Federal Law and Justice Institute የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት
الذهاب إلى القناة على Telegram
6 221
المشتركون
-524 ساعات
+167 أيام
+14630 أيام
أرشيف المشاركات
2ኛው ዙር የዓቃቤያነ ሕግ ሥልጠና ቪዲዮ የሚከተለውን link ሲጫኑ ያገኙታል
+5
2ኛው ዙር የዓቃቤያነ ሕግ ሥልጠና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ | ጥቅምት 20/2019 ዓ.ም
የፌዴራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤያነ ሕግ፣ በወንጀል ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ፣ በክስ አመሠራረትና የክርክር ክህሎት፣ በአስተዳደር ውል እንዲሁም በዓቃቤያነ ሕግ ሙያዊ ሥነ-ምግባር ዙሪያ ያተኮረ የሁለተኛ ዙር ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው መንግስቴ፣ ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት ለሕግና ለፍትሕ አካላት ሥልጠና የመስጠት፣ የሕግና የፍትሕ ጥናትና ምርምር የማካሄድ፣ የሕግ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የዳኝነትና የፍትሕ አካላትን ሪፎርም የመምራት እንዲሁም ብሔራዊ የሕግና ሕግ ነክ መረጃ ማዕከል በመሆን ተልዕኮዎቹን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም ኢንስቲትዩቱ ተቋማዊ አገልግሎቱን ይበልጥ ዘመናዊና ተደራሽ ለማድረግ የሪብራንዲንግ (Rebranding) ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የሁለተኛው ዙር ሥልጠናም የዓቃቤያነ ሕግን ሙያዊ ዕውቀትና የሥራ አፈጻጸም አቅም ለማሳደግ የተዘጋጀ መሆኑን በመግለጽ፣ ሰልጣኞች በሥልጠናው ቆይታቸው በንቃት በመሳተፍ ሥልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በበኩላቸው፣ ቢሮው የዓቃቤያነ ሕግን አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ሥልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ አሰፋ አክለውም ዓቃቤያነ ሕግ በሥልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችላቸውን ሥልጠና በጥብቅ ዲሲፕሊንና በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
+2
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ሕጎች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ | ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በማዕከል እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዓቃቤ ሕጎች ላለፉት አምስት ቀናት በ4 ዋና ዋና ርዕሶች ላይ ትኩረት በማድረግ ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና በዛሬው ዕለት አጠናቋል።
በሥልጠናው ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ለሰልጣኞች የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘካርያስ ኤርኮላ እንደገለጹት፤ የፍትሕ ሴክተሩን ለአገልግሎት ጠያቂው ሕዝብ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ያጋጠሙ ችግሮችን በጥናትና ምርምር በመለየት በየደረጃው ሥልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
ዶክተር ዘካርያስ አክለውም ሥልጠና መውሰድ በራሱ የመጨረሻ ውጤት አለመሆኑን ጠቁመው፤ ሰልጣኝ ዓቃቤ ሕጎች በቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የተቀላጠፈና ፍትሐዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በተያያዘም የዚሁ ሥልጠና ሁለተኛ ዙር ከጥቅምት 20/2019 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ከወጣው መርሃ-ግብር ለማወቅ ተችሏል።
=================
ዘገባው፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
+3

አቶ አሰፋ አክለውም ዓቃቤ ሕጎች በሥልጠናው የሚያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚረዳቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ ሥልጠናውን በነቃ ተሳትፎ፣ በጥብቅ ዲሲፕሊንና በጥንቃቄ እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
=================
ዘገባው፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
+3
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ለዓቃቤ ሕጎች ሥልጠና መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ | ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በማዕከልና በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕጎች በወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ፣ በክስ አመሰራረትና የክርክር ክህሎት፣ በአስተዳደር ውል፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በታክስ ሕግ እንዲሁም በዓቃቤ ሕጎች ሥነ-ምግባር ዙሪያ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘካርያስ ኤርኮላ የሥልጠናውን አስፈላጊነትና ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበትን ተልዕኮዎች አብራርተዋል። ዶክተር ዘካርያስ አክለውም ኢንስቲትዩቱ የዳኝነት ነፃነቱ ተከብሮ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በመወጣት ላይ እንደሚገኝና በአሁኑ ወቅትም ሥልጠናዎችን በጥሩ ሁኔታ ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው አስገንዝበዋል።
ዶክተር ዘካርያስ አያይዘውም የፍትሕ ሥርዓት መጎልበት በአንድ ሀገር ውስጥ ለዜጎች መብት መከበር የማይተካ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣ መንግሥት በዚህ ረገድ በርካታ የሕግ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።ሆኖም ሥልጠና በራሱ ግብ እንዳልሆነ የጠቆሙት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ምንም እንኳ የፍትሕ ሲስተሙ እየተሻሻለ ቢመጣም የሰው አመለካከት አብሮ ካልተሻሻለ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ መብራቴ በበኩላቸው ቢሮው የዓቃቤ ሕጎችን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት የተለያዩ ሥልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
+4
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመርያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
አዲስ አበባ | ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመርያው ሩብ ዓመት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ።
በግምገማ መድረኩ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊዎች ፣ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎችና መሪ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል።
የመጀመርያው ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በለውጥና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ አበበ ሹመት የቀረበ ሲሆን፤ ባለፉት ሦስት ወራት በኢንስቲትዩቱ የተከናወኑ አበይት ተግባራት፣ የተመዘገቡ ውጤቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
በቀረበው የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ የተቋሙን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚረዱ ገንቢ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተዋል። ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ከመድረኩ አስፈላጊው ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
የውይይት መድረኩን በንግግር ያጠናቀቁት የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶክተር ዘካርያስ ኤርኮላ፤ በተከናወኑት አበይት ተግባራት ላይ የተሻሉ አሰራሮችን አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ የታዩ እጥረት ያላቸውን ክፍተቶች ደግሞ በሚቀጥሉት ሩብ ዓመታት በማረም ወደተሻለ የሥራ ውጤት መሸጋገር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
=================
ዘገባው፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
+4
ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ነው
ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ረዳት ዳኞች በፍርድ ቤት መር አስማሚነት (Court-Annexed Mediation) ላይ ያተኮረ ሁለተኛ ዙር የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና መስጠት ጀመረ።
በሥልጠናው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶክተር ዘካርያስ ኤርኮላ እንደገለጹት፤ በፍርድ ቤት መር አስማሚነት የሚሰጡ ውሳኔዎች ባለጉዳዮች በክርክር የሚያጠፉትን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ፈጣን ፍትሕ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። አያይዘውም ይኸው አሰራር በሰዎች መካከል የሚኖርን ማህበራዊና መልካም ግንኙነት ሳይበላሽ እንዲቀጥል የሚያደርግ መሆኑን አብራርተዋል።
ዶክተር ዘካርያስ አክለውም በእርቅ ሂደት ተከራካሪ ወገኖች ለሁለቱም የሚበጅ (Win-Win) መፍትሔ በጋራ ማበጀት እንደሚችሉና በሂደቱ የሚነሱ ሀሳቦችና መረጃዎች ሙሉ በሙሉ ምስጢራዊነታቸው የተጠበቀ እንደሚሆን ጠቁመው የፍርድ ቤቶችን የሥራ ጫናም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ አስረድተዋል።