uz
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Kanalga Telegram’da o‘tish

📈 Telegram kanali የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU analitikasi

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 14 454 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 6 042-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 328-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 14 454 obunachiga ega bo‘ldi.

28 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 550 ga, so‘nggi 24 soatda esa 26 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 37.47% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.23% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 5 412 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 477 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 33 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Kanal uchun tavsif kiritilmagan.

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 29 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

14 454
Obunachilar
+2624 soatlar
+1347 kunlar
+55030 kunlar
Postlar arxiv
የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነገረ ሰብእ (አንትሮፖሎጂ) አንደኛው የጥናት ዘርፍ ነው። ይህ የጥናት ዘርፍ ስለ ሰው አፈጣጠርና ክብር የሚናገር ነ
የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነገረ ሰብእ (አንትሮፖሎጂ) አንደኛው የጥናት ዘርፍ ነው። ይህ የጥናት ዘርፍ ስለ ሰው አፈጣጠርና ክብር የሚናገር ነው። ስለ ፍጥረት አመጣጥ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው መጽሐፍ ኦሪት ዘፍጥረት ሰው በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠረ ክቡር ፍጡር መሆኑን ይነግረናል። ሊቀ ነቢያት ሙሴ ስለ አፈጣጠሩ ሲተርክልንም “እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፡ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ. ፩፡፳፮-፳፯) ይለናል። የሚወዱትን እንግዳ ሁሉን አዘጋጅቶ እንደሚጠሩት እግዚአብሔርም ለሰው የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድሞ ካዘጋጀ በኋላ ሰውን የፍጥረት መደምደሚያና መካተቻ አድርጎ ፈጥሮታል። እግዚአብሔር ሌሎች ፍጥረታትን በኀልዮ (በማሰብ) እና በነቢብ (በመናገር) ሲፈጥራቸው ሰውን ግን በእጁ ሠርቶታል። “እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” (ዘፍ. ፪፡፯) የተባለው ለዚህ ነው። ስለሆነም ሰው ክብሩና ልእልናው ከፍ ያለ ነው። ማንበብ ይቀጥሉ... 👇👇👇👇👇👇 https://eotc-gssu.org/a/የነገረ-ሰብእ-ትምህርት-ጉድለት-የወለደው/ የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

በሰንበት ት/ቤቶች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የ ፲፪ኛ ክፍል የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ተካሄደ ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016ዓ.ም ፤ (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በሰንበት ት/ት ቤቶች አንድነት የመጀመሪያ የሆነውና በሙከራ ትግበራ ላይ በነበረው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተማሩና በ2015ዓ.ም 12ኛ ክፍል ደርሰው ምዘናውን የወሰዱ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ። ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በበዓለ ወልድ አዳራሽ በተደረገው በዚህ ጉባኤ የምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ገዳማት መምሪያ ኃላፊ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አብነ ሉቃስ ፤ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ኃላፊ መጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ፤ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ምክትል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ፀጋ ወልደ ትንሳኤ፤ የሀገረ አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ም/ ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ ምስጋናውና የየደብራቱ መምህራን፣ ተመራቂዎችና በርካታ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል። በመርሐ ግብሩ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ኃላፊ መጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ በፀሎት ያስከፈቱ ሲሆን ወቅቱን የተመለከቱ ዪሬዳዊ ዝማሬዎች መነባንብና ወረብ ቀርቧል። የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ምክትል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ፀጋ እንዲሁም በሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክትና ቀጣይ የሥርዓተ ትምህርቱ አቅጣጫ ላይ ንግግር አድርገዋል። በመርሐ ግብሩ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት የመጀመርያ የ12ኛ ክፍል ምርቃት መደረጉ ፍሬ የማፍራቱ ማሳያ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባና በሌሎች አህጉረ ስብከቶች የትግበራ ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል። በመቀጠልም "ይህንን መልካም ሥራ እንድንሰራ መንፈስ ቅዱስ ጠራን" የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት መሠረት በማድረግ ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ ቃለ እግዚአብሔርን አስተምረዋል። በመጨረሻም ለተመራቂ ተማሪዎች ምስክር ወረቀት ያበረከቱት የምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ገዳማት መምሪያ ኃላፊ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፅዕ አቡነ ሉቃስ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን በመልዕክታቸው " የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ሆናቹ ክርስቶስን እንድትጠብቁ፣ ወደ ዓለም ስትሔዱ በተኩላው እንዳትወሰዱ ተጠንቀቁ" ሲሉ አባታዊ መልዕክት በማስተላለፍ በፀሎት የመርሐ ግብሩ ፍፃሜ ሆኗል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/EOTCNSSU ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Twitter👇 https://twitter.com/tibeb_feleg ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! "ልጅን በሚኼድበት መን
+3
🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!  "ልጅን በሚኼድበት መንገድ ምራው፤ በሸመገለም ጊዜ ከርሱ ፈቀቅ አይልም።" {ምሳሌ 22፥6}     በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ በ2015 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትምህርታቸውን  ተከታትለው  ያጠናቀቁ እና በሀገረ ስብከት በብሔራዊ ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ያለፉ  #የ4ኛ , #የ6ኛ እና #የ10ኛ ክፍል #ከ4500 በላይ ተማሪዎች የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር የዝግጅት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ታዳሚዎቻችንን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን!!! #ጥቅምት_4_2016_ዓ_ም  #ከቀኑ_7_00_ሰዓት_ጀምሮ  #በደብረ_ምጥማቅ_ሰዓሊተ_ምህረት_ቅድስት_ማርያም_እና_ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_ካቴድራል        #በዕለቱ_ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል!!! #ኑ_ተማሪዎቻችንን_በጋራ_እንመርቅ #ሰዓት_ይከበር #መቅረት_ያስቆጫል 💢የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት💢 ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔

"ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥ ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።" መዝ 102(103) ፡ 16 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩ
"ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥ ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።" መዝ 102(103) ፡ 16 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu