ምክር ለወጣቶች
الذهاب إلى القناة على Telegram
"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
7 288
المشتركون
-524 ساعات
+1227 أيام
+79230 أيام
أرشيف المشاركات
7 287
˓٭˛ ،🌸
من ظنَّ أن ذنبه لا يُغفر
فقد ظنَّ بالله سوءا..
استغفروا..🌱
˓٭˛✿🌹🍃
ወንጀል እንደማይማርለት ያሰበ ሰው፣ በእርግጥም በአላህ ላይ መጥፎን አስቧል (ጠርጥሯል).
ምህረትን ጠይቁ..🌱"**
7 287
የጧት ዚክር እንዳንረሳ!
اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.
አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል በአንተ ለምሽት እንበቃለን በአንተ ህያው እንሆነናን በአንተም እንሞታለን መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
መልካም ውሎ☕️🍫☕️🍫
•━════✿🍃🌺🍃✿════━•
https://t.me/nejashi_nejashi
7 287
✅السلام عليكم وراحمة الله و بركاته✅
ቁርአን ከቃኢዳ ጀምሮ መቅራት ምፈልጉ ብቻ በዚህ አናግሩኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Mujahid_Selefi
የምንቀበለው ተማሪ ብዛት
ቃኢዳ 5 ነዘር 5 ሂፍዝ 5 ተማሪ ብቻ ነው
7 287
🇸🇦ሰለፊዮች ሆይ የምርጥ የሰለፊይ መሻይኮች ኡስታዞች እንዲሁም ወንድሞች ቻናል እያለላቹ በየሙብተዲእ ቻናል ምን ትሰራላቹህ?
አሁን ጉዳዬ ላሳጥርላቹህ እና ከታች ጆይን የምትለዋን ምልክት ስትፈልጉ በአውራ ጣታቹ ስትፈልጉ በቀለበት ጣታቹ ብቻ በፈለጋቹት ጣታቹ ጆይን(JOIN) የምትለዋን ምልክት በመንካት ወደ ኢትዮጵያ የሰለፊዮች ቻናል ተቀላቀሉ🇸🇦
7 287
በቅጡ አንድ የአቂዳ ኪታብ ሳይቀሩ ንፅፅር ንፅፅር እያሉ የሚጃጃሉ እህቶችን ሳይ በጣም አዝናለው።እስኪ መጀመሪያ አቂዳቹን በእውቀት ገንቡት ንፅፅሩ ቀስ ተብሎ ይደረስበታል
7 287
👉 የአሕመዲን ጀበል ቅጥፈት በነብዩ ላይ !
ክፍል ሁለት
በክፍል አንድ ላይ ሶሞኑን የደረሰኝ አሕመዲን ጀበል ከጋዜጠኛ ለቀረበለት ኢትዮዽያ በሸሪዓ እንድትተዳደር ትፈልጋለህ ወይ ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ አጭር መልስ ከመመለስ ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም ሄዶ ነብዩ ሙሐመድ መዲናን ያስተዳደሩት በሴኩላር ( ሀይማኖትን በማይቀበል አለማዊ ህግ ) ነው የሚል ምላሽ መስጠቱን አይተናል ።
በዚህኛው ክፍል በአላህ ፈቃድ ንግግሩ ቅጥፈት መሆኑን ከስምምነት ሰነዱ ነጥቦች እናረጋግጣለን ። ( صحيفة المدينة ) ሶሒፈቱል መዲና የሚለው ሰነድ ወይም ህገ – መንግስት የተፃፈው በነብዩ ሙሐመድ በራሳቸው ሲሆን በውስጡ የያዘው ጭብጥ በመለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆነው ህያው ቃል ( ቁርኣን) በመታገዝ መሆኑን አላህ ሲነግረን እንዲህ ይላል : –
وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
ከልብ ወለድም አይናገርም ፡፡
إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ
እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም ፡፡
النجم ( 3–4)
የአላህ መልእክተኛ እንኳንስ ለዘመናት ዱስቱር ሆኖ የኢስላሙ ዓለም ከሌሎች ጋር በሚኖረው ግንኙነት የሚመራበት ህግ ይቅርና በማንኛውም የዲን ጉዳይ ከልብወለዳቸው አይናገሩም ነበር ። ለዚህም ነበር ስለሆነ ጉዳይ ሲጠየቁ በዛ ጉዳይ ወሕይ ያልወረደበት ከሆነ ጅብሪል እስኪመጣ ዝም ይሉ የነበረው ! የመዲናው የስምምነት ሰነድ ቁርኣንን ለሚያውቅና ከቁርኣን ጋር ግንኙነት ላለው የአላህ መልእክተኛ በነበራቸው ጥልቅ የቁርኣን ግንዛቤና እውቀት እንዲሁም በልባቸው የሸመደዱት ስለነበር ከዛ ላይ የወሰዱት ለመሆኑ በማያሻማ መልኩ ከተቀመጡ ነጥቦች ውስጥ እናገኘዋለን ።
የመዲና የስምምነት ነጥቦች በዋነኝነት የሚያጠነጥኑት በፍትህ ጉዳይ ላይ ሲሆን ሀገርን በጋራ ከጠላት መከላከልና በሙስሊም ሀገር ላይ የሌላ እምነት ተከታዮች እንደ ሀገር በቁርኣንና ሐዲስ እየተዳኙ በግል ህይወታቸው የመረጡትን እምነት ማራመድ እንደሚችሉ የሚደነግግ ነው ። ለመሆኑ የቁርኣን ሽታ ላሸተተ ሙስሊም እነዚህ መርሆች ከቁርኣን ውጪ አለማዊ መርሆች ናቸው ይላል ? ምናልባት ቁርኣንን የማያውቅ ከልብወለዱ የሚናገር አካል ካልሆነ በስተቀር !
በስምምነት ሰነዱ ወይም ( ሶሒፈቱል መዲና) ላይ ሙስሊሞች ፣ አዩሁዶችና አጋሪያን ዐረቦች ተስማምተው ሊያከብሯቸውና ሊሰሩባቸው ከፈረሙባቸው ነጥቦች ውስጥ በግልፅ ከተቀመጡት መካከል የመዲናው ኢስላማዊ መንግስት በበላይነት የሚያስተዳድርበት ህግ ቁርኣንና ሐዲስ መሆኑን እንደሚያውጅ በተለያዩ የነብዩ የህይወት ታሪክ ተዘግቦ እናገኛለን ።
የስምምነት ነጥቦቹ ከ47–51 የሚደርሱ ሲሆን አንዳንድ መዛግብቶች ሁለትና ሶስት ሀሳቦችን እንደ አንድ ስለዘገቧቸው 47 ሲያደርጓቸው አንዳዶቹ ነጣጥለው በመመዝገብ እስከ 51 ያደርሷቸዋል ። ይህ በትላልቅ መዛግብቶች ላይ ሲሆን አነስተኛ መጠን ያላቸው መዛግብቶች ጨምቀው እስከ 16 ያደረሷቸውም አሉ ። ነገር ግን ሁሉም የዘገቡትና የመዲና የሙስሊሙ መንግስት የበላይ ህግ ቁርኣንና ሐዲስ መሆኑን ስለሆነ ቁጥሩ ስለሚለያይ ዐረፍተ ነገሩን እንይ : –
1— وإنه مهما اختلفتم فيه من شيء فإن مرده إلى الله وإلى محمد .
ትርጉም : – " ነገሩ በአንዳች ጉዳይ የፈለገ ብትለያዩ ( ባትስማሙ) መመለሻው ወደ አላህና ወደ ሙሐመድ ነው " ።
ሁሉም የስምምነቱ አካላት በተሰጣቸው እድል ተስማምተው መፋረድ ካልቻሉ የበላዩ ዳኛ እንደ ሀገር የሚፈረድበት ድስቱሩ ቁርኣንና ሐዲስ መሆኑን በዚል ልክ ያስቀምጣል ። ለመሆኑ ይህ የነብዩ ህገ መንግስት ነው secular constitution ይዘት ያለው ? !!!
2— وإن ما كان بين أهل هذه الصحيفة من حدث، أو اشتجار يخاف فساده فإن مرده إلى الله وإلى محمد رسول الله – صلى الله عليه وسلم – وإن الله على أتقى ما في هذه الصحية وأبره.
ትርጉም : –
" ይህን የስምምነት ውል ሰነድ በተፈራረሙ አካላት መካከል የሚፈጠር አዲስ ነገር ወይም ነገሮች ማበላሸቱ የሚፈራ አለመግባባት መመለሻው ወደ አላህና ወደ ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ነው ። አላህ በዚህ ስምምነት አላህን ፈርቶ ካሳመረ ጋር ነው " ።
ተመልከቱ አሁንም በስምምነቱ ባልተቤቶች መካከል የሚፈጠሩ ማናቸውም አለመግባባቶች የሚዳኙት በቁርኣንና ሐዲስ በአላህና በነብዩ ህግ እንደሆነ በማያሻማ መልኩ ያስቀምጣል ። ታዲያ የአላህ መልእክተኛ መዲናን ያስተዳደሩት በሰው ሰራሽ አለማዊ ህግ ነው ወይስ በመለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆኑት ሁለቱ ወሕዮች ?
አላህ ሆይ ልባችንን ሐቅ እንዲያውቅ ካደረግኸው በኋላ ወደ ባጢል እንዲዘነበል አታድርግብን ።
አቶ አሕመዲን ጀበል የተጠየቀው የግል አመለካከቱን ሆኖ ሳለ ለምን ይሆን ከቀጥተኛ መልስ ወደዚህ ቅጥፈት መዞር የፈለገው የሚለውና ለጋዜጠኛዋ ጥያቄ መልስና በሸሪዓ መተዳደር በሚለው ነጥብ ላይ በኛና በኢኽዋኖች መካከል ያለውን ወርቃማ ልዩነት አላህ ካለ በሚቀጥለው ክፍል እናያለን ።
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
http://t.me/bahruteka
7 287
አንድ ቀን ....!
አንተን አፈር ዉስጥ ማስገባት
የቀብር ጨለማ ዉስጥ መጣል አንተን እደማክበር የሚቆጥሩበት ጊዜ ይመጣል ።
በቁምህ እያለህ ስትከብዳቼዉ ሲሰለቹህ የነበሩ ሰዎች የዛኔ አንተን አፈር ጋር ለመጨመር ያለ ሀይላቼዉን ይጠቀማሉ አትከብዳቼዉም ።
https://t.me/nejashi_nejashi
7 287
ውበት የት ነው? ቀለምና ዘርስ የት ናቸው?
ኩራት የት ነው? ማዕረግና ሹመትስ የት ናቸው?
ሀብት የት ነው? የተከማቸው ገንዘብስ የት ነው?
ትዕቢት የት ነው? መዝናናትና ደስታስ የት ናቸው?
إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُمْ مَيِّتُونَ
"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟች ናቸው።"
https://t.me/nejashi_nejashi
