uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 792 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 378-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 255-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 792 obunachiga ega bo‘ldi.

15 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 238 ga, so‘nggi 24 soatda esa 2 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 9.60% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.09% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 516 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 593 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 14 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 16 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 792
Obunachilar
+224 soatlar
+1737 kun
+23830 kun
Postlar arxiv
ለመልአከ ሰላም አምደ ወርቅ ደሴ የተደረገላቸው ታላቅ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ፡፡ 10 / 04 /2014 ዓ.ም

#በመዲናችን_በአዲስ_አበባ_በአገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፴፩ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ (ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ በውስጥ ጻፉልን፡፡) #በመዲናችን_በአዲስ_አበባ__በዓላቸው_የሚከበሩባቸው_ #፫ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባና አማኑኤል ገዳም፤ አድራሻው፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቦሌ ቡልቡላ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሳሪስ አቦ→ ቦሌ ቡልቡላ መድኀኔ ዓለም (ወይም ኮንዶሚኒየሙ ጋር እንደወረዱ ያገኙታል፡፡) ፪. ቦሌ ወረገኑ ደብረ ገነት አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ አድራሻው፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ወቄ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → አያት → ወረገኑ፤ ፫. ሲምሲ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል፤ (ሳጠራው ) (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ)፤ አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አልታድ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → ሲምሲ(አልታድ)፤ #በሃገራችንና_በዓለም_አቀፍ__በዓላቸው_የሚከበሩባቸው_ #፳፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. በቅድስት ዋልድባና በሥሩ በሚተዳደሩ ገዳማት፤ ፩.፩ ቅድስት ዋልድባ (ዋልድባ አብረንታንት መድኀኔ ዓለም) አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ማይጠ(ጸ)ብሪ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → ዓዲ አርቃይ → ዋልድባ አንረንታንት ገዳም (በእግር)፤ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ዳንሻ → ማይጋባ → ዋልድባ (በእግር)፤ ወይም፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → አኵሱም → ሽረ → በተከዜ ወንዝ ዋልድባ (በእግር)፤ ፩.፪ ቅድስት ዋልድባ ዳልሻህ አባ ሳሙኤል ገዳም፤ ዋልድባ ሰቋር) ፤ አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ማይጠ(ጸ)ብሪ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → ዛሪማ → ዋልድባ ዳልሻህ ገዳም (በእግር)፤ ፩.፫ ቅድስት ዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ቅዱስ ጊዮርጊስና መድኀኔ ዓለም ገዳም፤ አድራሻው፤ ሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ማይጠ(ጸ)ብሪ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → ዓዲ አርቃይ → ዋልድባ ሰቋር ገዳም (በእግር)፤ ፩.፬ ቅድስት ዋልድባ አቴና (መቃብረ ሳሙኤል)፤ (መጀመሪያ ክብርት ሥጋቸው ያረፈበት) (ከዋይዜማው ጀምሮ ሌሊቱንና ቀኑን ሙሉ ጧፍ እየበራ ሙሉ ገድላቸው በማንበብ የሚከበርበት) ፩.