Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 381 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 584,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 199 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 381 名订阅者。
根据 03 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 21,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 21.13%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.50% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 250 次浏览,首日通常累积 1 462 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 16。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 04 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 381
订阅者
-724 小时
+117 天
+2130 天
帖子存档
#መፃጕዕ፤ አራተኛው ሳምንት
አራተኛው ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ በመፃጕዕ የተሰየመው የእርሱ ስህተት ለእኛ ትምህርት፥ ተግሳጽ እንዲሆነን እንጂ፤ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው ጌታችን ሕሙማን መፈወሱን፣ ሙት ማስነሳቱንና ስለ ረቂቁ የነፍስ ደዌ ስለ ኀጢአትና ስለ ድኅነታችን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-37፣ ማር. 7፥13-37፣ ሉቃ. 17፥1-9፣ ዮሐ. 5፥1-18
በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡-
፨ #በሽተኛ፤ የዕለት ሕመም ወይም እስከ አንድ ዓመት የታመመ ሰው፡፡
፨ #ድውይ፤ እስከ አምስት ዓመት ሕመሙ የቆየበት፡፡
፨ #መፃጕዕ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት፤ ሲሆን ድውይ፥ በሕመም የሚማቅቅ፥ የዐልጋ ቊራኛ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ #መፃጕዕ የተባለው ስለሕመሙ #38_ዓመታት_መጽናት_እንጂ ስሙ አይደለም፡፡
በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ትርጕሙ /የምሕረት ቦታ/፤ በግእዙ ቀላየ አባግዕ (የበጎች መዋኛ) በተባለች ምጥምቃት ዘጵሩጳጥቄ በምትባል የጠበል መጠመቂያ ኩሬ ዳር የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፥ እውሮች፥ አንካሶች፥ ልምሾች፥ ሰውነታቸው የሰለለ የደረቀና ያበጠ ብዙ ድውያን ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የምሕረት ፈውስ ይዞ በሳምንት አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባርኮ ሲሄድ ቀድሞ የገባው በሽተኛ ይፈወስ ነበር፡፡
ተስፋ ሳይቈርጥ ለ38 ዓመታት ድኅነትን እየጠበቀ በሕመሙም እተሰቃየ በዚያ የተኛ አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን ይህን ሁሉ ዓመት እንደተሰቃየ አውቆ ድኅነት ሊሰጠው ወዶ መጣ፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡
መጠየቁ ፍጹም የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ሲያጠይቅ ነው፡፡ በተጨማሪም በዕለተ ዐርብ ‹‹ራሱ አዳነኝ እንጂ መቼ አድነኝ አልኩት!›› ብሎ ለመክሰስ ምክንያት እንዳያገኝ ጠየቀው፡፡
‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም›› አለው፡፡ ‹‹እንዲህ ያለው የ30 ዓመት ጎልማሳ ነውና አንስቶ ይጨምረኛል›› ወይም አምስት ገበያ የሚያህል ሕዝብ ይከተለው ነበርና ‹‹ከእነርሱ መካከል አዞልኝ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል›› ብሎ ነው እንጂ እንዲሁ ይፈውሰኛል ብሎ አልነበረም፡፡ ጌታ ግን ለመዳን መውደዱን ተመልክቶ ‹‹ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘው ፍጹም ድኅነት ነውና ወዲያው ሰውየው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሔደ፡፡ ያን ሰውም ጌታችን በምኵራብ አገኘውና እነሆ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል እወቅ አለው፡፡
