያዳምጡት ለተጨማሪ ት/ቶች ይህን ይጫኑ👇👇 t.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
📢 አስደሳች የደርስ ዜና በዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም ቻናል ቀጥታ ስርጭት Online ከዚህ በፊት በዳር አስ-ሱንና በአካል ሲሰጡ የነበሩ ደርሶችን ሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን፣ ኡሱል አስ-ሱንናን በፅሁፍ ሸርህ እያደረጉ ስለነበር ወደ ሀገር እስኪመለሱ በonline መቀጠል አልቻሉም ነበር፣ አሁን ግን ሸርሁን አጠናቀው لزوم السنة في شرح أصول السنة በሚል ርእስ ያጠናቀቁት ሲሆን እነሆ እስኪታተም በpdf ተለቆ ደርሱም እስኪመጡ በነበረበት በ online በተለመዱ ቀናት ጁምዐህ፣ ቅዳሜ፣ እሁድ ከምሽቱ 3:00 ላይ የሚቀጥል መሆኑን ከታላቅ ደስታ ጋር እናበስራችኋላን። በተመሳሳይ كتاب صحيح البخاري ከነገ ጀምሮ ጁምዓ ከተሰገደ በኋላ ዘውትር ጁምዓህ ጁምዓህ በነበረበት ወደ ሀገር እስኪመለሱ በ online ይቀጥላል። بشيخنا الدكتور حسين بن محمد السلطي حفظه الله በሸይኻችን ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ) የሚጀመርበት የነገው ጁምዐህ ግንቦት 16 መሆኑን እየገለፅን ለሁሉም እንዲዳረስ #ሸር_share በማድረግ የመልካም ስራ ተካፋይ ይሁኑ! ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
Show all...
👆👆👆👆👆👆👆 ⭕የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ📢 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሙስሊም  ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም(በአኺራ) የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል። 🔥በመሆኑም ተማሪ አህመድ እስሌማን በባህር_ዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና 5ኛ አመት ተማሪ (የዘንድሮ ተመራቂ፦ ማለትም የ2016 E.C) ሲሆን ባደረበት ህመም በባህር_ዳር ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሲረዳ ቢቆይም ህመሙ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እንዲታከም ሪፍር ተፅፎለት ምርመራውን አድርጎ በደም ካንሰር (Leukemia) መያዙ ስለታወቀ ካንሰሩ በፍጥነት ካልታከመ ባጭር ግዜ የሚያድግ እና ህይወቱን አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ ባስቸኳይ ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ መታከም እንዳለበት በሀኪሞቹ ተወስኗል በመሆኑም ለህክምናው ከ 2 ሚልዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተብሉዋል ። ይህንን የተጠየቀውን ገንዘብ ወጪ በቤተሰቦቹ አቅም የሚሸፈን ስላልሆነ በቤተሰቦች ላይ አስቸጋሪ ሁኖ ተገኝቱዋል ። በመሆኑም ውድ ወንድምና እህቶች ፣ ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለዲኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን  የአቅማቹህን እንድታበረክቱ  ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች  የእርዳታ ጥሪያችንን በአላህ ስም እናስተላልፋለን። ወንድማችን አህመድን ለመርዳት        👇የባንክ አካውንት ስም 👇 ➕TAJU ESILEMAN MUHAMMED 1⃣የንግድ   ባንክ አካውንት ቁጥር :- 1000455535647 (CBE) 2⃣የአቢሲኒያ ባንክ አካውንት ቁጥር፦ 43148117 (ABSINIYA) 3⃣የአዋሽ ባንክአካውንት ቁጥር ፦ 01425778677200 👉በገንዘብ መርዳት ባትችሉ #share በማድረግ እንተባበረው ። "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም(በአኺራ) የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ። ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች እና ግሩፖች ሼር እንድታደርጉልን በአላህ ስም እንጠይቃለን ።
Show all...
🟢የቀለጠው ሙሀመድ ሰኢድ 1⃣ ❓ስለ ዶ/ር ጀይላን አቋም ግለፁልን ኢኽዋኒ ናቸው ወይስ ? "እእእእእ ዶ/ር ጀይላን ..." 👉የድሮውን ነሻጣና አቋም ከአሁኑ መርበትበትና ተልቢስ ጋር አነፃፅሩት። ጭፍን ተከታዮቾ ሆይ: 👉ሰዎቹ ደዕዋቸውን ሽጠው ይህን የመሰለ ግልፅ መንሸራተትና መቅለጥ እያየንባቸው አልተቀየሩም እያላችሁ በአቅላችሁ እና በዲናችሁ አትጫወቱ?! https://t.me/Abuhemewiya
Show all...
