Yeka Education
Education is the passport of the future!! https://telega.io/c/dam76
إظهار المزيد📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Yeka Education
تُعد قناة Yeka Education (@dam76) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 42 348 مشتركاً، محتلاً المرتبة 4 336 في فئة التعليم والمرتبة 767 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 42 348 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 13 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 779، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 10، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 20.62%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 11.96% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 8 734 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 5 067 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 27.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“Education is the passport of the future!!
https://telega.io/c/dam76”
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 14 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة التعليم.
جاري تحميل البيانات...
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 14 يونيو | 0 | |||
| 13 يونيو | +30 | |||
| 12 يونيو | +48 | |||
| 11 يونيو | +63 | |||
| 10 يونيو | +49 | |||
| 09 يونيو | +29 | |||
| 08 يونيو | +54 | |||
| 07 يونيو | +28 | |||
| 06 يونيو | +46 | |||
| 05 يونيو | +9 | |||
| 04 يونيو | +56 | |||
| 03 يونيو | +5 | |||
| 02 يونيو | +14 | |||
| 01 يونيو | +43 |
| 2 | ✔️
በፈተና ዋዜማ ተማሪዎች አእምሮን ለማዝናናት በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ የተዘጋጁ ማጠቃለያዎችን ብቻ በአጭሩ መገምገም፣ የፈተና መገልገያ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት፣ ጤናማ ምግብ መመገብ እና አላስፈላጊ ጭንቀትን ማስወገድ አለባቸው።
⭐️በፈተና ዋዜማ እና የፈተና ጊዜ ስኬትን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ተግባራዊ ማድረግ ይገባል🔤➖
🔤በቂ እረፍት ማድረግ፡ አእምሮን ለማነቃቃት እና ጭንቀትን ለመቀነስ ቢያንስ ከ 7 እስከ 8 ሰዓታት የሚሆን ጥልቅ እንቅልፍ መተኛት ያስፈልጋል።
🔣የፈተና ቁሳቁስ ማሟላት፡ እስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ ማጥፊያ፣ መለያ (ID) እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች አስቀድመው በቦርሳ መዘጋጀት አለባቸው።
⏰አጭር ግምገማ ብቻ ማድረግ፡
አዳዲስ ርእሶችን ለማንበብ ከመሞከር ይልቅ ቀደም ሲል የተሰሩ ማጠቃለያዎችን እና ዋና ዋና ነጥቦችን ብቻ ማየት ይበጃል።
🔤ትክክለኛ አመጋገብ፡ አእምሮ በተገቢው መንገድ እንዲሠራ ቀላል፣ ሰውነትን የሚያነቃቁ እና ጤናማ ምግቦችን መመገብ ይገባል።
🔤ስሜትን መቆጣጠር፡ የፈተና ፍርሃትን እና ጭንቀትን ለመቀነስ ከመጠን በላይ ከማሰብ መቆጠብ፣ አዎንታዊ አስተሳሰብ መያዝ እና ዘና ማለት ያስፈልጋል።
🔤የፈተና ቦታን ማወቅ፡ የፈተናው ቦታ ሩቅ ከሆነ አስቀድሞ መንገድን በመለየት ሰዓት አክብሮ ለመገኘት እቅድ መያዝ ወሳኝ ጉዳይ ነው
✅ተማሪዎች ሆይ እንወዳቹሀለን👏
⭐️ቻናላችን ለናንተ የሚችለውን ሁሉ ጥረት አድርጓል ብለን እናምናለን
📌መልካም ፈተና👏
📌 መልካም ውጤት👏
⌨️⌨️⌨️⌨️
🔤🔤🔤
Our Channel
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76 | 4 891 |
| 3 | ✅የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው(በድጋሜ የተለጠፈ)
።
📌 ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለማድረግ ያስችለናል።
✔️ ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያደረፈርገናል ።
✔️ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ #ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ #እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ #ምክንያቶች ውስጥ #ጥቂቶቹ:
➡️ አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።
➡️ በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።
➡️ የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።
➡️ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት። እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።
✅ ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
⭐️ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ -
➡️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
➡️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ።
✅ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ። እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።
➡️ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
✅ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።
✅ ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
➡️ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ።
📌ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
➡️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
✔️ ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
➡️ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
➡️አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
➡️ ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
✅በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
➡️ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ •
✔️በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ
✅ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
✅ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
📌በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።
✅ ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት ያስፈልጋል።
⭐️የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የተወሰኑ ቀናት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1 ወር ያነሱ ቀናት ይቀሩታል!
