ምክር ለወጣቶች
前往频道在 Telegram
"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"
显示更多未指定国家未指定类别
7 288
订阅者
-524 小时
+1227 天
+79230 天
帖子存档
7 293
ትክክለኛው ውበቷኮ ያለው ዲኗ እና አኽላቃ ላይ ነው እና አንተ እዴት ነው በዲን በአኽላቅ ዜሮ የሆነችን ለገላዋ ብለህ ምታገባው?
አኺ ነቃ በልኝጂ🙌
7 293
የአሕመዲን ጀበል ቅጥፈት በነብዩ ላይ !
ክፍል ሶስት
አቶ አሕመዲን ጀበል ከትክክለኛ መልስ ለምን መዞር መረጠ ?
አቶ አሕመዲን ጀበል ከጋዜጠኛዋ ለቀረበለት ያንተ የግል አመለካከት ኢትዮዽያ በሸሪዓ ትተዳደር የሚል ነው ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ቀጥተኛ ባይሆን አላስብም በሚል መልሷል ። በዚህ አላቆመም ዙሪያ ጥምጥም ሄዶ ሸሪዓ ሲባል ሰዎች ይደነግጣሉ ነገር ግን በሸሪዓ መተዳደር ማለት ሚዲያ ላይ ያለውና መሬት ላይ ያለው እውነታ ይለያያል ። ካለ በኋላ ነብዩ ሙሐመድ መዲናን በበላይነት ያስተዳደሩበት ህግ የsecular ህግ ነው ወደሚል ነው የደረሰው ። ለምንድነው የዚህ አይነት መልስ መስጠት የፈለገው ከተባለ ከንግግሩ እንደምንረዳው ኢኽዋኖች የስልጣን ወንበር ላይ ቢወጡ በዲሞክራሲ ማስተዳደር እንደሚፈልጉ ለማሳየት ይመስላል ። ይህም የነብዩ ሸሪዓ በማስመሰል ሙስሊሙ እንዲቀበለው ለማድረግ ባለመመልኩ የተዘረጋ መረብ መሆኑ ግልፅ ነው ።
ከዚህ በፊት አቡ በከር አሕመድ ኢትዮዽያ ውስጥ ዲሞክራሲ ከተከበረ እምነቴን ይወክላል ። ኢትዮዽያ ውስጥ ኢስላማዊ ሸሪዓ መምጣት አለበት ብሎ ማሰብ ወንጀ ነው ብለን እናምናለን ብሎ ነበር ። ድምፁን በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ :–
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/3740
ስለዚህ የኢኽዋን መሪዎች የሚፈልጉት በሸሪዓ ስም ስልጣን እንጂ ሸሪዓን አይደለም ። የሚገርመው አለማዊውን የዲሞክራሲ ህግ የሸሪዓ ህግ ለማስመሰል መሞከራቸው ነው ።
አሁንም አቶ አሕመዲን ጀበል ኢትዮዽያ ውስጥ እንደግልም እውነተኛው የሸሪዓ ህግ ሊመጣ እንደማይፈልግ ነግሮናል ። ከዚህ የሚከፋው ነብዩ መዲናን ያስተዳደሩበት ህግ አለማዊ ህግ ነበር ማለቱ ነው ።
ለጋዜጠኛዋ ጥያቄ የኔ መልስ !
