cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Federal Justice and Law Institute

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 256
المشتركون
+324 ساعات
+367 أيام
+17030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ጉራማይሌና ወጥነት የጎደለው የስልጠና አተገባበር ወደ አንድ የሥልጠና ስርዓት መሰብሰብ እዳለበት ተጠቆመ (ሰኔ 18/2016 ዓ.ም) ጉራማይሌና ወጥነት የጎደለው የስልጠና አተገባበር ወደ አንድ የሥልጠና ስርዓት መሰብሰብ እዳለበት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የስራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ሰርካለም ቦጋለ ተናገሩ፡፡ ሥራ አስፈጻሚዋ ይህንን የተናገሩት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፌዴራልና የክልሎች የስልጠና አተገባበር ሥርዓትን ወደ አንድ ለማምጣት ያለመ ጽሁፍ በአዳማ ከተማ እየቀረበ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ጥናታዊ ጽሁፉ ያሳለፍናቸውን የስልጠና ሥርዓቶች በመቃኘት ለቀጣይ አገር አቀፍ የስልጠና አተገባበር ቀርጾ ለመስራት እንዲያስችል ታስቦ ‘’Base line survey of the disparities in implementation of trainings at federal and regional judicial training institutes’’ በሚል ርዕስ መዘጋጀቱን የተናገሩት ወ/ሮ ሰርካለም ያለፉ ክፍተቶቻችንን በመለዬት የቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ወሳኝ መድረክ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ የአንድን አገር እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስፈን የፍትሕ ዘርፉ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ ለዚህም ስኬት ጥራቱን የጠበቀና የተናበበ የስልጠና ስርዓት ማዘጋጀት አንዱና ተቀዳሚ ተግባራችን ልናደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 1071/2010 ከተሰጡት ተግባርና ሃላፊነቶች መካከል በአንቀጽ 6(4) ላይ እንደሚያሳዬን ተቋማችን ከክልል የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩቶች ጋር በመተባበር በሃገር አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚነት የሚኖረው የስልጠና ካሪኩለም ያዘጋጃል እንደሚል ያስታወሱት ወ/ሮ ሰርካለም በመሆኑም በቀረበው ጽሁፍ ላይ ተሳታፊዎች ገንቢ አስተያዬት በመስጠት የተዘበራረቁና ወጥነት የጎደላቸው የስልጠና አካሄዶቻችንን ወደ አንድ የሚመጣ ሃሳብ እንዲሰጡ አስሰበዋል፡፡ የጥናታዊ ጽሁፉ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ከሰባት የተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ የጥናት ቡድኑ አባላት የተዘጋጀ ሲሆን መስተካከል ያለባቸውና ወደፊት ሊዳብሩ የሚገባቸው ሃሳብና አስተያዬቶች ከተሳታፊዎች ተሰጥተውበታል፡፡ መረጃው፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
إظهار الكل...
ጉራማይሌና ወጥነት የጎደለው የስልጠና አተገባበር ወደ አንድ የሥልጠና ስርዓት መሰብሰብ እዳለበት ተጠቆመ
إظهار الكل...
01:12
Video unavailableShow in Telegram
41.15 MB
የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ የህግ ክፍል አመራሮች እና ሙያተኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ (ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ የህግ ክፍል አመራሮች እና ሙያተኞች በአዲስ አበባ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡ በዕለቱ በስልጠናው ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚኒስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍትህ እና የህግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን አንኳር ተግባራት በመጥቀስ ለሰልጣኞቹ የተናገሩ ሲሆን ከእነዚህም ተግባራት መካከል አንዱ የፍትሕ አካላትን በስልጠና የማብቃትና የማስታወስ ስራ መስራት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ኢንስቲትዩቱ ከያዛቸው አበይት ፕሮግራሞች መካከል ለመከላከያ የሚሰጡ ስልጠናዎች ከማንኛውም ተቋም ቅድሚያ የሚሰጡ ናቸው በማለት የቀጠሉት ሚኒስቴር ዴዔታው ዛሬ የሚሰጠው የስልጠና ዘርፍ ደግሞ የባለሙያ እጥረት ያለበትና ለወቅቱ አስፈላጊ የሆነ አርዕስት ስለሆነ በአግባቡ መከታተል አለብን ብለዋል፡፡ ስልጠና በራሱ ግብ አይደለም፤ ወደፊት ያሰለጠናቸው ስልጠናዎች ያመጡት ለውጥ ምንድን ነው የሚለውን በጥናት የተደገፈ ስራ እንሰራለን ያሉት የተከበሩ አቶ ዘካሪያስ በመሆኑም የምናገኛቸውን ስልጠናዎች ወደ ተግባር በመለወጥ የህብረተሰቡን የፍትሕ ጥማት ማስታገስ አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመከላከያ ሚኒስቴር የሠው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የዕድገት እና ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል አምሳሉ ኩምሳ በበኩላቸው የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የሚደርግላቸውን ትብብር በማድነቅ ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በዚህም እነዚህንና መሰል ስልጠናዎች በዘርፉ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን ለመድፈን የሚግዙ በመሆናቸው ብለዋል፡፡ እነዚህ አይነት ስልጠናዎች ሰራዊታችን በተለያዩ አጋጣሚዎች ለሚኖረው ግዳጅ ትጥቅና ስንቅ ናቸው ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራሉ በመሆኑም ሕግን የበለጠ በማወቅና በመረዳት የማስከበር ሃላፊነትም አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም በመከላከያ ውስጥ የሌለ ወይም ተግባራዊ የማናደርገው የህግ አይነት የለም ያሉት ጀነራሉ ነገር ግን እነዚህ ህጎች በጀግንነትና በወኔ ሳይሆን ህግና ስርዓት የተቀመጠላቸው በመሆኑ በየዘርፎች በቂ የሆነ እውቀት ልንይዝ ይገባል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት አራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የኮንስትራክሽን ሕግ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ ይሆናል ። መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
إظهار الكل...
የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ የህግ ክፍል አመራሮች እና ሙያተኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ
إظهار الكل...
This is very fantastic news for it's sound & detailed information.
إظهار الكل...
إظهار الكل...
የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካሪስ ኤርኮላ