#️⃣Share
⭐️ ለሁሉም ተፈታኞች
መልካም የጥናትና የፈተና ጊዜ!⭐️
🔠🔠🔠🔠
🔠🔠🔠
Our Channel
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76 | 6 175 |
| 4 | ⭐️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅
========================
⭐️ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::
⭐️ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:-
------------------------------------------------
✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
✅ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
✅ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
ቻናሉን ለወዳጅዎ
🌟Share ያድርጉ
🔤🔤🔤🔤
🔤🔤🔤
🤩🤩🤩🤩🤩
🤩🤩🤩🤩
https://t.me/dam76
👆👆👆👆 | 1 |
| 5 | Still working for pocket change?
Lisa
AI crushes profits in USD every single day. We deliver ready-to-use signals straight to your phone. Join for free before we close access. Tap here.
Ad. 18+ | 4 553 |
| 6 | ✔️ፈተና የእውቀት መመዘኛ እንጂ የማንነት መለኪያ እንዳልኾነ መገንዘብም ለሥነ ልቦና ጥንካሬ ትልቅ ድጋፍ ይሰጣል።
✔️ የፈተና ሥርዓቱ ቢለያይም በየትኛውም ደረጃ የሚወጣ ፈተና በፊት ከነበሩት የተለየ እንዳልኾነ መረዳት እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።
✅በተጨማሪም በፈተና ወቅት:-🔤
✅ ከመጠን በላይ አለመጨነቅ፤
✅ ትኩረትን የሚሰርቁ ነገሮችን በማስወገድ ሙሉ ትኩረትን ወደ ፈተናው ብቻ ማዞር ፤
✅ ጥሩ የአዕምሮ ዝግጅት እንዲኖር በቂ እንቅልፍ እና ተገቢ እረፍት ማድረግ፤
✅ ሁሌም ፈተናን ለተሻለ ውጤት እንደ ዕድል መቁጠር፤
✅ በራስ ዕውቀት እና የመተማመን ስሜት፣ በተረጋጋ መንፈስ ወደ ፈተና አዳራሽ መግባት፤
✅ ከውስጥ የመነጨ የተነሳሽነት ስሜት መፍጠር እና መሠል የሥነ-ልቦና ዝግጅቶችን ማድረግ ለውጤታማነት ወሳኝ መሆናቸውን ይመከራል።
via➡️MOE
⭐️ ለሁሉም ተፈታኞች
መልካም ፈተና
🔠🔠🔠🔠
🔠🔠🔠
Our Channel
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76 | 6 169 |
| 7 | 1,000,000 USDT awaits you!
Toobit
Ready to win 1,000,000 usdt rewards? Come to join Win the World event on Toobit.