፭ ዋልድባ አባ ናፃ የአቡነ ተሥፋ ሐዋርያት ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፮ ዋልድባ ማይ ለበጣ ቤተ እግዚአብሔር፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፯ ዋልድባ ደንደሮቃ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፰ ዋልድባ ማይጋባ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፱ ዋልድባ ደለሳ ቆቋ አቡነ አረጋዊ ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፲ ዋልድባ ማይ ሃርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፲፩ ዋልድባ ዕጣኖ ማርያም ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፲፪ ዋልድባ ዋልቅስ ኪዳነ ምሕረት ገዳም፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፲፫ ዋልድባ አ(ጽ)ምብላ አቦ፡፡ (በውዳሴ በሰዐታት በቅዳሴና በዝክር) ፩.፲፬ በዋልድባ ስር ባሉ የስዕል ቤቶችና የአትክልት ቦታዎች (በዝክር) ፪. አቡነ ሳሙኤል በመሠረቷቸውና ባስፋፏቸው ገዳማት ፪.፩ ደብረ ዐባይ አቡነ ሳሙኤል (አቡነ ሳሙኤል የመሠረቱት ገዳም)፤ (በኢትዮጵያ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ የደብረ ዐባይ ቅዳሴ ዋና ማስመስከሪያ) (እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ሁኔታ ክብረ በዓላቸው የሚከበርበት ቦታ) አድራሻው፤ ሽረ ሀገረ ስብከት፥ እንዳባጉና፥ ደብረ ዐባይ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → አኵሱም → ሽረ → ደብረ ዐባይ፤ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር …ደባርቅ …ዓዲአርቃይ.. ማየጠ(ጸ)ብሪ → ሽረ → ደብረ ዐባይ፡፡ ፪.፪ አብጠራ (አብጠራህ) አቡነ ሳሙኤል ገዳም (አቡነ ሳሙኤል በኪደተ እግር የረገጡት)፤ (ብዙ ገቢረ ተአምራት ያደረጉበት) አድራሻ፤ ሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደባርቅ፥ ወቅን፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ(ዳባት) → አብጠራ ሳሙኤል፡፡ ፪.፫ ጎንደር አዘዞ አባ ሳሙኤል፤ (በኪደተ እግራቸው የረገጡት) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ ፥ አዘዞ አባ ሳሙኤል፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር(አዘዞ)፡፡ ፪.፬ አቃቂ ደብረ ገነት አቡነ ሳሙኤል ገዳም (አቡነ ሳሙኤል በኪደተ እግር የረገጡት)፤ (በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የመብራት ኀይል ማመንጫ ግድብ የተሠራበት፤ የኀይል ማመንጫው ስሙም በአባ ሳሙኤል ነው የሚጠራው) አድራሻ፤ ደቡብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ አቡነ ሳሙኤል ኀይል ማመንጫ (ገዳም)፤ ትራንስፖርት፤ ከአፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → አቃቂ (ንግድ ባንኩ ጋራ) → ገዳም (አባ ሳሙኤል)፡፡ ፫. በስማቸው በታነጹ ገዳማትና አድባራት፤ ፫.፩ በተወለዱበት በርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ጽዮን አኵሱም ማርያም ፫.፪ ምንኵስናን በተቀበሉበት በደብረ በንኰል አቡነ መድኀኒነ አግዚእ ገዳም፤ (ሽሬ አጠገብ) ፫.፫ በቆብ ወንድማቸው በአባ ያሳይ መንዳባ መድኀኔ ዓለም ገዳም፤ (ጎርጎራ ፥ ጣና ፫.፬ በቆብ አያታቸው በአቡነ ተክለሃይማኖት ደብረ ሊባኖስ ገዳም፤ በውዳሴና በቅዳሴ (በደብረ ሊባኖስ ቅዳሴ በየቀኑ በማይቀደስበት፤ በዓመት ውስጥ ጥቂት ቀናት ብቻ በሚቀደሱበት ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የቅዳሴ ቀናቸው ከማይታጎሉ አንደኛውና ዋነኛው የአቡነ ሳሙኤል በዓለ ዕረፍት ነው፡፡) ፫.፭ አንጓ ቀርነጃ ታላቅ ሴራ ሳሙኤል ቤ.ክ.፤ አድራሻ፤ ሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደባርቅ፥ ቀርነጃ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → ድባ ባሕር → ቀርነጃ(በእግር)፡፡ ፫.፮ ነቀምቴ አቡነ ሳሙኤል ቤ.ክ.፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ወለጋ ሃገረ ስብከት፥ ነቀምት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ነቀምት፡፡ ፫.፯ ገፈርሳ(ታጠቅ) በዓለ ወልድ ወአቡነ ሳሙኤል ወአቡነ ኪሮስ ቤ.ክ.፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ገፈርሳ (ታጠቅ)፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ታጠቅ ወይም መናገሻ አዲስ ዓለም በሚል መኪና፡፡ ፫.፰ መቀለ ደብረ መዐዛ አቡነ አረጋዊ ወአባ ሳሙኤል፡፡ አድራሻ፤ መቀለ ሃገረ ስብከት፥ መቀለ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ፤ ፫.፱ ደባርቅ ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤ አድራሻ፤ ሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደባርቅ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ፡፡ ፫.፲ ዩኤስኤ አሜሪካ ቨርጂንያ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም፤ አድራሻ፤ ሰሜን አሜሪካ ዲሲ ሃገረ ስብከት፥ ቨርጂኒያ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → ዲሲ → ቨጂኒያ(በመኪና)፡፡ / #ክብረ_በዓላት #Feasts / #ኢትዮጵያውያን_ቅዱሳን #Ethiopian_Saints / #ገዳማትና_አድባራት #Monasteries_and_Churches / /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook...

