cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media

እሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 972
Obunachilar
+524 soatlar
+387 kunlar
+20430 kunlar
Post vaqtlarining boʻlagichi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Nashrni tahlil qilish
PostlarKo'rishlar
Ulashishlar
Ko'rish dinamikasi
01
Media files
10Loading...
02
"የዘራህው ካልሞተ አይነሳም"  1ቆሮ  15:36  ቅዱስ ጳውሎስ ትንሣኤን ያስረዳበት ትምህርት ነው። ከሞት በኋላ ትንሣኤ እንዴት እንደሚኖር።  አንዳንድ ሰው እግዚአብሔርን በአእምሯቸው ካልሳሉ ላያምኑ አይፈልጉም። እግዚአብሔር ደግሞ በሰው አእምሮ የሚረዳ አይደለም።  የስንዴ ዘር ከውጭ እስከ ሆነ ድረስ ደረቅ ወይም ሙት ነው። መሞቱን የምናውቀው እንቅስቃሴ ስለሌለው ነው። እንቅስቅሴ የህይወት ምልክት ነው። እንቅስቃሴ ከሌለ ሙት ነው። ካልተነፈስኩ ሞቻለሁ ማለት ነው። ከተንቀሳቀስኩ አለሁ ማለት ነው።  ይህ ዘር ካልቀበርከው ሕያው መኾን አይችልም። እንደ ቀበርከው ሕያው መኾን ይጀምራል ሕያው ነው። ካልቀበርከው ሕያው አይሆንም። ሙት ነው።  የምንወዳቸውን ስንቀብራቸው ሕያው መኾን ይጀምራሉ። በምድር ሳለን የሞቱ ዘሮች ነን። የሚንቀሳቀስ ዘር ነን። ስንቀበር እንኖራለን። እንደ ዘሩ። አፈር ሲጫነን ሕይወት እንጀምራለን።  አንድ ፍሬ ሲዘራ ብዙ ዘር ያፈራል። የምታገኘው የዘራህውን አይደለም እጥፍ ነው። ለቀበርነውን ሰው ሁሌ እናለቅስለታለን። ትክክል አይደለም። የምናምን ከሆነ የትንሣኤ ልጆች ነን። ለተነሣ ሰው አናዝንም። ስቀበር ሕያው ነኝ። ስኖር ሙት ነኝ።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
280Loading...
03
Media files
180Loading...
04
ሃምሳው ቀናት  ሃምሳው ቀናት እንደ አንድ ቀን ሆነው ይታያሉ። ረቡዕና ዓርብ ሳይቀር አይጾሙም። ጠዋት ይቀደሳል፣ በጠዋት ይበላል። በሃምሳው ቀን ጾም የለም። የጾም ቀኖና አይሰጥም።  እነዚህ ሃምሳ ቀናት ወጪ ገቢ በሆነው ወይም ሂያጅ linear ሓላፊ በሆነው አሁን ባለንበት ቀን አቆጣጠር Chronos በሆነው ጊዜ ሲታዩ ከሰኞ እስከ እሑድ እንዳሉት ቀናት ይኖራቸዋል  እንጂ በቤተ ክርስቲያን ወይም በትንሣኤ የቀን አረዳድ የማያልፈው ጊዜ (Kairos) ማሳያ ናቸው።  ይኽ ዘመን አልፎ ከትንሣኤ በኋላ መምሸት መንጋት የጊዜ መፈራረቅ የለም ሰኞ ማክሰኞ የሚባል ቀን የለም። አንድ ሕይወት ነው የሚኖረው። ከትንሣኤ በኋላ ያሉት ሃምሳ ቀናት የዚያ ዘለዓለማዊ ሕይወት ማሳያ ናቸው።  ሃምሳው ቀን ከትንሣኤ በኋላ ያለውን ሕይወት በጥቂቱ እየቀመስን ነው። “ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን” 2 ቆሮ.5:5  መያዥ ማለት ቀብድ ነው። ከዋጋው ያነሠ ሆኖ እቃውን ለመግዛት ማስያዣ ነው። ቀብድ የከፈለ ሰው ሙሉ ዋጋውን ከፍሎ እቃውን ይወስዳል። ቀብድ መክፈል እቃውን ለመግዛት ማረጋገጫ ነው። ዕቃውን ካልገዛ የከፈለው ቀብድ ይቀርበታል።  ክርስቶስ ከሞት በኋላ ለሚሰጠን ሕይወት ማረጋገጫ ሰጥቶናል። ለዚያ ሕይወት ማሳያ አንዱ ከትንሣው በኋላ ያለው የሃምሳው ቀን ነው። ትንሣኤ የሥጋ ትንሣኤ መያዣ ነው ትንሣኤ የሁሉም ነገር መሠረት ነው። ያለ ትንሣኤ ክርስትና አይኖርም ነበር። “ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት” 1.ቆሮ.15:17 ክርስትናችን የተመሠረተው በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ነው። ወደ ክርስትና የምንገባበት በር ጥምቀት ነው። የምንጠመቀው በሞቱና በትንሣኤ ልንሳተፍ ነው። ወደ ውኃው ስንገባ ሞት ወይም መቀበር ነው። ስንወጣ ትንሣኤ ነው። “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” ሮሜ.6:4 ሞትና ትንሣኤውን እንመሰክራለን የመጠመቂያው ገንዳ (ቦታ) ጎልጎታ ነው። ጌታ ሞቶ ባይነሣ ኖሮ ጥምቀት የለም ነበር። የተጠመቅነው በሞቱና በመነሣቱ ነው።  የምንቀበለው ሥጋና ደም በሞቱና በትንሣኤው የተመሠረተ ነው። ባይሞትና ባይነሣ ኖሮ ሥጋና ደሙን አይሰጠንም ነበር። ሥጋው መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው ነው። ሥጋውን በመስቀል ላይ የሰጠን ስለ ሞተ ነው። ሞትን ድል አድርጎ የተነሣ ስለሆነ እንቀበለዋለን። ሞቶ ባይነሣ ግን አንቀበለውም ነበርም።  ሞት ይዞት ያላስቀረው ሕያው ስለሆነ ሞት ሊይዘው ያልቻለ ሕያወ ባሕርይ ስለሆነ ሕይወትን የሰጠን ስለሆነ የእርሱን ሥጋ እንደበላለን ደሙን እንጠጣለን። ሞትን ድልን አድርጎ ስለተነሣ ሕይወት ነው። ሞቶ ቢቀር ኖሮ ሥጋውን ማን ይበላል ቢበላስ ምን ይጠቀማል?።  ሞትን ድል የሚያደርግ ሕይወት ስለሆነ የሞት መድኃኒት ስለሆነ The medicine of immortal “ኢመዋቲነትን የሚሰጥ ዘር” አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ።  ክህነት መሠረቱ ትንሣኤ ነው። በይሁዳ ምትክ ሰው ሲመርጡ መለኪያው የትንሣኤ ምስክር መሆንን ነው። “ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል” ሐዋ.1:21  ክህነት ያስፈለገው ሞትና ትንሣኤውን መመስከር ነው። መምህራን ያስፈለጉትም ለዚሁ ነው።  