uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 945 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 320-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 237-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 945 obunachiga ega bo‘ldi.

18 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 392 ga, so‘nggi 24 soatda esa 142 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 10.83% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.03% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 727 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 599 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 17 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 19 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 945
Obunachilar
+14224 soatlar
+1557 kun
+39230 kun
Postlar arxiv
ግንቦት_16 ተዛካር ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በእንተ ስብከቱ ቅዳሴ ቤቱ ውስተ ሀገረ እስክንድርያ ወሶበ ጽሕፈቱ ወዕረገቱ ውስተ ሰማያት ወርእዮቱ ለሠራዊተ ሰማያውያነ ፡፡ ✤ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ✤ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ ✤በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ ሰላም ለቅደሴ ቤትከ በእለ እስክንድርያ ሀገር ፡፡ እለ ሐነፅዋ ኬነውት ወጠበብታ ምክር፡፡ ወእንዘ ትበውእ ዮሐንስ ውስተ መቃብር ፡፡ ተኀባዕከ ወተሠወርከ በሥልጣን ኀይል መንክር ፡፡ ባሕቱ ልብሰከ ዘተተፈ ለዝክር ፡፡ #በተለያዩ_ቅጽል_ስሞች_የሚጠራ፤ (100 አካባቢ ከሚጠጉ ስሞቹ ጥቂቶቹን /21ዱን ስሞች ከጽሑፍ በስተመጨረሻ ይመልከቱ) #ሰዓሊ_የኾነ፤ የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለ፡፡ #ከ81ዱ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሎች_5ቱንና_ሌሎች_መጻሕፍትንም_(ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤ #ብዙ_ደቀ_መዛሙርትን_ያስተማረ፤ ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ #share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡ ✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤) ✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤) ✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /እመጽሐፈ ሰዐታት/ ፨ ‹‹ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፤ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ›› /መልክአ ኢየሱስ/ ፨ ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዓሞ፤ ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፤ ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፤ ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፤ ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ፡፡ /መልክአ ሥዕል/ ፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤ ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡ ወልደ #ዘብድዮስ ፥ ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥ ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥ ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡) ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥ ዮሐንስ #ድንግል ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡ 1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) 2. ዮሐንስ ድንግል 3. #ዮሐንስ_ፍንው 4. #ዮሐንስ_ካህን 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ 6. ዮሐንስ ሥርግው 7. #ዮሐንስ_ምዑዝ 8. ዮሐንስ ቅኑይ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ 11. #ዮሐንስ_ክቡር 12. ዮሐንስ ጻድቅ 13. #ዮሐንስ_ረድእ 14. ዮሐንስ ማኅቶት 15. #ዮሐንስ_ድንግል 16. ዮሐንስ ንጹሕ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ 18. ዮሐንስ መረግድ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ 20. ዮሐንስ መልአክ 21. #ዮሐንስ_ኪሩብ 22. #ቁጽረ ገጽ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ .....share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡ ›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ግንቦት ፩ 2013 ዓ.ም በ
‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡ ›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት ግንቦት ፩ 2013 ዓ.ም በቀ.ደ.ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉኀን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ በሥርዐተ ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ.ት.ቤት ወንድማችን ዲ/ን ኤልያስ ፀጋ እና፤ የፈጸምሽው የሰ.ት.ቤት እኅታችን ኢየሩሳሌም አየለ ፤ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላቹ፡፡ †<<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበስ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡ †<<ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፈ አጼ ዘርዓያዕቆብ፡፡ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት

/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/
+7
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#ግንቦት 𝟏𝟐፤ ፍልሰተ አጽሙ ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፠ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት የሚለኝ ሁሉ፤ በፍልሰቴ ቀን በገዳሜ ይገኝ እኔም ልጄ እለዋለው ከቅዱስ ሚካኤልና ከልጄ ፊልጶስ ጋር እባርከዋለው።