cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Injibara University

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
11 452
المشتركون
+124 ساعات
+167 أيام
+11730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ይመኛል። #መልካም በዓል ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወቂያ ለሬሜዲያል ተፈታኞች በሙሉ የትምህርት ሚኒስቴር የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3-10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ           የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤ ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ማሳሰቢያ፤ 1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል። 2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ  አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።                የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
إظهار الكل...
አቶ ይበሉ ደሳለው እጅግ ታታሪ እና ለሌሎቻችን አርአያ ተሸላሚ ሰራተኞችን ነበሩ፣ በአቶ ይበሉ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽኩኝ ፣ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን፣
إظهار الكل...
የሀዘን መግለጫ ------ አቶ ይበሉ ደሳለው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በግቢ ውበት ሲያገለግሉ ቆይተው ሚያዚያ 26/2016 ዓ.ም ባደረባቸው ህመም በተወለዱ በ50 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ይበሉ በግቢ ውበት ሥራቸው የሚታወቁ ለሌሎች ሠራተኞችም አርአያ የሆኑ ባሳዩት የሥራ ትጋትም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ ተሸላሚ ነበሩ። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ይበሉ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
إظهار الكل...
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎቹ ልዩ የምሳ ግብዣ አድርጓል። በድጋሜ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል። ሚያዚያ 27/2016 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#እንኳን_አደረሳችሁ! ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ! እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ይመኛል። #መልካም በዓል ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
إظهار الكل...
ለውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ  በመሰጠት ለሰው ልጆች ወደር የለሽ  ፅኑ ፍቅር ያሳየበት፣ ለበደሉት ሳይቀር  ይቅርታና ምህረትን የሰጠበት፣ ሞትንም ድል ያደረገበት መታሰቢያ በዓል በመሆኑ እኛም፣ እርስ በርሳችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም ሰው በመውደድ፣ በይቅርታ፣ በምህረትና በመረዳዳት እንድንኖር ፈጣሪ ይርዳን። ይህ የትንሳዔ በዓል  እየደበዘዙ  ለሄዱት ኢትዮጵያዊ  እሴቶቻችንም የትንሳኤ ጊዜ ያምጣልን!!! በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ በዓል ይሁንልን!!   መልካም በዓል!!!       ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት
إظهار الكل...
እንኳን አደረሳችሁ! እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን  ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል። መልካም በዓል! ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ Telegram-https://t.me/injiuniversity Website- https://www.inu.edu.et/ Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni Email- [email protected] Institution Email [email protected] Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/) YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity Explore Your Creative Potential.
إظهار الكل...
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ገመገመ። በግምገማው ዩኒቨርሲቲው ባለው ነባራዊ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆኖ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መቻሉን፣ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለመጨረስ የተወሰዱ እርምጃዎችን እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን ቦርዱ በጥንካሬ የገመገመ ሲሆን በቀጣይ በትኩረት መሠራት ያለባቸውንም ጉዳዮች ለይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ለሥራ እንቅፋት በሆኑ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች እና ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዲሁም ከዋጋ ግሽበት ጋር ያልተገናዘበው የተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ ቦርዱ ውይይት አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ የሱታና ንግድ እና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝም የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀርቦ በቦርዱ ተገምግሟል፡፡ የሥራ አመራር ቦርዱን ስብሰባ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሰቢ የሆኑት ፕሮፌሰር የሺጌታ ገላው መርተውታል፡፡ ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም
إظهار الكل...
