1 767
订阅者
+424 小时
+127 天
+2430 天
帖子存档
Repost from B-MY YOUTH Post
📌ዳዊት እና እግዚአብሔር በሚል ርዕስ ያለፋትን 17 ሳምንታት በጌታ እርዳታ ስንማር ቆይተናል …የዚህ ትምህረት መዝጊያ እና ሰፊ የጸሎት ጊዜ ነገ ሀሙስ ከ 11:00 ጀምሮ😇😇
ሁላችሁም በመገኘት ከእግዚአብሔር ቃል እንማር በዝማሬ ጌታን እናመልካለን እንጸልያለን ተጋብዛችኋል 😇
Bole Mekane Yesus Congregation
Telegram | Facebook | Instagram
ለጓደኛዎ ያጋሩ @BoleYouthPost
ሐምሌ 25 ሙሉ ቀን
ለሁሉም ወላጆች የተዘጋጀ ትምህርት እና ስልጠና
የልጆች አለኝታ ስለመሆን
ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከልጆች ስነልቦና አስተዳደግ (psychology and Human Development) ልጆችን እንዴት እናሳድግ በሚል የተዘጋጀ
የሙሉ ቀን ፕሮግራም
የፊታችን ቅዳሜ
ከ3:00 ጀምሮ ይኖረናል።
በታዳጊ ሕብረት እና በቤተሰብ አገልግሎት የተዘጋጀ
ወገኖች ሎኬሽኑ እስከ 40/60 ኮንዶሚኒየም ካደረሳችሁ በኋላ ቀጥሎ ያለውን አትከተሉ። በኮንዶሚኒየሙ ጀርባ ከደረሳችሁ በኋላ ሳትታጠፉ ወደፊት ስትሄዱ የምታያችሁ ኮንዶሚኒየም የሚመስለው ሕንፃ ነው። የመከላከያ ፋውንዴሽን የመጀመሪያ በር ብላችሁ ጠይቁ።
ሎኬሽኑ ብዙ ሰዎችን ስላሳሳተ፣ ከክራውን 40/60 ኮንዶሚኒየም ጀርባ እንደደረሳችሁ፣ ፊት ለፊት የሚታየው ኮንዶሚኒየም መሳይ ሕንፃ የመከላከያ ፋውንዴሽን የመጀመሪያው ግቢ ነው
የነገ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍሎች
ከሥላሴ በኋላ 5ኛ እሁድ
ደቀ መዝሙር ሆኖ እስከ መጨረሻ መኖር
ዘፍ 12:1-9
1ኛ ቆሮ 3:10-14
ማቴ 16:13-20
Repost from Bole Mekane Yesus channel
ውድ ምዕመናን
የእናታችን/እህታችን ጥሩዬ ዳሩሳ እና ቄስ ዳዊትን በጋራ የምንጽናናው እሁድ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ከቀኑ 06:30 ላይ ስለሆነ፣ በአዲሱ መኖሪያ አድራሻቸው ቃሊቲ ተገናኝተን እንድናጽናና ይሁን።
የቦታውን ሎኬሽን የምንልክ ሲሆን አሁድ አምልኮ እንዳለቀ አብረን የምንሄድ ይሆናል። መኪና ያሏችሁ ሰዎች ሌሎችን በመያዝ እንድታገለግሉ ስንል እናሳስባለን።
❗️ዛሬ ዛሬ ዛሬ ዛሬ ዛሬ ዛሬ❗️
"በላይ ያለውን እንሻ"
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ትምህርታዊ ኮንፈረንስ
"ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ" (ቆላ 3:1 አ. መ. ት)ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም፣ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ጀምሮ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ውድ ምዕመናን
የእናታችን/እህታችን ጥሩዬ ዳሩሳ እና ቄስ ዳዊትን በጋራ የምንጽናናው እሁድ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ከቀኑ 06:30 ላይ ስለሆነ፣ በአዲሱ መኖሪያ አድራሻቸው ቃሊቲ ተገናኝተን እንድናጽናና ይሁን።
የቦታውን ሎኬሽን የምንልክ ሲሆን አሁድ አምልኮ እንዳለቀ አብረን የምንሄድ ይሆናል። መኪና ያሏችሁ ሰዎች ሌሎችን በመያው እንድታገለግሉ ስንል እናሳስባለን።
"በላይ ያለውን እንሻ"
