Tesfa
Kanalga Telegram’da o‘tish
6 629
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+27 kun
-3230 kun
Postlar arxiv
6 629
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ብቻህን የምትሆንበት ቦታ ያስቀምጥሃል፤ የሚያስፈልግህ ነገር ሌላ ሳይሆን እርሱ ራሱ ብቻ እንደሆነ እስክትረዳ ድረስ ነው።
በዙሪያህ ካሉ ሰዎች፣ ከሁኔታዎች፣ ከዓለም ጫጫታ፣ ርቀህ ወደ ምድረበዳ በሚወስድህ ወቅት እግዚአብሔር ከልቡ ለልብህ ሊያናግርህና ፍቅሩን በጥልቀት ሊያሳይህ ነው። ያ የብቸኝነት ወቅት የተተውክበት ሳይሆን፣ ከእርሱ ጋር ይበልጥ ህብረት የምታደርግበት ጊዜ ነው። በምድረበዳህ እግዚአብሔር አለ!። እርሱ ያፅናናሀል፣ ይመራሀል ልብህን በፍቅሩ ጠል ያረሰርስሀል።
ስለዚህ በምድረ በዳህ ተስፋ አትቁረጥ፤ እግዚአብሔር ከልቡ ለልብህን በልዩ መንገድ የሚያናግርበት ስፍራ ነውና።
ሆሴዕ 2:14- ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
ምናልባት ዛሬ ማንም የማይረዳህ የሚመስልበት፣ በልብህ ያለውን ስቃይ በቃላት መግለጽ የሚያቅትህና እና ማረፍ የሚያስፈልግህ ጊዜ ላይ ትሆን ይሆናል። ነገር ግን በምታልፍበት ጭንቀት ውስጥ ሁሉ፤ እግዚአብሔር ይሰማሃል። ዳዊት በመከራው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ጩኸቱን ሰማ።
ስለዚህ በጭንቀት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጩኽ። ልብህን በፊቱ አፍስስ፤ እርሱ ይሰማሃል። በእርሱ ተስፋ አድርግ፤ በችግር መካከልም እንኳን እምነትህን በእርሱ ላይ አጽና።
2 ሳሙኤል 22፥7- በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
ችግሮች ሲደራረቡብህ፣ የምታደርገው ጠፍቶህ ግራ ስትጋባ፣ በዙሪያዬህ ብዙ ጫና ሲመጣብህ፣ ብዙ አቅም ያላቸው ያግዙኛል ምትላቸው ሰዎች ሲከዱህ፣ ብዙ ካለህበት ውጥንቅጥ ሊያወጣህ የሚችል ሁኔታን ልትፈልግ ትችላለህ ነገር ግን እውነተኛና አስተማማኝ ረዳት የሚመጣው ከእግዚያብሔር ዘንድ ብቻ ነው:: ረድኤትህ ከራስህ አቅም አይደለም፣ ከሰዎችም አይደለም እንዲሁም ከሁኔታ አይደለም። ረድኤትህ ተራሮችን ፈጥሮ፣ ሰማይን የዘረጋ፣ ምድርን ካጸናው ከእርሱ ከእግዚያብሔር ዘንድ ነው። ስለዚህ አይኖችህን ትልቅ ከምትላቸው ነገሮች ላይ አንስተህ እግዚያብሔር ላይ አድርግ እርሱ ብቸኛ አስተማማኝ ረዴትህ ነው :: ለእርሱ የሚከብድ ምንም ነገር የለም። ዛሬ ይሄ ጌታ ህይወትህ እንዲመራው ለመፍቀድ ዝግጁ ነህ?