ተክሊል መሠረቱ የክርስቶስ  ሞትና ትንሣኤ ላይ ነው። ጋብቻ ሊፈጽሙ የወሰኑ በአንድነት የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም በሚወስኑ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ጥንዶች በጸሎት ከብረው ሥጋወደሙን ተቀብለው አክሊል ደፍተው ጋብቻ የሚፈጽሙት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ላይ ነው። የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በተግባር ለመኖር ነው።  ክርስቶስ ሞትን ድል እንዳደረገ እናንተም በዚኽ ዓለም ያለ ውጣ ውረድን ክርስቶስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶ ድል እንዳደረገ እነርሱም ድል ያደርጉ ዘንድ አክሊል ይደፋሉ። ይኽ አክሊል ክርስቶስ የደፋው የአሸናፊነት  አክሊል ነው።  የክርስቶስ አክሊለ ሶክ ከብረት የጠነከረ ከጠንካራ የእንጨት እሾኽ የተሠራ ነው። የቤተ ክርስቲያን አክሊል የሚዋጋ ነው። ትዳር የደስታ ሕይወት አይደለም። ለብቻ ሆኖ የሚከብድን መስቀል ሁለት ሆኖ መስቀሉን ተሸክሞ መክበር ሕይወት ነው። የሚደፋው አክሊል የካሜራ ጌጥ አይደለም። አክሊለ ሶክ ነው።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
191Loading...
05
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት! ▪️የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ውጡ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ 11 ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ▪️መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ የፊጥኝ እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው መገኘታቸውን፤ ሙሉ ሪፖርቱን ከስር ባለው ሊንክ ይከታተሉ! 👉🏿 https://ehrc.org/?p=28122
670Loading...
06
የኢሰመጉ 40ኛ መደበኛ መግለጫ የኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምርመራ ግኝቶች ዓመታዊ መግለጫ የኢሰመጉ 40ኛ መደበኛ መግለጫ-ግንቦት 20/2016 ዓ.ም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይንኩ። https://t.me/ehrcow
720Loading...
07
ሰላም አደራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን
1820Loading...
08
Media files
1621Loading...
09
የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል። ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) በየዓመቱ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን የሚካሔደው ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ መሪነት የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሔዳል። በየዓመቱ የሚካሔዱት ሁለቱ ጉባኤያት አንደኛ ቋሚ በሆነ ቀን በጥቅምት 12 ሲጀምር ሁለተኛው ግን የአጽዋማቱን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣው የባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት በዓለ ትንሣኤ በዋለ 25 ኛ ቀን የርክበ ካህናት ጉባኤ ይከናወናል። በዚህ በ2016 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን በዋዜማው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፕትርክና መንበሩ ከግብፁ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም ወዲህ አስቸኳይ ጉባኤያትን ሳይጨምር 128 መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት መካሔዳቸውን ታሪክ ያስረዳል። ከነዚህ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቅዱሳን ፓትርያርኮች ጥረት ርእሰ መንበርነት የተመሩ ሲሆን በሁለት የተለያዩ ዓመታት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፓትርያርክ ባለመኖሩ ምክንያት በአቃብያነ መንበር በብፁዓን አባቶች ተመርተዋል። ከእነዚህ አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ በወቅቱ በነበረው አገዛዝ ምክንያት በግፍ ለግዞት ስለተዳረጉ ግንቦት 11 ቀን 1968 ዓ.ም የዋለውን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቃቤ መንበር በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የመላ ትግራይ ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት ተመርቷል። ሁለተኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በማረፋቸው ምክንያት የጥቅምቱ 12 ቀን 2005 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖደስ ምልዓተ ጉባኤን የወቅቱ አቃቤ መንበር የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በርእሰ መንበርነት መርተዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን እምነት የማጽናት ሥርዓትን ማስጠበቅ አስፈላጊ ከሆነም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች የማሻሻል ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ነው። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።” ሐዋርያት ፳፥፳፰
1601Loading...