ለአቶ አሕመዲን ጀበል ጥያቄ ላቀረበችውም ሆነ ሌሎች ሊጠይቁ ለሚፈልጉ በሙሉ ባሕሩ ተካ (ሰለፍዩ) ኢትዮዽያ ብቻ አይደለም አለም በሙሉ በሸሪዓ ህግ እንዲተዳደር እፈልጋለሁ ! ለዚህም አላህን እለምናለሁ ። ነገር ግን እናንተ አእምሮ ውስጥ ያለው በሸሪዓ መተዳደር ማለት መግደል ማረድ የሚል ቅዠት ከሆነ ምእራባዊያን በአእምሯችሁ ላይ የሳሉት ስእል ነው አጥፉት እላችኋለሁ ። አይ እኛ በሸሪዓ መተዳደር ማለት ያ አግባብ በግፍ ሰውን የገደለ ይገደል ፣ አይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ ፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበር ፣ ረሀቡን ለማስታገስ ሳይሆን በሰው ሐቅ ለመክበር የዘረፈን ( የሰረቀ ) እጁ ይቆረጥ የሚለውን ነው የማንፈልገው እናንተ ይህን ነው ወይ የምትፈልጉት ? ከሆነ በቅድሜያ እኔ አው እላለሁ ! ምክንያቱም አለም በምናቡ የሚያየው እውነተኛ የሀገር ሰላም ፣ ፍትህና ያለ ስጋት ወደ ፈለጉበት ወጥቶ መግባት ሊገኝ የሚችለው አለም በሸሪዓ ህግ ስትተዳደር ነው ። እነዚህ ሸሪዓዊ ድንጋጌዎች አላህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ባሮቹ በሰላም ፣ በመከባበር ፣ ፍትህ ተጠብቆ ለመኖር እንዲችሉ ነው ። ለዚህ ነው አላህ በተከበረው መለኮታዊ ቃሉ እንዲህ የሚለው : –
{ وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ }
البقرة (179)
" ለእናንተም ባለ አእምሮዎች ሆይ ! በማመሳሰል (ሕግ) ውስጥ ሕይወት አላችሁ ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ (ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ) " ፡፡
ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ የገደለን መግደል የደነገገው ትጠነቀቁ ዘንድ ነው ይላል ። ምክንያቱም ማንም መገደል ስለማይፈልግ ሰው አይገልም ። በዚህም የሰው ልጆች ህይወት ይጠበቃል ። ሌሎቹም ህግጋት እንደዚሁ ናቸው ። ለዚህ ነው አለም የሚፈልገው አይነት ሰላምና ፀጥታ በሸሪዓ ህግ በመተዳደር እንጂ ሊመጣ አይችልም የምንለው ።
በኛና በኢኽዋኖች መካከል በሸሪዓ ጉዳይ ላይ ያለው ወርቃማ ልዩነት !
እኛ ሰለፍዮች የሸሪዓ ህግ ስልን ከላይ በተገለፀው መልኩ አላህ ለሰው ልጆች በምድር ላይ ሊኖሩበትና ሊከተሉት የደነገገውን ህግ ነው ። ይህ እንዲሆን ስንፈልግ እኛ ስልጣን ላይ ያለውን አውርደን ወንበሩን ይዘን መሆን አለበት ሳይሆን ስልጣን ላይ ያለው አካል አላህ ሂዳያ ( ቅኑን መንገድ መመራቱን) ሰጥቶት በሸሪዓ ያስተዳድር በሚል ነው ።
ኢኽዋኖች ሸሪዓ የሚሉት ዲሞክራሲን ሲሆን ስልጣን ላይ ያለውን አውርደን እኛ ስልጣኑን ተረክበን በሸሪዓ ስም በዲሞክራሲ መምራት አለብን ነው የሚሉት ። ለዚህ ነው " ሊበሉዋት ያሰቧት አሞራ ጅግራ ይሏታል " እንደሚባለው ዲሞክራሲ ማለት ሸሪዓ ማለት ነው የሚሉት ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።
ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/7520
ክፍል ሁለትን ለማግኘት
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/bahruteka/7521
አበቃሁ!
http://t.me/bahruteka
7 293
ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ :-
አላህን ፈሪ ለመሆን ወንጀል አለመስራት መስፈርት አደለም። ከወንጀል ጥቡቅ መሆንም የግድ አደለም። ነገሩ እንደዛ ቢሆን ኖሮ በኡማው አንድም አላህን ፈሪ አይኖርም ነበር። ነገር ግን ከወንጀሉ የቶበተ አላህን ፈሪ ይሆናል። ወንጀሉን ሚያስምር ሌላ መልካም ስራ የሰራም ሰው አላህን ፈሪ ሚለው ውስጥ ይገባል።
📙:|[ሚንሀጁ ሱና (٧ / ٨٢) ]
https://t.me/nejashi_nejashi
7 293
˓٭˛ ،🌸
من ظنَّ أن ذنبه لا يُغفر
فقد ظنَّ بالله سوءا..
استغفروا..🌱
˓٭˛✿🌹🍃
ወንጀል እንደማይማርለት ያሰበ ሰው፣ በእርግጥም በአላህ ላይ መጥፎን አስቧል (ጠርጥሯል).
ምህረትን ጠይቁ..🌱"**
7 293
የጧት ዚክር እንዳንረሳ!
اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.
አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል በአንተ ለምሽት እንበቃለን በአንተ ህያው እንሆነናን በአንተም እንሞታለን መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
መልካም ውሎ☕️🍫☕️🍫
•━════✿🍃🌺🍃✿════━•
https://t.me/nejashi_nejashi
7 293
✅السلام عليكم وراحمة الله و بركاته✅
ቁርአን ከቃኢዳ ጀምሮ መቅራት ምፈልጉ ብቻ በዚህ አናግሩኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Mujahid_Selefi
የምንቀበለው ተማሪ ብዛት
ቃኢዳ 5 ነዘር 5 ሂፍዝ 5 ተማሪ ብቻ ነው