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ትምህርታዊ ኮንፈረንስ
"ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ" (ቆላ 3:1 አ. መ. ት)ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም፣ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ሐምሌ 19/2018 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ጀምሮ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
የነገ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍሎች
ከሥላሴ በኋላ 4ኛ እሁድ
ጽድቅና ርኅራኄ
ሆሴ 14:1-9
ሮሜ 2:1-13
ማር 9:42-50
ውድ ምዕመናን የእናታችን ጥሩነሽ ዳሩሳ(ቄስ ዳዊት ባለቤት) እህታቸው ስላረፉና ቀብር ዛሬ ስላስፈፀሙ በስልክ እየደወላችሁ እንድታጽኗኗቸው ይሁን።
ከሃዋሳ ሲመለሱ እንደ ማኅበር ቤታቸው ሄደን የምናጽናናበትን ቀን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
የቤተሰብ አገልግሎት
Family Ministry
የሳምንቱ የቤተሰብ አገልግሎት የባልና ሚስት ፕሮግራም
ርዕስ፦ የትዳር አጋሬ ስለ እኔ ቢያውቅ/ብታውቅ የምመኘው
ዓላማ ባልና ሚስት በትኩረት እርስ በእርሳቸውን በማዳመጥ የልብ ሃሳባቸውን እንዲረዱና ትዳራቸው ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መርዳት።በዚህ ሳምንት ከመደበኛው የትምህርት ቪዲዮ ይልቅ እርስ በርሳችሁን በጥልቀት የምታዳምጡበትን ጊዜ እንድትወስዱ እንጋብዛችኋለን። ከ30-45 ደቂቃ የሚወስድ ይህ ቆይታ የትዳር አጋራችሁን ልብ፣ ስሜት፣ ህልምና ፍላጎት እንድታውቁ ይረዳችኋል። ዛሬ ረብዑ ከምሽቱ 3:00 ይጠብቁን። ተባረኩ።
የቤተሰብ አገልግሎት
Family Ministry
የሳምንቱ የቤተሰብ አገልግሎት የባልና ሚስት ፕሮግራም
ርዕስ፦ የትዳር አጋሬ ስለ እኔ ቢያውቅ የምመኘው
ዓላማ ባልና ሚስት በትኩረት እርስ በእርሳቸውን በማዳመጥ የልብ ሃሳባቸውን እንዲረዱና ትዳራቸው ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መርዳት።በዚህ ሳምንት ከመደበኛው የትምህርት ቪዲዮ ይልቅ እርስ በርሳችሁን በጥልቀት የምታዳምጡበትን ጊዜ እንድትወስዱ እንጋብዛችኋለን። ከ30-45 ደቂቃ የሚወስድ ይህ ቆይታ የትዳር አጋራችሁን ልብ፣ ስሜት፣ ህልምና ፍላጎት እንድታውቁ ይረዳችኋል። ነገ ረብዑ ከምሽቱ 3:00 ይጠብቁን። ተባረኩ።
ሐምሌ 6-10
ታዳጊዎች (senior & junior) ትምህርት
በሙሉ ጊዜ አገልጋዬቻችን ተዘጋጅቶላቸዋል
በዚህ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ወላጆች እንድታመጧቸው ይሁን
የዛሬ ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍሎች
ከሥላሴ በኋላ 3ኛ እሁድ
ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት
መሳ 21:1-5, 15
1 ቆሮ 12:4-6, 12-27
ማር 3:31-35
ውድ የማኅበራችን አባላት በሙሉ
ባለፈው ሳምንት በማስታወቂያ እንደተነገረ፣ ነገ ከአምልኮ እና የጌታ እራት በኋላ አጭር የምክክር ጊዜ ከ20-30 ደቂቃ ስለሚኖረን አስባችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
የማኅበሯ የሽማግሌዎች አስተዳደር ኮሚቴ