#ታኅሣሥ_12_የአቡነ_ሳሙኤል_በዓለ_ዕረፍት ✤✤ #ፀሐይ_ማር_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_(#ዘገዳመ_ዋሊ_) ✤✤ ፠ በሃገራችን በኢትዮጵያ በብቸኝነት በጌታችን የተመሠረተው ገዳመ ዋልድባ፤ ኋላ በአሕዛብ ጠፍቶ ነበርና በ13ኛው ክፍል ዘመን እንደ መሶብ ከፍ አድርገው በ4ቱም አቅጣጭ በ4 ወንዞች (በሰሜን ተከዜ፥ በምስራቅ እንስያ፥ በምዕራብ ዛሪማ ፥ በደቡብ እንዞና ወይቦ) ዙሪያውን ከልለውና አጥረው ያስባረኩ አባት ናቸው፡፡ ፠ አዲስ አበባና አካባቢውን ከ700ዓመታት በፊት በአንበሳ እየተጓጓዙ በስብከተ ወንጌል እርሻነት፥ በሥነ ምግባር ማለስለሻነት ያረሱ አባት ናቸው፡፡ ፠ ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን፣ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት የኾኑ ናቸው፤ ይህንንም ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ40ቀን ዕረፍታቸው በመካነ መቃብራቸው ተገኝተው መልክዓቸውን ደርሰውላቸዋ፤ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው አውስተዋቸዋል፤ እንዲሁም በርካታ ቅዱሳን ደራስያን በየድርሰታቸው አንስተዋቸዋል፡፡ #ክቡር_መምህር፥ #የከበረ_መምህር፤ #መልአክ_ዘበምድር፥ #የምድር_መልአክ፤ #ካህን_ወድንግል፥ #ካህንና_ድንግል፤ #ፍጹም_ንጹሕ_ወልዑል፥ #ፍጹም_ንጹሕና_ልዑል፤ #ትጉህ_ወኅሩይ፥ #ትጉህና_ኅሩይ_የተመረጠ)፤ #ብእሴ_እግዚአብሔር፥ #የእግዚአብሔር_ሰው፤ #ለባሴ_ንጽሕና፥ #ንጽሕናን_የተላበሰ፤ #ወለብሰ_ብርሃናዌ፥ #ብርሃንን_የለበሰ፤ #ዘፈጸመ_ገድሎ_በሠናይ፨ #ገድሉን_በመልካም_ተጋድሎ የፈጸመ፨/ገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ/ ፠ ከረድአቸው አባ ብንያሚና፤ ከጓደኞቻቸው ከአባ አንበስ ዘሐዘሎና ከአቡነ ዘርዐ ቡሩክ ጋር በመኾን በወቅቱ ከነበሩት ርዕሰ አበው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ለመባረክ ወደ ዝቋላና ምድረ ከብድ የመጡና በረከትን የተቀበሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ያስተማሩ ናቸው፡፡ ፠ አናታቸው በሥጋ ሞት በሕፃንንታቸው ቢለይዋቸውም፤ በሕፃንነታቸው ጌታችን አውራ ጣቱን አትብቷቸዋል፡፡ ‹‹እንዘ ይተግህ ለጸልዮ ወያስተበርክ ለስኢል፤ መንኰብያቲሁ አጠበዎ ወልደ ማርያም ድንግል፡፡ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል ዘዋልድባ መነኮስ ኀያል፡፡›› /እንዲል ነግሥ/ ፠ የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትዕምርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ ፥ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ወደ ወንዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉም ሳይበላሽ ተሸግረዋል፡፡ ፠ ገባሬ ተዓምራት ወመንክራት የኾኑ፤ ⴲ ዝናብ በኾነ ጊዜ ዝሆኖች መጥተው እንደ ጥላ የሚያስጠልሉት፤ ‹‹ሳሙኤል አቡነ ሠረገላ ጸሎት፤ ጊዜ ርደቶሙ ለዝናማት፤ ዘከለሉከ ነጌያት፡፡›› እንዳለ መጽሐፈ ሰዐታት፤ ⴲ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ (ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት) ጋር መንበረ ጸባዖትን ለ12 ዓመታት አጥነዋል፤ በዚህም በጎንደር ደባርቅ አካባቢ የመሠረቱት ገዳማቸው አብ ጠራ(ህ) በሚል ተሰይሟል፡፡ ......................................የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ‹‹ሳሙኤል አቡነ ትሩፈ ምግባር፤ ዐምድ ጽኑዕ ፀወነ ሃገር፤ ወመልአክ ዘበምድር፡፡›› እንዲል መጽሐፈ ሰዐታት፣ ⴲ በዋልድባ ምድር ላይ ቀድሞ ውኃ የለም ነበርና፤ ፸ የሚጠጉ ምንጮችን በተለያዩ ቦታዎች አፍልቀዋል፡፡ ⴲ ቅዳሴ ማርያምን ወደ መሃል ሃገር ያመጡ፤ ⴲ ቅዳሴ ወውዳሴ ማርያምን ሲደግሙ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ያህል ከፍ የሚሉ፡፡ ⴲ በአናብስት ዘባን ላይ የሚጫኑ፤ መጻሕፍቶቻችውንም በአናብስት ላይ የሚጭኑ፡፡ ⴲ እመቤታችን ነጭ ዕጣን (ስለ ምዑዝ ክህነታቸው) እንዲሁም ዕንቊ (ስለ ንጽህናቸው፣ ቅድስናቸውና ድንግልናቸው) የሰጠቻቸው። ⴲ በሰኔ 21 ቀን በቀደሱበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ አንድ ክንድ ከስንዝር ከምድር ለቆ እንደ ደመና በአየር ላይ ቆሞ የታየላቸው፡፡ ⴲ ውኃውን ወደ ኀብስት የቀየሩና ከነ ደቀመዛሙርቶቻቸው የተመገቡ፤ ‹‹ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ፤ ረሰዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ፡፡ ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ፤ ሥረዪ ኀጢአትየ ወዕፀብየ አቅልሊ፤ አስመ ኵሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/ ‹‹ …አርአዮሙ ለመምህራን ዐበይተ ኀይላተ፤ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በኀበ ተአኵተ፥ ወለማይኒ ረሰዮ ኅብስተ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/ የምንኵስና ተወረዱም፤ አባት አባትን ሲወልድ፤ መምህር መምህርን ሲተካ፥ ቅዱስ ቅዱስን ሲያፈራ፥ ገዳም ገዳምን ሲወልድ ነውና ቅሉ፤ የምንኵስና ተዋረዱም፤ ፠ ….. ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን፤ ፠ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7ቱን ከዋክብት /ፀሐይ አቡነ ሳሙኤልንና ሌሎች ቅዱሳንን/፤ ፠ ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ ፀሐይ አቡነ ሳሙኤል ደግሞ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን (አባ ተሥፋ ሐዋርያትን፥ አባ ዘሩፋኤልን፥ አባ ብንያሚን፥ አባ በኪሞስን፥ …… ሌሎች እልፍ አእላፋት መነኰሳትን አምንኵሰዋል፣ ሊቃውንትን አስተምረዋል፤ መምህራንና ደራስያንን ተክተዋል ….