Hasen Injamo
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye
إظهار المزيد📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Hasen Injamo
تُعد قناة Hasen Injamo (@haseniye) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 017 مشتركاً، محتلاً المرتبة 7 928 في فئة الاقتصاد والمالية والمرتبة 2 351 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 017 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 19 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 66، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -7، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 30.93%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 13.16% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 645 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 976 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 32.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::
https://telega.io/c/Haseniye”
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 20 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الاقتصاد والمالية.
جارٍ تحميل البيانات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 20 أكتوبر | +1 | |||
| 19 أكتوبر | +1 | |||
| 18 أكتوبر | +4 | |||
| 17 أكتوبر | +6 | |||
| 16 أكتوبر | +8 | |||
| 15 أكتوبر | +4 | |||
| 14 أكتوبر | +2 | |||
| 13 أكتوبر | +3 | |||
| 12 أكتوبر | +4 | |||
| 11 أكتوبر | +2 | |||
| 10 أكتوبر | +4 | |||
| 09 أكتوبر | 0 | |||
| 08 أكتوبر | +3 | |||
| 07 أكتوبر | +4 | |||
| 06 أكتوبر | +29 | |||
| 05 أكتوبر | +24 | |||
| 04 أكتوبر | +1 | |||
| 03 أكتوبر | 0 | |||
| 02 أكتوبر | +1 | |||
| 01 أكتوبر | +2 |
| 2 | ቅን አሳቢ ሞልቷል እኮ | 1 358 |
| 3 | አንዳንድ ሕግ አስከባሪ ለ50 ሰከንድ እንኳ አደብ የለውም:: በአደባባይ, ትራፊክ ፖሊስ ባለበት, በርካታ መኪናዎች ተደርድረው ለሕግ ተገዢ ሆነው በሚጠባበቁበት ወለል ባለ ሜዳ V8 የያዙ most likely ባለሥልጣናት ወይም ልጆቻቸው በጥቁር ስቲከር ተነቅበው በ2 ቁጥር ታርጋ .. መብራት ይጥሳሉ:: ዝም ብለን ስናሰላው ቢሮኣቸው ውስጥ ምን ጉድ እየሠሩ ይሆን? ትራፊክ ፖሊሱን እንኳ አያስፈቅዱም:: ትራፊክ ፖሊሶችም ይፈራሉ:: ዘወር ብለው አሮጌ መኪና, የራይድና የጭነት መኪኖችን ያሳድዳሉ:: ያመናጭቃሉ:: የበላይ ሕግ አስከባሪ የሚባሉት ለሰከንዶች መታገስ እያቃታቸው ሀያና ሠላሳ ዓመታት በችግር የታገሱ ሰዎች ግን መመሪያና ዱ^ላ ይበዛባቸዋል:: ምእመኑ ከማን ምን ይማር? በለውጡ ሰሞን ባለሥልጣናት ከእንግዲህ ላንድ ክሩዘር አይዙም ተብሎ አሁን ግን ጭራሽ ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ መብራቱን እንዳሻቸው እየጣሱ ይረግጡታል:: ይህ ጥ^ጋብ መቸም ከላይ የወረደ እንዳልሆነ እንገምታለን:: ታዲያ የታችኞቹን ማስታገስ እንዴት ተሳነ? ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ቸኩለው ነው ካልክ ይብሳል:: ምክንያቱም ያለእቅድ ነው የሚጠዳደፉት ማለት ነው:: | 1 354 |
| 4 | ይልቃል ጌትነት በሰማያዊ ፓርቲ ይሁን በግራጫ ፓርቲ ምክንያት ታስሮ የረሃብ አድማ መታ:: ከዚያ ሊሞት ሲል ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በነፍሱ ደረሱና:-
ይልቅስ ይልቃል አሉት ... ድፍን ሀገሩ ረሃብተኛ በሆነበት ሀገር የረሃብ አድማ ብትመታ መሳቂያ ነው የምትሆነው:: ዜና እንድትሆን ከፈለግህ የጥጋብ አድማ መተህ ሰውነትህ መለስ ብሎልህ ስትወዛ እነተፈራ ዋልዋ እነደብረ ጽዮን እርሱ ይፈታና እኛን እሰሩን ብለው እጣ ይጣጣሉብሃል ብለውት መብላት ጀመረ ይባላል::
ብቻ ስጋ ያለመብላት አድማ የጠሩት የኤአይ በሬዎችና ጅቦች ይሆኑ እንዴ? ዛሬ በሄድኩበት ሁሉ ኤስ ኤች ዩ RO ሆነብኝ:: | 2 150 |
| 5 | ሁሉንም ፈትኑ::
የተመቻችሁን ያዙ::
=====
1. ኤቲስት (Atheist - ኢ-አማኝ)
አመለካከት: "አምላክ ወይም ፈጣሪ የለም" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ማንኛውንም የተፈጥሮ በላይ ኃይል ወይም አምላክ አይቀበልም። የዓለምን መፈጠር እና መንቀሳቀስ በተፈጥሮ ሕጎች እና በሳይንሳዊ መረጃዎች ብቻ ይረዳል::
2. ቴይስት (Theist - አምላክ አምላኪ / አማኝ)
አመለካከት: "ዓለምን የፈጠረ እና አሁንም የሚመራ አምላክ አለ" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: አምላክ ከፍጥረቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው (ጸሎት ይሰማል፣ ተአምራትን ያደርጋል፣ ነቢያትን ይልካል) ብሎ ያምናል።
3. አግኖስቲክ (Agnostic - ተጠራጣሪ / ያልወሰነ)
አመለካከት: "የአምላክ መኖር ወይም አለመኖር በሰው ልጅ አእምሮ ሊታወቅ አይችልም" ይላል።