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሶማሌ ክልል ፍትሕ አካላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ፡፡ (ሰኔ 8/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሶማሌ ክልል ፍትሕ አካላት ላለፉት ስድስት ቀናት በጅግጅጋ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ፡፡ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የተወካዮች ምክር ቤት አባልና በሚስቴር ዴዔታ ማዕረግ የፌዴራል የፍሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካሪስ ኤርኮላ በንግግራቸው ጠንካራ የፍትሕ ሥርዓት መኖር የሕግ የበላይነት የሚከበርበት፣ ዜጎች በእኩል አይን የሚታዩበት፣ ለሕግ ተገዢና በሕግ ተጠያቂነት የሚኖርበትና ዜጎችን በፍትሃዊነት ማስተናገድ የሚቻልበትን ከዚህም አልፎ ደግሞ ሁሉም ዘርፎች የሚደገፉበትን መንገድ መፍጠር ማለት ነው ያሉ ሲሆን ከዚህ ረገድ ተቋማችን የተሰጡትን ተግባርና ሃላፊነቶች እየተወጣ ነው ማለት ይቻላል ብለዋል፡፡ የፍትሕ ተቋመት ጠንካራ መሆን በዜጎች መካከል የሚኖረው ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ መስተጋብር ዋስትና እንዲኖረው ያደርጋል ያሉት ሚንስቴር ዴዔታው ባለፉት አምስት አመታት እየተካሄደ ባለው ለውጥ ሂደት ውስጥ ለፍትሕ ተቋማት በነጻነትን፣ በህግና ሕግ ላይ ብቻ ተንተርሰው እንዲሰሩ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፤ በርካታ አሳሪና አስከፊ የነበሩ ሕጎችን የማቻቻል ስራ ተሰርቷል ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የዳኝነት ነጻነት እንዲከበር ተጠያቂነት ላይ ያለው ስርዓትም የተመቻቸ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የሶማሌ ክልል ከሰላም አንጻር በርካታ ስራዎችን በመስራት የክልሉን አንጻራዊ ሰላምና ልማት እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት አቶ ዘካርያስ ለዚህም የፍትሕ ተቋማት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ እምነት አለን ብለዋል፡፡ በዕለቱስልጠናው ከስራቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው እደሆነና በስራ ቦታቸውም ላይ እንደሚጠቅማቸው በመግለጽ ነገር ግን ቢያንስ በዬ ስድስት ወሩ ስልጠና የሚገኙነትንና ለወረዳና ለዞን ሰልጣኞች ጭምር የሚመቻችበት መንገድ መቀየስ አለበት ያሉት አስተያዬት የሰጡ ሰልጣኞች ለተደረገላቸው ገነር ምስጋናቸውን አቅርበዋ፡፡ መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!

የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለሶማሌ ክልል ፍትሕ አካላት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ዛሬ ፍጻሜውን አገኘ፡፡

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.