ተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት
Ir al canal en Telegram
''ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዛኋችሁንም ሁሉ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው'' contact : 0111 23 99 96 Facebook : @temromastemar YouTube : https://www.youtube.com/channel/UCZI9ztt_MA_dRnqGH6PTCvw
Mostrar más1 935
Suscriptores
-224 horas
-67 días
+1230 días
Archivo de publicaciones
1 935
የተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት አባላትወርሃዊ መዋጮአችሁን በአካል መገኘትም ሆነ ወደ ባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባችሁ በCBE Mobile Banking እና CBE Birr በተዘጋጀው የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ከጥቅምት ወር ጀምሮ መክፈል የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቋል። ይህ አሰራር ደረሰኝ መያዝ ፣ በአካል መገኘት ሳያስፈልግ ክፍያን በዲጂታል አማራጭ መከታተል የሚያስችል አጋዥ System ነው። በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀደም በአካል በእሁድ ጉባዬ የተሰጠውን ሆነ በOnlineም የተቀመጠውን ቅጹ ሞልታችሁ በSMS ኮድ እና ወርሃዊ መዋጮ የተላከላችሁ አባላት ስምና የመዋጮ መጠናችሁን አረጋግጣችሁ መክፈል የምትችሉ ሲሆን፤ አከፋፈሉም እንደሚከተለው ይከናወናል፦
📲 በ CBE Mobile Banking (App / USSD) ለመክፈል፦ Log in ➔ Pay for ➔ School Fee ➔ Henon School Payment በ SMS የተላከውን Payment Code / Master ID ያስገቡ። ስምና መጠን አረጋግጣችሁ ይክፈሉ። 📲 በ CBE Birr (App / USSD) ለመክፈል፦ በ SMS በሚላክላችሁ የ CBE Birr የክፍያ አማራጭ መልእክት መሠረት መክፈል ትችላላችሁ።🎬 ከላይ ባሉ ቪድዮዎች፦ ዝርዝር አከፋፈሉን በተያያዙት ሁለቱ የቪዲዮ መመሪያዎች በመመልከት ብቻ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ። 📝 መረጃ ያልሞላችሁ አባላት፦ ቢል ተዘጋጅቶ እንዲላክላችሁ ከታች ባለው ሊንክ ስም፣ ስልክና የመዋጮ መጠን ጨምሮ መሰረታዊ መረጃዎችን ከታች ያለውን link 🔗 በመጠቀም መሙላት ይቻላል፦
https://forms.gle/pZJVhdffjPBHGjhN9የተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት
1 935
የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ገዳማችንን ጎበኙ!
የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ያቀረቡላቸውን ጥሪ በመቀበል በዓለ መስቀልን ለማክበር እና ለሐዋርያዊ አገልግሎት በቅርቡ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ መምጣታቸው እና በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ የከበረ አቀባበል እንደ ተደረገላቸው ይታወቃል። በዚኹ መነሻነት በዛሬው ዕለት መስከረም ፲፮/ ቀን ፳፻፲ወ፱ ዓ.ም. ወደ ምስካየ ኅዙናን መድኀኔ ዓለም ገዳምም በመምጣታት የክብር እንግዳ ኾነው በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።።
በጉብኝታቸውም ቤተ ክርስቲያኑን፣ ገዳሙን እና የገዳሙን መዘክር እንዲኹም የትምህርት ቤቱን እና ዐዲስ እየተሠራ የሚገኘውን ባለ ዐሥር ፎቅ ሕንጻ ተዟዙረው ጎብኝተዋል። ከቤተ ክርስቲያናችን አባቶች እና ምእመናን ጋር በመገናኘት የፍቅር፣ የወንድማማችነት እና የመንፈሳዊ አንድነት መልእክት አስተላልፈዋል።
የፓትርያርኩ እና የልዑካኑ ጉብኝት ከጥንት ጀምሮ በኹለቱ ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት መኻከል የነበረውን እና ያለውን የእምነት እና የወንድማማችነት ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መኾኑ ተገልጿል።
የአበው በረከት ለኹላችን ትድረሰን!!!