Ad. 18+ | 3 702 |
| 8 | ✔️ የተፈታኞች መብትና ግዴታዎች
✔️ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።
✔️ ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።
✔️ተፈታኙ/ኟ የሰራበትን የመልስ ወረቀት ለፈታኙ በመስጠት የጥያቄ ወረቀቱን ይዞ መውጣት ይችላል
✔️ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፎ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።
✔️ ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
✔️የሚሠራባቸው የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ለሌሎች ተፈታኞች ዕይታ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ሸፍኖ መስራት ይኖርበታል
✔️ ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።
✔️ እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።
✔️ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
✔️ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም
✔️ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው።
✔️ ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።
✔️ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም።
✔️ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።
✔️ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።
✔️ ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤
⭐️ለተፈታኞች የተፈቀዱ
✅ እርሳስ
✅ የተማሪዎች የደንብ ልብስ (UNIFORM)
✅ ADMISSION CARD
✅ ላጲስ፣ መቅረጫና ማስመሪያ
🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤
❌ለተፈታኞች የተከለከሉ❌
❌ ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም
❌ ካልኩሌተር
❌ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
❌ ሰዓት
❌ በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች
❌ የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ
✔️የፈተና ኦረንቴሽን ቀ
➡️ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል በ05/10/2018
✔️ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ
➡️ 6ኛ ክፍል ከሰኔ 8- 10 /2018 ዓ/ም
➡️8ኛ ክፍል ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ/ም ይሆናል
🥢https://t.me/dam76 | 10 294 |
| 9 | ✔️ለ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈተኞች የትምህርት አይነትና ኮድ
(ለአዲስ አበባ ተፈታኞች)
✔️የሚኒስትሪ ተፈታኞች ማድረግ የሚገባቸው 1ነገሮች
⭐️1.ለመልስ መስጫ ወረቀት እርሳስ ብቻ መጠቀም
⭐️2.የት/ት አይነት መለያ ኮድን ቡክሌት ኮድ በትክክል ማጥቆር
⭐️3.ቡክሌት ኮድን በትክክል ማጥቆር
⭐️4.የመልስ ወረቀት ላይ በአግባቡ ማጥቆር
⭐️5.የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የጥያቄዎቸን ቅደም ተከተል ጠብቆ መስረት
⭐️6.ለአንድ ጥይቄ አንድ መልስ ብቻ ማጥቆር
🌟7.የመለስ ወረቀት ላይ ሌላ ነገር አለመጻፍ
✅8.በፈታኞች የሚሰጠንንነ መመሪያ ተግባራዊ ማደረግ
⭐️ ለሁሉም ተፈታኞች
መልካም ፈተና
🔠🔠🔠🔠
🔠🔠🔠
Our Channel
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76 | 11 465 |
| 10 | Still working for pocket change?
Lisa
AI crushes profits in USD every single day. We deliver ready-to-use signals straight to your phone. Join for free before we close access. Tap here.
Ad. 18+ | 4 802 |
| 11 | ወደ ድር እቅድ ይቀጥቁ!
🔥 እነዚህ ኦንላይን ስራዎች በእጅግ ቀላል መነሳት ነው! ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንደ ፍራንስ ማገናዘብ ቆይታ ከፍ እንዲያው አድርጋለሁ።
- ⚡ ይገኙ በቀላሉ የገንዘብ ማግኘት መንገዶች
- 💰 ወይንም የወቅትና ውለቀመን መተዳደር
- 🚀 ይቀበሉ ኦነታ | ወይንም በሚያይዘዝ ብር (እንዲያው ይመጣ)
- 🌐 ኦንላይን መርሐግብ ምንጭ ከማህበራችንም
ወይንም ድምፀው ሀይማኖታችንና መላዕክቶችን ገብስ ቀንጂቃቤዋ እንዎቃዓዝ አዋፍ እታመ እዚህ ነጻ እንዲሆን ከንባቤ ድወዋだけ⏳
👉 ይቀጥቁ ከነዚህ ወደ መሰብሰል!
#ad 📢 InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች | 71 |
| 12 | ወደ ድር ኢንተርኔት በየመለኪያ ዉስጥ ይሂዱ… የተያዘበት ዋጋ ነው? 🤔🌐 ወደ ነፃ ይውሰዱ ያዊየዉነም ዋይዳው ይቀመጡ። ነፃ የኢንተርኔት ጀምሩ ወተለያዩ ዳኛዎች ለግምገማ!
የነገር አለመመገብን ለመውነትና ለይበሉ እንደ የወቅቱ ምርጦች ለአንድ ዞር! 👉 ወንበር ላይ ወደ ነፃ ይፈጥሩ
#ad 📢 InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች | 284 |
| 13 | የታላቅ መረጃ ናቸው! እንደተወሰኑ እንደዚህ ያለ ምንጭ ጠቃሚ ስህተቶችን ፈትሹ!" 🌿✨
የበለጠ ክፍያ ማጣት በኢትዮ የምናጸነስ ችግኝ አይደለም! እንኳን እንደምን ተመኽሮ፤ አስተሳሰር ማጤመጣ ነው። የዚህ አስተዳደር የዳመይ ቻርየብን የመለወጥ እንደ ነበይት ክርክዕ አይቆ ፍቅር ይኖራቹ!
