ch
Feedback
ABRET PRO

ABRET PRO

前往频道在 Telegram

የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን የምንዘክርበት ቻናል ነው @Abretpro

显示更多
4 436
订阅者
+524 小时
+137
+1330
帖子存档
የሰው ልጅ ሀሳቡ ምኞቱ ብዙ ነው... ይመጣል የተባለው ዘመን የሚመጣ አይመስለውም... ልጅ የሆነ እንደሆነ አድጌ ፂም አበቅላለው ብሎ አይልም... ደርሼ ትልቅ ሰው(ሽማግሌ) እሆናለሁ ብሎ አይልም..
የሰው ልጅ ሀሳቡ ምኞቱ ብዙ ነው... ይመጣል የተባለው ዘመን የሚመጣ አይመስለውም... ልጅ የሆነ እንደሆነ አድጌ ፂም አበቅላለው ብሎ አይልም... ደርሼ ትልቅ ሰው(ሽማግሌ) እሆናለሁ ብሎ አይልም... ነገር ግን ሁሉም ወዲያውኑ መጥተው ይደርሳሉ:: ከሰው ልጅ ብዙ የኖረው 1000 አመት ነው... አንድ ሁለት ሰዎች ከዛ የጨመሩ አሉ:: ሺ አመት የቆየውም ቢሆን ጨርሶ ሄዷል... ሰው የሆነ እንደሆነ እንደ እንጨት ቆሞ የሚቀር(የሚኖር) ነገር የለም:: እድሜው ትንሽ ነው... የሰራበት የሆነ እንደሆነ ብዙ ነው... ካልሰራበት ግን ትንሽ ነው:: ከ ሠይዲ አባ ራሙዝ ወአዝ የተወሰደ

اللهُ أَكْبَر، اللهُ أَكْبَر، اللهُ أَكْبَر لَا إِلَهَ إِلَّا الله وَاللهُ أَكْبَر اللهُ أَكْبَر وَلِلّٰهِ الْحَمْد اللهُ أَكْبَر كْبِيرا ، وَالْحَمْدُ لِلّٰهِ كَثِيرا وَسُبْحَانَ اللهِ بُكْرَة وَأَصِيلا لَا إِلَهَ إِلَّا اللّٰه وَلَا تَعْبُدُ إِلَّا إِيَّاهُ مُخْلِصِيْنَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كرِهَ الْكَافِرُونَ لَا إِلَهَ إِلَّا الله وَحْدَه صَدَقَ وَعْدَه وَنَصَرَ عَبْدَه وَأَعَزَّ جُنْدَه وَهَزَمَ الْأَحْزَابَ وَحْدَه لَا إِلَه إِلَّا الله وَاللهُ أُكْبَر، اللَهُ أَكْبَر وَلِلِّهِ الْحَمُد

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁዑን ሀያታቸውን ሙሉ በሸኾቹ መንገድ የኖሩ ፣ በሠይዲ ውዴታ እጅግ የዋለሉ ፣ ለዱኒያ ብልጭልጭ ቅንጣት ያልጏጉ ታላቅ ሙሪድ (ጋሽ አብደላ) በድንገት አመለጡን:: አላህ በወ
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁዑን ሀያታቸውን ሙሉ በሸኾቹ መንገድ የኖሩ ፣ በሠይዲ ውዴታ እጅግ የዋለሉ ፣ ለዱኒያ ብልጭልጭ ቅንጣት ያልጏጉ ታላቅ ሙሪድ (ጋሽ አብደላ) በድንገት አመለጡን:: አላህ በወደዷቸው ፣ እድሜያቸውን ሙሉ በተከተሏቸው ሸይኾቻቸው ጥላ ስር ከነብያችንﷺ ጋር ያጎራብትልን:: ለወዳጅ ቤተሰብ ሁሉ ሶብሩን ይስጥልን🤲

የቀድሞው የጠሮ መስጂድ ኢማም ሀጅ አብድልከሪም ሐፊዘሁላህ የዒድ ተክቢራ አዲስ አበባ እስታዲዯም https://youtu.be/-TpZD-RGwCw?si=HsJFQemkrn1sgIuc

