uz
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Kanalga Telegram’da o‘tish

📈 Telegram kanali የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU analitikasi

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 14 484 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 6 043-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 334-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 14 484 obunachiga ega bo‘ldi.

30 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 530 ga, so‘nggi 24 soatda esa 23 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 39.14% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.20% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 5 666 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 477 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 33 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Kanal uchun tavsif kiritilmagan.

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 01 Iyul, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

14 484
Obunachilar
+2324 soatlar
+1447 kunlar
+53030 kunlar
Postlar arxiv
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነተ  በሀገረ ስብከቱ ሥር ለሚገኙ  በአዲሱ ሥርዓተ  ትምህርት መሠረት የ4ተኛ እና የ8ተኛ ክፍል  የሚኒስትሪ ፈተና ተሰጠ።   የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ምዘናው በጭሮ  በአራቱ አድባራት  ተማሪዎች  የፈተናውን አሰጣጥ ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ   ከማደራጃው ኃላፊ  መጋቤ ሥርዓት ዘነበ ብርሐኑ  እንዲሁም የአንድነቱ ተቀዳሚ ሰብሳቢ  መ/ር መኮንን አብዩ  ሌሎቹችም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አማራር በመገኘት  የሀገረ ስብከቱ ስራ  አስኪያጅ ቡራኬና ጸሎት ሰጥተው  ፈተናውን አስጀምረዋል።  ፈተናውም በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ   እንዲሁም  በአቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤት ተሰጥቷል። በተጨማሪም በወረዳ  ላሉት የሰንበት ትምህርት  ቤት ተፈተኞች   1. በጡሎ  ዶባ ወረዳ  በሂርና  ሁለቱ አድባራት ና በዶባ  ቅ/ሚካኤል  ቤተክርስቲያን 2.በቦኬ ኦዳ ቡልቱም ወረዳ  በበዴሳ  ሁለቱ አድባራት ና በመካኒሳ ቅ/ገብርኤል  ቤተክርስቲያን  3. በዳሮ ለቡ ወረዳ  መቻራ መድኃኔዓለም    ቤተክርስቲያን 4. በሀብሮ ወረዳ   ገለምሶ ሁለቱ አድባራት እና  በልበሊቲ ቅ/ጊዮርጊስ   ቤተክርስቲያን   5. በገመቺስ ወረዳ  በቁኒ ሁለቱም አድባራት ፈተናው መስጠት ተችሏል።  ይህ የስርዓተ ትምህርት የምዘና ስራ አምና በአንድ ወረዳ ብቻ ተሰጥቶ ቢሆንም  ዘንድሮ በ5 ወረዳ እና  ከ16 ለሚበልጡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች  ፈተናው ተዘጋጅቶ መበተን ተችሏል። በርዕሰ ከተማው ለሚገኙ ተፈታኞችም የሀገረ ስብከቱ    ሊቀ ጳጳስ  አቡነ እንጦንስ  በፈተናው ማብቂያ ላይ በመገኘት ልጆቻቸውን ሲያበረቱ ምክር ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬን በመስጠ በጸሎት ማጠቃለያ ማድረግ ተችሏል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ ማደራጃ እና የሰንበት ትምህርት  ቤቶች አንድነት በሚቀጥለው የትምህርት  ዘመን  በ9 ወረዳዎች  ተዳራሽ ለማድረግ ስራዎችን ከወዲሁ እየሰራ ይገኛል። የረዳን እግዚአብሔር  ይመስገን። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

በምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የ2018 ዓ.ም ሀገረ ስብከት አቀፍ የ4ኛ ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሞዴል ፈተናዎች ሰጠ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ ሰንበት
+3
በምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የ2018 ዓ.ም ሀገረ ስብከት አቀፍ የ4ኛ ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሞዴል ፈተናዎች ሰጠ፡፡   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም ሀገረ ስብከት አቀፍ  የሞዴል ተሰጠ። በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ 6 ወረዳ ቤተ ክህነት  መንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ አዳማ ፣ቢሾፍቱና አካባቢው፤ ሉሜ ፣አዳሚ ቱሉ፤ዱግዳ ፣እና በቦሰት ወርዳ ቤተ ክህነት በስሮቻቸው ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርቱን ሲከታተሉ ለቆዩት 3000 ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም ሞዴል  ፈተና በቀን 07/09/2018 ዓ.ም  ተሰጥቷል፡፡  የሞዴል ፈተናው  ስድስት የትምህርት አይነቶችን   ለየብቻቸው ተዘጋጅቶ  ተሰጥቷል። የተሰጠው ፈተና  መሠረተ ሃይማኖት፤ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ፤ልሳነ ግዕዝ ፤የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ለእያንዳንዱ ትምህርቶችን 50 ጥያቄዎችን ያከተተ ሲሆን  በሀገረ ስብከቱ አንድነት የሚዘጋጀው የ4ተኛ 8ተኛ እና 10ኛ ክፍል ሀገረ ስብከት አእቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና በወጣይ ወር  በሁሉም ወረዳዎች ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ይሰጣል። መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ እንኳን ለዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ! የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ ጉባኤ በአንድነት ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚመክሩበት፣ የትውልዱን መጻኢ ጉዞ የሚተልሙበት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለነገው ትውልድ ሊያሻግሩ የሚችሉ ዐውደ ሐሳቦች ለውይይት የሚቀርቡበት ታላቅ በዓል ነው። ይህ በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ተሰጥቶት በየዓመቱ እየተከናወነ የሚገኘው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ዘንድሮ በሀገራዊ ጉዳይ ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ደረጃ ጠቅላላ ጉባኤውን በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማከናወን ባይችልም በሁሉም አህጉረ ስብከት፣ በየወረዳው እና በየአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ዕለቱ በደማቅ ሁኔታ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ይውላል። ቅዱስ ጳውሎስ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ብቻ አይደለም ያለን ይህንንም የመንፈስ አንድነት እንዴት መጠበቅ እንዳለብን በመንገርም ጭምር ነው እንጂ። ይኸውም በፍጹም የዋሕነት፤ ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ፣ እየታገሣችሁ፣ ለወንድሞቻችሁም እሺ እያላችሁ፣ በፍቅር እየተጋችሁና እየተባበራችሁ በማለት ነው። የአንድነታችንንም ዓላማ እንዳንዘነጋ ሲገልጽልን “ለአንዱ ተስፋችሁ እንደመጠራታችሁ” ይለናል። እኛም የ15ኛ ዓመት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ቀንን ስናከብር ከወትሮ በላቀ የመንፈስ አንድነታችንን ለመጠበቅ መትጋት እንዲገባን ይህን የቅዱስ ጳውሎስን ምክር መርሐችን አድርገናል። ከሁል ጊዜው በላይ ዓለምም ሆነ ሀገራችን እየተጓዘችበት ካለው አስፈሪ የጥፋት ጉዞ ትውልዱን መጠበቅ፣ ማዳንና ማሰማራት የሚቻለው የመንፈስ አንድነታችንን ለመጠበቅ ስንተጋ ብቻ ነው። የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ትውልዱን በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ለመጠብቅ የመንፈስን አንድነት መርሕ ይዞ የሚጓዝ መዋቅር ነው። ታዲያ ይህንን አንድነታችንን ከውስጥም ከውጭም ፈተናዎች ለመጠበቅ እየታየ ያለውን በጎ ፍሬ ለማስቀጠል ትጋትን ገንዘብ ልናደርግ ይገባናል እንላለን። ምን እንኳን በበዓለ ጰራቅሊጦስ የዘንድሮውን ዓለም አቀፋዊ ጠቅላላ ጉባኤያችንን ማከናወን ባንችልም በያለንበት መዋቅር ዕለቱን ልንዘክረው ይገባናል። በመጨረሻም የዘንድሮውን ዓለም ዓቀፍዊ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የሚከናወንበትን ዕለት በቅርቡ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን እንኳን ለዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ እንላለን።   የመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ግንቦት 22/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:- "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህ
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:- "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የ2018ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት የ12ኛ ክፍል የናሙና ምዘና ተሰጠ። የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ግንቦት 17 2018ዓ.ም በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህር
+6
የ2018ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት የ12ኛ ክፍል የናሙና ምዘና ተሰጠ። የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ግንቦት 17 2018ዓ.ም በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አዘጋጅነት እየተተገበረ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው ለሀገር አቀፍ ለሙከራ የናሙና ምዘና የደረሱ ተማሪዎችን ለ4ኛ ጊዜ አስፈተነ። ለዚህ የናሙና ምዘና የደረሱ በአዲስ አበባና በሸገር ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አጥቢያዎች ሲሆኑ ምዘናውንም ግንቦት 16 ቀን ወስደዋል። በመቀጠልም በወርሐ ሰኔ መጨረሻ የማጠቃለያ ምዘና እንደሚወስዱ ይጠበቃል። (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)

ለሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅር:- የሰንበት ትምህርት ቤቶች  የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ ሰነድ በዚህ ሊንክ በተያያዘው ሰነድ መሠረት ተልኳል። https://eotc-gssu.org/a/የሰንበት-ት-ቤቶች-የሥራ-አመራር-ምርጫ-ማስ/ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

ለሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅር:- የሰንበት ትምህርት ቤቶች  የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ ሰነድ በዚህ ሊንክ በተያያዘው ሰነድ መሠረት ተልኳል። https://eotc-gssu.org/a/የሰንበት-ት-ቤቶች-የሥራ-አመራር-ምርጫ-ማስ/

ስቅለት! እንኳን አደረሳችሁ! “ሕመማችንንም ተሸክሞአል” ኢሳ 53፡4 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube
ስቅለት! እንኳን አደረሳችሁ! “ሕመማችንንም ተሸክሞአል” ኢሳ 53፡4 የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

በውጭ ዓለም ለሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅርና ተባባሪ አካላት የእንግሊዘኛ ትርጉም ተሳትፎ ጥሪ። በየሀገረ ስብከቱ ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት ለተጀመተው የሰንበት
በውጭ ዓለም ለሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅርና ተባባሪ አካላት የእንግሊዘኛ ትርጉም ተሳትፎ ጥሪ። በየሀገረ ስብከቱ ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት ለተጀመተው የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት የእንግሊዘኛ ትርጉም ፕሮጀክት ሥራ ግብዓትና ተሳታፊዎችን ለመላክ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ። https://eotc-gssu.org/a/የእንግሊዝኛ-ትርጉም-ሥራ-የተሳትፎ-ጥሪ/

ሥርዓተ ትምህርቱን ለሚያስተገብሩ የአብነት መምህራንና ደቀመዛሙርት ሥልጠና ተሰጠ። (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የካቲት 24/2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው የአሰላ ማኅደረ ስ
+2
ሥርዓተ ትምህርቱን ለሚያስተገብሩ የአብነት መምህራንና ደቀመዛሙርት ሥልጠና ተሰጠ። (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የካቲት 24/2018 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው የአሰላ ማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያምና ቅዱስ ፋኑኤል ወቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ገዳም ለሚገኙ የአብነት መምህራንና ደቀ መዛሙርት ከየካቲት 21-22/2018 ዓ.ም ለኹለት ተከታታይ ቀናት ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በተላኩ ልዑካን በመ/ሃ ቀሲስ ይታገሡ ደሴና በመ/ር ሚኪያስ ግዛቸው የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ፣ ልሳነ ግዝ የማስተማር ዘዴ፣ ትምህርተ ሃይማኖትና ብቁ መምህራን እንዴት ማፍራት ይቻላል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ሥልጠናው ተሰጥቶዋል። በሥልጠናው የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች ክፍል ሓላፊ መ/ምሕረት ወልደ ሰንበት"፣ ክቡር የገዳሙ አስተዳዳሪና የሥልጠናው አዘጋጅ መልአከ ስብሐት ገረመው ሸዋዬ ተገኝተው ሥልጠናውን በማነቃቃት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል። ከሥልጠናው በኋላም የአብነት መምህራኑ በሥርዓተ ትምህርቱ የተካተተውን ልሳነ ግእዝና ትርጓሜ መጻሕፍት ለሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንደሚያስተምሩ ይጠበቃል። (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

አድዋ "በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።" መዝ 43፡5 እንኳን ለአድዋ ድል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
አድዋ "በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን።" መዝ 43፡5 እንኳን ለአድዋ ድል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የመተከል ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር   በቀን 14/06/2018 ዓ.ም. ለአድባራት አለቆች ለመምህራን እና ለሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሐላፊዎች ስልጠና ሰጠ። በእለቱ ከየወረዳ ቤተ ክህነቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሐላፊ ከ39 አቢያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና መምህራን በተገኙበት ስለ ኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አደረጃጀት እና አወቃቀር  እንድሁም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህት ምንነት እና ትግበራ ዙሪያ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:00 ድረስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በተላከው መምህር ያሬድ ዮናስ አማካኝነት ሥልጠናው ከተሰጠ በኋላ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይትምተደርጓል። በዕለቱ የመተከል ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መ/ም/ኅሩይ ብሩ እና የሰንበት ክፍል ሐላፊ ቀሲስ ንብረት እጅጉ የውይይት መርሐ ግብር ያደረጉ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ጥያቄ እና መልስ ከተደረገበት በኋላ ለሥልጠና መርሐ ግብሩ  መሳካት አስተዋፅዖአቸው ለላቀ አካላት እና ለሥልጠናው ተሳታፊዎች  የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል። በመጨረሻም ሠልጣኞች ወደ አጥቢያቸው እንደተመለሱ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር ሥርዓተ ትምህርቱን እንዲያስቀጥሉ በወረዳ ደረጃ የሰንበት ትምህርት ቤትን በማቋቋም ደረጃ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አፅዕኖት በመስጠት አባታዊ መመሪያ ሰጥተው የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ተጠናቋል። መረጃው የመተከል ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website