cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Injibara University

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
11 537
Obunachilar
+1824 soatlar
+837 kunlar
+14430 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች 83 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል። ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential. #እንጅባራ_ዩኒቨርሲቲ
Hammasini ko'rsatish...
በማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ እየተሠራ ባለው የድንች ምርጥ ዘር ብዜት ላይ ጉብኝት ተካሄደ፡፡ በጉብኝቱ የዩኒቨርሲቲው ክፍተኛ አመራሮች፣ የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደ ግብርና መምሪያ ኃላፊ፣ ከእንጅባራ ከተማ አስተዳደር እና ባንጃ ወረዳ የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች ተገኝተዋል፡፡ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ  ግብርና የሀገራችን ዋና የኢኮኖሚ መሰረት መሆኑን ከግምት በማስገባት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና እና አረንጓዴ ልማትን ቁልፍ የትኩረት መስክ አድርጎ በድንች ብቻም ሳይሆን በተመረጡ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ-ብዙ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው  አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል። የድንች ዝርያ ማሻሻል እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ላይ እየተሳተፉ ላሉ ምሁራን ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ https://www.facebook.com/share/p/qoudCY6Ci1wTgDob/?mibextid=oFDknk
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ይመኛል። #መልካም በዓል ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ ለሬሜዲያል ተፈታኞች በሙሉ የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3-10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ           የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤ ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ማሳሰቢያ፤ 1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል። 2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ  አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።                የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
Hammasini ko'rsatish...
አቶ ይበሉ ደሳለው እጅግ ታታሪ እና ለሌሎቻችን አርአያ ተሸላሚ ሰራተኞችን ነበሩ፣ በአቶ ይበሉ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽኩኝ ፣ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን፣
Hammasini ko'rsatish...
የሀዘን መግለጫ ------ አቶ ይበሉ ደሳለው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በግቢ ውበት ሲያገለግሉ ቆይተው ሚያዚያ 26/2016 ዓ.ም ባደረባቸው ህመም በተወለዱ በ50 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ይበሉ በግቢ ውበት ሥራቸው የሚታወቁ ለሌሎች ሠራተኞችም አርአያ የሆኑ ባሳዩት የሥራ ትጋትም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ተሸላሚ ነበሩ። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ይበሉ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
Hammasini ko'rsatish...
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎቹ ልዩ የምሳ ግብዣ አድርጓል። በድጋሜ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል። ሚያዚያ 27/2016 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
#እንኳን_አደረሳችሁ! ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ይመኛል። #መልካም በዓል ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
Hammasini ko'rsatish...
ለውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ  በመሰጠት ለሰው ልጆች ወደር የለሽ  ፅኑ ፍቅር ያሳየበት፣ ለበደሉት ሳይቀር  ይቅርታና ምህረትን የሰጠበት፣ ሞትንም ድል ያደረገበት መታሰቢያ በዓል በመሆኑ እኛም፣ እርስ በርሳችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም ሰው በመውደድ፣ በይቅርታ፣ በምህረትና በመረዳዳት እንድንኖር ፈጣሪ ይርዳን። ይህ የትንሳዔ በዓል  እየደበዘዙ  ለሄዱት ኢትዮጵያዊ  እሴቶቻችንም የትንሳኤ ጊዜ ያምጣልን!!! በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ በዓል ይሁንልን!!   መልካም በዓል!!!       ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት
Hammasini ko'rsatish...
እንኳን አደረሳችሁ! እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን  ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል። መልካም በዓል! ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
Hammasini ko'rsatish...
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ገመገመ። በግምገማው ዩኒቨርሲቲው ባለው ነባራዊ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆኖ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መቻሉን፣ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለመጨረስ የተወሰዱ እርምጃዎችን እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን ቦርዱ በጥንካሬ የገመገመ ሲሆን በቀጣይ በትኩረት መሠራት ያለባቸውንም ጉዳዮች ለይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ለሥራ እንቅፋት በሆኑ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች እና ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዲሁም ከዋጋ ግሽበት ጋር ያልተገናዘበው የተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ ቦርዱ ውይይት አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ የሱታና ንግድ እና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝም የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀርቦ በቦርዱ ተገምግሟል፡፡ የሥራ አመራር ቦርዱን ስብሰባ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሰቢ የሆኑት ፕሮፌሰር የሺጌታ ገላው መርተውታል፡፡ ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም
Hammasini ko'rsatish...
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.