10
https://www.youtube.com/live/8xRsV3llPwU?si=nKveXCvx00rdTZks
2560Loading...
11
ለካ ጳጳስም ይበላል እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጳጳስ ወደ ገጠር ሄዶ ስለማያስተምርና ሕዝቡ በአካል ስለማያውቀው ጳጳስ በአብዛኛው ሰው ዘንድ ከሰውነት ከፍ ያለ ተደርጎ ይታሰብ ነበር። አብዛኛው ሰው ጳጳስ ሲባል የሚበላ ራሱ አይመስለውም ነበር። በቅርብ ነው ባለፈው ዓመት ጥር ፲፬ ላይ በሕገ ወጥ መልኩ የተሿሿሙ ሰዎች ደመወዙም አበሉም እስከ 400,000 (አራት መቶ ሺ ብር) እንደሚደርስ ከራሳቸው አንደበት የሰማነው። ይህን የሰማ ጳጳስ የሚበላ የማይመስለው የነበረ ምእመን ደነገጠ። ይባስ ብሎ እኒህ ሰዎች ንፁሕ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ አማራ እየተባባሉ በዘረኝነት በሽታ ተለክፈው በየአደባባዩ ሲናገሩ ሰማን። ንጹሕ ኦሮሞ ሾምንላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ አሉን። እኛም ተሳቀቅን። በነገራችን ላይ ጥር ፲፬ በኦሮሚያ የተደረገውም፣ ሐምሌ ፲፭ በትግራይ የተደረገውም ሁለቱም ሕገ ወጥ እና ከቀኖና ያፈነገጡ ናቸው። የኦሮሞው ገዥዎቹ ኦሮሞ በመሆናቸው ወደሲኖዶስ እንዲቀላቀል ተደረገ። የትግሬው ግን ገዢዎቹ ከአራት ኪሎ ስለተባረሩ እንደተወገዘ ቀረ። አሳዛኙ ነገር ይህ ነው። ሲኖዶስ በብልጽግና ፓርቲ ተጽእኖ ስር ወድቆ ውሳኔው እንኳ ቀኖናዊ ሳይሆን ዘርን መሠረት ያደረገ ሆነ። አሁን ላይ የምለው ቢኖር አባቶች ከብልጽግና ይልቅ እግዚአብሔርን ፈርተው እግዚአብሔር የሚወደውን በቀኖና የተጻፈውን እንዲተገብሩ እመኛለሁ። በነገራችን ላይ የባለፈው ዓመት የቀኖና ጥሰት እስካሁን ስላልተስተከከለ ሲኖዶሱ በአሁኑ ያስተካክለዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ተረስቶ ዝም ይባላል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ ተሳስተችኋል። © በትረማርያም አበባው የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
2600Loading...
12
አብይ አህመድ ቤተክርስቲያንን ገና እንደ ሚያፈራርሳት በግልጽ ነው ሚናገረው እኛ ካልፀናን መከራው ገና እየተጀመረ ነውን ሰላም አደራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን
4234Loading...
13
በእነ በጀኔራል ይልማ መርዳሳ የቦርድ ሰብሳቢነት በነ አቶ መስፋን ጣሰው ስራ አስፈፃሚነት የሚመራው የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ዓለም አቀፍ civil aviation law በመተላለፍ ወታደራዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው ተባለ። በተደጋጋሚ ወታደሮች እና ተተኳሽ ሚሳይሎችን በማጓጓዝ በዐማራ ሕፃናት በዐማራ እናቶች ላይ ለሚፈጸመው ጭፍጨፋ ተባባሪ ሆኗል ሲሉ የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል። https://t.me/Moamediamoresh
3242Loading...
14
🤔🤔🤔
3221Loading...
15
https://www.youtube.com/live/YXydBoxke9A?si=7dLjnT8YwU4T7m3n
2770Loading...
16
Media files
2820Loading...
17
#ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡  ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ? - የሃይማኖት ተቋማት የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት። - የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን አለባቸው። - የሃይማኖት ተቋም በራሱ #የገቢ_ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ለዚሁ ሥራ ሲባል የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ አለበት። - ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ሲያሳውቅም ፦ ° የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እና አድራሻ፣ ° የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነት እና መጠን ፣ ° ስጦታው / ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት አለበት። - ማንኛውም  የሃይማኖት ተቋም  የበጀት ዓመቱ ባለቀ በ3 ወር ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር አለበት። የኦዲተሩን አቋም እና የውሳኔ ሐሳብም መያዝ ይኖርበታል። - የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል። #ሪፖርተርጋዜጣ @tikvahethiopia
2831Loading...