ከየትኛውም የአለም ጥግ ይምጣ ፣ ሀብታም ይሁን ድሀ ፣ አረብ ይሁን አጀም ልዩነት የለም:: VIP ፕሮቶኮል የለም:: ሚሊዮኖች እንደ አንድ ኡማ ለሀጅ ይሰበሰባሉ:: ዒድ ሙባረክ 💚
+2
ከየትኛውም የአለም ጥግ ይምጣ ፣ ሀብታም ይሁን ድሀ ፣ አረብ ይሁን አጀም ልዩነት የለም:: VIP ፕሮቶኮል የለም:: ሚሊዮኖች እንደ አንድ ኡማ ለሀጅ ይሰበሰባሉ:: ዒድ ሙባረክ 💚

ለመላው ሙስሊም ሙስሊማት እንኳን ለዒደል አድሀ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: በአሉ የአንድነት ፣ የመተዛዘን ፣ የመዋደድና የመካከበር ይሆንልን ዘንድ ምኞታችን ነው:: #ኢድተክቢራ #EidTekbira #ዒድተክቢራ #tekbira #ተክቢራ #Ethiopian

💚🔥መገርገቢያ || ዒዘተ አልኢስላም ሠላም ዐለይኩም ዒዘተ አልኢስላም ² አባ ራሙዜ ሙንተሐአልመራም የወጣቶች የሺሊላ መሽረብ

ትውስ ሲለኝ ሁሉ የሚነደኝ : ውስጤን እንደ እሳት የሚፈጀኝ : እጅግ የሚቆጨኝ በሠይዲ... ዒልማቸው ወደር በሌለው ፣ ዊላያቸው እንደ ፀሀይ ፍንትው ብሎ በታይው ታላቅ ሸይኽ ዘመን ደርሼ መጠቀም ያለ
ትውስ ሲለኝ ሁሉ የሚነደኝ : ውስጤን እንደ እሳት የሚፈጀኝ : እጅግ የሚቆጨኝ በሠይዲ... ዒልማቸው ወደር በሌለው ፣ ዊላያቸው እንደ ፀሀይ ፍንትው ብሎ በታይው ታላቅ ሸይኽ ዘመን ደርሼ መጠቀም ያለብኝን ያህል ሳልጠቀም ሰዉም በሚገባ ሳይጠቀምባቸው ያመለጡን ነገር ነው::

عين فضل الله باب وجه الله نور محيط في جلال الله
عين فضل الله باب وجه الله نور محيط في جلال الله

የሀገራችን ሰው እንደሆነ በትንሽ ነገር ይሸነገላል:: አሁን በአንዳንድ ሀገር ያሉ ሙእተዚላዎች ሀገራችን ቢገቡ ብዙዎቹ እንደ ሸህ ይሆኑ ነበር:: ብዙው ሰው ፋይዳ ቢስ ይሆን ነበር:: ተውሒዱን ጠብቆ
የሀገራችን ሰው እንደሆነ በትንሽ ነገር ይሸነገላል:: አሁን በአንዳንድ ሀገር ያሉ ሙእተዚላዎች ሀገራችን ቢገቡ ብዙዎቹ እንደ ሸህ ይሆኑ ነበር:: ብዙው ሰው ፋይዳ ቢስ ይሆን ነበር:: ተውሒዱን ጠብቆ መቆም ያቅተው ነበር:: ሸሪአውንም ችሎ ጠብቆ መቆም ያቅተው ነበር:: ከሠይዲ አባራሙዝ ወአዝ የተወሰደ

ኸሚስ 💚🔥 | ራምሳ እስከነ ፅሁፉ | ደዌ እጅግ ውብ የሆነ የራምሳ ቅጂ እስከነ ፅሁፉ በሸይኽ አሊ ሰማን بسم الله الرحمن الرحيم ٢ اللهم صل على زين الوجود & صلى الله على محمد صلى الله عليه وسلم   https://youtu.be/Q3FDcGbrQEE?si=woZSnrkH5mJWWVLl

በጀማ ንጉስ(ሠይድ ሙሐመድ ሻፊ) እና በሠይድ አባ ሙሐመድ(ጌታው ሠይድ) ዘመን ሰው ተቀላቅሎ አብሮ ይኖር ነበር:: ይሄ የኔ ነው ያ ያንተ ነው የሚባል ነገር አልነበረም:: ሠይድ ጀማሉል ዐንይ ይህን
+2
በጀማ ንጉስ(ሠይድ ሙሐመድ ሻፊ) እና በሠይድ አባ ሙሐመድ(ጌታው ሠይድ) ዘመን ሰው ተቀላቅሎ አብሮ ይኖር ነበር:: ይሄ የኔ ነው ያ ያንተ ነው የሚባል ነገር አልነበረም:: ሠይድ ጀማሉል ዐንይ ይህን ከለከሉ...ዘመኑ እንደበፊት አይደለም:: አሁን አኺር ዘማን ነው አሉ:: እያንዳንዱ ሀቅ ሀቁን ይጠብቅ... አንዱ የሌላውን ሀቅ ይጠብቅ አሉ:: አንዳድን ነገር ሊያወሩትም ያሳዝናል:: | ከሠይዲ አባራሙዝ ወአዝ የተወሰደ |

ባለፉት የስድስት አመት የ YouTube ቆይታችን ውስጥ በጥቅሉ 6.5 million እይታ 54,900 likes 5,400 comments 82,500 shares እና 28,160 subscribers አግኝተና
ባለፉት የስድስት አመት የ YouTube ቆይታችን ውስጥ በጥቅሉ 6.5 million እይታ 54,900 likes 5,400 comments 82,500 shares እና 28,160 subscribers አግኝተናል:: ይህ በዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያና ቪዲዮ ክሊፕ ለተቀናበሩ ነሺዳዎች ትንሽ ቢሆንም በቆዩ original የሀድራ መንዙማዎች ሲሆን ቀላል አይደለም:: እጅግ አድካሚም ነው:: የምንለቃቸውን መንዙማዎች በማየት like እና share በማድረግ ፣ ፎቶ, ኪታብ, የሀድራ ቅጂዎችን ወ.ዘ.ተ. በመላክ ፣ ገንቢ በሆኑ ሀሳብቦችና በዱዓ ብርታት ለሆናችሁን ተከታታዮቻችን በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረሳቹ 🙏

💚🔥መገርገቢያ || በሕረ ጁዲላህ ሸይኽ ሠይድ ሚቅባሰል ኑር አብሬትይ አባታቸውን(ሸይኻቸውን) የመደሁበት እጅግ ውብ መድህ እስከነ ፅሁፉ የአብሬትዩ ሳኒ በጣም ቅርብ በነበሩት ታላቁ ሙሪድ ካቲብ ኑር ሁሴን ልጅ በሸይኽ ኢምራን ሸይኽ ኑር ሁሰይን እና ማዲህ ፉዓድ መልካ እስከነ ፅሁፉ سلام عليكم بحر جود الله ٢ غياث الأحباب باب فضل الله ሠላም ዓለይኩም በሕረ ጁዲላህ ² ጊያሡል አህባብ ባቡ ፈድሊላበ https://youtu.be/9X7f2W8tbQE?si=rRhaWvgBS8L5jMYF

ማጠቃለያ፦ አላህን ስንተረጉም-> 20 ዋጂብ + 20 ሙስተሒል + 1 ጃኢዝ = 41 (በአላህ መብት) ነቢያትን ስንተረጉም:-> 4 ዋጂብ + 4 ሙስተሒል + 1 ጃኢዝ = 9 (በነቢያት መብት) በጠቅላላው = 50 የዐቂዳ መሠረቶች (አቃኢድ አል-ኸምሲን) ማወቅ ይጠበቅብናል:: እነዚህ ያልተማረ ሰው ሊደነጋገረው ይችላል::