፤ በዚህም ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ፥ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት አባ ሳሙኤል በመባልም ይታወቃሉ፡፡ #አቡነ_ሳሙኤል_፤ በአኵስም ከተማ አካባቢ በ1295 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው ዓመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በአኵስም ጽዮን ከነበሩት መምህራን ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ተምረዋል፡፡ ወላጆቻቸው በልጅነታቸው በሞት ተለይተዋቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ሞት በኋላ ወደ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘንድ ሔደው ደብረ በንኰል ገዳም ገቡ፡፡ በዚህም ገዳም እያገለገሉ በወቅቱ ከነበሩት ሊቃውንት የብሉያትና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ሥርዐተ ምንኵስናን ተምረው ከገዳሙ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ከሌሎች 11ድ ወንድሞቻቸው ጋር አብረው መነኰሱ፤ ቆባቸውም እንደ አቡነ አረጋዊ የድንጋይ ቆብ ነበር፡፡ በዚህም ገዳም እህል ሳይበሉ ቅጠል ብቻ እየተመገቡ ይኖሩ ነበር፡፡ እግራቸው እስኪያብጥም ድረስ ይሰግዱ ነበር፡፡ **ኋላ ወደ ጣና ገብተው ከቆብ ወንድማቸው ከአቡነ ያሳይ ጋር ለ12 ዓመታት በሱባኤ ቆዩ፤ **በስተመጨረሻም ጌታችን ወደ መሠረተውና በመሃልም ጠፍ ሆኖ ወደ ነበረው ብዙ ቅዱንን፣ መምህራንን፣ ሊቃውንትንና መናንያንን ወደ ወለዱበት ዋልድባ ገዳም ገብተው ለ70 ዓመታት ያህል ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው፣ ግርማ ሌሊቱን፥ ፀብአ አጋንንቱን ፥ ድምፀ አራዊቱን፥ የሌሊቱን ቊር፥ የቀኑን ሐሩር ታግሠው፣ ረሃቡንና ጽሙን ችለው፣ መላ ዘመናቸውን በጽድቅ ጎዳና ተጕዘው በ1395ዓ.ም ታኅሣሥ 12 ቀን በዋልድባ አቴና ገዳም ዐርፈዋል፡፡ #ባርከኒ አባ እንሣእ ጸሎተከ፤ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ አባ ሳሙኤል ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፨ /ጸሎተ መሐረነ አብ/ #በታኅሣሥ ፲፪ በበዓለ ዕረፍታቸው ጊዜም፤ ሮም በጴጥሮስና በጳውሎስ ዕረፍት እንዳለቀሰች፤ ቅድስት ገዳማቸው ገዳመ ዋልድባ (ዋሊ) አልቅሳለች፨ ‹‹በከየት ወለሀወት ገዳምከ በሞትከ ዮም፤ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፤ ምድረ ዋልድባ ቅድስት ሰሚዓ ዜና ሞትከ፤ እንዘ አንተ ሰብእ ምድራዊ ወመልአክ ተሠመይከ፤ ካህነ አርያም ሳሙኤል መንበረ ሥላሴ ዘአጠንከ፤ አንበሳ ወነምር ይሰግዱ ለከ፤ ወይልህሱ ጸበለ እግርከ፤ ዕንቈ ወዕጣነ ማርያም አምጽአት ለከ፤ በቅዳሴሃ ሶበ ጸለይከ፤ በከየት ወለሐወት ገዳምከ።>> እንዲል ዚቅ፨ #ታኅሣሥ #፲፪ ፤ #በዓለ_ዕረፍቱ_ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_፡፡

