💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Kanalga Telegram’da o‘tish
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Ko'proq ko'rsatish9 030
Obunachilar
-424 soatlar
-337 kunlar
-13630 kunlar
Postlar arxiv
Repost from دروس وفوائد أبي حزام عبدالرحمن بن سعيد
ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አል በድር በጠና ታማ ወደ አኺራህ ስለሔደችዉ እህታቸው የፃፏት ሪሳላህ ናት
ወደ አኺራህ የቀደሙን እህቶቻችንን አላህ በሰፊው እዝነቱ ይማራቸው
آه ما أجمل آثر الأخت على أهلها
وفقدها غصة تترك فراغاً لا يملؤه غيرها، لكن عزاء المؤمن أن الأثر الطيب لا يموت، وما زرعته من حنان وصبر ودعوات صالحات يبقى يظلها ويظل أهلها حتى يجمع الله الشمل في مستقر رحمته.
🌹 በባልሽ ዘንድ ተወዳጅና የተከበርሽ ለመሆን ከፈለግሽ ⁉️
በባልሽ ዘንድ ሁልጊዜም ተወዳጅ፣ የተከበርሽና የልቡ ንግሥት ሆነሽ መኖር ትፈልጊያለሽ? እንግዲያውስ ይህንን ትልቅ የትዳር ሚስጥር በተግባር አሳይው።
🌹 ባልሽን መከባከብና እሱን ማስደሰት እንዲሁ ተራ ተግባር ሳይሆን፣ አላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ "ዒባዳ" መሆኑን እወቂ።
🌹 ባልሽን እንደ ባል አክብሪው አላህ ለወንዶች የሰጠውን የኃላፊነት ቦታ (ቀዋሚነት) እወቂለት። እሱን ማክበርሽ አንቺን ዝቅ አያደርግሽም፤ ይልቁንም በዓይኑ ላይ ትልቅ ያደርግሻል። አላህን በማመፅ እስካላዘዘሽ ድረስ የታዛዥነትሽን ልብ ስጪው።
🌹 የቤትሽ "ሰከን" (መረጋገጫ) ሁኚለት ከውጭ በስራና በኑሮ ደክሞት ሲመጣ፣ ቤትሽ የሰላም ወደብ ይሁንለት። ንጭንጭንና ጭቅጭቅን አስወግጂ። በለሰለሰ ንግግርና በፈገግታ ተቀበዪው። ነቢዩ (ﷺ) እንደተናገሩት፦ "ምርጥ ሴት ማለት ስትመለከታት ደስ የምታሰኝህ ናት ብለዋልና።"
🌹 እልክና ፉክክርን ተዪ ትዳር የሁለት ተፋቃሪዎች መርከብ እንጂ የፉክክር ሜዳ አይደለም።ከባልሽ ጋር እልህ ውስጥ አትግቢ፣ ለባልሽ ንቀት አታሳይ። ስህተቱ የሱ ቢሆንም እንኳ በትህትናና በጥበብ ለማሳመን ሞክሪ እንጂ በባልሽ ላይ ድምፅሽን ከፍ አታድርጊ።
🌹 የትዳር ሀቁን ጠብቂለት የባልሽን ስሜት መጠበቅና በሐላል ደስተኛ እንዲሆን ማድረግ የአንቺ ትልቁ ኃላፊነት ነው። በዚህ ረገድ አትዘንጊ፣ አትለግሚ። እሱ ካንቺ ዘንድ እርካታን ካገኘ፣ ልቡ ሙሉ በሙሉ የአንቺ ይሆናል።
🌹 ቤትሽንና ራስሽን ጠብቂ፦ ቤቱን በንጽህና ያዢ፣ ለአንቺም እንዲመቸው አድርጊው። ለባልሽ በሚያምር ሁኔታ ተዘጋጂ። ይህ ማድረግሽ ለሱ ያለሽን ፍቅርና ክብር መግለጫ ነው።
🌹 ይህንን ሁሉ ስታደርጊ ለዱንያ ጥቅም ብቻ ሳይሆን የአላህን ውዴታ ፍለጋ ይሁን። "ባሌን ካስደሰትኩ አላህ ይወደኛል" ብለሽ ነይቺ። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዲት ሴት አምስት ወቅት ሶላቷን ሰግዳ፣ የረመዳንን ወር ጾማ፣ ብልቷን ጠብቃና ባሏን ታዛ ከሞተች፤ ከፈለግሽበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች።" (ኢማም አሕመድ ዘግበውታል)
እህቴ ሆይ! ባልሽን ለአላህ ብለሽ ካከበርሽው፣ አላህ በእሱ ልብ ውስጥ ያንቺን ፍቅርና ክብር ይዘራዋል። ትዳርሽን በኢማንና በጥሩ ስነ-ምግባር አድምቂው።
ያንችው ወንድም አቡ ሒበቲላህ
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👉እናቷን እንዲህ አለቻት እናቴ ለምን
ከቤት ስንወጣ ሽቶ ከለከልሽኝ?