መዝሙር 121:1-2 ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
ጸጋ ማለት በራስህ ጥረት ልታገኘው የማትችለው፣ የማይገባህ እንኳ ቢሆንም እግዚአብሔር ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ በነፃ የሚሰጥህ ስጦታ ነው። እግዚአብሔር በሕይወትህ የሚያጋጥሙህን ፈተናዎችና ችግሮች በራስህ ኃይል ብቻ እንድትወጣቸው አልተወህም። በሚያስፈልግህ ጊዜ የሚረዳህን ጸጋ ሰጥቶሀል።
ከውድቀቶችህ፣ ከድክመቶችህና ከጥፋተኝነት ስሜትህ ጋር ወደ እርሱ ብትመጣ፣ በምሕረቱ እንድትቀበልና ይቅርታን እንድታገኝ በኢየሱስ በኩል መንገድ ከፍቶልሃል። ብትወድቅ ወይም ብትሰናከል፣ ከእርሱ ልትሸሽ አይገባም።
ዛሬ የምታልፍበት ሁኔታ ምንም ያህል ከባድ ቢሆን፣ ችግርህን፣ ፍርሃትህን፣ ድካምህን ሁሉ ይዘህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ። በክርስቶስ በኩል ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት የመቅረብ መብት አለህ። እርሱ የምሕረቱን ይቅርታና በድካምህ የሚደግፍህን ጸጋ ይሰጥሃል።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ዕብራውያን 4:16
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ ሃሳቡም ለተጠሩት በህወታቸው የሚያልፈውን ማንኛውንም ነገር ለመልካም መቀየር የሚችል ሃያልና ሉዓላዊ ነው ::እግዚያብሔር ዛሬም ባንተ ሂወት የሚያልፉትን የትኛውንም ነገር ለበጎ ያደርገዋል :: አሁን ያለህበትን መከራ ውጣ ውሯድ እና ተግዳሮቶች ሁሉም ተጠቅልሎ እግዚያብሔር ለመልካም መቀየር የሚችል አምላክ ነው :: እግዚያብሔር ባንተ ሂወት የጀመረውን የራሱን አላማ ሳይቸርስ ስቃይ ውስጥ ጥሎህ አይሸሽም :: ስለዚህ በሙሉ ልብህ በርሱ ተማመን ::
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8:28
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
በሕይወትህ ውስጥ የማታውቀው የወደፊት ሁኔታ፣ የሚያስጨንቁ ችግሮችና የሚያስፈሩ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። ነገር ግን ኢየሱስ በችግሮች መካከል እንኳን ልብህን የሚያረጋጋ ሰላሙን ይሰጥህል።
የዓለም ሰላም ብዙ ጊዜ ሁኔታዎች ሲስተካከሉና የምትፈልገው ነገር ሲሳካ የሚሰማህ እርካታ ነው። የኢየሱስ ሰላም ግን በሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ አይደለም። በማዕበል ውስጥ እንኳን እርሱ ልብህን በሰላሙ ያረጋጋል።
ዮሐንስ 14:27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
በሕይወትህ በጭንቀት፣ በፍርሃት፣ በኃጢአት ወይም በመንፈሳዊ ድካም ውስጥ ነህ? እውነተኛ እረፍትና እፎይታ የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እርሱ የሚሰጥህም እረፍት ከኃጢአትና ከበደል ነፃ የሚያወጣ፣ ከጭንቀትና ከፍርሃት የሚያሳርፍ፣ በልብህ ውስጥ ሰላምና እፎይታ የሚሰጥ እረፍት ነው። በእርሱም የዘላለም ሕይወት አለ።
ማቴዎስ 11:28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
ፍርሃት በሚሰማህ ግዜ አይኖችህን ወደ እግዚአብሔር አንሳ። የሚያስፈራህን ሀሳብ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ጣል።
እግዚአብሔር ከፍርሃትህ ይበልጣል፤ በድካምህ ይረዳሃል፤ ቀኝህን ይይዛል፣ መንገድህንም ይመራሃል፣ ብቻህንም አይተውህም።
አትፍራ! ብቻህንም አትታገል፤ ወደ ሚያሳርፍህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ።
ኢሳይያስ 41:13 እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፡— አትፍራ፥ እረዳሃለሁ፡ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
እግዚአብሔር ፊት ያቀረብከውን ልመና መልሱን ለረጅም ጊዜ እየጠበቅህ ሊሆን ይችላል። ጸሎትህ የዘገየ ሊመስልህ፣ ሁኔታህም እንደማይለወጥ ሊሰማህ ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር ጩኸትህን ይሰማል። እርሱ ወደ አንተ ያዘነብላል፤ ከጥፋት ጉድጓድና ከረግረግ ጭቃ ያወጣሃል፣ እግሮችህንም በጽኑ ዓለት ላይ ያቆማል። ስለዚህ እግዚአብሔርን ጠብቅ። በጊዜው ያወጣሃል፣ አረማመድህንም ያጸናል።