- የእኛን ቻናል ዩቱብ ይቀይሩ: ይመልከቱ 📺
- በግብይት ድጋፍ ይዞታ ይመኙ።
- እንዲህ ከባጋሪ ከነይ ይምጡ: ምዕመናዊ በምንጭ ይወዳድሩ 💫
✨ ክንውኖት ይሁን በዚህ ቀጥ ተደርገዋል። 👉 ለአስተዳደር በሚጠናቀይ ቡድን ይርዳል!
#ad 📢 InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች | 497 |
| 14 | ✅የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው
።
📌 ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለማድረግ ያስችለናል።
✔️ ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያደረፈርገናል ።
✔️ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ #ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ #እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ #ምክንያቶች ውስጥ #ጥቂቶቹ:
➡️ አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።
➡️ በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።
➡️ የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።
➡️ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት። እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው።
✅ ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
⭐️ ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ -
➡️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
➡️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ።
✅ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ። እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።
➡️ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
✅ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል።
✅ ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
➡️ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ።
📌ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
➡️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
✔️ ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
➡️ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
➡️አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
➡️ ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
✅በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።
➡️ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ •
✔️በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ
✅ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
✅ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
📌በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።
✅ ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት ያስፈልጋል።
⭐️የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የተወሰኑ ቀናት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1 ወር ያነሱ ቀናት ይቀሩታል!
#️⃣Share
⭐️ ለሁሉም ተፈታኞች
መልካም የጥናትና የፈተና ጊዜ!⭐️
🔠🔠🔠🔠
🔠🔠🔠
Our Channel
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76 | 11 816 |
| 15 | ⭐️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅
========================
⭐️ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::
⭐️ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:-
------------------------------------------------
✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
✅ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።
✅ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።
✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።
✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
ቻናሉን ለወዳጅዎ
🌟Share ያድርጉ
🔤🔤🔤🔤
🔤🔤🔤
🤩🤩🤩🤩🤩
🤩🤩🤩🤩
https://t.me/dam76
👆👆👆👆 | 9 637 |
| 16 | ⭐️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅

| 17 | 1,000,000 USDT awaits you!
Toobit
Ready to win 1,000,000 usdt rewards? Come to join Win the World event on Toobit.
Ad. 18+ | 3 573 |
| 18 | ⭐️በትምህርት ስኬታማ ለመሆን ጠንክሮ ማጥናት ብቻ በቂ አይደለም - በብልሃት ማጥናት ነው። ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ፡-
✅ ጥረትን ወደ ውጤት የሚቀይሩ ውጤታማ የአጠናን ስልቶችን ይጠቀማሉ። ደስ የሚለው ነገር- ማንኛውም ተማሪ እነዚህን ስልቶች መማር እና ተግባራዊ ማድረግ ይችላል። የአጠናን ስልቶቹ የሚከተሉት ናቸው:-
🌟 1. ስታጠኑ ግልጽ የሆነ ዓላማ ይኑራችሁ
✅የምታጠኑትን መጽሐፍ ወይም ደብተር እንዲሁ አትግለጡት- መጀመሪያ ለምን እንደምታጠኑ እወቁ።
✅እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡- በዚህ የጥናት ጊዜዬ ምን መረዳት ወይም ማሳካት እፈልጋለሁ?