የኢብን ሙነወር የድሮ አቋሙ እንዲህ ነበር ።የሱ ተከታዮች ይህንን ምክሩን በደንብ ተቀበሉት።ዛሬ ላይ በምቀኝነት ታውሮ ሰዎች ላይ ስለቀጠፈ ብቻ ሀቅን የያዘ እንዳይመስልህ። ይህ የሱ ፁሁፍ ነው👇👇አንብቡት "ተመይዩዝ"— ትኩረት የተነፈገው ሐቅ የሰለፍያ ደዕዋ አንዱ መታወቂያ ተመይዩዝ ነው፣ የዐቂዳ ልዩነት ካላቸው አፍራሽ ሃይሎች ጋር አለመጋፋት። እራስን ችሎ መቆም። መልለየት። ዐቂደቱል በራእ ከካፊር ጋር ብቻ አይደለም፣ በኢስላም ስም ከሚንቀሳቀሱ የጥመት አንጃዎችም ጭምር እንጂ። ባይሆን ሚዛን ትጠብቃለህ። ማለትም ከነሱ አንፃር የሚኖርህ አቋም ባለባቸው ጥፋት ልክ ይሆናል ማለት ነው። እንጂ ሚዛን ትጠብቃለህ ማለት ትላንት ከነበረህ አቋም ትንሸራተታለህ፣ ትላንት ስታወግዛቸው የነበሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይመለሱ ታደንቃለህ ማለት አይደለም። ሚዛን ትጠብቃለህ ማለት መሰረታዊ የአህሉ ሱንና አቋሞችን ለድርድር ታቀርባለህ ማለት አይደለም። ይሄ ግልፅ ነው። ተመይዩዝ ብዙ ትርፍ አለው። ለምሳሌ ያክል ① ተመይዩዝ አብሮ በመሰለፍ ሊከተል ከሚችል የአቋም መሟሸሽ ያተርፋል። መቼስ በጋራ መድረክ ላይ ሙብተዲዖችን ማውገዝ አይቻልም። ② ተመይዩዝ ወደ ሙዳሀና (መመሳሰል) ከመውረድ ይጠብቃል። አብረህ ስትሆን ግን "እከክልኝ ልከክልህ" ፖሊሲ በቦታው ይነግሳል። ③ ተመይዩዝ ተራው ሙስሊም ዘንድ በአህሉ ሱንና እና በቢድዐ አንጃዎች መካከል ያለው ልዩነት በግልፅ እንዲታይ ያደርጋል። አብሮ መጓዝ ሲኖር ግን የአቋም ልዩነቶችንም፣ ጤነኛና በሽተኛ አካሎችንም መለየት አይቻልም። ይሄ ከባድ አደጋ ነው። ለምሳሌ ከኢኽዋኖች ጋር ብትሰለፍ ሙስሊሙን በጅምላ የሚያከፍረው፣ ሶሐባ የሚያብጠለጥለው፣ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብለውን ሰይድ ቁጥብ ሲያወድሱ ያንተም አቋም ተደርጎ እንዲታሰብ ያደርጋል። ④ ተመይዩዝ የጥፋት አንጃዎችን ጭፍራ ከማድመቅ፣ ሃይላቸውን ከማጠናከር ያቅባል። ⑤ ተመይዩዝ ለአህሉ ሱንና የጥንካሬ መንሰኤም ነው። ከቢድዐ አንጃዎች ጋር አብረህ የምትሰለፍ ከሆነ ሃይላቸው ሀይልህ፣ ህብረታቸው ህብረትህ እየመሰለህ በከንቱ ትደክማለህ። ከነሱ ተነጥለህ እራስህን ችለህ ስትቆም ግን መፍተሄ የምትፈልገው፣ አንድነትህን የምታጠናክረው ከመሰሎችህ ጋር ነው። መሰረታዊ መርሆዎችህን ሊንድ ከተሰለፈ አካል ጋር ሆነህ ደካማ ጎንህን አታሳይም። ሴራ ለሚጠነስሱ አካላት እራስህን አታመቻችም። ተመይዩዝ ማለት እራስን ከማህበረሰብ ማግለል አይደለም። ስለ ተመይዩዝ ስናወራም ከማህበረሰብ ወደ ማግለል እየተጣራን አይደለም። ይሄ የተክፊሮች አካሄድ ነው። ተመይዩዝ ከህዝብ ሳይሆን ከቢድዐ ተጣሪዎች እራስን ማግለል ነው። ያለ ተመይዩዝ የሱንናን የበላይነት እውን ማድረግ አይቻልም። ይህ የሱንና ዑለማዎች አቋም ነው። ለምሳሌ ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– ولن تقام سنة رسول الله صلى الله عليه وعلى آله وسلم إلا بالتميّز، "የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወዐላ ኣሊሂ ወሰለም ሱንና በመልለየት እንጂ አትቆምም።" (ቱሕፈቱል ሙጂብ: 85) «وننصح أهل السنة أن يتميزوا …، فإنّهم لن يستطيعوا أن ينشروا سنة رسول الله صلى الله عليه وعلى آله وسلم