መዝሙር 40:1-2 ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ። ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
በህይወት ጉዞ የሚጠብቅህን ሁሉ አስቀድመህ ማወቅ አትችልም። የሰው ማስተዋል ውስን ነው፤ አንተ የዛሬን ብቻ ታያለህ፣ እግዚአብሔር ግን ረጅሙን የሕይወትህን ጉዞ በሙሉ ያያል።
ስለዚህ ይህን ሳምንት ስትጀምር በራስህ ጥበብ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ተደገፍ። በመንገድህ ሁሉ እርሱን ፈልግ፤ እርሱም መንገድህን ያቀናልሃል።
ምሳሌ 3:5-6በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤
በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
ዓለም ሰው የሚፈልገውን ለማግኘት ማታለልን፣ ተንኮልንና ራስ ወዳድነትን እንደ ጥበብ በምትቆጥርበት ጊዜ፣ በእውነትና በቅንነት መኖር እንደ አለመሳካት ሊታይ ይችላል: አንዳንዶች በማይታወቅ መንገድ ብዙ ነገር ሲያገኙ ታያለህ።ነገር ግን የሰው ስኬት የእግዚአብሔር ልኬት አይደለም። እርሱ የልብን እውነት ያያል። በቅንነት መኖርህ በሰዎች ዘንድ ምንም ዋጋ ባይሰጠውም፣ በእግዚአብሔር ፊት ግን ውድ ነው።አንተ በቅንነት ስትመላለስ ሁሉን ነገር በፍጥነት ላይሆንልህ ይችላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ከመልካም ነገር አያሳጣህም!። ሰው ባያይህም እግዚአብሔር ያይሃል፤ ዋጋህንም ያውቃል። ስለዚህ ቅንነትህን አትተው። በእግዚአብሔር ፊት በእውነት መመላለስን ምረጥ፤ እርሱም ከመልካም ነገር ሁሉ አያጎልህም።
መዝሙር 84:11 እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን፡ ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
በሕይወትህ የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሲበዙ የገንዘብ፣ የጤና፣ የቤተሰብ ወይም ሌላ ጉዳይ ብቻህን አትሸከም። እያንዳንዱን ጭንቀት ወደ ጸሎት አምጣ፤ ፍርሃትህን፣ ልመናህንና የልብህን ሁሉ ለእግዚአብሔር ንገረው።
የትናንት ታማኝነቱ ዛሬም አልተለወጠም። ጌታ ቅርብ ነው፤ ስለዚህ ጭንቀትህን ለእርሱ ስጥና በሰላሙ እረፍ።
ፊልጵስዩስ 4:6 ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
አምላክ መድኃኒትህ ነው። የኃጢአትን ቁስል በራስህ ጥረት ልትፈውሰው አትችልም፤ ነገር ግን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶሃል። መዳንህ በራስህ ጥረት የተገኘ ሳይሆን፣ በክርስቶስ ጸጋ የተሰጠህ ስጦታ ነው።
እርሱ ኃይልህም ነው። በራስህ ኃይል ሁሉን መሸከም አትችልም። ድካም ሲመጣ፣ ፈተና ሲበዛ፣ ተስፋ ማድረግ እንኳን ከባድ ሲሆን፣ እርሱ የሚያበረታህ ኃይል ይሆናል።
እርሱ ዝማሬህም ነው። በሐዘን መካከል፣ በለቅሶ ውስጥ፣ መልሱን ሳታውቅ እንኳን እርሱ ታማኝ እንደሆነ በማመን ማመስገን ነው።
ስለዚህ ችግር ቢኖርም፣ ከችግርህ የሚበልጥ አምላክ እንዳለህ እወቅ። ሕይወት ስትከብድ እርሱ መድኃኒትህ ነው፤ ስትደክም ኃይልህ ነው፤ ስታዝን ዝማሬህ ነው።
ዛሬ የሚያስፈራህ ነገር ቢኖር፣ በችግሩ ላይ ብቻ አትመልከት፤ ወደ ኢየሱስ ተመልከት። እርሱ ከኃጢአት ሊያድንህ፣ ከባርነት ነፃ ሊያወጣህ፣ በድካምህ ኃይል ሊሆንህ እና በሐዘንህ መካከል ዝማሬህ ሊሆንህ ይችላል።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። - ትንቢተ ኢሳይያስ 43:1
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
ዓለም ብዙ መንገዶችን ብታሳይህም፣ እውነተኛ የሕይወት መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው። እርሱ በእውነት በመንገድ ላይ ይመራሃል። ከእርሱ ጋር ያለ የሕይወት መንገድ እውነተኛ ደስታን ይሰጥሀል፤ ከፊቱ ደስታ፣ በቀኙም የዘላለም ፍሥሐ አለ። የዚህ ዓለም ደስታ የሚጠፋ ነው፤ በእግዚአብሔር ያለው ደስታ ግን ዘላለማዊ ነው።
ዛሬ በሳምንቱ መጀመሪያ መንገድህን ለእርሱ አስረክብ፤ እርሱ ወደ እውነተኛ ሕይወት ይመራሀል፤ ደስታም ያጠግብሀል።
የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ። - መዝሙር 16:11
#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
እንኳን ለ2019 በሰላም አደረሳችሁ!
ኢየሱስ፣ የማይጠፋ ተስፋ!
በሕይወትህ ምንም ቢለወጥ፣
ሁኔታዎች ምንም ቢሆኑ፣
ተስፋህ አለ።
ምክንያቱም ተስፋህ በምታየው ነገር ላይ አይደለም፤
ተስፋህ ኢየሱስ ነው።
እርሱ ሞትን አሸንፎ ተነስቷል።
እርሱ ሕያው ነው፤
እርሱ ከአንተ ጋር ነው፤
እርሱም የማይጠፋ ተስፋህ ነው።
አንድ ቀን የምንጠብቀው ተስፋ ይፈጸማል።
ኢየሱስ ይመጣል!
1 ጴጥሮስ 1:3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።
#የማይጠፋ_ተስፋ #tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
መልካም አዲአ አመት!
በእውነት ፍጻሜ አለህና፥ ተስፋህም አይጠፋምና። - ምሳሌ 23:18
#የማይጠፋ_ተስፋ #tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
በዚህ አዲስ አመት ተስፋን የሚናገር ዲጂታል ፖስት ካርድ ለወዳጆ በነጻ ይላኩ ✉️
የሚልኩለትን ሰው ስም አስገብተው ዲጂታል ፖስት ካርድ ለቤተሰብ፥ ለጓደኛ ፥ ለወዳጆ በቀላሉ ይላኩ። ፖስት ካርዱን ለማዘጋጅት እና ለመላክ ይህን ቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ 👉 https://t.me/tesfa_postcard_bot
በሁለት የቋንቋ አማራጭ ያገኛሉ (አማርኛ እና afaan oromo)
Postcard @tesfa_postcard_bot
Follow tesfa on Telegram
#የማይጠፋ_ተስፋ #tesfa #hope
6 629
ክርስቶስ፣ የክብር ተስፋ!
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የገለጠው ታላቅ ምሥጢር ነው።
ክርስቶስ በአንተ ውስጥ ስለሚኖር፣
ተስፋ አለህ!
ከእግዚአብሔር ጋር የዘላለም ሕይወት ተስፋ አለህ!
ዛሬ ያለህበት ሁኔታ ቢከብድም፣
የምታየው ነገር ተስፋ የሚያሳጣ ቢመስልም፣ ተስፋህ በሁኔታህ ላይ አይደለም።
ተስፋህ ክርስቶስ ነው።
እርሱም በአንተ ውስጥ ያለው
የክብር ተስፋ ነው።
ቆላስይስ 1:27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።
#የማይጠፋ_ተስፋ #tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
6 629
በዚህ አዲስ አመት ተስፋን የሚናገር ዲጂታል ፖስት ካርድ ለወዳጆ በነጻ ይላኩ ✉️
የሚልኩለትን ሰው ስም አስገብተው ዲጂታል ፖስት ካርድ ለቤተሰብ፥ ለጓደኛ ፥ ለወዳጆ በቀላሉ ይላኩ። ፖስት ካርዱን ለማዘጋጅት እና ለመላክ ይህን ቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ 👉 https://t.me/tesfa_postcard_bot
በሁለት የቋንቋ አማራጭ ያገኛሉ (አማርኛ እና afaan oromo)
Postcard @tesfa_postcard_bot
Follow tesfa on Telegram
#የማይጠፋ_ተስፋ #tesfa #hope
6 629
ሕያው ተስፋ!
ምናልባት ዛሬ በሕይወትህ ብዙ ነገሮች እየተለወጡ ይሆናል።
የምታየው ሁኔታም ተስፋ የሚያሳጣ ሊመስልህ ይችላል። ነገር ግን ተስፋህ በምታየው ነገር ላይ አይደለም።
ተስፋህ በሕያው በሆነው ክርስቶስ ላይ ነው።
ኢየሱስ ከሙታን በመነሳቱ፣
ሕያው ተስፋ ተሰጥቶናል።
እግዚአብሔር ለአንተ ያዘጋጀው ርስት የማይጠፋ፣ የማይበላሽና የማያልፍ ነው።
ይህንን ያዘጋጀልህን ርስት ለመጠበቅ፣ አንተንም በእምነት ለመጠበቅ ደግሞ የእግዚአብሔር ኃይል አለ።
ስለዚህ ዛሬ ሁኔታው ቢከብድም፣
ብትደክምም፣ መልሱ ቢዘገይም፣ ተስፋህን አትልቀቅ።
በሁኔታህ ላይ ሳይሆን፣
በሕያው በሆነው ክርስቶስ ላይ ታመን።
1 ጴጥሮስ 1:3-5 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤
#የማይጠፋ_ተስፋ #tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