መግለጫ: አምላክ ለመኖሩም ሆነ ላለመኖሩ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ የለም ብሎ ስለሚያስብ "አምላክ አለ" ወይም "የለም" ብሎ እርግጠኛ ከመሆን ይቆጠባል።
4. ዲይስት (Deist - የተፈጥሮ አምላክ አማኝ)
አመለካከት: "አምላክ ዓለምን ፈጥሯል፤ ነገር ግን አሁን ጣልቃ አይገባም" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ፈጣሪ ዓለምን እና የተፈጥሮ ሕጎችን ፈጥሮ እንደ ሰዓት ካስኬደ በኋላ ትቷታል። ጸሎት፣ ተአምራት ወይም ሃይማኖታዊ መጻሕፍት አያስፈልጉም ብሎ ያምናል።
5. ፓንቴይስት (Pantheist - ተፈጥሮ-አምላኪ)
አመለካከት: "ዓለም/ተፈጥሮ እና አምላክ አንድ ናቸው" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: አምላክ ከዓለም ተለይቶ የሚኖር አካል ሳይሆን፣ አጽናፈ ዓለም (Universe) እና ተፈጥሮ በሙሉ እራሱ አምላክ ነው ብሎ ያምናል።
6. ሚሶቴይስት (Misotheist - አምላክ ጠሊ)
አመለካከት: "አምላክ አለ፤ ነገር ግን ክፉ/ጨካኝ ስለሆነ እጠላዋለሁ" ይላል።
መግለጫ: በአለም ላይ ያለውን መከራ እና ስቃይ በማየት አምላክ እንዳለ ቢያምንም፣ አምላክን እንደ አፍቃሪ ሳይሆን እንደ ጨካኝ ወይም ኢ-ፍትሐዊ አካል አድርጎ ይመለከተዋል፤ ስለዚህም ይጠላዋል።
7. ሄኖቴይስት (Henotheist - ከአንድ በላይ አማልክት ባሉበት አንዱን አብልጦ አምላኪ)
አመለካከት: "ብዙ አማልክት እንዳሉ ይቀበላል፤ ነገር ግን አንዱን ዋና አምላክ አድርጎ ያመልካል"።
መግለጫ: የሌሎችን አማልክት ህልውና ሳይክድ፣ ለእሱ ወይም ለወገኑ ግን አንዱን የተወሰነ አምላክ ብቻ የላቀ አድርጎ ያመልካል።
8. ፖሊቴይስት (Polytheist - ብዙ-አማልክት አምላኪ)
አመለካከት: "ከአንድ በላይ የሆኑ ብዙ አማልክት አሉ" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: እያንዳንዱ አምላክ የየራሱ የኃይል ወይም የተፈጥሮ ክፍል (የዝናብ፣ የፀሐይ፣ የጦርነት አምላክ...) አለው ብሎ ያምናል። (ለምሳሌ፦ የጥንታዊ ግሪክ እና ሮማውያን እምነት)።
9. ሞኖቴይስት (Monotheist - አንድ-አምላክ አምላኪ)
አመለካከት: "በእውነት ያለ እና የሚመለክ አምላክ አንድ ብቻ ነው" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ከእሱ ውጭ ያሉ አማልክትን በሙሉ የሉም ወይም ሀሰተኛ ናቸው ብሎ ይኖራል።
10. ፓነንቴይስት (Panentheist - አምላክ በተፈጥሮ ውስጥ እና ከዚያም በላይ)
አመለካከት: "ዓለም በአምላክ ተከቦ ይኖራል፤ ነገር ግን አምላክ ከዓለም ይበልጣል" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ተፈጥሮ የአምላክ አካል ቢሆንም፤ ግን አምላክ ከፍጡራኑ እና ከአጽናፈ ዓለም ወሰን በላይ የሆነ የራሱ ህልውና አለው ብሎ ያምናል። (ወሃb እዚህ ግድም ይመደባል)
11. ኦቶቴይስት (Autotheist - እራስ-አምላኪ)
