cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

በዚኽ ቻናል ጽሑፍ የሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
11 020
Obunachilar
+2724 soatlar
+1707 kunlar
+93530 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ግራ የገባ ነገር ቤተ ክርስቲያን ዘሎ ዘክር የኾኑ አስመሳይ ጠንቋዮችን አደብ ማስገዛት አቅቷት ጳጳሳት ለገዛ ጥቅማቸው እሽሩሩ የሚሏቸው እነ ዐይነ ጥላ ሄኖክ፣ እነ መልአከ አንከርት፣ እነ ጆቢራውን በየዶላርና ፓውንድ ያለበት እየተርመሰመሱ ያንጫጩታል።
Hammasini ko'rsatish...
👎 4🤔 3👍 1
ጥያቄ ርክበ ካህናት ምን ማለት ነው? የሲኖዶስስ ስብሰባ በዚኽ ጊዜ ለምን ኾነ?
Hammasini ko'rsatish...
በራፊድ የተሰነጠቀው ዓለት  እግዚአብሔር እስራኤልን በምድረ በዳ ወደ ምድረ ከነዓን ሲወስዳቸው በመካከል ላይ ጥያቄ አነሡ። ሙሴን አብዝተው ጨቀጨቁት :- “ የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም።  ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም፦ ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው። ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፦ እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ” ዘጸ.17:1 ያለ ውኃ መጓዝ አይችሉም ልጆቻቸውም ከብቶቻቸውም የሚጠጡት የለም። ጉዞው ደግሞ የበረሃ ጉዞ ነው።  ሙሴ እግዚአብሔርን ጠየቀው እግዚአብሔርም መለሰለት “  ሙሴም፦ ሊወግሩኝ ቀርበዋልና በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።  እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ወንዙንም የመታህባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ።  እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ” ይላል ዘጸ.17:5  እስራኤል በራፊድ በተሰነጠቀው ዓለት መካከል ውኃ ፈለቀ እንደ ታላቅ ባህር ሆነ ወንዞችንም ሞልቶ ይፈስ ነበር። ቦታውን መሪባ አሉት በእግዚአብሔር አብሯቸው መኖርና አለመኖር ክርክር አድርገው ነበርና “ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው” ዘጸ.17:7 የብሉይ ኪዳን ታሪክ የሐዲስ ኪዳን ጥላ ነው። አዲሱ ኪዳን እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ነው። ፍጻውን ያገኘው በክርስቶስ ሰው መኾን ነው።  ቅዱስ ጳውሎስ አይሁድን ሲያስተምራቸው የቀደመ የአባቶቻቸውን ታሪክ አንስቶ ፍጻሜው ክርስቶስ መኾኑን ሲያስረዳቸው “ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።  አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤  ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤  ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤  ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ” አለ። 1 ቆሮ.10:1-4 እስራኤላውያን በባሕር መካከል ማለፋቸው ሊመጣ ላለው የጥምቀት ምሳሌ ነበር። (And that that sea was a sacrament of baptism) የካርቴጁ ሳይፕሪያን። በወቅቱ አይሁድ የተጠመቁት በሙሴ ትእዛዝና  በሕግጋት ነበር።  ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ሲናገር “ ሙሴ በእግዚአብሔር ወደ ግብጽ እንደ ተላከ ወልድ (ኢየሱስ) ከአባቱ ዘንድ ወደ ዓለም ተላከ። የሙሴ ተልዕኮ ስደተኛ ሕዝብን ከግብጽ ለማውጣት መምራት ነው። የክርስቶስ ተልዕኮ በኃጢአት ቀንበር የነበረውን የዓለም ሕዝብ ማዳን ነው። “There Moses was sent by God into Egypt; here Christ was sent from the Father into the world. Moses' mission was to lead out of Egypt a persecuted people; Christ's was to rescue all the people of the world who were under the tyranny of sin. (Cyril of Jerusalem commentary on 1st. Corinthian 10 የዚኽ የራፊድ የተሰነጠቀው ዓለት ቅርጽን ስንመለከት የልብ (Heart) ቅርጽ ይዞ ያለ ለሁለት የተሰነጠቀ ሲሆን በአንደኛው ዓለት የፈለቀው ውኃ እንደ ሸረሸረው ይታያል። ቅዱስ ጳውሎስ ያ ዓለት ክርስቶስ ነው ብሏል። እስራኤል የጠጡት መንፈሳዊ መጠጥ ምልክቱ ክርስቶስ ነበር። የዓለም ኃጢአት በርስ ላይ ተሸክሞ በዕለተ ዓርብ ተሰቀለ። ከጭፍሮች አንዱ መጥቶ መሞቱን ሊያረጋግጥ በጦር ወጋው “ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ” ዮሐ.19:34 ከጌታችን ጎን በፈሰሰው ደምና ውኃ ቤተ ክርስቲያን ተመሠረተች። ሰው ቅዱስ ደሙን እየጠጣ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖር ለዓለም አፈሰሰው። ደሙ ምድርን በነካ ጊዜ በአዳም ያገኛት መርገም በደሙ መታጠብ ነጻች መርገም ከሰው ተነቀለ። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።  ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ” ዮሐ.6:54 ሙሴ  በምድረ በዳ በበርት የመታው ዓለት ውኃ አፍልቆ አርባ ዓመት ሙሉ ወንዝ እየተከተለ እንደ ጠጡ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የፈሰሰውን ደሙን እኛ እንጠጣና ከዓለም መንፈሳዊ ጥማት እንድን ዘንድ ነው።  “እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።” ዮሐ.4:14 መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Hammasini ko'rsatish...
👍 8 4
ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር ሉቃ.24፤15 https://youtu.be/6nXiG3PTBRc
Hammasini ko'rsatish...

Photo unavailableShow in Telegram
ለራሳችን ትክክለኛ መልስ መስጠን ያለብን ጉዳይ ሰይጣን በእኛ ላይ በምን መልኩ ነው ሥራ የሚሠራብ ወይም የሚጠቀምብን፣ የሚሰለጥንብን?
Hammasini ko'rsatish...
🤔 9👍 6 4