18
👆👆👆 ይህ ነገር በቀጥታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን አሽመድምዶ ለመጣል ሆን ተብሎ ታስቦበት የራቀቀ አዋጅ ነው።
3030Loading...
19
ሰርግ 💍❤️ በዛሬዋ ዕለተ ሰንበት በመቐለ ከተማ በሥርዓተ ተክሊል ቅዱስ ጋብቻቸውን ለፈጸሙት ለጀግናዋ * አትሌት ለተሰንበት ግደይ እና * ለዲያቆን ፍስሐ ኪሮስ ቅዱስ ጋብቻችው የአብርሃምና የሣራ ይሁን‼ ርሑስ ጋማ🌹 📷 Petros Ashenafi
3762Loading...
20
ዐብይ እንደ ሸንኮራ ልጣኝ አኝኮ ይተፋሃል።የገዛ ወገኖቹን ሃጫሉ ሁንዴሳንና ባቴ ኡርጌሳን በሞት ያስወገደ፥ለማ መገርሳን ከሥልጣን ያባረረ፥ታዬ ደንደአን ወደ ዘብጥያ ያወረደ ዐብይ ለአንተም ቀን እየቆጠረልህ ነው።ከእግዚአብሔርም ከሕዝቡም ተጣልተሃል።መውደቂያ ወዴት ይሆን!የበደልካትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ጠይቅ።
3630Loading...
21
በመጨረሻው ዘመን…! "…በኢሰመጉ ላይ መንግሥት እየፈጸመ ያለው ከፍተኛ ጥቃትና ጫና አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል! ሲል ራሱ የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በይፋ ገልጿል። "…ዜጎች ተበደሉ፣ ተገደሉ፣ ተፈናቀሉ ብሎ ከመጮህ የዘለለ በመንግሥት ላይ ይሄን ያህል ጉዳት የማይፈጥረውና ዘገባ ከማውጣት የዘለለ፣ መንግሥት አጥፊዎችን ለፍርድ ያቅርብ እያለ ከመወትወት ያለፈ ሥልጣን የሌለው ኢሰመጉ በመጨረሻ ራሱ ለራሱ አስጊ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መግለጫ አውጥቶ ሁሉም ይወቅልኝ ብሏል። • መከራውማ ሁሉም ቤት መግባቱ ግድ ነው።
2800Loading...
22
የተስፋ ስሜት ወንድማችን ዲያቆን Yosef Fiseha Sewunet ከዐመት በፊት፦ "እስረኞቹ" የተሰኘውን መጽሐፍ በዘኪ ቲዩብ ቀርቦ ዳሶ ነበር። ዘንድሮ ግን እርሱም ከእስረኞች ጋራ ተደምሯል። ሰው አልባው ወንድሜ እንደ ዋዛ ታስሮ መቅረቱ ዘወትር ያሳስበኛል። በተለይም ቶሎ ለማስፈታት ያደረኩት ጥረት አለመሳካቱ ያንገበግበኛል። ይልቁንም ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ ጣቢያ ከተዛወረ በኋላ ገብቼ መጠየቅ አለመቻሌ ይቆጨኛል። ኾኖም በቅርቡ የሚፈታ ይመስለኛል። የተስፋ ስሜትም አድሮብኛል። ያቺን ቀን ሳስባት ብቻ ደስ ይለኛል። አምላከ ዮሴፍ ወንድሜን በቅርቡ ቢያስፈታልኝ፥ ለመቅደሱ የማስገባው ስእለት ይኖረኛል። እንደሚያደርግልኝ አምናለኹና መሻቴን ይፈጽምልኛል። ኤፍሬም የኔሰው
3820Loading...
23
ነገረ  ሆዳም!!!… ሆዳም ሰው በሆዱ ስለማይደራደር እናቱንም ቢሆን ከመሸጥ ወደ ኋላ አይልም።ዛሬም እናታቸውን ቤተ ክርስቲያንን የሚሸጧት ሆዳሞች ሆዳቸው በልጦባቸው  ነው።በዘረኝነት የተጨማለቀውን የኦነግ ብልጽግናን አገዛዝ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ከርሳቸውን ለመሙላት ሰው ያደረገቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ሸጧት።አዎ ፈጽሞ ርኅራሄ ለሌለው ለአረመኔው ዐብይ አሕመድ ሸጧት።
3390Loading...
24
ማንኛውም ተፅኖ ይፈጥራል የሚባል ሰው ይታሰራል
3960Loading...
25
ዛሬ ለምን እዚህ ደረስን? የኔታ ገ/መድህን መልስ አላቸው አድምጡት
4323Loading...
26
አድምጡት እስከ መጨረሻው ጠቃሚ ትምህርት ነው
4184Loading...
27
👆👆👆አድምጡት
4190Loading...
28
Media files
3970Loading...
29
ጎበዝ ከአዲስ አበባ በቅርብ እረቀት ላይ የሚገኘው ታላቁ የበረከት ምንጫችን ከመላው ኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም የሚበቃ የበረከት ምንጭ የሆነው ደብረ ሊባኖስ ገዳም የእኛን ድጋፍ ይሻል ። ለሰከንድ ያክል ስብሃተ እግዚአብሔር የማይቋረጥበት በዚኸ ገዳም የሚኖሩ መናንያን ፣ መነኮሳት እና የአብነት ትምህርት ተማሪዎች የእለት ቁራሽ ተቸግረዋል ። ስለሆነም ከታች በተቀመጠው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሕጋዊ የባንክ አካውንት የምንችለውን እናድርግ ። የደብረ ሊባኖስ ገዳም ሒሳብ ቁጥር CBE 1000280193667 D/L ABUNE TEKLEHAYMANOT ANDINET GEDAM ዘካርያስ ኪሮስ
5601Loading...
