cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media

እሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
1 893
Obunachilar
+424 soatlar
+557 kunlar
+19630 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አባቶቻችን እንደኛ በባዶ የሚመጻደቁና ሰነፎች ቢሆኑ ኖሮ ኢትዮጵያ እንደ እሥራኤል ከዓለም ካርታ ትፋቅ ነበር የኢኦተቤ'ንም ከቱርክ ክርስቲያኖች በከፋ  ትጠፋ ነበር።እነርሱ ከሠሩት የሩብ ሩቡን እንኳ ብንሠራ የመከራው ዶፍ እንዲህ ባልወረደብን ነበር።ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ላለመጥፋት እድል አለንና የአቅማችንን እንሥራ።
Hammasini ko'rsatish...
የሰጠህኝን ሰጠሁህ ዮሐ.17:1 መንጎችን ጠብቆ ላስጠበቀው ማስረከብ ትልቁ የምድር ኃላፊነት ነው። ጌታችን ኢየሱስ እርሱ መልካሙ እረኛ ነው። አባቱ እንዲጠብቃቸው የሰጠውን እርሱ የመረጣቸውን ሐዋርያት በትምህርት እና በተአምራት አስተምሮ ጠበቀ። እንቢ ብሎ ትንቢት እንዲፈጸምበት ራሱን የሰጠው ይሁዳ ግን ሐዋርያ የመሆን እድል ቢሰጠው፣ ትምኖ ገንዘብ እንዲይዝ ቢደረግ ግን ከመልካሞቹ መንጎች አልቆጠር አለ።  ከአብ ተልኮ የመጣው ሕይወት የሆነው ራሱን ያውቁት ዘንድ ነው። ወልድ አባቱን ነገረን "ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው"  አሁን በቀደመ የአብ ክብር ሊገባ ዋዜማው ነው። ከዚኽ ጸሎት በኋላ ወደ አደባባይ አልወጣም ይኽ የማክሰኞ ማታ ጸሎቱ ነው። ጌታ ከአባቱ የተረከበውን ጠብቆ ሲያስረክብ እንዲህ አለ "ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል" በአደራ የተሰጡትን አንተ ማን እንደሆንኩ አስተማርኳቸው ማለቱ ነው። የሰሙትንም ጠብቀዋል አምነዋል።  በስሙ አምነው እንዲድኑ እንዲናገራቸው መጥቷልና "የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ" በእኔ እመኑ በአባቴም እመኑ ያላቸውን ማመናቸው ነው።  የሚኖሩበት ዓለም አስቸጋሪ በመሆኑ ዘለአለማዊ ጥበቃው እንዳይለያቸው ጸለየ። መከራ ስደትን እንዲቋቋሙ ከክፉ እንዲጠበቁ ለአብ አደራ ሰጣቸው። እንደ እኔ አሁን በሞት ከዓለም እንዲለዩ ሳይሆን በዚሁ ዓለም እንዲጠበቁ ነው አለ። "ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም"  የአንተ ባሕርይ የእኔ ባሕርይ ነው እኔና አንተ አንድ ነን። እኔና አንተ አንድ በሆንበት ፍቅር እነርሱም አንድ ይሁኑ  "እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል"  እኔ እንደወደድኳቸው በኋላም ከእኔ ጋር ሊኖሩ እወዳለሁ በማለት መንግሥቱንም እንደሰጣቸው ይናገራል "አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ"  ይኽ የአንድ እረኛ ትልቅ ድርሻን ያመለክታል። የተሰጠውን አደራ ተቆጣጥሮ ለባለቤቱ ማስረከብ። ከጥፋት ልጅ በቀር ማንም አልጠፋም አለ። ዛሬ በዚኽ ወንበር የሚቀመጡት ጭንቀታቸው መንጋ ወይስ ለቆሙለት ለሾማቸው ፓርቲ?  ብሔር? ወገን። ጌታ እንዳደረገ ለሁሉም ለተሾሙበት ሁሉ ይጠየቃሉ። እንዲህ ስንጠየቅ የምናስረክበው ነገር ይኖረን ይሆን?  ታድያ ለቤተክርስቲያን ክብር የቆመ የተጨነቀ ማን ይሆን? ያም ወገኔ ብቻ፣ ይኼም ወገኔ ብቻ ይኼ ከእረኛ ይጠበቅ ይሆን። መንጋውን ትተው ላሰማራቸው ብቻ ጥብቅና መቆም ከወቀሳ አያድንም።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Hammasini ko'rsatish...
አረመኔው አብይ አህመድ ባህር ዳር ምን ገጠመው? ሰላም አደራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን
Hammasini ko'rsatish...
6🥰 1
"ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ ፥ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር። አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሃ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥ከባለጠጋውም ማእድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር ፤ ውሻዎች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር ። ድሃውም ሞተ፥መላእክትም ወደአብርሃም ዕቅፍ ወሰዱት፤ባለጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ ።በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በዕቅፉ ።" ሉቃ 16፥19-23 ገዢዎች ጥሩ ሰራን ብለው በጥፋታቸው እንዲበረቱ የሚገፋፉዋቸው እንዲህ አይነት የሞራል ውሀ ልካቸው የተዛባ ባለሀብቶች ናቸው። ወገንህን ከረሀብ ታደግ ቢባል ኪሱ እንደ መርፌ ቀዳዳ የሚጠበው ነው ፣የብልጽግናን ተወዳጅነት ለማትረፍ እንዲህ ገንዘቡን የሚዘረግፈው። ጸረ ልማት ካልከኝ ጸረ ሰው እልሀለሁ
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
ሰበር በየረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል በእሳት አደጋ ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ !
Hammasini ko'rsatish...
👍 3
አሳዛኝ እልቂት!! 😭በድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጨፈጨፉ! በሸዋ ይፋት ቀጠና በቀወት ወረዳ የለን ቀበሌ ጉሎ  ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ሁለት ጊዜ በተከታታይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል። ከተገደሉት ውስጥ የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች የሆኑ 4 መምህራን ይገኙበታል። ከ27 በላይ ንፁሃን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እግራቸውን እና እጃቸውን በድሮን ጥቃት ያጡት ወገኖች ህክምና ተቋም መድረስ ባለመቻላቸው ብዙ ደም ፈሷቸው ሕይወታቸው እያለፈ ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።
Hammasini ko'rsatish...
👍 1
የሶፊያ ሽባብው ነገር🤔🤔🤔
Hammasini ko'rsatish...
🤔 4
Take a look at this post… 'የክርስቶስን ትንሳዔ ስናከብር እኛም ለመነሳት መወሰን ይኖርብናል'. http://speak-truth-in-love-forever.blogspot.com/2024/05/blog-post.html
Hammasini ko'rsatish...
የክርስቶስን ትንሳዔ ስናከብር እኛም ለመነሳት መወሰን ይኖርብናል

