ተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት
前往频道在 Telegram
''ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዛኋችሁንም ሁሉ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው'' contact : 0111 23 99 96 Facebook : @temromastemar YouTube : https://www.youtube.com/channel/UCZI9ztt_MA_dRnqGH6PTCvw
显示更多1 778
订阅者
+324 小时
+67 天
+930 天
帖子存档
1 778
ማሳሰቢያ!
ለማኅበሩ አባላት በሙሉ!
በቅድሚያ እንኳን ለምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ቅዳሴ ቤት ለሚከበርበት እና የመድኀኔ ዓለም ታቦት ለሚነግሥበት ብቸኛ ዓመታዊ በዓላችን አደረሳችኁ፡፡
ኹላችኁም እንደምታውቁት ይኽ በዓላችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዓን አባቶቻችን ሊቃነ ጳጳሳት ጭምር የሚገኙበት፤ ከተለያየ ስፍራ የሚመጡ ምእመናን ተገኝተው የሚባረኩበት፤ እኛም በጉጉት ነጭ ልብሳችንን ለብሰን በዝማሬ እና በእልልታ ከቤተሰቦቻችን ጋር ውዳሴ የምናቀርብበት ብቸኛ እና ልዩ በዓላችን መኾኑ ይታወቃል፡፡
ስለ ኾነም በዓለ ንግሡ በተያዘለት መርሐ ግብር እንዲካሄድ፤ ለተመደቡ አስተናባሪዎች ፍጽምት በኾነች ፍቅር በመታዘዝ፤ ከታቦቱ የሚገባውን ርቀታችንን በመጠበቅ፤ በመድረክ ላይ ለሚካሄዱ መርሐ ግብሮች፤ ለብፁዓን አባቶቻችን ሊቃነ ጳጳሳት እና እንግዶች ዋናውን መድረክ በመልቀቅ፤ ለሚመጡ እንግዶች ቅድሚያውን በመስጠት በዓለ ንግሡን እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
++++++++++++++++++++++++
አባታችንና አምላካችን ቸሩ መድኀኔ ዓለም በዓሉን የሰላም፤ የበረከት እና የፍቅር ያድርግልን፡፡
++++++++++++++++++++++++
1 778
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