30
ኦርቶዶክሳውያን በባሌ በታጣቂዎች ታፍነው ተወሰዱ። ********** በቀን 13/9/2016 ማግሰኞ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን በአጋርፋ ወረዳ በነጌሌ ቀበሌ ባልታወቁ ሃይሎች ስድስት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ላይ እገታ ተደርጔል፡፡ በታጣቂዎቹ የታገቱ አገልጋዮችና ምእመናንም 1.መምህሬ ተክሉ ወ/ገብርኤል 2.ቦጋለ ገመቹ 3.አስቻለው ተስፋዬ 4.ጎሳ ሚንዳው 5.ገዙ ገዛብኝ 6.በየነ ሞገሴ የሚባሉ ሲሆኑ ከስድስቱ ውስጥ ሁለቱ 1) ቦጋለ ገመቹ እና 2) በየነ ሞገሴ የመድኃኔዓለም ቤ/ክ ሰበካ ጉባኤ አባል ናቸው፡፡ በኦሮምያ ክልል እምነትን መሰረት ያደረገ ግድያና እገታ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ይህንንም ለማስቆም ከቤተክህነቱም ይሁን ከመንግስት በኩል የሚደረግ ጥረት አለመኖሩ ችግሩን የከፋ አድርጎታል። ምንጭ ሞዓ ተዋሕዶ https://t.me/beletekassa
2870Loading...
31
ትኩረት 1) እውነት ነው መንፈሳዊ አባቶችን ፥መምህራንን በአጠቃላይ የበላያዮቻችንን የማክበር ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴት አለን።ይህ የሚሆነው ግን እነርሱ ከዚህ ማዕቀፈ እሳቤ ውስጥ ሲኖሩ ብቻ ነው።ከማዕቀፈ እሳቤ ካፈነገጡ ግን በፈጹም ተቀባይነት የላቸውም። 2) ሁሉን ነገር ወደ ሚድያ አውጥተን ማውራታችን ለጠላት ኀይል እንደሚሆን የማይካድ ሃቅ ነው።ነገር ግን አባቶቻችን ላይ እንዲህ ጠንከር ያለ አቋም ከማሳየታችን አስቀድመን ግብረኀይል ተቋቁሞ ጥያቄ ቀርቧል፥ብዙ የውጭ ሃገር ማኅበራት ደግመው ደጋግመው በመግለጫ አሳስበዋል።መምህራንና ምዕመናንንም በአካል ሄዶ በማነጋገር፥ስልክ በመደወል፥መልእክት በመላክ ብዙ ተማጽነዋል።እነርሱ ግን ያሾፉባቸው ይቀልዱባቸው ነበር። 3) አሁን ባለንበት ሁኔታ ገበና መጠበቅ የሚባል ነገር አይሠራም።እየሆነብን ያለው ነገር ከገመና በላይ ነው። 4) አባቶችን የምንከተለው እነርሱ የሚሉንን የምንሰማው እንዲሁም አባትነታቸውን የምንቀበለው ለተሾሙለትና ለተሾሙበት ዓላማ ጸንተው ሲገኙ ብቻ ነው።
3060Loading...
32
"ርዕሰ አንቀፅ" "…ከ No More እስከ No Go… "…የሸንኮራ ጥቅሙ ወይ በጥርስህ ትልጠዋለህ፣ አልያም ከድጋይ ከዛፍ ታጋጨውና ትሰብረዋለህ፣ አልያም በካራ ትሸነሽነዋለህ። ከዚያ በጉንጭህ ልክ አፍህ ውስጥ ከተህ በጥርስህ እያኘክ፣ እያላመጥክም ጣፋጩን ጨምቀህ መጥጠህ ትውጥና ቀሪዉን ተፍተህ ትጥለዋለህ። የአገዳ ጭማቂ ወይ ለከብት መኖ ይሆናል አልያም ደግሞ ለእሳት ራት ማገዶ ይሆናል። አለቀ። የኮንደምም አገልግሎቱም ተመሳሳይ ነው። "…አንድ የሃይማኖት አባት ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምርጫ የተሾመ አገልጋይ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን ማገልግል ትቶ ከፓርቲው አባላት በበለጠ እወደድ ባይነት ከሃዲ፣ አረመኔ፣ ለነፍሰ ገዳይ ዲዮቅልጢያኖስ የመሰለ አገዛዝ ለማገልገል ከባከነ መጨረሻው No Go ነው። "…ማገልግለስ “ ለዘላለም የማይጥለውን ጌታ፤” ሰቆ. 3፥31 …ማገልገልስ ሕዝቡን የማይጥለውን፣ ርስቱንም የማይተወውን እግዚአብሔርን" መዝ 94፥14 የተባልነውም “አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፤ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።” ዘዳ 10፥20 ነው። አለቀ። "…በእያንዳንዱ ቤት፣ ሰፈር፣ ድርጅት፣ መስሪያቤት፣ መንደር፣ ጎጥ መከራው ይገባል። የፈለገ ብታሽቃብጥ፣ የፈለገ ብትገረድ፣ አይቀርልህም። አንተ ባልጠበቅከው፣ ባልገመትከው፣ ይሆናልም ብለህ ባላሰብከው መንገድ በመከራ በትር ትዠለጣለህ፣ የመከራ ቀንበርም ላይህ ላይ ይወድቃል። የፈለገ አልኩህ እልል እያልክ ብታሽቃብጥ ወገብ ዛላህን ቆምጦ ሳይለንት ሙድ ላይ ቆልፎህ እያለህ ድራሽ አባትህን ያጠፋሃል። "…ይልቁኑ በቶሎ ንስሐ ግቡ…“አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።” ዘዳ 13፥4። ወደ ልባችሁ ተመለሱ። ንስሐም ግቡ። • No Go…
2610Loading...