በአጥቢያችን ለምትገኙ የጽዋ ማኀበራትና ወጣቶች በሙሉ የጥምቀት በዓል እንደተለመደው በደመቀ ሥነ ሥርዓት እንድናከበር በአጥቢያው የምትገኙ የጽዋ ማኅበራት ፣ ምንጣፍ በማንጠፍና በመጥረግ እንዲሁም በተለያዩ አገልግሎቶች ለማገልገል የተዘጋጃቹሁ ወጣቶች፤ ሰንበት ት/ቤችን በመሰል ጕዳዩች ሊያወያያቹሁ ስለሚፈልግ ዛሬ ታኅሣሥ 7 ከምሽቱ 12 ሰዓት በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፡፡ ሰ/ት/ቤቱ

ታኅሣሥ 7 ፤ በዚህችም ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዱስ ያሬድ ዜማ በቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ጀመረች፤ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ የታኀሣስ 7 ክብረ በዓል ወድ ታኅሣሥ 11 ዞሮ ክብረ በዓሉ ታቦቱ ወጥቶ ይከበራል ፡፡ (አድራሻ፤ ጎተራ ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ፡፡) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ያሬድ በፊት ከሕገ ኦሪት በፊት በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በዜማ ማመስገን ነበር፡፡ ይህም በማሕዝኒና በበገና ብቻ እንደነበር መጻሕፍት ይናገራሉ ፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የምንሰማው ውርድና ቁም ንባብ የዘመነ ብሉይ ውጤቶች ናቸው ፡፡ለምሳሌ ‹‹ መልዕክተ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ ›› እይ ፡፡ የዜማ መሣሪያዎችንም ከዘመነ ኦሪት ጀምሮ ስትገለገለበት ቆይታለች ( ከበሮ ፣ መሰንቆ ፣ በገና ፣ መለከት )‹‹መዝ 8››፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከተሰወረ በኃላ ደቀ መዛሙርቶቹ በእርሱ እግር ተተክተው ዜማውን ማስተማር ቀጠሉ፡፡ አክሱም ጽዮን ማርያምንም ጽርሐ አርያም አስመስለዋት ነበር፡፡ በአባ ገሪማ ገዳም ውስጥ እና ደብረ ዳሞ ድረስ በመሄድም ጕባዔ እየዘረጉ ማስተማሩን እና ማስፋፋቱን ቀጥለው ነበር፡፡ ደቁ መዛሙርቶቹም ትምህርቱን አስተምረው በተለያየ ተጋድሎ ከአረፉ በኃላ ፡፡ የዜማው ትምሕርት ትግራይ ውስጥ በሚገኙ ታላላቅ ገዳማትና አድባራት ፣ በጣና ቂርቆስ ፣ በጎሐ ጽዮን ፣ በተድባበ ማርያም ፣ በመርጡለ ማርያም በዙር አባ ሁሉ ተዳረሰ ፡፡ በሒደትም የቅዱስ ያሬድ ጣዕመ ዜማ ተስፋፋ ፡፡ ተጨማሪ እዚህ አንብብ---›https://t.me/medihanaelem/6363 የቅዱስ ያሬድ ሌሎች መጠሪያ ስሞች ፠ ጥዑመ ልሳን፤ ፠ የሱራፌል አምሳያ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤ ፠ መዓርዒረ ዜማ፤ ፠ ዓርከ ሊቃውንት፤ ፠ ደራሲ፤ ፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤ ፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ፠ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ፤ …… ማን እንደርሱ:: …... ተጨማሪ እዚህ አንብብ---›https://t.me/medihanaelem/6363 /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ኢትዮጵያውያን_ቅዱሳን #Ethiopian_Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts