ልባም ሴት
በሴቶች ውስጣዊ ማንነት ላይ ትኩረት በማድረግ ሴቶች ልባም ሴት ወደ መሆን እንዲያድጉ የሚረዳ መንፈሳዊ ቻናል:: ለአስተያየት @SamriiGetu Buy ads: https://telega.io/c/lebamsett
إظهار المزيد📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ልባም ሴት
تُعد قناة ልባም ሴት (@lebamsetttt) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 10 911 مشتركاً، محتلاً المرتبة 8 441 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 3 037 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 10 911 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 26 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -126، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 4، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 11.17%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.11% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 1 219 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 449 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 23.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“በሴቶች ውስጣዊ ማንነት ላይ ትኩረት በማድረግ ሴቶች ልባም ሴት ወደ መሆን እንዲያድጉ የሚረዳ መንፈሳዊ ቻናል::
ለአስተያየት @SamriiGetu
Buy ads: https://telega.io/c/lebamsett”
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 27 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
جاري تحميل البيانات...
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 27 يونيو | 0 | |||
| 26 يونيو | +9 | |||
| 25 يونيو | +5 | |||
| 24 يونيو | +9 | |||
| 23 يونيو | +8 | |||
| 22 يونيو | +11 | |||
| 21 يونيو | +2 | |||
| 20 يونيو | +5 | |||
| 19 يونيو | +8 | |||
| 18 يونيو | 0 | |||
| 17 يونيو | +3 | |||
| 16 يونيو | +4 | |||
| 15 يونيو | 0 | |||
| 14 يونيو | 0 | |||
| 13 يونيو | 0 | |||
| 12 يونيو | 0 | |||
| 11 يونيو | 0 | |||
| 10 يونيو | 0 | |||
| 09 يونيو | +2 | |||
| 08 يونيو | 0 | |||
| 07 يونيو | +1 | |||
| 06 يونيو | +2 | |||
| 05 يونيو | +1 | |||
| 04 يونيو | +4 | |||
| 03 يونيو | 0 | |||
| 02 يونيو | 0 | |||
| 01 يونيو | +1 |
| 2 | የሌላው ሰው ውድቀት የእናንተ የስኬት መሰላል አይደለም!
በአሁኑ ጊዜ በሰዎች ስህተት ላይ ኢንቨስት የሚያደርጉ ሰዎች በጣም በዝተዋል። የሌላውን ሰው ጉድለት አጉልቶ በማሳየት በዛ ጥላ ስር ራሳቸውን "ትክክለኛ" እና "ተወዳጅ" አድርገው ለማቅረብ የሚሮጡ በርክተዋል። ነገር ግን እውነታው ይሄ ነው የሌላውን ሰው ስም በማጠልሸት ወይም ስህተቱን በማውራት የሚገኝ መወደድ ከንቱ ነው ነው። እውነተኛ ክብር የሚመጣው ሌላውን ጥሎ በማለፍ ሳይሆን በትህትና አብሮ በመደጋገፍ እና የራስን ማንነት በቅንነት በማነፅ ብቻ ነው። የሰው ስህተት ሲገጥመን ሰዎቹን በቅንነት የምናርምበት እንጂ ራሳችንን የምናገዝፍበት እድል አይደለም። ተወዳጆች የአንድ ሰውን ስህተት ስታዩ ያንን ስህተት በትልቅ ማጉያ መነፅር አጉልታቹ ለሰው ለማሳየት አትሩጡ እሺ። እንደዚ የሚያደርጉ ሰዎች ምን አይነት ሰዎች መሰሏችሁ አንደኛ በራስ መተማመን የላቸውም ራሳቸውን በራሳቸው ጥረትና ብቃት ማሳደግ ያቃታቸው ሰዎች፣ ሌሎችን በማሳነስ ራሳቸውን ትልቅ አድርገው ለመሳል ይሞክራሉ። የሌላው ሰው ዝቅ ማለት እነሱን ከፍታ ላይ የሰቀላቸው ይመስላቸዋል እውነታው ግን ነገ የሚያጭዱትን ዘር እያበላሹ መሆኑ ነው። ሁለተኛው ደግሞ መገለጫቸው ደግሞ ተወዳጅነት ፍለጋ ሚንከራተቱ ናቸው ሌላውን ሰው በመተቸት እና ስህተቱን በማውጣት መሃል ራሳቸውን እንደ ፍፁም እና ለሰው አሳቢ አድርገው በማቅረብ የሰዎችን ጭብጨባ መግዛት ይፈልጋሉ ይህም ምንም ያህል ጠንቃቃ ሰው ብንሆን ከስህተት የፅዳን አይደለንምና ትርፉ ትዝብት ነው። የመጨራሻው ደግሞ የገዛ ጥፋታቸውን መሸፈኛ ለማድረግ ነው የሌላው ሰው ጉድለት በጣም ሲጎላ የእነሱ የራሳቸው ትላልቅ ስህተቶች በሰዎች ዘንድ ትኩረት የማይሰጣቸው ይመስላቸዋል። እውነታው ግን የሰውን ስም በማጠልሸት ወይም ስህተቱን በማጉላት የሚገኝ መወደድ እንደ ጤዛ ነው ከጊዜ በውሀላ ሀቁ መውጣቱ አይቀርም። መሠረቱ በሰው ውድቀት ላይ የተገነባ ማንነት መጨረሻው ፈራሽ ነው ስለዚህ ተወዳጆች የሰውን ስህተት ይዛችሁ ለመሮጥ አትጣደፉ ግድ የለም በመልካምነት በቅነነት የሰውን ድካም መሸፈን ይሻላል እሺ ተባረኩ!! | 431 |
| 3 | ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
— 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17 | 686 |
| 4 | የፊታችሁን ቆዳ በጥልቀት የሚያፀዳውን ፊታችሁን ለስላሳ እና ብሩህ የሚያደርገውን ለዕለታዊ አጠቃቀም ተስማሚ እየተጠቀምንበት ያለን ሰዎች በጣም የወደድነው ይሄን የፊት መታጠቢያ ብሩሽ ባልፈው እንደጨረስኩ ነገሪያችሁ ነበር አሁን ግን በብዛት ስላስገባው መግዛት ትችላላችሁ!
💰ዋጋ : 900
📩 ለማዘዝ : @SamriiGetu
✨ ነፃ ዴሊቨሪ በተወሰኑ አካባቢዎች አለን እንዲሁም ለነጋዴ በብዛት እና በቅናሽ እናስረክባለን!
🚨በቅርብ ጊዜ ውስጥ Giveaway ስለሚኖረን
ቻናላችንን ተቀላቀሉ https://t.me/Herglowbar
እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ! | 807 |
| 5 | ቀለበት በ200 ብር 😍
ቀለማቸውን የማይለቁ ውብ እና የተለያዩ ዲዛይን ያላቸው ቀለበቶችን ለዛሬ በታላቅ ቅናሽ ይዘንላችሁ መጥተናል። አንዱን ፍሬ በ200 ብር ብቻ እየሸጥን ነው።
👇 ለማዘዝ እና ለመግዛት ፦ @SamriiGetu
✨ አዳዲስ እቃዎችን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/Herglowbar | 1 011 |
| 6 | አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ
ሲገለጥ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ
አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ
ሲታይ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ
የኑሮዬ ለሊት እንዲነጋ የማውቅበት
የሕይወቴ ለሊት ማዳኑን የማይበት
ዝም ባለው በድቅድቅ ለሊት አጋዥ በሚያሻበት
ግራ ቀኝ እያየሁ ስጣራ ፈልጌ ረዳት
አምላኬ መንፈሴን አንቅቶ አበራልኝ እውነቱን
በከበበኝ ጨለማ መሃል አሳየኝ ምሕረቱን
በሰማይ ያሉ ከዋክብት ሲመሽ እንደሚደምቁት
ዙሪያዬ ሲጨልምብኝ የአምላኬን ማዳን አየሁት
ሊያባብለኝ በምድረበዳ ወሰደኝ
አስተምሮ አስተካክሎ ሊቀርፀኝ
በውዴ ላይ በርሱ ብቻ ተደግፌ
ይህች ማን ናት የሚሉኝን እንዳይ አልፌ
ያለኝን በሙሉ ወዲያ ማዶ
አሻገረው ብቻዬን ሊያይ ወዶ
ሲታገለኝ ቆየ በጨለማው
አስቸጋሪው ልቤን እስክረታው
ሥሜን ሊቀይር አድኖም ሊያስቀረኝ
የሁለት ክፍል ሰራዊት ሊያረገኝ
ሥርዓቱን እማር ዘንድ አስጨነቀኝ(4*) | 1 355 |
| 7 | ከማንኛውም አለባበስ ጋር የሚሄድ አለባበስሽን ይበልጥ የሚያሳምር ቀበቶ በተለያየ የከለር አማራጭ ከእኛ ማግኘት ትችላላችሁ!
ዋጋ: 400 ብር ብቻ
📩 ለማዘዝ @SamriiGetu
🚚 ዴሊቨሪ በተወሰኑ አካባቢዎች አለን እንዲሁም ለነጋዴ በብዛት እና በቅናሽ እናስረክባለን!
👉ቻናላችንን ተቀላቀሉ https://t.me/Herglowbar
🙏 እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ! | 1 166 |
| 8 | የማይካድ ሀቅ!!!
• ለራሳችሁ ፕሮግራም ካላወጣችሁ፣ ሰዎች ፕሮግራም ያወጡላችኋል፡፡
• የራሳችሁን ሕይወት ካልመራችሁ፣ ሰዎች ወደፈለጉበት ይመሯችኋል፡፡
• ሕይወታችሁን በመልክ በመልኩ ካላደረጃችሁት፣ የመጣውን ሁኔታ ሁሉ እየተቀበላችሁ ለመኖር ትገደዳላችሁ፡፡
• እቅድ አውጥታችሁ የምትከተሉት ነገር ከሌላችሁ፣ ከሁኔታዎች እንደሸሻችሁ ትኖራላችሁ፡፡
• ብዙ እምቅ ብቃት ኖሯችሁ ካለምንም እቅድ እና አደረጃጀት ከኖራችሁ፣ ምንም እውቀት የሌላቸውና የተደራጁት እንደነዷችሁ ትኖላችሁ፡፡
አስቡበት | 1 469 |
| 9 | የማትገመቱ ሰዎች ሁኑ ለሊት ትንሽ ልጸልይ ብላችሁ ተነሱና ስትፅልዩ በዛው አንጉ 😊 | 1 603 |
| 10 | ጥራት ያለው ላይክ ሂውማን በፈለጋቹት አይነት በ2800 ብር መረከብ የምትፈልጉ አናግሩኝ @SamriiGetu | 146 |
| 11 | ለ exit exam ተፈታኞች በሙሉ፤
ይኸው ረጅሙና አድካሚው የዩኒቨርሲቲ ጉዞ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ደረሳችሁ እግዚአብሔር ይመስገን ላለፉት ዓመታት ባሳያችሁት ጥረት፣ ያሳለፋችሁት እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች እና ባሳያችሁት ጽናት ዛሬ እዚህ ደርሳቿል ለዛም ጌታ ይባረክ። ነገር ግን እውነቱን ለመናገር በግቢ ከሚሰጠው የትምህርት ፈተና ይልቅ፣ በየቀኑ በዚያ ግቢ ውስጥ ያለውን ሕይወት፣ ብቸኝነትን፣ ተስፋ መቁረጥን ውጣ ውረዱንና ብዙ ግፊትን በሙሉ ተቋቁሞ፣ ተስፋ ሳይቆርጡ ዛሬ እዚህ መድረስ በራሱ ትልቅ ድል ነው! እናንተ ደግሞ ያንን ሁሉ ነገር ያሸነፋችሁ ጀግኖች ናችሁ። ይህ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የእውቀታችሁ መለኪያ ብቻ ሳይሆን የዚሁ የፅናታችሁ ማረጋገጫም ጭምር ነው። በዚህ ጊዜ በውስጣችሁ የሚፈጠረው ስጋት ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ አንድ ነገር ግን አትዘንጉእናንተ ከዚህ ፈተና በላይ የሆኑ ትልልቅ የሕይወት መሰናክሎችን አልፋችሁ እዚህ የደረሳችሁ ብርቱዎች ናችሁ! ተወዳጆች ዋናው ትልቁ እውነት ደግሞ ይህ ነው ይህ ፈተና ቢሳካም ባይሳካም፣ እናንተ እግዚአብሔር ካሰበላችሁና ካዘጋጀላችሁ ትልቅ ክብርና ቦታ ጋር መድረሳችሁ ፈጽሞ አይቀርም እውነት እኔ ለዚህ ምስክር ነኝ! ወድቆም አልፎም እንደሚያውቅ ሰው ከልቤ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር… ምናልባት ነገሮች እንደተመኛችሁት ባይሆኑ እንኳ፣ ነገ በፅናትና በተሻለ ዝግጅት እንደገና ተነስቶ ማለፍ ይቻላል። ሕይወት በአንድ ፈተና አታበቃምና መንፈሰ ጠንካሮች ሁኑ። እግዚአብሔር የልፋታችሁን፣ የድካማችሁንና የዕንባችሁን ዋጋ መቼም ቢሆን አይረሳውም! እርሱ ታማኝ ነው፤ በጊዜው መልካሙን ነገር ሁሉ ያደርግላችኋል። ስለዚህ አእምሯችሁን አረጋጉ በቂ እንቅልፍ ወሰዱ፣ ፀልዩ ልባችሁን በእግዚአብሔር ላይ ጣሉ እንዴት ታሪክ እንደሚሰራ ታያላቹ። ፈተናችሁን በድል እንድታጠናቅቁ፣ ውጤታችሁ ለእናንተም ለቤተሰቦቻችሁም ትልቅ ኩራት እንዲሆን ከልብ እንመኝላቹሀለው እግዚአብሔር ፍፃሜያቹን በድል ይቋጭላችሁ። 🎓✨
መልካም ፈተና 🥰 | 2 136 |
| 12 | በክፍል 5 «ሙያዊ እና ሥራ ፈጠራ እድገት (Career & Finance)»
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ጠንካራ፣ ባለሙያ እና ባለራዕይ ሴት ከተጻፉት ውብ ክፍሎች መካከል ምሳሌ 31 ዋነኛው ነው። ብዙ ጊዜ ይህ ጥቅስ ሲነሳ የሚታየን የቤት ውስጥ ሥራዎችን የምታከናውን ሴት ብቻ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ቃሉን በጥልቀት ስንረዳው ይህች ሴት ያልተሰማራችበት የሕይወት ክፍል የለም በጣም ትጉ ሰው ናት! ነገር ግን ሥራ ጉዳይ ስንመለከታት “እርሻውን ታያለች ትገዛዋለችም፤ በእጅዋም ፍሬ የወይን ቦታ ትተክላለች።... ሥራዋ መልካም እንደ ሆነ ታውቃለች፤ መብራትዋ በሌሊት አይጠፋም።” ( ምሳሌ 31፥16,18) ከዚህች ሴትም ሦስት ታላላቅ የሕይወት መርሆችን እናገኛለን፦
1.ዕድሎችን የማየትና የመተንተንን ብቃት እንማራለን፦ ጥቅሱ “እርሻውን ታያለች” ይላል። ዝም ብላ በስሜት አትገዛም፤ ቦታውን ታጠናዋለች፣ ለነገ የሚያወጣትን ትርፍ ትገምታለች። አንቺም ዛሬ በዙሪያሽ ያሉትን ክፍተቶችና የገበያ ዕድሎች በማጥናት ንቁ አእምሮ ሊኖሽ ይገባል።
2. ካላት ትንሽ ነገር መነሳትን እንማራለን (Reinvestment)፦ “በእጅዋም ፍሬ የወይን ቦታ ትተክላለች” ይላል። ይህ ማለት ከመጀመሪያው ሥራዋ ያገኘችውን የተረፈችውን ትርፍ (ፍሬ) መልሳ ሌላ ትርፍ ሊያስገኝላት ለሚችል ነገር ላይ ታደርጋለች እንጂ አታባክነውም። ለምታልመው ትልቅ ሕልም ትልቅ ካፒታል እስኪኖራት አልጠበቀችም፤ ካላት ትንሿ ፍሬ ተነስታ ነው ሰፊውን የወይን ቦታ የገነባችው። የኔ ቆንጆ አንቺም የሆነ ተአምር እስኪፈጠር አትጠብቂ ባለሽ ጥቂት ነገር በመነሳት ያሰብሽበት መድረስ ትቺያለሽ!
3. በሥራዋ ላይ ያላት እምነትና ጥራት (Confidence & Diligence)፦ “ሥራዋ መልካም እንደ ሆነ ታውቃለች” ይላል። የምትሠራውን ሥራ በጥራትና በልበ ሙሉነት የምታከናውን ናት!
ይህች መጽሐፍ ቅዱሳዊት ሴት የምታስተምረን ትልቁ ቁምነገር፣ አንዲት ሴት ራሷን ችላ ስትቆም፣ ስትሠራና ስታገኝ ይበልጥ ለቤተሰቧና ለችግረኞች የምትተርፍበትን አቅም እንደምታገኝ ነው ስለዚህ እህቴ፤ ፈጣሪ የሰጠንን ጊዜ፣ አእምሮና ጉልበት ተጠቅመን በታማኝነት መሥራት፣ መለወጥና ሀብት ማፍራት ዓለማዊነት ሳይሆን መንፈሳዊ መሆኑን አትዘንጊ። ሰነፍና ተመኪ መሆን ሰብአዊነትሽንም ሆነ መንፈሳዊ ማንነትሽን አይገልጽም። የሆነ ሥራ ስትጀምሪ ሥራ ምንም ሳትንቂ ስሪ ደግሞ ለመቶ ብር ትርፍ አይባልም ለምን 10 ብር አይሆንም ሲቸግርሽ ማን ሊሰጥሽ ነው ቆይ ሀቢቢ መስራት መለወጥ ግዴታሽ ነው ቤተሰብ ሚያረገውን አድርጎ እዚ አድርሶሻል አሁን ሕይወትሽን የማሻሻል ግዴታ ያለብሽ አንቺ ነሽ ሰበብ አታብዢ ዘጠኝ ምክንያት አትደርድሪ እሺ ወይ ደግሞ የሆነ ሃብታም ሰውዬ መጥቶ ነገር ዓለሜን ይቀይራል ብለሽ አትጠብቂ እሱም ቢሆን ግዴታ የለበትም እሺ የሆነ የጠባቂነት መንፈስ አይኑርሽ አንቺም ሙሉ ሰው ነሽ ከሰራሽ ገንዘብ የምር ላይኖርሽ የሚቺል ነገር አይደለም ደግሞ መስራት ግዴታሽ ነው በቃ እመኚ ልክ ነው የኛ ጊዜ ብዙ ነገር ለማድረግ ያስቸግራል ግን ደግሞ በዚህ ውስጥ ተፈጥረናል ምንም ማድረግ አንችልም በምንችለው አቅጣጫ መሮጥ ግድ ነው!
ደግሞም ራስሽን ማሳመን ያለብሽ ሌላኛው ነገር ሥራ ለመጀመር በሚሊዮን የሚቆጠር ብር፣ ትልቅ መጋዘን ወይም የቅንጦት ቢሮ አያስፈልግሽም። ዋናው ነገር የአስተሳሰብ ለውጥ እና ካለሽ ጥቂት ነገር መነሳት ነው። ዛሬ ባለንበት የዲጂታል ዘመን በእጅሽ ያለው ስማርት ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ለመለወጥ ያለሽ ጉጉት ትልቅ መነሻዎችሽ ናቸው። ሌላው መረሳት የሌለበት ነገር በአንድ ለሊት የሚመጣ ተአምር የለም እሺ ሥራ ላይ ሁሉም ነገር ጊዜ ይፈልጋል ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው!
ሥራ መጀመር ፈልጋችሁ ካፒታል ላጣችሁ እህቶቼ መነሻ ገንዘብ ብዙ ሳያስፈልጋችሁ ፎቶዎችን ቪዲዮ እየሰራችሁ በማህበራዊ ሚዲያ (በኦንላይን) ላይ በመሸጥ የራሳችሁን ትርፍ እየያዛችሁ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ! ተማሪዎች የቤት እመቤቶች, ተቀጣሪ ሰራተኞች ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም ብቻ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ! እንዲሁም ደግሞ ሥራ መጀመር ፈልጋችሁ ከምን መጀመር እንዳልገባችሁ ያላወቃችሁ እና ደግሞ affordable በሆነ ዋጋ የሚያቀርብላችሁ ሰው ከፈለጋችሁ ልታወሩኝ ትችላላችሁ! እንዲሁም ደግሞ እኔም የስራ ሌላ ቻናል እንዳለኝ ታውቃላችሁ https://t.me/Herglowbar እና ደግሞ የኔም ሥራ እዚህ ቻናል ላይ መጥቼ በማስታወቂያ ሳደክማችሁ ስላልሰለቻቹኝ ምስጋናዬ ከልብ ነው ከዚህ በውሃላም ስለምትረዱኝ አመሰግናለሁ ደግሞም 1 ወር ሳይላ 390 ሜምበር ደርሰናል እስቲ ቀለለል አድርገን 500 እናስገባት 😍 ደግሞም አዲስ አበባም ከአዲስ አበባ ውጪ ያላችሁ ደንበኞቼ በጣም አመሰግናለሁ ተባረኩልኝ ሌሎቻችሁም ደግሞ ቻናሉን Join, Share እያደረጋችሁ እንዲሁም እየገዛችሁ አበረታቱኝ አመሰግናለሁ 🥰
ነገ በክፍል ስድስት < ጤናማ ግንኙነቶች> በሚል ሃሳብ እንቀጥላለን 🌸
ይህንን መልእክት ለምትወዷቸው እህቶቻችሁ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ! 🌸🌷
https://t.me/lebamsetttt | 1 679 |
| 13 | Don’t let anyone told you that your dream wish and faith are breakable, unrealistic and foolish. Let them talk let them judge LET THEM.
በመቅደሱ ያወራችሁትን እናንተና እግዚአብሔር ናችሁ የምታውቁት፣ ለምትመኙት ልትኖሩት ለምትወዱት ሕይወት የከፈላችሁትን የምትከፍሉትን ዋጋ፣ ወጣትነት ደስታን ራስን ማሸነፍን ብዙ ነገር ታግላችሁ ችላችሁ መጠባበቃችሁን እግዚአብሔር እና እናንተ ናችሁ የምታውቁት። በልባችሁ ሀሳቡን ያኖረ እሱ ላይ እንድትፀኑ የረዳ የሚረዳ የጠየቁትን የማይረሳ ተስፋን የሰጠ ታማኝ እረኛ ሰጥቶ የማያልቅበት እጁ ሙሉ የሆነ እግዚአብሔር ነው የሚያውቅላችሁ ላይሰጥ የማያስመኝ የተሻለ የሚያሳስብ የሚሰጥም እርሱን ብቻ ለህልማችሁ ታመኑ ለራእያችሁ ጠብቁት።
መልካም ቀን ✨
የካቲት 2-2018 | 1 694 |
| 14 | https://youtu.be/pta8H27LIKU?si=IS5uyu2-146B8aUe | 1 610 |
| 15 | KHAMRAH LATTFA PERFUME 100ML
ዋጋ 3300
📩 ለማዘዝ DM @SamriiGetu
👉ቻናላችንን ተቀላቀሉ https://t.me/Herglowbar
🙏 እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ 🥰 | 77 |
| 16 | ጥራት ያለው ላይክ ሂውማን በፈለጋቹት አይነት ብዛት ከ 5 ጀምሮ በ2800 ብር መረከብ የምትፈልጉ አናግሩኝ @SamriiGetu | 2 001 |
| 17 | ቀለማቸው ማይለቁ የተለያዩ ዲዛይን ያላቸው ቀለበቶች
ዋጋ : ከ10 ፍሬ በላይ 200 በፍሬ 300
📩 ለማዘዝ DM @SamriiGetu
👉ቻናላችንን ተቀላቀሉ https://t.me/Herglowbar
🙏 እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ 🥰 | 1 679 |
| 18 | Pov : When you start trusting God in your life . | 1 548 |
| 19 | ✨ Olive Oil Hair Polisher
ፀጉርሽን ስትሰሪ ወይም ካክስ ስትገቢ በትንሹ ቆዳሽን እና ፀጉርሽን ተቀብተሽ ትገቢያለሽ ፀጉርሽ ወዛማ፣ ለስላሳ እና የሚያበራ እንዲሆን ያደርጋል
እንዲሁም ፀጉርሽን ካክስ ስትገቢ ምንም ባለመቀባትሽ ምክኒያት የሚወጣውን ነጭ ነጭ ነገር (flaking) በጣም እንዲቀንስ ያግዛል ከእሳት የሚመጣውን heat damageing ጉዳትም ይከላከላል ከተሰራሽ በኋላም ብትቀቢው ፀጉርሽ የበለጠ ውብና ወዛማ እንዲሆን ያደርጋል ይሆናል!
እኔም እየተጠቀምኩበት ነው ወድጄዋለሁ 🙏
ዋጋ : 800 ብር
📩 ለማዘዝ DM @SamriiGetu
👉ቻናላችንን ተቀላቀሉ https://t.me/Herglowbar
🙏 እንዲሁም ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ 🥰 | 1 386 |
| 20 | ክፍል (4)፦ ራስን መውደድ እና መንከባከብ (Self-Care) 💖
ለመሆኑ ራስን መንከባከብ ማለት ምን ማለት ነው?
ራስን መውደድ እና መንከባከብ ማለት አንድ ሰው የራሱን ሰውነት፣ አእምሮ እና መንፈሳዊ ሕይወት በጤናማ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያደርጋቸው ዕለታዊ እንክብካቤዎች ናቸው።**
ብዙዎቻችን “ራስን መንከባከብ” ሲባል ውድ ውበት ሳሎን መሄድ ወይም ብራንድ ልብሶችን መግዛት ብቻ ይመስለናል። ነገር ግን እውነተኛ ራስን መንከባከብ በየቀኑ ከምንወስናቸው ትናንሽ ምርጫዎች ይጀምራል። ራሷን የማትንከባከብ ሴት ለሌላው ሰው መትረፍ አትችልም። ልክ በአውሮፕላን ጉዞ ላይ “አደጋ ሲያጋጥም መጀመሪያ የኦክስጅን ጭምብሉን ለራስሽ አድርጊ፣ በመቀጠል ለሌሎች አድርጊ” እንደሚባለው ሁሉ፤ እኛም መጀመሪያ ራሳችንን በሰላም፣ በጤና እና በጥንካሬ ካልሞላን ለቤተሰባችንም ሆነ ለሥራችን የምንሰጠው የተሟላ አቅም አይኖረንም።
ታዲያ አንዲት ወጣት ሴት ሦስቱን የሕይወት ዘርፎች በየቀኑ ለመንከባከብ ልታደርጋቸው የሚገቡ ዕለታዊ ልምዶች ምንድናቸው?