33
የሰይጣን ፈተና  በዕብራይስጥ שָׂטָן የ “ሰይጣን” ትርጉም ተቃዋሚ፣ የሚቃወም the adversary” ማለት ሲሆን። እግዚአብሔርን የሚቃወም የእግዚአብሔር የኾነውን ሁሉ ተቃዋሚ ነው። ባላጋራ ተብሎም ይተረጎማል።  በግሪክኛው ዲያብሎስ ማለት ከሳሽ፣ ጠላት ማለት ነው። በሐዲስ ኪዳን በብዛት የምናገኘው ዲያብሎስ የሚለውን ቃል ነው። የሐዲስ ኪዳን አብዛኛው ምንጭ ግሪክኛ ስለሆነ ነው።  ሰይጣን ሐሳባችንን፣ ድርጊታችንን፣ ፍላጎታችንን፣ ድርጊታችንን፣ እውቀታችንን፣ የኑሮ ደረጃችንን ተክለ ሰውነታችንን፣ ጽሑፋችንን፣ ንግግራችንን ፣ ጠባያችንን፣ ሥራችንን (ሙያችንን) አምስቱንም የስሜት ሕዋሳቶቻችንን….. ሁሉ ለውጊያ ይጠቀምባቸዋል።  የሰይጣንን ፈተና መቁጠር አይቻልም። እንደ ዝናም ጠል ነው የሚያወርደው። በዚያም ላይ የማያቋርጥ ነው። ለዚኽ ነው የሰይጣንን ተንኮል እወቁበት የተባልነው። “በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።” 2 ቆሮ.2:11  የሰይጣን ፍላጎት የሰውን ልጅ ሁሉ በአንድ ቀን ገድሎ መጨረስ ነው። በአንድ ክርስቲያን ቁጣ የሚጀምረውና በጣም መጥላት የሚጀምረው የተጠመቀ ቀን ነው። አንድ ሰው (ሕጻን) ከመጠመቁ በፊት ሰይጣንን ይክዳል። የክርስትና አባት ወይም እናት አውራ ጣቱን ይዘው “ሰይጣንን እክዳለሁ በክርስቶስ አምናለሁ” እያሉ ወደ ምዕራብ ዞረው ይክዳሉ።  ሰይጣን ከክብሩ ከወደቀ ቀን ጀምሮ በፈታኝነት የሰለጠነ ስለሆነ ልምዱ ከፍተኛ ነው። የሰውን ዘር ሁሉ በመፈተን ከፍተኛ የሥራ ልምድ አለው።  ፈተናዎቹም አዲስ አይደሉም። የታወቁና የተደጋገሙ ናቸው። ግን እጅግ ብዙ ናቸው። የትኛውን ፈተና መቼና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። ብዙ ቅዱሳንን ፈትኗል እነርሱን በፈተነበት ፈተና ዛሬም ክርስቲያኖችን ይፈትናል።  ነገር ግን ይኽንን ክፉ ጠላት ጌታ ቀስቱን ሰብሮታል። ይኽ ማለት እንዳይፈትን አድርጎታል ማለት አይደለም። የሚሸነፍ ኃይል አድርጎታል፣ ሥልጣን አሳጥቶታል ማለት እንጂ የሚናቅ ባላጋራ አይደለም። ዕረፍት አልባ ጠላት ነው።  “ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ” ሉቃ.22:31 ተብሎለታል።  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን ሐዋርያት የሰበኩን ቅዱሳን በሕይወት ተጋድለው ያሳዩን ይኽንን እንዴት እንደምናሸንፍ ነው።  “የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።” ኤፌ.6:11 ክርስቲያን በየቀኑ ውጊያ ላይ መኾኑን ይወቅ። በየትኛው መንገድ ሊያጠቃው እንደሚችል ንቁ ይሁን። አውቆም ይቃወመው። የራዕይ ትርጉምን በጻፍኩበት ጽሑፍ ይመልከቱ።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
3180Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
"የዘራህው ካልሞተ አይነሳም"  1ቆሮ  15:36  ቅዱስ ጳውሎስ ትንሣኤን ያስረዳበት ትምህርት ነው። ከሞት በኋላ ትንሣኤ እንዴት እንደሚኖር።  አንዳንድ ሰው እግዚአብሔርን በአእምሯቸው ካልሳሉ ላያምኑ አይፈልጉም። እግዚአብሔር ደግሞ በሰው አእምሮ የሚረዳ አይደለም።  የስንዴ ዘር ከውጭ እስከ ሆነ ድረስ ደረቅ ወይም ሙት ነው። መሞቱን የምናውቀው እንቅስቃሴ ስለሌለው ነው። እንቅስቅሴ የህይወት ምልክት ነው። እንቅስቃሴ ከሌለ ሙት ነው። ካልተነፈስኩ ሞቻለሁ ማለት ነው። ከተንቀሳቀስኩ አለሁ ማለት ነው።  ይህ ዘር ካልቀበርከው ሕያው መኾን አይችልም። እንደ ቀበርከው ሕያው መኾን ይጀምራል ሕያው ነው። ካልቀበርከው ሕያው አይሆንም። ሙት ነው።  የምንወዳቸውን ስንቀብራቸው ሕያው መኾን ይጀምራሉ። በምድር ሳለን የሞቱ ዘሮች ነን። የሚንቀሳቀስ ዘር ነን። ስንቀበር እንኖራለን። እንደ ዘሩ። አፈር ሲጫነን ሕይወት እንጀምራለን።  አንድ ፍሬ ሲዘራ ብዙ ዘር ያፈራል። የምታገኘው የዘራህውን አይደለም እጥፍ ነው። ለቀበርነውን ሰው ሁሌ እናለቅስለታለን። ትክክል አይደለም። የምናምን ከሆነ የትንሣኤ ልጆች ነን። ለተነሣ ሰው አናዝንም። ስቀበር ሕያው ነኝ። ስኖር ሙት ነኝ።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Hammasini ko'rsatish...
ሃምሳው ቀናት  ሃምሳው ቀናት እንደ አንድ ቀን ሆነው ይታያሉ። ረቡዕና ዓርብ ሳይቀር አይጾሙም። ጠዋት ይቀደሳል፣ በጠዋት ይበላል። በሃምሳው ቀን ጾም የለም። የጾም ቀኖና አይሰጥም።  እነዚህ ሃምሳ ቀናት ወጪ ገቢ በሆነው ወይም ሂያጅ linear ሓላፊ በሆነው አሁን ባለንበት ቀን አቆጣጠር Chronos በሆነው ጊዜ ሲታዩ ከሰኞ እስከ እሑድ እንዳሉት ቀናት ይኖራቸዋል  እንጂ በቤተ ክርስቲያን ወይም በትንሣኤ የቀን አረዳድ የማያልፈው ጊዜ (Kairos) ማሳያ ናቸው።  ይኽ ዘመን አልፎ ከትንሣኤ በኋላ መምሸት መንጋት የጊዜ መፈራረቅ የለም ሰኞ ማክሰኞ የሚባል ቀን የለም። አንድ ሕይወት ነው የሚኖረው። ከትንሣኤ በኋላ ያሉት ሃምሳ ቀናት የዚያ ዘለዓለማዊ ሕይወት ማሳያ ናቸው።  ሃምሳው ቀን ከትንሣኤ በኋላ ያለውን ሕይወት በጥቂቱ እየቀመስን ነው። “ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን” 2 ቆሮ.5:5  መያዥ ማለት ቀብድ ነው። ከዋጋው ያነሠ ሆኖ እቃውን ለመግዛት ማስያዣ ነው። ቀብድ የከፈለ ሰው ሙሉ ዋጋውን ከፍሎ እቃውን ይወስዳል። ቀብድ መክፈል እቃውን ለመግዛት ማረጋገጫ ነው። ዕቃውን ካልገዛ የከፈለው ቀብድ ይቀርበታል።  ክርስቶስ ከሞት በኋላ ለሚሰጠን ሕይወት ማረጋገጫ ሰጥቶናል። ለዚያ ሕይወት ማሳያ አንዱ ከትንሣው በኋላ ያለው የሃምሳው ቀን ነው። ትንሣኤ የሥጋ ትንሣኤ መያዣ ነው ትንሣኤ የሁሉም ነገር መሠረት ነው። ያለ ትንሣኤ ክርስትና አይኖርም ነበር። “ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት” 1.ቆሮ.15:17 ክርስትናችን የተመሠረተው በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ነው። ወደ ክርስትና የምንገባበት በር ጥምቀት ነው። የምንጠመቀው በሞቱና በትንሣኤ ልንሳተፍ ነው። ወደ ውኃው ስንገባ ሞት ወይም መቀበር ነው። ስንወጣ ትንሣኤ ነው። “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” ሮሜ.6:4 ሞትና ትንሣኤውን እንመሰክራለን የመጠመቂያው ገንዳ (ቦታ) ጎልጎታ ነው። ጌታ ሞቶ ባይነሣ ኖሮ ጥምቀት የለም ነበር። የተጠመቅነው በሞቱና በመነሣቱ ነው።  የምንቀበለው ሥጋና ደም በሞቱና በትንሣኤው የተመሠረተ ነው። ባይሞትና ባይነሣ ኖሮ ሥጋና ደሙን አይሰጠንም ነበር። ሥጋው መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው ነው። ሥጋውን በመስቀል ላይ የሰጠን ስለ ሞተ ነው። ሞትን ድል አድርጎ የተነሣ ስለሆነ እንቀበለዋለን። ሞቶ ባይነሣ ግን አንቀበለውም ነበርም።  ሞት ይዞት ያላስቀረው ሕያው ስለሆነ ሞት ሊይዘው ያልቻለ ሕያወ ባሕርይ ስለሆነ ሕይወትን የሰጠን ስለሆነ የእርሱን ሥጋ እንደበላለን ደሙን እንጠጣለን። ሞትን ድልን አድርጎ ስለተነሣ ሕይወት ነው። ሞቶ ቢቀር ኖሮ ሥጋውን ማን ይበላል ቢበላስ ምን ይጠቀማል?።  ሞትን ድል የሚያደርግ ሕይወት ስለሆነ የሞት መድኃኒት ስለሆነ The medicine of immortal “ኢመዋቲነትን የሚሰጥ ዘር” አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ።  ክህነት መሠረቱ ትንሣኤ ነው። በይሁዳ ምትክ ሰው ሲመርጡ መለኪያው የትንሣኤ ምስክር መሆንን ነው። “ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል” ሐዋ.1:21  ክህነት ያስፈለገው ሞትና ትንሣኤውን መመስከር ነው። መምህራን ያስፈለጉትም ለዚሁ ነው።  ተክሊል መሠረቱ የክርስቶስ  ሞትና ትንሣኤ ላይ ነው። ጋብቻ ሊፈጽሙ የወሰኑ በአንድነት የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም በሚወስኑ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ጥንዶች በጸሎት ከብረው ሥጋወደሙን ተቀብለው አክሊል ደፍተው ጋብቻ የሚፈጽሙት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ላይ ነው። የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በተግባር ለመኖር ነው።  ክርስቶስ ሞትን ድል እንዳደረገ እናንተም በዚኽ ዓለም ያለ ውጣ ውረድን ክርስቶስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶ ድል እንዳደረገ እነርሱም ድል ያደርጉ ዘንድ አክሊል ይደፋሉ። ይኽ አክሊል ክርስቶስ የደፋው የአሸናፊነት  አክሊል ነው።  የክርስቶስ አክሊለ ሶክ ከብረት የጠነከረ ከጠንካራ የእንጨት እሾኽ የተሠራ ነው። የቤተ ክርስቲያን አክሊል የሚዋጋ ነው። ትዳር የደስታ ሕይወት አይደለም። ለብቻ ሆኖ የሚከብድን መስቀል ሁለት ሆኖ መስቀሉን ተሸክሞ መክበር ሕይወት ነው። የሚደፋው አክሊል የካሜራ ጌጥ አይደለም። አክሊለ ሶክ ነው።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት! ▪️የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ውጡ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ 11 ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ▪️መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ የፊጥኝ እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው መገኘታቸውን፤ ሙሉ ሪፖርቱን ከስር ባለው ሊንክ ይከታተሉ! 👉🏿 https://ehrc.org/?p=28122