አንድ ሙስሊም ማወቅ ያለበት የተውሂድ ትምህርት 50 ናቸው ==================== ✍️@haseniye እያንዳንዱ አካለ-መጠኑ የደረሰና አእምሮው ጤናማ የሆነ ሰው ሊያውቃቸው የሚገቡ 50 የዐቂዳ መሠረቶች (አቃኢድ አል-ኸምሲን) አሉ። እነዚህም በአላህ መብት 41፣ በነቢያት መብት ደግሞ 9 ናቸው። 1) ስለአላህ ማወቅት ያለብን 41 መሠረታዊ ትምህርቶች (20 ዋጂብ, 20 ሙስተሂል እና 1 ጃኢዝ ናቸው) //ሀ\\ ዋጂብ (በአላህ ላይ ሊኖሩ የሚገቡ 20 ፍጹማዊ መገለጫዎች እነዚህ መገለጫዎች አላህ በእነሱ መገለጹ ግድ የሆነና አእምሮ የነሱን አለመኖር ፈጽሞ የማይቀበላቸው ናቸው። ማለትም አእምሯችን በፍጹም አልቀበልም የማይላቸውና አላህም የግድ ሊገለጽባቸው የሚገቡ 20 ሲሆኑ እነሱም በአራት ይመደባሉ:: 👉🏼ምድብ አንድ:- ነፍሲያ (የማንነት/የመኖር ባህሪ) አንድ ነው:: እርሱም:- 1️⃣ ውጁድ (وجود) ይባላል:: ትርጉሙም መኖር ማለት ነው:: (አላህ ያለ ነው፣ መኖሩም የራሱ ባህሪ ነው)። ---------- 👉🏼ምድብ ሁለት ሰልቢያ (ጉድለትንና ፍጡራንን የመሰሉ ባህሪያትን የሚገፉ ወይም የማይቀበሉ) 5 ናቸው:: 2️⃣ ቂደም (قدم): ቀዳሚነት (መጀመሪያ የሌለው መሆን)። 3️⃣ በቃእ (بقاء): ዘላለማዊነት (መጨረሻ የሌለው መሆን)። 4️⃣ ሙኻለፈቱሁ ሊል-ሐዋዲሥ (مخالفته للحوادث): ፍጡራንን ፈጽሞ አለመምሰል (በማንነቱም፣ በባህሪውም ሆነ በሥራው)። 5️⃣ ቂያሙሁ ቢነፍሲህ (قيامه بنفسه): ራሱን ቻይነት (መገኛ ቦታ/አካል ወይም አስገኚ ጌታ የማይፈልግ መሆን)። 6️⃣ ወሕዳኒያ (وحدانية): አንድነት (በማንነቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቶቹ አጋርና ቢጤ የሌለው መሆን)። ------- 👉🏼 ምድብ ሦስት:- መዓኒ (የማንነት መገለጫ የሆኑ የረቂቅ ኃይል መገለጫዎች) 7 ናቸው:: 7️⃣ ቁድራ (قدرة): ችሎታ/ኃይል (ሁሉን አድራጊነት)። 8️⃣ ኢራዳ (إرادة): ፍላጎት/ውሳኔ (ሁሉን በራሱ ምርጫና ጥበብ መሻት)። 9️⃣ ዒልም (علم): ዕውቀት (ሁሉን ነገር የነበረውን፣ ያለውንና የሚሆነውን አስቀድሞ አዋቂ መሆን)። 🔟 ሐያት (حياة): ሕያውነት (ፍጹም የሆነ ሕይወት ያለው)። 1️⃣1️⃣ ሰምዕ (سمع): መስማት (ድምፅና ጆሮ ሳይሻ ሰሚ መሆን)። 1️⃣2️⃣ በሶር (بصر): ማየት (ብርሃን ዓይን ሳይሻ ተመልካች መሆን)። 1️⃣3️⃣ ከላም (كلام): ንግግር (ፊደል፣ ቋንቋና ድምፅ ሳይሻ ተናጋሪ መሆን)። ---------- 👉🏼 ምድብ አራት:- መዕነዊያ (እላይ የተጠቀሱ የመዓኒ ባህሪያት መኖራቸውን የሚያረጋግጡ) 7 መገለጫዎች 1️⃣4️⃣ ከውኑሁ ቃዲረን (كونه قادرا): ቻይ/ኃያል መሆኑ። 1️⃣5️⃣ ከውኑሁ ሙሪደን (كونه مريدا): ፈቃጅ መሆኑ። 1️⃣6️⃣ ከውኑሁ ዓሊመን (كونه عالما): አዋቂ መሆኑ። 1️⃣7️⃣ ከውኑሁ ሐየን (كونه حيا): ሕያው መሆኑ። 1️⃣8️⃣ ከውኑሁ ሰሚኧን (كونه سميعا): ሰሚ መሆኑ። 1️⃣9️⃣ ከውኑሁ በሲረን (كونه بصيرا): ተመልካች መሆኑ። 2️⃣0️⃣ ከውኑሁ ሙተከሊመን (كونه متكلما): ተናጋሪ መሆኑ። ******** \\ለ// ሙስተሒል (በአላህ ላይ ሊኖሩ የማይችሉ/የማይገቡ) 20 ባህሪያት:- እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የ20ዎቹ ዋጂብ ባህሪያት ቀጥተኛ ተቃራኒዎች (ጉድለቶች) ሲሆኑ፣ በአላህ ላይ መኖራቸው በአእምሮም በሸሪዓም ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። 1. ዐደም (عدم): አለመኖር። 2. ሑዱሥ (حدوث): አዲስ መሆን (አስገኚ መፈለግ) 3. ፈናእ (فناء): መጥፋት/መውደም። 4. ሙማሠለቱሁ ሊል-ሐዋዲሥ (مماثلته للحوادث): ፍጡራንን መምሰል። 5. ኢሕቲያጁሁ ኢላ መሐሊን አው ሙኸሲስ (احتياجه إلى محل أو مخصص): ቦታን ወይም አስገኚን መፈለግ። 6. ተዓዱድ (تعدد): ከአንድ በላይ መሆን (መቆጠር, መብዛት)። 7. ዐጅዝ (عجز): ድክመት/አለመቻል። 8. ከራሃ (كراهة): ተገዳጅነት (የሆነ ነገር ያለፍላጎቱ መከሰት)። 9. ጀህል (جهل): አለማወቅ/ስንፍና። 10. መውት (موت): መሞት። 11. ሶመም (صمم): መስማት አለመቻል። 12. ዐማ (عمى): ማየት አለመቻል። 13. በከም (بكم): መናገር አለመቻል። 14. ከውኑሁ ዐጂዘን (كونه عاجزا): ደካማ መሆንን 15. ከውኑሁ ካሪሀን (كونه كارها): ተገዳጅ መሆንን 16. ከውኑሁ ጃሂለን (كونه جاهلا): የማያውቅ መሆንን 17. ከውኑሁ መይተን (كونه ميتا): ሙት መሆንን 18. ከውኑሁ አሶም (كونه أصم): ደንቆሮ መሆንን 19. ከውኑሁ አዕማ (كونه أعمى): ዕውር መሆንን 20. ከውኑሁ አብከም (كونه أبكم): ዲዳ መሆንን 👆🏾እነዚህ ሸሪዓተል ኢስላምም ይሁን አዕምሮ ሊቀበላቸው የማይችሉና ጉድለቶች ናቸው:: አምላክ እነዚህ ባሕሪያት በፍጹም የማይነኩት ነው:: _ (((ሐ))) ጃኢዝ (በአላህ ላይ ሊሆንም ላይሆንም የሚችል) 1 መገለጫ አለ:: 1️⃣ ፊዕሉ ኩሊ ሙምኪኒን አው ተርኩሁ (فعل كل ممكن أو تركه): ማድረግም አለማድረግም የሚቻል, አላህ ቢያደርገውም ባያደርገውም መሆን የሚችል ይባላል:: ማንኛውንም ሊኖር የሚችልን (ፍጡር) ነገር መፍጠር ወይም አለመፍጠር፤ ማድረግ ወይም አለማድረግ የአላህ ፍጹም ምርጫ ነው። (ለምሳሌ፦ ሰውን ማበልጸግ ወይም ማደህየት፣ ሰማይን መፍጠር ወይም አለመፍጠር በአላህ ላይ ግዴታ የለበትም፣ ሙስታሒልም አይደለም፤ የራሱ ፍላጎትና ውሳኔ ብቻ ነው)። ስለ አላህ እነዚህ 41 አተረጓጎም ማወቅ ለሙስሊም እጅግ አስፈላጊና ተቀዳሚ ትምህርት ነው:: ይህ የሰፊው ሕዝብ የተውሂድ ትምህርት ይባላል:: በትምህርት የመጠቀም ይሁን የጀመረ ሰው ማወቅ ያለበት ዕውቀት ነው:: ቀጣዩ የነቢያት መገለጫዎች ናቸው:: በነቢያት መብት ላይ የሚገቡ ባህሪያት (9 ዝርዝሮች) አሉ:: ሀ. ዋጂብ:- በነቢያት ላይ ሊኖሩ የሚገቡ ፍጹም ባህሪያት 4 ናቸው:: ነቢያትና መልክተኞች የአላህን ቃል ለሕዝብ የሚያደርሱ በመሆናቸው፣ እነዚህ ባህሪያት ሊኖሯቸው ግድ ነው። 1) ሲድቅ (صدق): እውነተኛነት (በንግግራቸውም ሆነ በተግባራቸው ፍጹም እውነትን መናገር) 2) አማና (أمانة): ታማኝነት (ከውስጥም ከውጭም ከኃጢአትና ከነውር የጠሩ መሆን)። 3) ተብሊግ (تبليغ): መልዕክትን ማድረስ (የታዘዙትን መለኮታዊ ትዕዛዝ ሳይደብቁና ሳይቀንሱ ማድረስ)። 4. ፈጧና (فطانة): ንቁነት/ብልህነት (ከፍተኛ አእምሯዊ ብቃትና ተከራካሪዎችን የመርታት ችሎታ)። ለ. ሙስተሒል በነቢያት ላይ ሊኖሩ የማይችሉ/የማይገቡ 4 ባህሪያት ከላይ የተጠቀሱት የ4ቱ ዋጂብ ባህሪያት ቀጥተኛ ተቃራኒዎች ሲሆኑ፣ በነቢያት ላይ መከሰታቸው የማይቻል ነው፦ 1. ኪዝብ (كذب): ውሸት ወይም መዋሸትን 2. ኺያና (خيانه): ክህደት (ኃጢአት ላይ መውደቅ ወይም ታማኝነትን ማጉደል።) 3. ኪትማን (كتمان): መልዕክትን መደበቅ። 4. በላዳ (بلادة): ዝንጉነት/የአእምሮ መደንዘዝ። ሐ. ጃኢዝ በነቢያት ላይ ሊሆን የሚችል ሰዋዊ ባህሪ ሲሆን ይህም በአንድ ምድብ ይጠቃለላል:: አል-አዕራድ አል-በሸሪያ (الأعراض البشرية): የነቢይነትና የመልክተኝነት ደረጃቸውን የማይቀንሱ ሰዋዊ ባህሪያት በእነርሱ ላይ መከሰቱ የሚቻል ነው። (ለምሳሌ፦ መታመም፣ መራብ፣ መጠማት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ ማግባት፣ መገበያየት፣ መተኛትና መሞት)።