እናቷም፦
አበቦች ሽቶ አያስፈልጋቸውም።
ያ አሏህ!
ከቅናቻ በኋላ አታንሸራተን፡፡
ከታጠብን በኋላ አታጨቅየን፡፡
ከተነሳን በኋላ አትጣለን፡፡
ከቶበትን በኋላ አትመልሰን፡፡
ካንተ ጋር የሕይወትን ጥፍጥና
ከቀመስንና ካጣጣምን በኋላ አትጣላን፡፡
እህቴ ሞደልሽ ይህች ነች!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
እናታችን አዒሻ እንዲህ ነበረች፦
➩«በቤታችሁ ውስጥ ተሰተሩ(እርጉ)»የሚለውን አንቀፅ ስታነብ«መሸፋፈኛዋ» እስኪረጥብ ድረስ ታለቅስ ነበር።
رواه البخاري(4467)
فما بال نساء المسلمين
في الأسواق يزاحمن
الرجال .....
በየገበያው ውስጥ ከብዙ
ወንዶች.....ጋር #የሚጋፉት የኛዎቹ ሙስሊም ሴቶችስ..!?
Repost from 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🫵 የጁሙዓ_ኹጥባ (ምክር) - 5
•التحذير_من_ذنوب_الخلوات!!
• ከድብቅ_ወንጀሎች_ማስጠንቀቅ!!
🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3
t.me/AbumuslimAlarsi/14106
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
Repost from قَنَاةُ أَبِي رَيِّسٍ لِنَشْرِ السُّنَّةِ
🫵 የጁሙዓ_ኹጥባ (ምክር) - 5
•التحذير_من_ذنوب_الخلوات!!
• ከድብቅ_ወንጀሎች_ማስጠንቀቅ!!
🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3
t.me/AbumuslimAlarsi/14106
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
🔖የጁሙዓ ቀን ሱናዎች!
〰〰〰〰〰〰〰
①) ገላን መታጠብ
②) ሲዋክ መጠቀም
③) ጥሩ ልብስ መልበስ
④) ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤) ሽቶ መቀባት (ለወንዶች)
⑥) ሑጥባ በጥሞና ማዳመጥ
⑦) በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
⑧) በነብዩ ﷺ ላይ ሶላትና ሰለዋት ማብዛት
⑨) ዱአ ተቀባይነት ያለበትን ሰአት ስላለ መታጠብ
Repost from ስለ ስልካችን
👈 وَكُلُوا۟ وَٱشْرَبُوا۟ وَلَا تُسْرِفُوٓا۟ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلْمُسْرِفِينَ
ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ (አላህ ሱብሀነሁ ተአላ) አባካኞችን አይወድምና፡፡
~
🌷 ሰው በውበቱ አይከበርም፤ በኢማኑና በአክላቁ ነው የሚያምር።
ልብሽን በሀያእ፣ አንደበትሽን በዚክር፣ ሕይወትሽንም በሶላት አሳምሪ። 🌸
ያኔ ሁሉም ቦታ ቦታውን ይይዛል!!
🔖
አንድ ሰው ወደ ሀሰነል በስርይ መጣና፦ የሰኢድ አባት ሆይ ቀልቤ ደርቋል ምን ላድርግ ብሎ ስሞታ አቀረበ። እሳቸውም በዚክር ስርአት አሲዛት አሉት።
[ ذم الهوى: 69 ]✅ነፍስ በ3 መንገዶች ስኬታማና፤ የጠራች ትኾናለች።
قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ١٤ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ١٥
የተጥራራ ሰው በእርግጥም ዳነ፤ የጌታውንም ስም ያወሳ፤ የሰገደም። [አል‒አዕላ (14—15)]
-
➀. እንዳትቆሺሽ ተገቢውን ክትትል በማድረግ፤
➁. የአላህን ስም ያለማቋረጥ በማውሳት እና፤
➂. ነፍስን በሶላት ጊዜ ከአላህ ጋር በማስተሳሰር።
t.me/https_Asselfya
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በኢማራት የሚቀርበው የደዕዋ ፕሮግራም በዚህ የቴሌግራም ቻናል የሚተላለፍ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ
-
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
~ዉድ የቻናላችን ቤተሠቦች .....!
ኢድ ሙባረክ تقبل الله منا ومنكم
ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን ።
🔖 እህቴ ሆይ አደራ !!
ለዒባዳና ወደ አላህ ለመቃረብ ከቤት ስትወጪ አላህን ከማስቆጣትና ሸሪዓውን ከመጣስ ተጠንቀቂ!
የአላህ ውዴታ እሱን በማመጽ አይገኝም።~ t.me/https_Asselfya
Endi mavjud! Telegram Tadqiqoti 2025 — yilning asosiy insaytlari 
