የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 442 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 042 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 328 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 442 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 28 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 550، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 26، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 37.47%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.23% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 5 412 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 477 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 29 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
14 442
المشتركون
+2624 ساعات
+1347 أيام
+55030 أيام
أرشيف المشاركات
የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ
በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነገረ ሰብእ (አንትሮፖሎጂ) አንደኛው የጥናት ዘርፍ ነው። ይህ የጥናት ዘርፍ ስለ ሰው አፈጣጠርና ክብር የሚናገር ነው። ስለ ፍጥረት አመጣጥ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው መጽሐፍ ኦሪት ዘፍጥረት ሰው በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ የተፈጠረ ክቡር ፍጡር መሆኑን ይነግረናል። ሊቀ ነቢያት ሙሴ ስለ አፈጣጠሩ ሲተርክልንም “እግዚአብሔርም አለ፤ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ፡ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ. ፩፡፳፮-፳፯) ይለናል። የሚወዱትን እንግዳ ሁሉን አዘጋጅቶ እንደሚጠሩት እግዚአብሔርም ለሰው የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድሞ ካዘጋጀ በኋላ ሰውን የፍጥረት መደምደሚያና መካተቻ አድርጎ ፈጥሮታል። እግዚአብሔር ሌሎች ፍጥረታትን በኀልዮ (በማሰብ) እና በነቢብ (በመናገር) ሲፈጥራቸው ሰውን ግን በእጁ ሠርቶታል። “እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” (ዘፍ. ፪፡፯) የተባለው ለዚህ ነው። ስለሆነም ሰው ክብሩና ልእልናው ከፍ ያለ ነው።
ማንበብ ይቀጥሉ...
👇👇👇👇👇👇
https://eotc-gssu.org/a/የነገረ-ሰብእ-ትምህርት-ጉድለት-የወለደው/
የነገረ ሰብእ ትምህርት ጉድለት የወለደው አገራዊ ቀውስ
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
በሰንበት ት/ቤቶች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የ ፲፪ኛ ክፍል የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ተካሄደ
ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016ዓ.ም ፤ (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በሰንበት ት/ት ቤቶች አንድነት የመጀመሪያ የሆነውና በሙከራ ትግበራ ላይ በነበረው ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተማሩና በ2015ዓ.ም 12ኛ ክፍል ደርሰው ምዘናውን የወሰዱ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የምርቃት መርሐ ግብር ተከናወነ።
ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በበዓለ ወልድ አዳራሽ በተደረገው በዚህ ጉባኤ የምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ገዳማት መምሪያ ኃላፊ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አብነ ሉቃስ ፤ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ኃላፊ መጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ፤ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ምክትል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ፀጋ ወልደ ትንሳኤ፤ የሀገረ አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ም/ ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ ምስጋናውና የየደብራቱ መምህራን፣ ተመራቂዎችና በርካታ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።
በመርሐ ግብሩ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ኃላፊ መጋቤ ብርሃናት ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ በፀሎት ያስከፈቱ ሲሆን ወቅቱን የተመለከቱ ዪሬዳዊ ዝማሬዎች መነባንብና ወረብ ቀርቧል። የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው ምክትል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ፀጋ እንዲሁም በሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ.ን ስንታየሁ የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክትና ቀጣይ የሥርዓተ ትምህርቱ አቅጣጫ ላይ ንግግር አድርገዋል።
በመርሐ ግብሩ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት የመጀመርያ የ12ኛ ክፍል ምርቃት መደረጉ ፍሬ የማፍራቱ ማሳያ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባና በሌሎች አህጉረ ስብከቶች የትግበራ ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።
በመቀጠልም "ይህንን መልካም ሥራ እንድንሰራ መንፈስ ቅዱስ ጠራን" የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት መሠረት በማድረግ ቆሞስ አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ ቃለ እግዚአብሔርን አስተምረዋል።
በመጨረሻም ለተመራቂ ተማሪዎች ምስክር ወረቀት ያበረከቱት የምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ገዳማት መምሪያ ኃላፊ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፅዕ አቡነ ሉቃስ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን በመልዕክታቸው " የቤተ ክርስቲያን ሙሽራ ሆናቹ ክርስቶስን እንድትጠብቁ፣ ወደ ዓለም ስትሔዱ በተኩላው እንዳትወሰዱ ተጠንቀቁ" ሲሉ አባታዊ መልዕክት በማስተላለፍ በፀሎት የመርሐ ግብሩ ፍፃሜ ሆኗል።
(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)
✍️YouTube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
✍️ FaceBook 👇
https://www.facebook.com/EOTC.GSSU
✍️Telegram 👇
https://t.me/EOTCNSSU
✍️Website👇
https://eotc-gssu.org/a/
✍️Twitter👇
https://twitter.com/tibeb_feleg
✍️Tiktok👇
https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion
🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
"ልጅን በሚኼድበት መንገድ ምራው፤ በሸመገለም ጊዜ ከርሱ ፈቀቅ አይልም።" {ምሳሌ 22፥6}
በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ በ2015 ዓ.ም በሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ እና በሀገረ ስብከት በብሔራዊ ደረጃ ምዘና ተደርጎላቸው ያለፉ #የ4ኛ , #የ6ኛ እና #የ10ኛ ክፍል #ከ4500 በላይ ተማሪዎች የዕውቅና መስጠት መርሐ ግብር የዝግጅት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ታዳሚዎቻችንን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን!!!
#ጥቅምት_4_2016_ዓ_ም #ከቀኑ_7_00_ሰዓት_ጀምሮ
#በደብረ_ምጥማቅ_ሰዓሊተ_ምህረት_ቅድስት_ማርያም_እና_ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_ካቴድራል
#በዕለቱ_ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል!!!
#ኑ_ተማሪዎቻችንን_በጋራ_እንመርቅ
#ሰዓት_ይከበር
#መቅረት_ያስቆጫል
💢የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት💢
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
🔔🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔 💫💫💫💫 🔔🔔🔔🔔🔔
"ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤ ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥ ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።" መዝ 102(103) ፡ 16
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
ሰናይ ሌሊት!
✍️Youtube 👇
https://www.youtube.com/@eotc-gssu
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
