የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 296 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 167 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 365 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 296 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 20 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 492، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 16، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 52.64%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 13.12% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 7 523 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 875 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 29.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 21 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
14 296
المشتركون
+1624 ساعات
+1157 أيام
+49230 أيام
أرشيف المشاركات
+3
ሦስተኛ ዙር የ፲፪ ክፍል ምርቃት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት ተከናወነ።
12/01/2018 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
በሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ከሙከራ ትግበራ ጀምሮ ትምህርታቸውን ለተከታተሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና የዕውቅና መርሐ ግብር ተከናወነ።
የዕውቅና መርሐ ግብሩ የተከናወነው በ2015 ዓ.ም የዐሥረኛ ክፍል ምዘናን በሀገረ ስብከት ደረጃ ወስደው ለዘንድሮ የዐሥራ ኹለተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ምዘና ለወሰዱ በአዲስ አበባና በሸገር ሀገረ ስብከት የሚገኙ አጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነው።
ይህ የዕውቅና መርሐ ግብር በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ቤተክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ሲከናወን ለሦስተኛ ጊዜ ነው።በመርሐ ግብሩ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሣኤ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በጉባኤው የተገኙት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የማዕከላዊ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ "ይህ የትምህርት መጨረሻ እንዳልሆነ እና የተማረ ትውልድ ለቅድስት ቤተክርስቲያን እንደሚያስፈልጋት" ተናግረው አባታዊ መልዕክት እና ቃለ ቡራኬ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች የምሥክር ወረቀት እንዲሁም ለደረጃ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል። የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ሰ/ት/ቤት ከሌሎች ተፈታኝ ሰ/ት/ቦእቶች የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
+3
ቅዱስነታቸው በተገኙበት የተቀጸል ጽጌ በዓል በድምቀት ተከበረ !!!
#የተቀጸል ጽጌ በየዓመቱ መስከረም 10 ቀን የሚከበር ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው በዓል ነው !!!
#በዓሉ የመስቀልን በዓል ከምስጋና ና ከደስታ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን፣ በተጨማሪም ክረምት አብቅቶ የመጸው (የአበባ) ወቅት መግባትን የሚያመለክት ነው።
#በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከበረው በዚህ በዓል ላይ
#ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
#ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ የበላይ ኀላፊ
#ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ፣የሐዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ
#ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያውና የየድርጅት ኃላፊዎች
#የአዲስ አበባ ሀገረስብከት የሥራ ኀላፊዎች፣ የአድባራት ና ገዳማት አስተዳዳሪዎች
#ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ማህበረ ካህናት ወጣት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል ።
#በበዓሉ ልዩልዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች ቀርበዋል።
#ስለ በዓሉ አመጣጥና አጠቃላይ ይዘት ትምህርተ ወንጌል ከተሰጠ በኃላ በቅዱስነታቸው አባታዊ ቡራኬ በጸሎት ተፈጽሟል !!
መረጃው የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
እንኳን ደስ አላችሁ!
ሦስተኛ ዙር የ፲፪ኛ ክፍል የምርቃት መርሐ ግብር
በ2017 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የ፲፪ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ምዘና የተመዘኑ ተማሪዎች ምረቃ
ዕለተ እሑድ መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ
ከቀኑ ፯ ጀምሮ
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
+5
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማ የመንበረ ጵጵስና ገዳማትና አድባራት የሰ/ት/ቤቶች የሥርዓተ ትምህርት አተገባበር የመምህራን የአሠልጣኞች ሥልጠና መርሐ ግብር ተከናወነ።
በመርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ዘካርያስ ፀጋው፤ የሀ/ስብከቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት ትሕትና አበበ የሀ/ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሐላፊ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዘሪሁን ጣፋ ተገኝተዋል።
ሀ/ስብከቱ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተቀረጸውን ሥርዓተ ትምሕርት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል። ሥልጠናውንም ቁጥራቸው ከ40 በላይ የሚ ሆኑ የአብነት መምህራን ፣ የስብከተ ወንጌል መምህርና ከሰንበት ትምህር ቤቶች የተውጣጡ የሰንበት ትምርህት ቤቶች መምህራ ወስደዋል።
መረጃው ያደረሰን የሀገረ ስብከቱ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
+5
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሰዎ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል ።
በዕለቱም ብፅዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የምሥራቅ ደቡብ ትግራይ እና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ልዩ ልዩ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ እና ሰንበት ተማሪዎች ተገኝተዋል።
መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኀን ነው።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