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የኢሰመጉ 40ኛ መደበኛ መግለጫ የኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምርመራ ግኝቶች ዓመታዊ መግለጫ የኢሰመጉ 40ኛ መደበኛ መግለጫ-ግንቦት 20/2016 ዓ.ም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይንኩ። https://t.me/ehrcow
Hammasini ko'rsatish...
🥰 1
ሰላም አደራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን
Hammasini ko'rsatish...
የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል። ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) በየዓመቱ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን የሚካሔደው ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ መሪነት የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይካሔዳል። በየዓመቱ የሚካሔዱት ሁለቱ ጉባኤያት አንደኛ ቋሚ በሆነ ቀን በጥቅምት 12 ሲጀምር ሁለተኛው ግን የአጽዋማቱን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣው የባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት በዓለ ትንሣኤ በዋለ 25 ኛ ቀን የርክበ ካህናት ጉባኤ ይከናወናል። በዚህ በ2016 ዓ.ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጀምር ሲሆን በዋዜማው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፕትርክና መንበሩ ከግብፁ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም ወዲህ አስቸኳይ ጉባኤያትን ሳይጨምር 128 መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት መካሔዳቸውን ታሪክ ያስረዳል። ከነዚህ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቅዱሳን ፓትርያርኮች ጥረት ርእሰ መንበርነት የተመሩ ሲሆን በሁለት የተለያዩ ዓመታት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፓትርያርክ ባለመኖሩ ምክንያት በአቃብያነ መንበር በብፁዓን አባቶች ተመርተዋል። ከእነዚህ አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ በወቅቱ በነበረው አገዛዝ ምክንያት በግፍ ለግዞት ስለተዳረጉ ግንቦት 11 ቀን 1968 ዓ.ም የዋለውን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቃቤ መንበር በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የመላ ትግራይ ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት ተመርቷል። ሁለተኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በማረፋቸው ምክንያት የጥቅምቱ 12 ቀን 2005 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖደስ ምልዓተ ጉባኤን የወቅቱ አቃቤ መንበር የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በርእሰ መንበርነት መርተዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን እምነት የማጽናት ሥርዓትን ማስጠበቅ አስፈላጊ ከሆነም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች የማሻሻል ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ነው። “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።” ሐዋርያት ፳፥፳፰
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
አጣብቂኙ ውስጥ የገባው ሲኖዶስ! // ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ?// ቆይታ ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ ጋር #ethiobeteseb

አጣብቂኙ ውስጥ የገባው ሲኖዶስ! // ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ?// ቆይታ ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ ጋር #ethiobeteseb

4