አመለካከት: "እራሴ ወይም የሰው ልጅ እራሱ አምላክ ነው" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: ከውጭ የሚጠበቅ መንፈሳዊ ኃይል የለም፤ የሰው ልጅ የራሱ ህይወት፣ እጣ ፈንታ እና መንፈሳዊነት የበላይ ገዢ እራሱ ነው የሚል አስተሳሰብ ነው።
12. ዲስቴይስት (Dystheist - አምላክ ሙሉ በሙሉ መልካም አይደለም)
አመለካከት: "አምላክ አለ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ቸር/መልካም አይደለም" ብሎ ያምናል።
መግለጫ: አምላክ ፍጹም መልካም እንዳልሆነ እና አንዳንዴም ክፉ ወይም ግራ የሚያጋባ ባህሪ ሊኖረው እንደሚችል እንደ ፍልስፍናዊ እውነታ ይቀበላል።
13. ኢግኖስቲክ (Ignostic - የትርጉም ጥያቄ አቅራቢ)
አመለካከት: "'አምላክ' የሚለው ቃል ግልጽ የሆነ ትርጉም ስለሌለው ስለ እሱ መከራከር ትርጉም የለውም" ይላል።
መግለጫ: አምላክ አለ ወይም የለም ብሎ ከመከራከር በፊት "ለመሆኑ አምላክ ማለት ምን ማለት ነው?" የሚለው ትርጉም በግልጽ ካልተበየነ በቀር ውይይቱ ፍሬ አልባ ነው ብሎ ያምናል።
14. አፓቴይስት (Apatheist - ደንታ-ቢስ)
አመለካከት: "አምላክ ቢኖርም ባይኖርም ለእኔ ምንም አያግደኝም/አያስጨንቀኝም" ይላል።
መግለጫ: የአምላክ መኖር ወይም አለመኖር በሰው ልጅ እለታዊ ህይወት ላይ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም ብሎ ስለሚያስብ ስለ ጉዳዩ ማሰብም ሆነ መከራከር አይፈልግም። | 2 251 |
| 6 | <<በቤት ኪራይ ተሰቃየን:: መሄጃ አጣን:: እሺ መሬት ስጡን:: አዲሱ ትውልድ የት እንግባ>> እያለች ታለቅሳለች:: ይህ የሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው:: 1968 ላይ መሬት ላራሹ ተብሎ አዋጅ ታውጆ ትውልዱ መሬት አገኘ:: ከዚያ ወዲህ መሬት የሚባል ነገር አልተሰጠም:: መንግሥት መሬትን የሚያህል ሀብት አንቆ ይዞ ሊደባ^ደብ የሚሄደው የግለሰብ አከራዮች ጋር ነው:: መንግሥት ብር, መሬት, ቀረጥ, ሕግ ሁላ ይዞ ያልቻለውን መንግሥታዊ ሪል ኢስቴት ማለትም ኮንዶሚኒየም ሳይሰጥ... የግል አልሚዎች ካላሟላችሁ ይላል:: መንግሥት መሬትን በአግባቡ ማደል ሲገባው በሊዝ ያከራያል:: ትውልዱ ይሰቃያል:: ቢቸግራቸው ተሰደው ለፍተው መጥተው የወጠሩትንም ላስቲክ ያፈርሱባቸዋል:: መንግሥት መሬት ይስጥ, ኮንዶሚኒየም ይገንባ, የግሎችም የተረፈውን ይሸፍኑ:: በዋለ ባደረ ቁጥር ትውልዱ እየጨመረ የቤት ግንባታ ባለበት ቆሞ ወይም ቀንሶ እንዴት ሊጣጣም ይችላል? መጠለያ መሠረታዊ ፍላጎት ስለሆነ ወደድንም ጠላንም አብዮት ያስነሳል:: ምግብ መሠረታዊ ስለሆነ አብዮት ያስነሳል:: | 2 406 |
| 7 | በመደበኛ ባንክ እና በወለድ በነጻው ባንክ መሃል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ስጋትን (Risk)ን መጋራት ነው::
መደበኛውና ለዘመናት የምናውቀው ባንክ በተወሰነ መልኩ ስጋት (risk) ይጋራል:: ለቆጣቢ መጠነኛ የግሽበት ማካካሻ ይሰጣል:: ከተበዳሪም በኩል ያልሠሩበትን ዘመን ትርፍ አያስከፍልም:: ውሉም ግልጽ ነው::
ወለድ በነጻው ግን በፍጹም ስጋት (Risk) አይጋራም:: ቆጣቢ ብር በነጻ ያመጣል:: ተበዳሪም "የተሸጠ ዕቃ አይመለስም" በሚል አሠራር ያልሠራበትን ዘመን ትርፍ ይከፍላል:: ባንኩ ብር ማከራየቱን ባላየ ለማለፍ ሲሚንቶ ወይም ብረት ልግዛልህ ይላል:: ከደሃ ቆጣቢ ደግሞ ሲሚንቶ ቆጥቡ ... ብረት ቆጥቡ አይልም:: አታሎ በነጻ ይቀበልና በትርፍ ያበድራል:: ውሉ እጅግ የተቀሸበና ግልጽነት የጎደላቸው አናቅጽ አሉበት:: ብዙ ውሎች እጄ ላይ ስላሉ ነው:: የኢስላም ሕግጋትን በጽኑ ይጻረራሉ:: ባንኩ በመደበኛው አሠራር ሲጋራቸው የነበሩ ስጋቶችን (Risks) ከራሱ ላይ ሲያሸሽ ወለድ በነጻ ይሆናል:: በነገራችን ላይ ከቲዎሪው በተቃራኒው ነው:: ሙዷረባን እንዴት 180 ዲግሪ እንደገለበጡት ፊያት መገበያያና ወለድ መጽሓፍ ላይ በዝርዝር አለላችሁ:: | 2 321 |
| 8 | ለፋይናንስ ሲስተሙ ግማሽ መንገድ (50%) ለመጓዝ ቤት መግዛት ነው ተባብለናል:: ታዲያ ቤት ስትገዙ ሁለት ነገሮች መሟላታቸውን ከግምት አስገቡ:: አንደኛው ዲጂታል ካርታ መያዙን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ካርታው የያዘው ማነው? የሚለው ነው:: ባለይዞታው አሁናዊ የትዳር ሁኔታው ወሳኝ ነው:: ተፋተው ወዲያው ያላገባ ሊያወጡ ይችላሉ:: የንብረት ክፍፍል ውሳኔ ከነአፈጻጸሙ ካልያዙ ዱዲ መክፈል አያስፈልግም:: እዚሁ ጋር የእዳ, ዋስትናና እግድ ጉዳዮች ይታያሉ:: ከእነዚህ ሁሉ ጽድት ያለ ካላገኘህ መክፈልህ ቤት አለኝ አያስብልህም:: ለሪል ኢስቴት ቀብድ ከከፈልክ ቤት ሳይሆን ኢንቨስትመንት ነው:: በአንዴ ከምከፍል እየሠራሁ ቤት ይኑረኝ ዐይነት ነገር ነው:: ታማኝ አልሚ ካገኘህ እድለኛ ነህ:: በሒደት ቤት ይኖርሃል:: ካላገኘህ ግን በርቶብሃል:: ሿሿ ላይ ነህ:: ውሱን ጥሩ አልሚዎች አሉ:: እነርሱም በሚወጡ ሕጎችና መመሪያዎች ሊወላከፉ ይችላሉ:: ገንብተው ካርታ ለመበተን ቢያንስ የውስጥ ፓርቲሽን መጨረስ አለባቸው:: ለየቤቱ ስም ለማዞር በርና መስኮት ገጥመው የመጠቀሚያ ፈቃድ አውጥተው ከገቢዎች ክሊራንስ መጨረስ አለባቸው:: ምሳሌ:- አንድ ሕንጻ 60 ቤቶች ቢኖሩት 60 ሽንሽን ካርታ እና 60 የገቢዎች ክሊራንስ ይኖሩታል:: ክሊራንሱ የሚያገለግለው ለሦስት ወራት ብቻ ነው:: ባንኮች የሚሰሙህ ዲጂታል ካርታ ስትይዝ ብቻ ነው:: ቤቱ የሌላ ሰው ከሆነ የብድር ዋስ ሊሆንህ ይችላል:: እናልህ ካርታ የሌለው ስቴዲዮም አለኝ ከምትል ሰነዱ ጽድት ያለ ስቱዲዮ ይሻልሃል:: የሀብታምነት ጉዞ ላይ 50% ደርሰሃል:: ቀሪው ንግድ ፈቃድ አውጥቶ ቢዝነስ መሥራት ነው:: (መ-ገንዘብ 2 እና 3 ይህንን ያስረዳሉ):: | 2 636 |
| 9 | coffe_order_en_new.jpg | 2 529 |
| 10 | አሁን በቅርብ ያለው ስልጠና ይህ ብቻ ነው:: ኢምፖርት ግን እናሳውቃለን:: | 2 644 |
| 11 | ''Finance for Non-Finance Managers''
ለ 3 ቀናት
ጥቅምት 10, 11 እና 12
ጠዋት
ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር
ACC. No. 1000762139646
HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
1. በድርጅቱ ድረ-ገጽ
www.hab.et/register
ወይም
2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
3. 🤳 +251990555599 | 2 548 |
| 12 | ''Finance for Non-Finance Managers'' ለ 3 ቀናት ጥቅምት 10, 11 እና 12 ጠዋት ክፍያ: ቫትን ጨምሮ 13,800 ብር ACC. No. 1000762139646 HAB Management and Technologies
መመዝገቢያ ሊንክ:
በድርጅቱ ድረ-ገጽ www.hab.et/register
ወይም 2. በቴሌግራም
t.me/hab_management
🤳 +251990555599 | 1 |
| 13 | ከስልጠና ወደ ስልጠና ያለረፍት እየተጓዝን ነው:: ከሁሉም የሚገርመው 5 የተለያዩ ዓይነት ስልጠናዎችን አዘጋጅተን ቢያንስ ሦስቱን የተሳተፉ ብዙ ናቸው:: አምስቱንም የወሰዱ አሉ:: ሳናውቀው ለካ ብዙ ቤተሰብ አለን:: ደስ ይላል:: ይህኛው ፎቶ ከትናንትና ወዲያ ሐሙስ የተጠናቀቀው የኢምፖርት ስልጠና ነው:: የኢምፖርት ይቀጥላል:: የትራንዚቱን በትራንዚተር ብቻ ሳይሆን ጉምሩክ በሠሩና በቂ ስልጠና ባላቸው አሰልጣኞች ... የውጭ ምንዛሪ ላይ ምርጥ በሚባሉ ባንኮች የ International Banking Divisions ባለሙያዎችን ... የ Single windowsም እንደዚያው በባለሙያ ... የቻይናውም ከቻይና Live እንገባለን:: ሌላውም በሚመለከተው ክፍል ነው የሚሰጠው:: ዳሸን ባንኮች ገራሚ ስልጠና ነው የሰጡልን:: አንድ እርምጃ የቀደመ ስልጠና::
_
Finance for non-financial managers የሚል ስልጠና የፊታችን
ማክሰኞ, ረቡዕና ሐሙስ
የሦስት ግማሽ ግማሽ ቀናት ስልጠና አለ::
ምዝገባ መጨረሻው ቀን ላይ ነን::
ቦታ አዲስ አበባ አፍሪካ ሕብረት አካባቢ
በአካል ብቻ | 2 466 |
| 14 | መ-ገንዘብ መጽሓፍ ከፍሎ በወቅቱ አድራሻ በትክክል ጽፎ ያልተላከለት ያለ አይመስለኝም:: እስካሁን ያልደረሰው ምእመን
- ወይ ፖስታ ቤቶች ሲደውሉ ስልኩ ዝግ የሆነ
- ወይ ወትሮም አድራሻ ያልሞላና ዘግይቶ ሰጥቶን ፕሮሰስ ላይ ያለ
- ወይ ከነጥራሹኑ ያልሰጠን
- ወይ Bot ላይ ሲሞላ የሆነ ለተወሰነ ሰዓታት ክራሽ ያደረገ ወቅት ነበር:: ያኔ ሞልቶ ሳይደርሰን የቀረ::
ቢሆንም ቢሆንም 99% ፐርሰንት በላይ ለከፈለ አድርሻለሁ:: የቀረ ምእመን በክብር የማድረስ ውዴታ አለብኝ:: መጨረሻ ላይ አድራሻ ሰጥታችሁኝ ያልተላከ እጅግ few የሚባል ሰው አለ:: አጣራና በቅርቡ እልካለሁ:: ማጣሪያው ነው የሚያደክመው:: እንዳያመናጭቁዋችሁ እኔው እራሴው ነኝ የማስተናግደው::
ያልገዛ ግን ጃእፈር ጋር | 2 241 |