إلا بالتميّز وإلا فالمبتدعة لن يتركوهم ينشرون السنة» اهـ «تحفة المجيب على أسئلة الحاضر والغريب» (ص: 208) "የሱንና ሰዎችን የምንመክረው እንዲለዩ ነው። … ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወዐላ ኣሊሂ ወሰለም ሱንናን በመልለየት እንጂ ሊያሰራጩ አይችሉምና። ካልሆነ ግን ሙብተዲዖች ሱንናን ሲያሰራጩ አይተዋቸውም።" (ቱሕፈቱል ሙጂብ: 208) « وأنصح الإخوة السلفيين أن يبتعدوا عن هؤلاء الحزبيين، لأنّهم لا يريدون إلا تكثير سواد حزبهم. "ሰለፊ ወንድሞቻችንን ከነዚህ ቡድንተኞች እንዲርቁ እመክራቸዋለሁ። ምክንያቱም ጭፍራቸውን ማብዛት እንጂ አይፈልጉምና።" (ቱሕፈቱል ሙጂብ: 117) ጌታችንም እንዲህ ብሏል:— وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنْصَرُونَ_ [هود: 113] "ወደነዚያም ወደበደሉት አትጠጉ። እሳት ትነካችሁዋለችና። ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም። ከዚያም አትረድዱም።" (ሁድ: 113) የዚች አንቀፅ መልእክት ከሃዲዎች ላይ የተገደበ እንዳልሆነ ይልቁንም ሙብተዲዖችንና ሌሎች ወንጀለኞችንም እንደሚያካትት ቁርጡቢ ይገልፃሉ። አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልገጠሙ በስተቀር ይሄ ከአጥፊዎች መራቅ ቋሚ ህግ ነው። ባይሆን አስገዳጅ ሁኔታ ማለት ተጨባጭ ምክንያት እንጂ ያልተረጋገጠ ሰበብ፣ የተለጠጠ ምኞት፣ ስብስባዊ ፍላጎት አይደለም። ✍ibn munewor ዱሮ እንዲህ ያለ የነበረውን ሰውዬ ዛሬ ተከርብቶ እያዬሀው በጭፍን ምትከተለው ከሆነ ኣንተ ስለ መንሃጅ አሰለፍ ድጋሚ ቁጭ ብለህ ልትማር ይገባል። t.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll
Show all...
Ibn Awol

الحق يقال ولو كان مرا

👉 አዲስ pdf عنوان:- أسباب الخشوع في الصلاة ولذة المناجاة وموانعها.pdf በሶላት ውስጥ ኹሹዕ የማግኛ ሰበቦችና ከአላህ ጋር በሚመሳጠሩበት ወቅት ልዩ ጠዕም ማግኛ መንገድና ከልካዮቹ بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله السلطي حفظه الله ✍🏻አዘጋጅ:- የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና በቅርብ ወደ አኼራ የሄዱት የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም ተማሪ በሆነው በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ ቴሌግራም ቻናል ⤵️ https://t.me/HussinAssilty (ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Show all...
00:39
Video unavailableShow in Telegram
🎤 ወላሂ ወሰጢያ ማለት ዲንን ማሟሟት አይደለም፡፡ ወሰጢያ ማለት ከነቢዩ የፀደቀ ሱና ማለት ነው፡፡ የትም ቦታ ሱናን ካገኘህ በሱም ላይ ከፀናህ ሙተሸዲድ ብትባልም እንኳን ኣንተ ወሰጢይ ነህ፡፡ 🎙በሼህ ሱለይማን አሩሀይሊ t.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll t.me/ibnawolllll
Show all...