›› /ገድለ ተክለ ሃይማኖት/ ፠ አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠ ግንቦት 12 በደብረ ሊባኖስ ትልቁ በዓል ነው፡፡ ጥንተ መሠረቱም፤ 12ቱ እጨጌዎች ከያሉበት ቦታ እየመጡ 1ድ 1ድ ወር ሙሉ በፈረቃ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ቅዱስ አጽም ተራ ገብተው ያጥኑ ነበር፡፡ ግንቦት 12 ግን ሁሉም ከያሉበት ተሰባስበው በአንድነት ያከብራሉ፡፡ #የጻድቁ_ዋና_ዋና_የታሪክ_ሂደቶች፤ ፠ከአባታቸው ከቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከቅድስት እግዚዕ ኀረያ፤ መጋቢት 24 ቀን ተጸንሰው፤ በታኅሣሥ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም. በእቲሣ ተወለዱ፡፡ ፠በተወለዱ በ3ኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ፡፡ ፠በተወለዱ በ40ኛው በደብረ አጋዓዚት ማርያም ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተበለው ተጠሩ፡፡ ፠እስከ 7 ዓመታቸው ድረስ ከአባታቸው ከጸጋዘአብ ዘንድ እየተማሩ ፠በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከጌርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡ ፠በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ጌርሎስ ዘንድ ቅስናን ተቀበሉ፡፡ ፠በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡ ፠በኅዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን አጠኑ ፠በሐይቅ እስጢፋኖስ 10 ዓመት፥ በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ ፠በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እየተዘዋወቱ አስተምረዋል፤ በአኵሱም ጽዮን፣ በዋልድባና በዙሪያቸው ባሉ ገዳማት እየዞሩ ተሳልመዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመውረድም ተሳልመው ተመልሰዋል፤ ሲመለሱም ብዙ ቅዱሳን አብረዋቸው ተመልሰዋል፡፡ /እነ እጨ ዮሐንስ ዘጎንድ (ዘጠገሮን) ልብ ይሏል፡፡ ፠በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ፡፡ ፠፠፠አባታችን ባረፉ በ54ኛ ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም በአፄ ሰይፈ አርዕድ ዘመን ለ4ኛው እጨጌ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ ፠የደብረ ሊባኖስንም ቦታ የሰጠው ሐኖ (ተክለ ሃይማኖት) /የግራርያ ሰው/፤ ሲሆን ዓፄ ልብነ ድንግል በነገሠ በ8ኛው ዓመት ‹መርሕ› ከምትባል ስፋራ ታቦቱ ከነዋየ ቅድሳቱ ጋር ‹ከምድኃሬ› ተዛውሯል፡፡ ይህንንም ያደረገው እጨጌው አባ ጴጥሮስ ነበር፡፡ #የጻድቁ_ክብረ_በዓላቶቻቸውም፤ #ኅዳር 24፤ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑበት #ታኅሣሥ 24፤ የአባታችን ልደት #ጥር 24፤ የአባታችን ስባረ አጽም #መጋቢት 24፤ የአባታችን ጽንሠት #ግንቦት 12፤ የአባታችን ፍልሰተ አጽም #ነሐሴ 24፤ የአባታችን በዓለ እረፍት ናቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ .....share ፠ ትዌድሶ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤ እስመ በውስቴታ ተገብረ ፍልሰተ ሥጋሁ ወአጽሙ፡፡ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

ሐ. በሥርዓተ ጸሎት፤ ከዓመት እስከ ዓመት ለሚከናወኑ (የዘመናትና የሳምንታትን ጨምሮ) ማንኛውም ሥርዐተ ጸሎት ዋና መሪው የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ነው፡፡ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ፍትሐቱ፣ ጥምቀተ ክርስትናው ሁሉ በዜማው መሪነት የሚከናወኑ አገልግሎቶች ናቸው፡፡ መ. ለቱሪዝም ሀብት (መስህብነት)፤ ክርስቲያናችን በየወሩና በየዓመቱ ከምታከብራቸው በዓላት ላይ ከሚቀርቡት ዝግጅቶች አብዛኛውን ክፍል የሚይዘው በቅዱስ ያሬድ ዜማ የሚቀርበው የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት ነው፡፡ #ማሕሌቱን_ለማሕሌት_አባት_እናቅርብለት:: Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