ትንሳዔን የምናከብረው እኛ ራሳችን ልንነሳ ነው! አዘቅት ውስጥ ሆነው ክንፍ ስላበቀሉት መዘመርና በዓል ማክበር በእግርም አያራምድም! በንስሐ ለመብረር መነሳት ይቀድማል! ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳማዊ ቃል ...

👆👆እባካችሁ ርዕሱን ብቻ አንብባችሁ እንዳትሳሳቱ ሙሉውን አንብቡት
Hammasini ko'rsatish...
ኤርትራስ እንኳንም ተገነጠለች ሱዳን ውሥጥ አንድ ቤተ-ክርስቲያን አለ። እዛ አንድ ኢትዮጵያዊ ካህን ያገለግላሉ። እና እሳቸው ኹልግዜም የአባታችንን የኪነ ጥበብን መዝሙር ነበር የሚከፍቱት። ከዚያ ቤተክርስቲያንም አንድ ኤርትራዊ ሽማግሌ አባት ነበሩ። ከካህኑ ጋር ጓደኛሞች ነበሩና አንድ ቀን ከካህኑ ቤት ይመጣሉ። ሲገቡ የኪነ ጥበብ መዝሙር እየተሰማ ነበር። <<ይሔን ዘማሪ በጣም ነው የምወደው። ዘወትር አዳምጠዋለሁ>> አሉ ኤርትራዊው። << እስዎም ያዳምጡታል?>> <<ሳላዳምጠው ውየ አላድርም። እንዴው ግን በሕይወት አለ? >> ሲሉ ጠየቁ <<አወ አለ። >> <<አላረጀም? ድምፁ አሁንም አለ?>> << ትንሽ እንደ ማርጀት ብሏል። ድምፁ ግን አሁንም አለ>> አሉ ቄሱ << እና እንዴት ነው? ስንት ፎቅ ገንብቷል?>> አሉ ኤርትራዊው በዚኽ ጊዜ ኢትዮጵያዊው ካህን ሳቁ። <<እንኳን ፎቅ ሊገነባ የሚቅየረው ጫማም የለውም። በድህነት ነው የሚኖር>> ሲሉ መለሱላችልው ። ሥለ ሕይወቱም በደምብ አጫወቷቸው። <<እግዚኦ... ይኽንን የመሰለ ዓለማቀፍ ተደማጭነት ያለው ኦርቶዶክሳዊ ዘማሪ እንዴት ትጥሉታላችሁ? ኢትዮጵያዊያን ግፈኞች ናችሁ። ኤርትራስ እንኳንም ተገነጠለች>> ሲሉ በቁጭት ተናገሩ አሉ። አባታችን ይኽንን ያኽል ጀግና ነው። ጀግና የተዋሕዶ አርበኛ። እዚኽ አዲሳበባ 6 ኪሎ ዩንበርስቲ የአባታችንን መዝሙር ጋብዘውት እሱን በማዳመጥ ብቻ ተጠምቆ ክርስቲያን ኹኖ በሃይማኖት ጎልምሶ በመጨረሻም በሥርዓተ ቤተክርስቲያን ያገባ ሙስሊምም እንደ ነበር ሰምተናል። እና ይኽንን ታሪክ የነገረን አባታችን አይደለም። እንደኛ እሱን ለመጠየቅ ከሔዱ ሰዎች ነው የሰማነው። አባታችን ታሪኩን ያውቀዋል። ግን እንዲወራ አይፈልግም። ከንቱ ውዳሴ ይኾናል ብሎ ይሸሻል።
Hammasini ko'rsatish...
6