cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Tikvah-University

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
215 370
Obunachilar
+15824 soatlar
+7527 kunlar
+2 18730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በ Doctor of Medicine መምህራን አወዳድሮ ለመቅጠር ባለፈው ወር ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልታችሁ የተመዘገባችሁ ብቻ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና መጠራችሁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ ተፈታኞች ለፈተና ስትሔዱ መታወቂያ መያዝ እና በሰዓቱ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ማንኛውም ተፈታኝ የሞባይል ስልክ ይዞ ወደ ፈተና መግባት አይችልም፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 45 7👏 2
በቻይና ሼንዘን ከተማ በተካሔደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ.ሲ.ቲ. ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተገኙ ሦስት ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ተሳትፈዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎቹ፤ የውድድሩ ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡደን ጋር መጋራት መቻላቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሶስት የውድድር ትራኮች (Innovation, Network and Computing) ተካፋፍሎ ተካሒዷል፡፡ @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 92👏 30🥰 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
ስድስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም ላይ ካሉ ሁለት ሺህ "ከፍተኛ ደረጃ" ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ለመካተት ቻሉ። የዩኒቨርሲቲዎች ዓመታዊ ደረጃ የሚያወጣው Center for World University Rankings (CWUR) የተባለ ተቋም የዩኒቨርሲቲዎችን የ2024 ጀረጃ ይፋ አድርጓል። ደረጃ ከተሰጣቸው 20,966 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 2,000 ዩኒቨርሲቲዎች ወይም 9 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ብቻ "ከፍተኛ" ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በተቋሙ የ2024 ደረጃ መሠረት፦ 1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ➭ 841ኛ 2. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ➭ 1701ኛ 3. መቐለ ዩኒቨርሲቲ ➭ 1748ኛ 4. ጅማ ዩኒቨርሲቲ ➭ 1767ኛ 5. ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ➭ 1886ኛ 6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ➭ 1982ኛ መሆን ችለዋል። በዘንድሮው ደረጃ ከቀዳሚ አስር ዩኒቨርሲቲዎች፣ ስምንቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። ላለፋት 12 ዓመታት ደረጃ ሲያወጣ የቆየው ተቋሙ፤ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት የትምህርት ጥራት፣ የምርምር ጥራት እና የፋክሊቲ ደረጃ በመሳሰሉት መለኪያዎች ይገመግማል። መንግሥታት እና ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት እና የምርምር ውጤቶቻቸውን እንዲያሻሽሉ በማማከር የሚታወቀው ተቋሙ፤ የዩኒቨርሲቲዎችን ዓለም አቀፍ ደረጃ ከአላማ፣ ግልፅነት እና ዘላቂነት መርሆች አንፃር ይመድባል። የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃን ይመልከቱ፦ https://cwur.org/2024.php @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 117 13👎 8👏 3😢 3😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Tecno #Camon30Pro5G ልዩ ዲዛይን እና ቴክኖሎጂ አጣምሮ የቀረበዉ Tecno Camon30 Pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ! #Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
Hammasini ko'rsatish...
👍 9 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ ኢኖቬቲቭ፣ ሊተገበር የሚችል እና ተፅዕኖ የሚፈጥር የቢዝነስ ሀሳብ አለዎት? ወጣት ተማሪ ነዎት? እንግዲያውስ የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶችን የሚያበረታታው Youth Challenge Fund ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ! መስፈርቶች፦ ➧ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ➧ የቅድመ ምረቃ ተማሪ ከሆኑ ዕጩ ተመራቂ መሆን ያለብዎት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የማስተርስ እና ፒ.ኤች.ዲ ትምህርትዎን እየተከታተሉ ከሆነም ማመልከት ይችላሉ፡፡ ➧ ለግብርና ምርታማነት፣ ዘላቂነት እና እሴት መጨመር አስተዋፅኦ ለሚያደርግ ማንኛውም የትምህርት መስክ የምትማሩ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ እንዴት ማመልከት ይቻላል? በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ [email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከሆኑ [email protected] ላይ ማመልከቻዎን ይላኩ። በተጨማሪም [email protected] እና [email protected] ላይ ግልባጭ ያድርጉ፡፡ ምን ድጋፍ ይደረጋል? አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳቦች ከ 5,000 እስከ 20,000 ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የቢዝነስ ኮቺንግና ክትትል እገዛ ይደረግላቸዋል፡፡ የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👉 ሰኔ 1/2016 ዓ.ም @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 73👎 7 5😢 4🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
#የቻናል_ጥቆማ 🔔 ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ‼️ የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት? 📚 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀት ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን! 👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ 👉 አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣ 👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣ 👉 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡ Join Us :- ✅on Telegram 👇 https://t.me/ethioengineers1 https://t.me/ethioengineers1 ✅on TikTok tiktok.com/@ethiocons tiktok.com/@ethiocons
Hammasini ko'rsatish...
👍 18
#MoH በአገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተጠናቋል። የጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና በሃገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 15 እና 16/2016 ዓ.ም በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በኮምፒውተር በታገዘ የፈተና አሰጣጥ ስርዓት ፈተናውን ወስደዋል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 49 22👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ይመዝገቡ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለወጣቶች በቤት አያያዝ ሙያ (Domestic Work) የአጭር ጊዜ ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡ ከዛሬ ግንቦት 18/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሜክሲኮ ገነት ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት መመዝገብ ይቻላል። ምዝገባው እስከ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፤ ስልጠናው ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ይጀምራል፡፡ የምዝገባ መስፈርቶች፦ ➧እድሜ ከ 18 እስከ 35 ዓመት ➧ስምንተኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች ➧ለ21 ቀናት ሳያቆራርጡ መሰልጠን የሚችሉ ➧የብቃት ምዘና ለመመዘንና ለመመዝገቢያ 100 ብር ያስፈልጋል። @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 21 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Tecno #Camon30Pro5G Tecno Camon 30 pro 5G እያንዳንዱ ፎቶ እና ቪድዮ ከፍተኛ ጥራት እንዲላበሱ የSony IMX890 ካሜራ ሴንሰር ገጥሞ ቀርቧል! #Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
Hammasini ko'rsatish...
👍 10 5👎 3👏 3😱 1
የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገለፀ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ይህ የተገለፀው። በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሠራው የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 13 ተቋማት ላይ አስተደደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡ በዚህም የወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል። ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሠጠቱም ተገልጿል። #ሪፖርተር @tikvahuniversity
Hammasini ko'rsatish...
👍 235 27😱 10🥰 8👏 8🙏 7