1. የአእምሮ ዕለታዊ እንክብካቤ (Mental Self-Care)
= ማህበራዊ ሚዲያ ወሰን ማበጀት፦ጠዋት ገና ዓይናችን ሲገለጥ ስልካችንን ከማንሳት መቆጠብ እና ከመተኛታችን 1 ሰዓት በፊት ማህበራዊ ሚዲያን መዝጋት። ይህ አእምሮ በቀን መጀመሪያና መጨረሻ ላይ እረፍት እንዲያገኝ ያደርገዋል።
= ራስን በበጎ ቃላት መመገብ (Self Talk)፦ ራስን በበታችነትና በፀፀት ስሜት ከመውቀስ ይልቅ፣ “ዛሬ መልካም ቀን ይሆንልኛል፣ እኔ ብቁ ነኝ፣ ከስህተቶቼ እማራለሁ” በማለት አእምሮን ማበረታታት።
=ለራስ ርኅራኄ ማሳየት (Self Compassion)፦ እህቴ እዚህ ምድር ላይ ከስህተት የፅዳ ፍጹም ሰው የለም። ስህተት በሠራሽ ጊዜ ራስሽን በጥፋተኝነት ስሜት ከመግረፍ ይልቅ፣ ለራሽ ይቅርታ ማድረግና ከስህተትሽ መማር ነው ያለብሽ።
2. የሰውነት ዕለታዊ እንክብካቤ (Physical Self Care)
= በቂ ፈሳሽ መውሰድ ፦በቀን ውስጥ ቢያንስ 2 ሊትር ውሃ በመጠጣት ለሰውነታችን የሚበቃንን ያህል ፈሳሽ መውሰድ።
=ቀላል ዕለታዊ እንቅስቃሴ፦በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ያህል በፈጣን እርምጃ መራመድ ወይም ቤት ውስጥ ቀለል ያሉ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን መስራት።
=በቂ እንቅልፍ መተኛት ፦ በየዕለቱ ከ7-8 ሰዓት በተመሳሳይ ሰዓት መተኛት። በቂ እንቅልፍ ለቆዳችን ውበት፣ ለሰውነታችን ጥንካሬና ለአእምሯችን መረጋጋት የመጀመሪያው ሚስጥር ነው።
3. የመንፈሳዊ እና የማህበራዊ ሕይወት እንክብካቤ (Spiritual & Social)
= የማለዳ ጸሎት እና ቃልን ማሰላሰል፦ ቀኑን ከመጀመራችን በፊት ለጥቂት ደቂቃዎችን ለመፀለይ እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ቢያንስ አንድ ጥቅስ ማንበብ እና ማሰላሰል።
= ጤናማ ወሰን ማበጀት (Boundaries)፦ ሰላምሽን ለሚሰርቁ፣ ጊዜሽን ለሚያባክኑ ወይም ጉልበትሽን ለሚበዘብዙ (Toxic) ሰዎችን መራቅ እና የማትፈልጊውን ነገር በይሉኝታ ማደረግን አልፈልግም ማለትን መለማመድ ቆንጅዬ ይህ ንፉግነት ሳይሆን ራስን መውደድ ነው :: ቆንጂዬ ራስሽን ካልወደድሽ፣ ካልተንከባከብሽና ካላከበርሽ ሌላውን ሰው እንዴት አድርገሽ በትክክል መውደድና ማክበር ትችያለሽ? ፈጣሪ የሰጠሽን ውድ ሕይወት (ሰውነትሽን፣ አእምሮሽንና መንፈስሽን) ማክበርና በጤናማ መንገድ መያዝ እግዚአብሔርን ማምለኪያ አንዱ መንገድ ነው።
ነገ ማታ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ በክፍል 5 «ሙያዊ እና ሥራ ፈጠራ እድገት (Career & Finance)» ላይ እንወያያለን!
ይህንን መልእክት ለምትወዷቸው እህቶቻችሁ ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ! 🌸🌷
https://t.me/lebamsetttt | 1 231 |
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