| 15 | መኖሪያ ቤት ከምትገዛ በብሩ ነግድበትና በትርፉ ቤት ትገዛለህ ይባል ነበር:: በወቅቱ ስህተት ላይሆን ይችላል:: ምክንያቱም ግሽበት ብዙም ስላልተስፋፋ የእቃ ይሁን የቤት ዋጋ ጭማሪ ብዙም አይራመድም ነበር:: አሁን ግን ተቃራኒው ነው ያለው:: ስለዚህ አሁን ደግሞ እጅህ ላይ ባለው ብር ቤት ትገዛና ቤቱን አስይዘህ በሞኝ የቁጠባ ብር ትነግዳለህ:: ይህ ሲባል ከሰው ሰው ይለያያል:: ሥራህ ፈጣን ትርፍ የሚያመጣበት ወቅት ላይ ከሆንክ ንግድህን አጧጡፍ:: ግን ቤት ለመግዛት አትዘግይ:: ምክንያቱም ከባንክ የመጀመሪያውን ብድር ለማግኘት ያለው ውጣ ውረድ ቀላል አይደለም:: ከዚያ ግን የሞባይል ካርድ መሙላት በለው:: ቤት ግዛ ስልህ ደግሞ አደራ:: ዲጂታል ካርታ የያዘና የባለቤትነት ችግር የሌለበት ማለትም ባለትዳሮች የተስማሙበት እና የውርስ ችግር የሌለበት ይሁን:: ይሄ ሪል ኢስቴት ላይ ቀብድ ከፍሎ ቁጭ ማለት ክሪፕቶከረንሲ ላይ የሆነ ብር ቀርቅረህ የሚሆነውን እንደመጠባበቅ ነው:: እርሱን ታማኝ ገንቢ ካገኘህ እና እንደ ኢንቨስትመንት ከቆጠርከው ጥሩ ሊሆን ይችላል:: ቀስ እያልክ ቤት ይኖርሃል:: ይህኛው ባንዴ መግዛት ለማይችል እና ባወጣው ያውጣው ለሚል ነው:: እርሱን አላልኩም:: እኔ እያወራሁ ያለሁት ስለፋይናንስ እና ታክስ አድቫንቴጅ ነው:: አስማት የሚመስለውን የእድገት ምሥጢርን ነው:: ጅብ ግልቢያ ሁሁይ የለውም:: Pure ማትስ ነው:: በራስህ ንጹሕ ብር ግንባታውም ሰነዱም የተጠናቀቀ ቤት ትገዛና ብሩን በንግድ ፈቃድህ በኩል ትስበዋለህ:: ይህንን multiply ✖️ ማድረግ ነው::
መኪና አስቀድሞ መሯሯጥ የሚመርጥ ይኖራል:: ይህም ስህተት ላይሆን ይችላል:: የፋይናንስ ሥርዓቱ መቆሚያ ሁለቱ እግሮች ኢንተረስና ታክስ ናቸው:: እነርሱን ነው የምታጫውተው:: | 3 528 |
| 16 | የግብርና ባንክ በቅርቡ እንደሚቋቋም ሰምተናል:: በጣኣኣኣኣም ደስ ይላል:: እኔ ላቋቁመው ሳይሆን ላስቋቁመው ብዙ ወትውቻለሁ:: ምክንያቱም በግለሰብ ደረጃ የሚቋቋም ተራ ባንክ አይደለም:: እጅግ በጣም ግዙፍ እና ሀብታም ባንክ ስለሆነ ብዙ ዝግጅት የሚፈልግ ነው:: መንግሥት ቀድሞም አስቦበት ይሆናል አላውቅም:: እንደዚያ ነው ብለን እናስብ:: የእኔ አካሄድ የሚመለከታቸው የመንግሥት ቢሮዎች በአንክሮ እንዲመለከቱት ማድረግ በመሆኑ ቀዳማይ ታርጌቴ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የመንግሥት ሚዲያ አደረግሁ:: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስፈለገው ካሪኩለም እንዲያሻሽል ሲሆን የመንግሥት ሚዲያ ደግሞ ስለባንኩ ምንነት እንዲያስረዳ ነበር:: ለዚህም ETVን በተለይ ጋዜጠኛ አብርሃምና የዝግጅት ክፍሎችን አመሰግናለሁ:: ቀጣይ የነበረው የግብርና ሚኒስቴር እና ብሔራዊ ባንክ ነበሩ:: ለዚህም Concept note አዘጋጅቼ ሞቅ ያለ ፕሮግራም ልናዘጋጅ ሰነዶቹን ልኬ ነበር:: ችግሩ ስሜን አልጽፍበትም:: ማንም ይጀምረው ማን ዋናው መጀመሩ ነው::