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክቶች ግምገማ ተካሄደ። ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በ2015 ዓ.ም ተጀምረው ባልተጠናቀቁት እና በ2016 ዓ.ም መጀመር ባለባቸው ግንባታዎች ላይ ያተኮረ ከአማካሪ ድርጅቱ እና ከስራ ተቋራጮች ጋር ውይይት አደርገዋል። ውይይቱን የመሩት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ እንደገለጹት የምክክር መድረኩ ዓላማ በ2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ተጠናቀው አግልግሎት መስጠት የነበረባቸውን ነባር ፕሮጀክቶችን እና መጀመር የነበረባቸውን አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመለየት አሁንም ነባር ፕሮጀክቶች የሚጠናቀቁበትን እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችም የሚጀመሩበትን ስልት ለመቀየስ እንደሆነ አብራርተዋል። በውይይቱም የበርካታ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ይቀርፋሉ የተባሉት የመምህራን መኖሪያ አፓርትመንቶች እና የአስተዳደር ህንጻዎች በቅርቡ ተጠናቀው ለአግልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እንዲቻል ከአማካሪ፣ ከስራ ተቋራጮች እና ከዩኒቨርሲቲው የሚጠበቁትን ኃላፊነቶች በመለየት እና ልዩ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት መረባረብ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም የአዳዲስ ፕሮጀክቶች ግንባታ ማለትም የስብሰባ አዳራሽ፣ የመማሪያ ክፍል፣ ተጨማሪ የመምህራን መኖሪያ፣ የሰራተኞች መዝናኛ እና የተማሪዎች ማደሪያ በቅርቡ መጀመር እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ሁሉም አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መግባባት ላይ ተደርሷል። በውይይቱ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ስራ ተቋራጮች እና የአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
إظهار الكل...
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክቶች ግምገማ ተካሄደ። ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች በ2015 ዓ.ም ተጀምራው ባልተጠናቀቁት እና በ2016 ዓ.ም መጀመር ባለባቸው ግንባታዎች ላይ ያተኮረ ከአማካሪ ድርጅቱ እና ከስራ ተቋራጮች ጋር ውይይት አደርገዋል። ውይይቱን የመሩት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ እንደገለጹት የምክክር መድረኩ ዓላማ በ2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ተጠናቀው አግልግሎት መስጠት የነበረባቸውን ነባር ፕሮጀክቶችን እና መጀመር የነበረባቸውን አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመለየት አሁንም ነባር ፕሮጀክቶች የሚጠናቀቁበትን እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችም የሚጀመሩበትን ስልት ለመቀየስ እንደሆነ አብራርተዋል። በውይይቱም የበርካታ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ይቀርፋሉ የተባሉት የመምህራን መኖሪያ አፓርትመንቶች እና የአስተዳደር ህንጻዎች በቅርቡ ተጠናቀው ለአግልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እንዲቻል ከአማካሪ፣ ከስራ ተቋራጮች እና ከዩኒቨርሲቲው የሚጠበቁትን ኃላፊነቶች በመለየት እና ልዩ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት መረባረብ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም የአዳዲስ ፕሮጀክቶች ግንባታ ማለትም የስብሰባ አዳራሽ፣ የመማሪያ ክፍል፣ ተጨማሪ የመምህራን መኖሪያ፣ የሰራተኞች መዝናኛ እና የተማሪዎች ማደሪያ በቅርቡ መጀመር እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ሁሉም አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መግባባት ላይ ተደርሷል። በውይይቱ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ስራ ተቋራጮች እና የአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
إظهار الكل...
#የሀዘን መግለጫ *** የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት እቅድና ሥራ አመራር /Educational Planning and Management/ ትምህርት ክፍል፣ 2ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ብርቱካን ጥበቡ ወሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ዩኒቨርሲቲው በተማሪ ብርቱካን ጥበቡ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ፣ የተማሪዋን አስክሬን ወደ ትውልድ ስፍራዋ ሸኝቷል። እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለቤተሰቦቿ፣ ለጓደኞቿ እና ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሙሉ መፅናናትን ይመኛል!
إظهار الكل...
የአትክልት ልማት (የአፕል እና ሽቅብ ግብርና/Vertical Farming) የማስተማሪያ እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ላይ ጉብኝትና ውይይት ተካሄደ፡፡ https://www.facebook.com/share/vQGob3tiiU4p3cmu/?mibextid=oFDknk
إظهار الكل...