cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

EPS (Ethio-Parents' school)

Ethio-Parent's School Student Resource Center

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
8 834
Obunachilar
-324 soatlar
+107 kunlar
-3830 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

አክሲዮን ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር አዳዲስ አክሲዮኖችን በማውጣት ለነባርና አዲስ ለሚገዙ ባለአክሲዮኖች በመሸጥ ላይ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ለሦስተኛ ጊዜ የተራዘመው የመሸጫው የጊዜ ገደብ የካቲት 17ቀን 2016 ዓ.ም ያበቃ ቢሆንም የማህበሩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሽያጩ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲራዘም የወሰነ ስለሆነ ለመግዛት የምትፈልጉ ዘወትር በሥራ ሰዓት ገርጂ በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ አክሲዮኖችን ለመግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
reminder
Hammasini ko'rsatish...
ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች የ2016ዓ.ም የ4ተኛዉ ሩብ ዓመት የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ከሚያዝያ 21 ቀን 2016ዓ.ም እስከ ግንቦት 5 ቀን 2016ዓ.ም ወይም April, 29/2024-May13/2024 እንደሆነ ይታወቃል፡፡በመሆኑም መደበኛ የመክፈያ ጊዜዉ ከመጠናቀቁ በፊት ለተጨማሪ ወጪ/ቅጣት/ እና ካላስፈላጊ እንግልት እንዳይዳረጉ ክፍያዉን በወቅቱ እንዲከፍሉ ከታላቅ ትህትና ጋር እናሳስባለን፡፡ ት/ቤቱ
Hammasini ko'rsatish...
በገርጂ፣ ጉለሌ፣ እና ጉርድ ሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች ልጆቻችሁን በማስተማር ላይ ለምትገኙ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የአራተኛው ሩብ ዓመት የትምህርት አገልግሎት የመክፈያ ጊዜ የሚጠናቀቀው ግንቦት 05 ቀን 2016 ዓ.ም ( May 13/2024) ስለሆነ የተሰጠው ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ክፍያውን እንድታከናውኑ አበክረን እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አ.ማ(ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት)
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
ኢትዮ-ፓረንትስ በቴስት-ፕሬፕ አዘገጃጀት ላይ የነበረው ሚና | The Role of Ethio-Parents in the making of TestPrep

በዚህ ቪዲዮ ላይ የኢትዮ-ፓረንትስ ትምህርት ቤቶች እናት ድርጅት የሆነው የኆኅተ ጥበብ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ገነነ ይልማ ፤ ትምህርት ቤቱ የቴስት-ፕሬፕ ዝግጅት ላይ የተጫወተውን ሚና ያብራራሉ። አቶ ገነነ የኢትዮ-ፓረንትስ ትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች ላይ ተደጋጋሚ ስኬቶችን ለማስመዝገብ የቻሉበትን ሂደት አጉልተው አሳይተዋል። ይህንን ስኬት በተመጣጣኝ ዋጋና ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማካፈል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸው ፤ ቴስት-ፕሬፕ ለዚህ ግብ ትክክለኛውን መድረክ እንዴት እንዳቀረበ ያብራራሉ። In this video, Ato Genene Yilma, CEO of Hohete Tibeb, the parent company of Ethio-Parents Schools, discusses the role these schools played in the development of TestPrep. Ato Genene highlights Ethio-Parents Schools' proficiency in using technology to achieve consistent success in college entrance exam pass rates across its branches. He explains their desire to share this success at scale in an affordable and accessible way, and how TestPrep provided the perfect platform for this goal.

Photo unavailableShow in Telegram
Hammasini ko'rsatish...
የቴስት-ፕሬፕ ባህሪያት | Features of TestPrep

በዚህ ቪዲዮ የኤች.ኤስ.ቲ ኮንሰልቲንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘክረ ንጋቱ ፤ የቴስት-ፕሬፕን ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ አዘገጃጀት ፣ በተለያዩ መሳሪያዎች ላይና ኢንተርኔት ባለበት ቦታ ሁሉ መጠቀም እንደሚያስችል ያናገራሉ። በተጨማሪም ቴስት-ፕሬፕ ያለፈባቸውን የጥራት ማረጋገጫና የዝግጅት ሂደቶችን ያብራራሉ። በተካተቱት የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች ላይም ገለጻ አድረገዋል። በተዘጋጁት ተመጣጣኝ የክፍያ ተመኖች ላይና ቀላል የክፍያ መፈጸሚያ ዘዴዎች ላይም ተናግረዋል። In this video, Mr. Zekrie Negatu, Managing Director of HST Consulting, explores TestPrep's user-friendly design, accessible on any device with internet access. He also explains the rigorous quality assurance and preparation processes TestPrep went through. Mr. Zekrie also sheds light on the subjects covered, grade levels addressed, and the affordable pricing plans with convenient payment options.

Hammasini ko'rsatish...
ቴስት-ፕሬፕ ምንድን ነው? | What is TestPrep?

በዚህ ቪዲዮ ላይ የኤች.ኤስ.ቲ ኮንሰልቲንግ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዘክረ ንጋቱ ፤ ቴስት-ፕሬፕ እያሽቆለቆለ ያለውን የብሔራዊ ፈተና ማለፍ ተግዳሮትን ለመፍታት ሀሳቡ እንደ ተጠነሰሰና በቀጣይነት አገግልግሎቱን በማሻሽል ከፈተና ዝግጅት ባለፈ ተማሪዎችን ሰፋ ባለ መልኩ ለመጥቀም ያለውን አላማ ጠቅለል አድርገው ያብራራሉ። ቴስት ፕሬፕ ተደራሽ እና ውጤታማ የፈተና ዝግጅት መድረክን ለመፍጠር የኤች.ኤስ.ቲን የለርኒንግ ማኔጅመንት ሲስተም እንዴት እንደሚጠቀምም ገለጻ አድርገዋል። አቶ ዘክረ በቴስት ፕሬፕ አዘገጃጀት ላይ ተማሪዎቹን ስኬታማ በሆነ ሁኔታ ለብሔራዊ ፈተና በማዘጋጀትና በማብቃት ከሚታወቀው ከኢትዮ-ፓረንትስ ትምህርት ቤትና ከራዲየም ኤዱኬሽናል ሶሉሽንስ ፣ በፈተና ዝግጅት የማማከር ባለሙያዎች ጋር የተደረገውን የአጋርነት ስምምነትና የትብብር ስራም አብራርተዋል። In this video, Mr. Zekrie Negatu, Managing Director of HST Consulting, explains how TestPrep was born from a desire to address the declining national exam pass rate. He discusses how TestPrep leverages HST's learning platform for accessible and effective exam preparation. He also explains the collaborative effort with Ethio-Parents Schools, renowned for their exceptional student results, and Radium Educational Solutions, experts in test preparation consulting.