ar
Feedback
የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል!

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የጥበብ ማዕድ

تُعد قناة የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 968 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 354 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 100 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 968 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 26 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 661، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 94، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 2.60‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 2.13‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 415 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 341 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 10.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ዝም ብለህ ተቀላቀል!

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 27 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 968
المشتركون
+9424 ساعات
+2527 أيام
+66130 أيام
أرشيف المشاركات
ቤተሰቦች ዛሬ ቅዳሜ ነው በቻናላችን የማንን ሙዚቃ እናጫውትላችሁ?!

አንዳንድ ሰው መላ ሰውነቱ ትከሻው ብቻ ነው የሚመስለው!

ሁሌም መገኛህ ብቻ ዋጋህን አይናገርም!      የትም ተገኝ ዋናው ግን ጥቅምህ ነው ካለህበት እንድትለይ ሚያደርግህ።

ልብ ያለው ያውቃል።

'ይሰበር ይሆን እያልክ የማታስበው ምርኩዝ: ፈጣሪህን ብቻ አድርግ!!!

፡ ልብስ ሰፊዋ በከተማው አደባባይ እምብርት ላይ የተሰቀለው ባንዲራ ብዙ ክረምትና በጋ ስለተፈራረቀበት ተጎሳቁሏል፡፡ በክረምት ዝናብ ረጥቧል፡ በበጋ አቧራ አድፏል፡ በሃሩር ንዳድ ገርጥቷል፡፡ በነፋስ ሳቢያ ተቀዷል፡፡ ግን ማንም ልብ ያለው፡ ማንም ደንታ የሰጠው አልነበረም፡፡ ፖለቲከኞቹ "በትላልቅ ጉዳዮች" ተጠምደዋል፡፡ ወታደሮቹ የሀገሪቱን ድንበር ከጠላት እየጠበቁ ነው፡፡ የመንፈስ አባቶች ነፍሳትን ከሲኦል በማዳን፡ ሕዝቡ ደግሞ ኑሮውን በማሸነፍ ሩጫ ተጠምደዋል፡፡ ከአደባባዩ በስተግራ በኩል ጥግ ላይ ምስኪን ልብስ ሰፊ ግን በባንዲራው ጉዳይ ተብከንክናለች፡፡ አንድ ቀን ከሰዐት በኋላ በአጠገቧ በጥድፊያ የሚያልፈውን ቁመተ ሎጋ ሰው አስቆመችና ባንዲራውን እንዲያወርድላት ጠየቀችው፡፡ "ለምን?" ብሎ ጠየቃት፡፡ "ለምን ...? እያየኸው .... እጅግ ቆሽሿል፡ ቀለሞቹ መለየት እስኪያቅት ገርጥቷል፡፡ በዚያ ላይ ተቀዷል፡፡ ቀለሞቹን መመለስ ባልችል እንኳን፡ ቢያንስ አጥቤ ልስፋው ብዬ እኮ ነው ... ልብስ ሰፊ እኮ ነኝ" ብላ መለሰችለት፡፡ ሰውዬው ሣቀና እንዲህ አላት፡ "ምንሸ ተነካና? ባንዲራ አይደል ... ምን አገባሽ ... የድሃ ቅንጡ ነሽ ባክሽ ... እስቲ መጀመሪያ የተቀደደ ልብስ ስፊና የራስሽን ቀዳዳ ድፈኚ ... የደላሽ!" ጭንቅላቷን ባለመስማማት ነቀነቀች፡፡ "ግን እኮ ተቀዷል ... " ከማለቷ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡ ጥቂት ካሰበች በኋላ ሁለት የጎዳና ጎረምሶችን ብር አስጨብጣና ምሰሶውን እንዲወጡ አድርጋ፡ ባንዲራውን አስወረደች፡፡ አጠበችው፡ ሰፋችው፡፡ ልጆቹ መልሰው እንዲሰቅሉላት ካደረገች በኋላ ሲውለበለብ እየተመለከተች ፈገግ ብላ፡ "ጎበዞች! እንደ ቀድሞ ግርማ ሞገሱ ባያስደነግጥም ከቀዳዳ እና ከቆሻሻው ይሄ ይሻላል" አለች፡፡ በነጋታው ከዚህ በፊት ዐይታቸው የማታውቅ ሰዎች አዲስ ባንዲራ ይዘው መጡ፡፡ አጥባና ሰፍታ የሰቀለችውን ባንዲራ አውርደው ጣሉና በአዲሱ ተኩት፡፡ አንዱን ፈራ ተባ እያለች ተጠጋችውና፡ "ምነው እስከዛሬ ሳታዩት ገና እስተካክዬው ስሰቅለው ልትተኩት መጣችሁ?" ስትል ጠየቀችው፡፡ ሰውዬው ዞርም ብሎ ሳያያት፡ "ለዐይን ይቀፋል፡፡ እንዲህ እንደነገሩ የተጣፈ ባንዲራ በዋና አደባባያችን ላይ ተሰቅሎ ማየት በጣም ይቀፋል" ብሎ መለሰላት፡፡ (ዥዋ ዥዌ) ፡

ከአንድ ጊዜ በላይ የተደጋገመ ስህተት ምርጫ ነው ምርጫ ደሞ ፍላጎት ነው

ቤተሰብ ሕይወትን ይሰጥሃል! ትኩረት አድርገህ እየው እስቲ ያደረገልህን እያደረገልህ ያለውንም።       አመስጋኝ እንሁን!!!

መምህር ብቻ ነው አስተምሮህ እንድትበልጠው ሚፈልግ!

ስትኖር ልክ እንደ ባህር ዳር አሸዋ ባለህበት መጥቶ የሚያርስህ ነገር አይጠፋም።

አንዳንዴ በለት ተዕለት ተስፋ መቁረጥ በአዳዲስ ተስፋ እንድትታደስ ያደርገሃል።

ማሰብ ምታስበው ላይ ተፅዕኖ እንደማሳደር ነው እርሱም ያስብሃል።

እንኳን አደረሳችሁ መልካም የፆም ወቅት ይሁንላችሁ
እንኳን አደረሳችሁ  መልካም የፆም ወቅት ይሁንላችሁ

: መሔድ ምን አመጣው       ፍላጎት ከቆመ በ'ይበቃል ታስሮ! ከአረማመዱ ፊት     መንገድ ጀማሪ ነው               የሚገኘው ከስሮ!!!       አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

፡ በዳይ   ከበደል ጋር          ሕብረት ስላኖሩ ልቡን ካል'ገራው ዘንድ                   ከምስኪን አደሩ ያ ምስኪን ደግሞ        ሰው ያልታደለ                  ማመንን ተችሮ     እንደ መስታወቱ          ያንጸባርቅ ጀመር               ጥርጣሬን ቀብሮ የኋላ የኋላ        የጉድ ቀን ሲመሻሽ             ጥላ'ቸው ሲከፈል                       ሁለት ሲሆን አንዱ ብቻውን ይቀራል      ምስኪኑ ተበዳይ            የቀረበውን                    እየገፋ ክንዱ!      አቡ

ጉድለቱ ግቡ ከሆነ ሰው ጋር እንዴት ተከራክረህ ትረታዋለህ?!         ተወው አትድከም!!!

አብዝቶ ይቅርታ ጥፋትን ያላምዳል።

የራስ ሸክም አይከብድም!

ስለ ጠፋብህ ንብረት ቀዳሚ ተጠያቂ ጎረቤትህን አድርግ ባይወስድ እንኳን ሲወሰድ አድምጦ ሊሆን ሊያተርፍም ይችል ነበር።

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የዓብይ ፆም በሰላም አደርሳቹ እያልን ፆሙ የሰላም የበረከት እንዲሆንላቹ እንዲሆንልን ቻናላችን ይመኛል ! መልካም ወረሃ ፆም ❤️