አልጋውንም ተሸክመህ ሂድ ያለው 38 ዓመት የተሸከመችው ጠንካራና የብረት አልጋ ስለተሸከመ ፍጹም መዳኑ እንዲታወቅ ነው፡፡ መጻጕዕ የተፈወሰው በእለተ ቀዳሚት ስለነበረ ፤ በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት፣ ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር፡፡
በሽተኛው የተደረገለትን ተአምር ረስቶ በዕለተ ዐርብ ጌታን ከሰሰው፤ በጥፊም መታው ወዲያው እጁ ሰለለ፡፡
#ቅዱስ_ያሬድም ጌታችን ሰንበትን ለዕረፈት ስለፈጠራት፤ ሕሙማንን በመፈወስ (#የመቶ አለቃውን ልጅ በመፈወስ ማቴ. 8፥1-15፤ #የዕውራንን ዓይኖች በማብራት ማቴ. 20፥24-30፤ ዮሐ. 9፤ #ሽባ የነበረውን በመፈወስ) #በዕለተ_ሰንበት_ከበሽታቸው_እንዲያርፉ_አደረገ፡፡
በእኛ በሰው ልጆች ላይ በሽታ በተለያየ ምክንያት ይመጣል፡፡
† በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ፡፡ ዘኍ. 21፥4-9
† የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ ዮሐ. 9፥13
† ሰዎች ከእግዚአብሔር ዋጋ እንዲያገኙበት ከዲቢያሎስ የሚመጣ የፈተና በሽታ አለ እንደ ጻድቁ ኢዮብ፡፡ መጽ.ኢዮብ
† ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ እንዳይታበዩ ማሳወቂያ የሚሆን በሽታ አለ፤ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ራስ ምታት፡፡
† የበደለውን የሚቀጣበት በሽታ አለ፤ እንደ ሳዖል አጋንንት አድሮበት ይሰቃይ ነበር፣ የመጻጕዕ እጁ የሰለለው በሁለተኛ በደሉ ነው፡፡
† ያልታመመው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን፥ የታመመው ምሕረትን እንዲለምን የሚመጣ በሽታ አለ፡፡
#share
Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
የሰንበት ት/ት ቤታችን የ2 ዓመታት ጥያቄ ዛሬም #_በብጹዕ_አቡነ_መልከጸዴቅ_የአዲስ_አበባና_የጉራጌ_አህጉረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ የሰ/ት/ቤቱ ጥያቄ #_የመጨረሻ_ውሳኔ_አገኘ
#_ውሳኔው የመጣው በ10/07/2013 ዓ.ም ቢሆንም አፈጻጸሙን ሰላማዊ በሆነ መልኩ በሽምግልና እንዲያልቅ ስንጥር እስከዛሬ ድረስ ውሳኔውን ሳናሳውቃችሁ ቆይተናል
******************************
በ29/06/2013 ዓ.ም ሰ/ት/ቤቱ ፣የአጥቢያው ምዕመናን ፣ የአጥቢያ ሰንበት ት/ት ቤቶች ፣ የአካባቢው ወጣቶች በጋራ በመሆን ወደ ሐገረ ስብከት በመሄድ ጥያቄያችንን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ብጹዕነታቸውም በቃል ማብራሪያ የቀረቡትን ሃሳቦች በተገቢው መንገድ ከተመለከቱና ከሰሙ በኋላ የማያዳግም ውሳኔ ለመስጠት በአካልም ሄጄ ማየት አለብኝ ብለው ደብራችን ላይ በመገኘት የደብሩ አስተዳደርና ማኅበረ ካህናት የሚሉትን አማራጮች እንዲሁም በሰንበት ት/ት ቤታችን በኩል የቀረቡ አማራጮችንም በአካል ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ በ10/07/13 ዓ.ም በደብዳቤ #ቁጥር 3008/13/2013 ለደብራችን በተጻፈ ደብዳቤ ሰንበት ት/ት ቤቱ #_በመደበኛነት_የመዋዕለ_ሕጻናቱ_ግቢ_እንዲሰጠው ፣ በመዋዕለ ሕጻናት ውስጥ በመማር ላይ የሚገኙት ሕጻናት እንዳይበተኑ ደብሩ ቦታ አፈላልጎ የመማርያ ቦታ እንዲያመቻችላቸው ተወስኗል፡፡
#_ብጹዕ_አባታችን
የብጹዕነትዎ ቡራኬ ይደርብንና በየካቲት 29/2013 ዓ.ም ፡- ከ 2ዓመታት በላይ በሰ/ት/ቤቱና በደብሩ አስተዳደር መካከል የቆየውን አለመግባባት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አመራር ና ውሳኔ እንዲሰጡን ለመጠየቅ ወደ ሃገረ ስብከትዎ ስንመጣ ምንም እንኳ ለአቤቱታችን እንግዳ ቢሆኑም የሚመሩት ሃገረ ስብከት የቤተክርስቲያኒቱን ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ባሳየ መልኩ ከሁለታችንም ወገን ችግሩን በዝርዝር ከመስማት ባለፈ ሳይውሉ ሳያድሩ ደብራችን ድረስ ተገኝተው ሁሉንም በአይንዎ ተመልክተው ቆራጥ አመራር እና ፈጣን ውሳኔ ስለሰጡን ለእርስዎ ለብጹዕ አባታችን ያለን ክብርና አድናቆት ታላቅ ነው፡፡ በሁሉም የቤተክርስቲያናችን ችግሮች ይህ አይነት ቆራጥ አመራርና ውሳኔ ያስፈልጋልና ከዚሁ አንጻር የወሰዱትን እርምጃ የሃገረ ስብከቱን ገጽታ በእጅጉ ከፍ አድርጎ ያሳየ ነውና #_ምስጋናችን_ይድረሶት፡፡ እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜና ሰፊ ጤና ይስጥልን፡፡
የሃገረ ስብከታችን ዋና ስራ አስኪያጅ #_መምህር_አካለወልድ_ተሰማ እንዲሁም ዋና ጸሐፊ #_መ/ር_ታዲዮስ እና የሃገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጅያ ዋና ክፍል ሃላፊ #_መ/ር_ዳዊት ወደ ሀገረ ስብከቱ በአመራርነት ከመጣችሁበት ጊዜ ጀምሮ በእኛና በደብሩ መካከል ይቀርቡ የነበሩትን ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ሳትሰለቹ በመስማት ውሳኔ ሰጥታችኋል፡፡ በተጨማሪም ያሉትን ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ትልቁን ድርሻ ተወጥታችኋልና ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡
#_የአ.አ_ሰ/ት/ቤቶች_አንድነት_የስራ_አመራር_አባላት ምንም እንኳ ኃፊነታችሁ ቢሆንም ከእኛም በላይ ጉዳዩን የራሳችሁ አድርጋችሁ ሙሉ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ይህ ውሳኔ እንዲገኝ ያበረከታችሁት አስተዋጽኦ ለታሪክ የሚቀመጥ ነውና #_እናመሰግናችኋለን፡፡
በደብራችን የጠፋው ሰላም እንዲመለስ ተቆርቁራችሁ ልትሸመግሉን የመጣችሁ አባቶችና ወንድሞች ረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ በሽማግሌነት ያኑራችሁ፡፡የአጥቢያችን ወጣቶችና ምዕመናን እንዲሁም በቅርብ የምትገኙ ሰንበት ት/ት ቤቶች በተለይ ( ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ #ፍቁረ_እግዚእ ሰ/ት/ቤት ፣ #ገነተ_ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት ፣ #ምስካየ_ኅዙናን ተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት ፣ ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል ሰ/ት/ቤት ፣ ደብረሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ዕፀ ጳጦስ ሰ/ት/ቤት) የሰ/ት/ቤቱ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው ያገባናል ይመለከተናል ብላችሁ ለሰጣችሁን ድጋፍ እና ለተወጣችሁት ኃላፊነት ሁሉ ከልብ እናመስግናለን፡፡
#_ውድ_የደብራችን_አባቶች በተገኘው ውሳኔ አሸናፊና ተሸናፊ የለም ይልቁንም ቋሚ የህጻናትና ወጣቶች መማርያ ቦታ ውሳኔ ተሰጠበት እንጂ ፡፡ ክርክራችን ደግሞ የሰ/ት/ቤቱ የመማርያ ቦታ ከዚህ ይልቅ ያኛው ይሻላል የሚል የአባትና የልጅ ነው፡፡ ብጹዕነታቸው ደግሞ ይህንን ክርክር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመወሰን የሚመለከተውን ሁሉ አናግረው በአካልም ቦታው ድረስ ተገኝተው የመጨረሻ ፠ ግራ ቀኙ በደንብ የታየበት ፤ ሁሉንም የማይጎዳ ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ውሳኔ ለ3ኛ ጊዜ የመጣ ዉሳኔ ነው ፡፡ ስለሆነም ከዚህ በኃላ በመካከላችን የተፈጠረውን አለመግባባት በፍጹም እርቅ አስወግደን ውሳኔውን በጋራ ተረባርበን አስፈጽመን ደብራችንን ወደ ቀደመ ሰላሙ እንድንመልሰው ሰ/ት/ቤቱ ዛሬም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ስለ ሁሉም ነገር ክብር #_ለመድኃኔዓለም!
#share
Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
#የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል
#በየረር ተራራ እየነደደ ነው
በየረር ተራራ የረር ቅዱስ ቴዎድሮስ … የየረር ሦላሴና የየረር በአታለማርያም ገዳም ደን እየነደደ ነው ፡፡ እሣቱ ሰው ሰራሽ መሆኑ ከምስሉ መረዳት ይቻላል፡፡
ቤተ ክርስቲያንን እስከ መሠረቷ ድረስ ፈጽሞ አፍርሱ የሚሉትን ጎስቋሎችን የሚበቀላቸው አምላካችን ብፁዕ ነው፡፡ /መዝ. 136/
xበጀውኃ ከተማ የሚገኝ የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እየነደደ ነው
ሰሜን ሸዋ፤ከሸዋ ሮቢት አለፍ ብሎ #በጀውኃ ከተማ የሚገኝ #የሊቀ_ሰማዕት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ቤተ_ክርስቲያን_ተቃጥላል::
ካህናቱ ታርደዋል ፣ ምእመናንም ታርደዋል ፣ የክርስቲያን መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል።
#መዝሙረ ዳዊት 73፤ ‹‹#መቅደስህንም_በእሳት_አቃጠሉ፤ … #አቤቱ_ተነስ_በቀሌንም_ተበቀል፡፡››
ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንጸልይ
‹‹ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ!፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: ማቴ. 10፥28::
።
#share
Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