✅በዓላማ የሚያጠና ተማሪ በትኩረት ያነባል፣ የተሻለ ያስታውሳል፣ ጊዜውን አያባክንም።
➡️ ምሳሌ፡- “ሳይንስ ወይም ባዮሎጂ አጠናለሁ” ከማለት ይልቅ “የሰው ልጅ ልብ እንዴት እንደሚሰራ ••• እረዳለሁ” በሉ።
🇪🇸 2. ተግባራዊ የንባብ ስልትን ተጠቀሙ፣ እንዲሁ ለማንበብ አትሞክሩ
✔️ማንበብ ብቻውን በቂ አይደለም። አእምሮ በንቃት ሲሳተፍ አንድን ነገር በተሻለ ሁኔታ መረዳት ትችላላችሁ።
ለምሳሌ ይህንን ሞክሩ፦
➡️ ያነበባችሁትን ነገር በራሳችሁ አገላለጽ ወይም ቃላት ከልሱት።
➡️ ፅንሰ-ሀሳቡን ለጓደኞቻችሁ አስረዱ።
➡️ በምታጠኑበት ጊዜ ለራሳችሁ ጥያቄዎችን ጠይቁ።
📌 አንድን ፅንሰ-ሀሳብ በቀላሉ ማስረዳት ከቻላችሁ፣ በትክክል ተረድታችሁታል ማለት ነው።
⏰ 3. ጊዜያችሁን በጥበብ አስተዳድሩ
✅ጊዜ ትልቁ ሀብት ነው። ስኬታማ ተማሪዎች ተነሳሽነትን አይጠብቁም - የራሳቸውን የጥናት መርሃ ግብር አዘጋጅተው በዚያ ይመራሉ።
📌 ጊዜያችሁን በጥበብ ለመጠቀም የሚከተሉትን ቴክኒኮች/ዘዴዎች ተጠቀሙ፦
➡️ አእምሮአችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ ከ25–50 ደቂቃዎች ያህል በትኩረት አጥኑ።
➡️ በመካከል አጭር እረፍት ውሰዱ።
➡️ ከባድ ለሆኑ ትምህርቶች ቅድሚያ ስጡ
#️⃣አስተውሉ: በየቀኑ የሚደረጉ ትናንሽ ነገር ግን ወጥ የሆኑ ጥረቶች በመጨረሻ ሰአት ላይ የሚኖር መጨናነቅን ይበልጣሉ።
🗓 4. አስቀድማችሁ በማቀድ በተደራጀ ሁኔታ አጥኑ
🔤ግልጽ የሆነ እቅድ ጭንቀትን ይቀንሳል፤ በራስ መተማመንንም ይጨምራል።
➡️ ማስታወሻ ደብተር ወይም እቅድ ማውጫ ተጠቀሙ።
➡️ ትላልቅ የጥናት ተግባራትን ወደ ትናንሽ ደረጃዎች ከፋፍሏቸው።
➡️ ዕለታዊ እና ሳምንታዊ የጥናት ግቦችን አዘጋጁ።
📌 ጊዜያችሁን ስታቅዱ፣ የወደፊት ሕይወታችሁን ትቆጣጠራላችሁ።
🔁 5. አዘውትራችሁ ከልሱ
🔤መርሳት ተፈጥሯዊ ነው—ነገር ግን ክለሳ መርሳትን ይፋለመዋል።
➡️ በጥናት ወቅት የምታዘጋጇቸውን ማስታወሻዎቻችሁን ምንጊዜም በ24 ሰዓታት ውስጥ ከልሱ።
➡️ ከዚህ በፊት የተጠኑ የተለያዩ ርዕሶችን በየሳምንቱ እንደገና ለማየት ሞክሩ።
➡️ ያለፉ ጥያቄዎችን በመስራት ተለማመዱ
#️⃣አስተውሉ: አንድን ነገር መደጋገም ችሎታን ይገነባል።
✅ 6. ማንበብ ብቻ ሳይሆን ለልምምድ ትኩረት ስጡ
✔️በተለይ እንደ ሂሳብ፣ ፊዚክስ ወይም ኬሚስትሪ ላሉ ትምህርቶች ልምምድ ሁሉም ነገር ነው።
➡️ ኘሮብሌሞችን ለመፍታት ጥረት አድርጉ Solve Problems
➡️ ማስታወሻዎችን (notes) ሳትመለከቱ እራሳችሁን ፈትሹ
➡️ ከስህተቶቻችሁ ተማሩ
📌 ስህተቶች ውድቀቶች አይደሉም—ምርጥ አስተማሪዎች ናቸው።
✔️ 7. ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግዱ
አካባቢያችሁ ስኬታችሁን ይቀርፃል።
➡️ ስልካችሁን ከአጠገባችሁ አርቁ ወይም ድምፁን አጥፉት።
➡️ ጸጥ ያለ የጥናት ቦታ ምረጡ።
➡️ በአንዴ ብዙ ነገሮችን ከማከናወን ተቆጠቡ።
📌 ባለንበት ሃሳብን በሚከፋፍል ዓለም ውስጥ #ትኩረት ማድረግ ሃይልን የሚያጎናፅፍ ልማድ ነው።
💪 8. ሰውነታችሁን እና እምሮዎአችሁን ተንከባከቡ