ስተዋልን ቀስሞ፤ ወደ አጎቱ ተመልሶ ተምሮና ትምህርትን አምላክ ገልጾለት መምህረ መምህራን ሁኖ እንገኘዋለን፤ /እግዚአብሔር አምላክ ለቅዱስ ያሬድ ያንን ኹሉ ጥበብ ቶሎ ያልገለጸለት በቀላሉ ቢያገኘው ኋላ እንዳይታበይ ብሎ ነው፤ የሐዊራ ብስድር እስክንድራን ታሪክ ልብ ይሏል) ፠#መምህር ነው ስንል፤ መናኝ ባሕታዊ ኾኖ እናገኘዋለን፤ /በደብረ ሐዊ ለ22ዓመታት መመኑን ልብ ይሏል/ ፠#መናኝ ነው ስንል የተለያዩ የሃገራችንን ክፍሎች ገዳማትና አድባራት ሲጎበኝ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሲጓዝ እንገኘዋለን፤ /ጣና ቂርቆስ፤ ዙር አባ አቡነ አረጋዊ፣ …. ሌላውንም ልብ ይሏል) ፠#ወደ ገዳማትና አድባራት ይጓዛል ስንል፤ ወደ ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ በደመና ተጭኖ ሂዶ ምሽቱን ወደ በዓቱ ሲመለስ እንገኘዋለን፡፡ ፠#በሃገራችን በዋና ከተማ አኵሱም ተወልዶ ያደገ ነው ስንል፤ ሰው ሊኖርበት በማይችለው፥ በረድ በሚፈላበት፥ የነፋስ እሩምታ በሚያይልበት፥ ቅዝቃዜው አጥንት በሚሰነጥቅበት፥ ውርጩ እጅጉን በሚቀዘቅዝበት፥ ደመና በሚፈስስበት በራስ ደጀን ተራራ አጠገብ በደብረ ሐዊ መንኖ እናገኘዋለን፡፡ ፠#ከሰዎች ጋር አብሮ ኑሯል ስንል፤ ከሰው የማይቀርቡና በዐለማችን ላይ ብርቅዬ ኾነው በሃገራችን የሚገኙ ከሃገራችን ኢትዮጵያም በሰሜን ተራሮች በአብዛኛው ከሚገኙት ዋልያ ጋር አብሮ ሲኖር፤ ዋልያዎችንም እንደ መጓጓዣና እንደ መጫኛ ሲያገለግሉት እንገኛለን፡፡ ፠#በሙራደ ቃል የመላእክት ዜማ ተገልጾለት ተማረ ስንል፤ የግእዝ ቋንቋ ምሁርና ጠበብት ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ለተሰዓቱ ቅዱሳን መምህር መሆኑን ልብ ይሏል) ፠#የዜማ ጀማሪ አባት ነው ስንል ባለቅኔ ኾኖ እንገኘዋለን (ሕንፄሃ ወሡራሬሃ …. የሚለው ቅኔውን ልብ ይሏል)፤ ፠#ባለቅኔ ነው ስንል መተርጕም ኾኖ እንገኘዋለን፤ (ድጓው የብሉይና የሐዲስ ትርጓሜ መሆኑን ልብ ይሏል) ፠#መተርጕም ነው ስንል ባለታሪክ፥ የታሪክ ምሁር ኹኖ እናገኘዋለን፤ ፠#የታሪክ ምሁር ነው ስንል፤ የመርሐ አዝማን ሊቅ ኹኖ እናገኘዋለን፤ (ዓመቱን በሚገርም ሁኔታ ከወቅታቱ ጋራ አገናዝቦ መሠየሙን ልብ ይሏል) ፠#የመርሐ አዝማን ሊቅ ነው ስንል ቅዱስ ኾኖ እንገኘዋለን፤ የቅዱሳንም ጓደኛ ኹኖ እንገኘዋለን፡፡ /የአቡነ አረጋዊ፣ የአጼ ገብረ መስቀልን ታሪክ ልብ ይሏል፡፡/ ፠#ነቢይ ነው ሰንል ሐዋርያ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ (ስለ ዳግም ምጽአት፣ ስለ መንግሥተ ሰማያትና …. ሌሎችንም ልብ ይሏል) ፠#ሐዋርያ ነው ስንል ሰማዕት ኹኖ እናገኘዋለን፡፡ (እግሩን በጦር መወጋቱን ልብ ይሏል)፤ ሌላም ሌላም …. ፠#በአጠቃላይ ምድራዊ ነው ስንል ሰማያዊ፤ ሰማያዊ ነው ስንል ምድራዊ (ብእሲ ሰማያዊ ወመልአክ ምድራዊ) ሁኖ እናገኘዋለን፡፡ #ዜማውን በግዕዝ ዕዝል አራራይ የዜማ ስልት የደረሰ፤ #በዓለም ደረጃ የዜማ ምልክቶች ባልታወቁበት ጊዜ ዜማዎቹን በምልክት የቀመረ፤ #የዜማ ሥርዓትን በመንደፍ የዓመቱን ቀለም ያዘጋጀ፤ #ዜማውን በ4ት ዘመናት ከፋፍሎ፤ ዘመናቱን በንዑሳን ዘመናት ከፋፍሎ ለወራቱና ለሰሙኑ ለእለቱ የሚገባውን ቀምሮ የደረሰ፤ #እንኳን በእርሱ ዘመን ዛሬ እንኳን ብዙ ነገሮች ተሰባስበዋል በተባለበት ዘመን ሊሠራ አይደለም ሊታሠብ በማይችሉ መልኩ መጽሕፍትን እንደ ንብ እየቀሰመ፤ እንደ ወይን እየጨመቀ፤ እንደ አረቂ እያጣራ፤ እየተረጐመ ላሰበው ድርሠት ያዋለ፤ … ስለ ቅዱሱ ምኑን ተናግረን እንጨርሰዋለን፡፡ … ##.. ይኼማ ኢትዮጵያዊ ሊኾን አይችልም ብለው ብዙ የውጭ ሃገራት ወደ ራሳቸው ለመውሰድ የሚዳዳቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ #የቅዱስ_ያሬድ_የዜማው_ይዘት_፤ #የዜማው_ጠባያት_፤ #ከሌሎች_ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይና_ #የዜማው_ጥቅም #ሀ_የቅዱስ_ያሬድ_የዜማው_ይዘት ፠ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ያዘጋጀው ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንት መጻሕፍት እየመረጠ ለምስጋናና ለጸሎት እንዲኾኑ አድርጎ ነው፡፡ ፠ዜማው ምስጢሩ የማይጠገብ፥ቃሉ የሚያረካ፥ አነጋገሩ የተሳካ፥ ጣዕመ ቃሉና ኀይለ ቃሉ ደስ የሚያሰኝ፥ ልብን የሚነካ ነው፡፡ ፠በይዘቱም የሥነ ፍጥረት ውበትን በማድነቅና የሥነ ፍጥረት አስገኝ የኾነውን እግዚአብሔርን በማመስገን ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ፠በአጠቃላይ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ጌታ ለሰው ልጆች ሲል በዚህ ዓለም የፈጸመውን የማዳን ሥራ ሁሉ ገልጦ የሚያስረዳ ነው፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን፣ የቅዱሳን መላእክትን፣ የነቢያትን፣ የሐዋርያትን፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን ክብርና ቅድስና በማውሳት በስማቸው መማፀንና መጸለይ የሚያስገኘውን ጥቅም የሚያስረዳ ታላቅ ዜማዊ ሀብት ነው፡፡ ፠ከእርሱ በፊት የነበሩና በእርሱ ዘመን የተጻፉ የቅዱሳን ገድላትና ድርሳናትን እንዲሁም የበዓላትን ጥንታዊ አመሠራረት ውስጠ ምሥጢር በማስረዳት በዜማ ድርሰቱ አካቷል፡፡ ፠ምስጋናውንም ለአራቱ ክፍላተ ዘመን ለክረምት፣ ለመፀው (ለጥቢ)፣ ለሐጋይ (ለበጋ)፣ ለጸደይ (ለበልግ) እንዲኾን አዘጋጅቶታል፡፡ #ለ_የዜማው_ጠባያት ፨የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሰማያዊ በመኾኑ ኅሊናን የመመሠጥ፣ ሥጋዊ ደስታንና ኀጢአትን ከማሰብ የመጠበቅ፣ ሰማያዊውን ድንቅ የምስጋና ምስጢር የማሳወቅ ኀይል አለው፡፡ ፨ከእግዚአብሔር የተገኘ ስጦታም በመኾኑ ብልየት (እርጅና)፣ ውላጤ (መለወጥ) የማይታይበት ዘወትር ሕያው የኾነ ብቸኛ ዜማ ነው፡፡ ፨የመንፈስ ቅዱስ ስጦታም በመኾኑ ዘወትር አዲስና የማያልቅ ጥልቅ ምንጭ ያለው ሕይወትን የሚያለመልም ነው፡፡ ፨ዜማውም ሰማያዊና መንፈሳዊ፣ ከእግዚአብሔር የተገኘ ለመኾኑ ማስረጃ የሚኾነን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውጪ ያሉ ሰዎች ዜማውን ለተለያየ ዐላማ ይመኙታል፤ ነገር ግን ለመያዝም ኾነ ለመወሰን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም በምድራዊ ጥበብና ፍልስፍና የሚያዝ የሚወሰን ሳይኾን ታላቅ መሥዋዕትነትን የሚጠይቅ፣ ሌት ተቀን ልቡናን ለሥላሴ ሰጥተው ከእግዚአብሔር የሚያገኙት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሚያጸኑት፣ የሚማሩትና የሚያዜሙት እንጂ በገንዘብ የማይገዛ ታላቅ ጸጋ መኾኑ ነው፡፡ #ሐ.#የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ከሌሎች _ዓለማዊ_ዜማዎች_የሚለይበት_ጠባይ፤ ፠ዜማው አሳብን የሚገዛ፣ ከሥጋ ይልቅ በመንፈስ መመላለስን የሚያስተምር በመኾኑ፤ ፠ በአቀራረቡም የተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ያለው በመኾኑ፤ ፠ ዜማው በአዝማናት ተለይቶ በወቅት ተከፋፍሎ የሚዜም መኾኑ፤ ፠ ማንኛውም ሰው ከተወሰነ የዜማ ስልትና ቀመር ውጪ በራሱ ፍላጎት የድምፅ ቅላጼውን ለማሳመር ስለፈለገ የሚያሻሽለው ወይም የሚለውጠው አለመኾኑ፤ ፠ ዜማው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌና ምሥጢር የተሞላ መኾኑና ፠ የዜማው ምልክቶችና ዐይነቶች ጥልቅ ምሳሌና ምስጢር ያላቸው መኾናቸው ነው፡፡ #መ_የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_ጥቅም ሀ. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በመጠበቅ፤ በየትኛውም አካባቢ የምትኖር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት መዝሙር፣ አንድ ዓይነት ቅዳሴ፣ አንድ ዓይነት ማኅሌት፣ አንድ ዐይነት ሥርዐት በአንድ ዓይነት ጊዜ በአንድ ቀን ማቅረብና መፈጸም እንድትችል አስችሏታል፡፡ ለ. በነገረ መለኮት ትምህርት፤ ሊቁ የትርጓሜ መምህር ስለሆነ ከብዙ መጻሕፍት ስለሚጠቅስና የሃይማኖት ትምህርቱትንም በዜማ አቀነባብሮ መድረሱ በጣም ተወዳጅ ትምህርት እንዲሆን አድርጎታል፡፡