እኔ በሠራሁት ጥናት ግብርና ባንክ በጣም ሀብታም ባንክ ነው:: ምክንያቱም የሀብቱ ምንጭ ፊያት ሳይሆን ምርት ነው:: ማእድናትም ጭምር ስከሚያካልል ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚለምኑት ከግብርና ባንክ ነው:: ፔፐሩን ከፈለጋችሁ በኮሜንት አለላችሁ::
ሙሉ ፔፐር 👇🏼👇🏼👇🏼
https://etd.aau.edu.et/server/api/core/bitstreams/d2a9e377-3330-48ac-9ea5-b4b0593b8820/content
👇🏼👇🏼👇🏼ከጆርናል
www.ijmdrr.com/admin/downloads/070820234.pdf | 3 963 |
| 17 | https://youtu.be/EKldyKCjsv0?si=H85HL6dXtpUvDTaY | 4 152 |
| 18 | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ CBDC እጀምራለሁ ብሏል:: CBDC ምንድነው? ከንግድ ባንክ ዲጂታል መገበያያ በምን ይለያል? ይህንን ነጥብ ለታዳጊዎች በሚገባ ቋንቋ ሳይቀር ጽፌዋለሁ:: ለልጆች በሚገባ መልኩ መጻፍ ይከብድ ነበር:: ያው ግን ተወጥቼዋለሁ:: በአዋቂዎችም በታዳጊዎችም መጽሓፍ ውስጥ አለላችሁ:: የገዛችሁ ሰዎች መልሳችሁ ገርቡት:: BRICS ደግሞ እንደ መገበያያ ያስቀመጠው ወርቅ የደገፈው CBDC ነው:: ብሪክስ ግብይቱ ከንግድ ባንክ ይልቅ ብሔራዊ ባንክ ጋር ይሆናል:: ብሔራዊ ባንክ ከወርቅ ጋር ትስስር አለ:: ብሪክስም ከእኛ ጋር የምትዋዋሉት በባዶ ፊያት ሳይሆን ወርቅ ጋር የተደገፈ ሲቢዲሲ ይሁን ብለዋል:: እኛም ወርቅን ማንጠር ጀምረናል:: ብቻ ደስ የሚል ነገር ይታየኛል:: ያድርገው:: ስለግብርና ባንክ ስሰማ ደግሞ በደስታ እንባዬ ነው የመጣው:: በትክክል የሚተገበር ያድርገው:: | 4 167 |
| 19 | የግብርና ባንክ በሦስት ወራት ውስጥ ይጀመራል የሚል ዜና Capital መጽሔት ላይ አነበብኩ:: Congratulations 🎈🎉🍾
=========
የቻይና ግብርና ባንክ ባየሁ እና በተጠቀምሁ ቁጥር ሀገሬ ላይ እንደሚኖረን እመኝ ነበር:: ይልቅስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፔፐሬም በዚሁ ላይ ነው:: ፔፐሩም ከጋዜጠኛ አብርሃም ታደሰ ጋር በተከታታይነት አቅርበነዋል:: የባንኩ ሠራተኞች ዝግጅት በተመለከት ተጨማሪ ባለሙያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋብዤ በETV አቅርበነዋል:: በመጽሓፎቼም ርዕስ ሰጥቼ የዕድገታችን የመፍትኄ አካል አድርጌ ሠርቼዋለሁ:: ልዩ ትኩረት ከሰጠሗቸው ጉዳዮች ግብርና ባንክ ከበፊተኞቹ ነው:: መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ለመጀመር መድረሱ የተሰማኝ ደስታ ወደር የለውም::
ፎቶ:- ቻይና ከ Agricultural Bank of China (ABC) ፊትለፊት | 3 517 |
| 20 | ሆድህ ሲበዛ ጾታህ ይቀያየራል::
(ዋናው ፖስቱ ግን ይህ አይደለም):: | 3 642 |