✔️የደከመ አእምሮ ውጤታማ በሆነ መንገድ መማር አይችልም።
➡️ በቂ እንቅልፍ አግኙ
➡️ ጤናማ ምግብ ተመገቡ
➡️ በየጊዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ
📌 ጠንካራ ሰውነት ጠንካራ አእምሮን ይፈጥራል።
🚀 9. በየጊዜው አቅማችሁን ማሻሻል እንደምትችሉ እምነት ይኑራችሁ
👌ብዙ ተማሪዎች የሚወድቁት ከሌሎች ያነሰ የማሰብ ችሎታ ስላላቸው ሳይሆን በራሳቸው እምነት ስለሌላቸው ነው። | 12 814 |
| 19 | 🎚የአለማችን ታዋቂ ሰዎች ስለንባብ ከተናገሩት
✅1 “ማንበብ ትልቅ ሀብትን ያጎናፅፋል። እስከዛሬ በአለማችን ላይ ስለተከሠቱ እና በሌሎች ሰዎች ስለተሰሩ ነገሮች በሙሉ ማወቅ የምንችለው ማንበብ ስንጀምር ነው።” (አብርሃም ሊንከን)
✅2. “በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መፀሀፍቶች ውስጥ አሉ። የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መፀሀፍ “እንካ አንብብ” ብሎ የሚሰጠኝ ነው።” (አብርሃም ሊንከን)
✅4. “ዘወትር ባነበብኩኝ ቁጥር ውስጤ የነበረውና ያለው ትልቁ የመቻል አቅም ይቀሰቀሳል።”
(ማልኮምኤክሥ)
✅5. “የኔን የግል ህይወት ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ህይወት መለወጥ የቻሉ ሀሳቦችን መተግበር የቻልኩት መፀሀፍ በማንበቤ ነው።” (ቤል ሑክሥ)
🌟6 “ለአንድ ሠው መፀሀፍ ስትሸጥ የሸጥከው ብዙ ወረቀቶችን፣ የተፃፈበትን ቀለምና ጥራዙን አይደለም። ለርሱ የሸጥክለት ዋናው ነገር ሙሉ የሆነ አዲስ ህይወትን ነው።”(ክርስቶፈር ሞርሌይ)
🔇7. “መፀሀፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት በድሮ ዘመን ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰው ጋር መወያየት ማለት ነው።”(ሬኔ ዴካርቴሥ)
✅8. “ከየትኛውም ነገር በላይ ትልቁንና ከፍተኛውን ደስታ የማገኘው ሳነብ ነው።”(የፋሽን ዲዛይነሯ ቢልብላሥ)
✅9. “ማንበብ ከቻልክና አንዴ ማንበብ ከጀመርክ በቃ አንተ ነፃነት ያለህ ሠው ነህ።”(ፍሪድሪክ ዳግላሥ)
⭐️10. “አላዋቂነትንና ችኩልነትን የምንዋጋበት ብቸኛው ወሳኝ መሣሪያ ማንበብ ነው።”(ሌኖርድ ቤይንሥ ጆንሰን)
✅11. “ለአንድ ጨቅላ ልጅ መፅሐፍ እንዲያነብ ከማድረግ በላይ ልንሠጠው የምንችለው ትልቅ ሥጦታ የለም።”(ሜይ ኤለን ቼሥ)
✅12. “አንድ መፀሀፍ ባነበብን ቁጥር እዚህ ምድር ላይ በሆነ ቦታ ለኛ አንድ በር እየተከፈተልን ነው።”(ቬራናዛሪያን)
(ፎቶ👉ቤተ መጽሀፍት በቻይና😮)
⌨️⌨️⌨️⌨️
⌨️⌨️⌨️
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76 | 11 089 |
| 20 | 1,000,000 USDT awaits you!
Toobit
Ready to win 1,000,000 usdt rewards? Come to join Win the World event on Toobit.
Ad. 18+ | 3 001 |
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 