እነሆ በአላህ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያላቸው የተባረኩ አስር የዙልሂጃ ቀናት ደርሰዋል። እነዚህ ውድ ቀናቶች በአላህ ቸርነት:- የልብ እድፍ የሚፀዳበት ሀጢያቶች በተውበት እንባ የሚታጠቡበት ትርፋማ ዕድል
እነሆ በአላህ ዘንድ ትልቅ ቦታ ያላቸው የተባረኩ አስር የዙልሂጃ ቀናት ደርሰዋል። እነዚህ ውድ ቀናቶች በአላህ ቸርነት:- የልብ እድፍ የሚፀዳበት ሀጢያቶች በተውበት እንባ የሚታጠቡበት ትርፋማ ዕድል ናቸው። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሙእሚኖች ከቸልተኝነት ይነቃሉ... መልካም ስራን ያበዛሉ:: በነዚ ቀናቶች የምህረት ደጆች በበረከት የተከፈቱ ናቸውና በዒባዳ እንበራታ:: [ ስኬት የሚገኘው ከአላህ ብቻ ነው። ]

ሠላም ያረሱለላህ 🔥💚አዲስ ነሺዳ በሙንሺድ Fuad Melka ✦✦✦ እንደ አባራሙዞ ነው የናፍቆት ጉዞ እንደ ሠይድ ሚቅባስ ቀን ሌት በእምባ መራስ እንደሠይድ አርባው በፍቅሮ ሚያነባው እንደ ጫሌው ጌታ ክንድ ይሚያበረታ ሁሉ ለየቅል ነው ሠላም ያረሱለላህ ሙሓባ ውዴታው

ሠላም ያረሱለላህ 🔥💚አዲስ ነሺዳ በሙንሺድ Fuad Melka ✦✦✦ እንደ አባራሙዞ ነው የናፍቆት ጉዞ እንደ ሠይድ ሚቅባስ ቀን ሌት በእምባ መራስ እንደሠይድ አርባው በፍቅሮ ሚያነባው እንደ ጫሌው ጌታ ክንድ ይሚያበረታ ሁሉ ለየቅል ነው ሠላም ያረሱለላህ ሙሓባ ውዴታው