የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
تُعد قناة የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 484 مشتركاً، محتلاً المرتبة 6 043 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 334 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 484 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 30 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 530، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 23، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 39.14%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.20% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 5 666 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 477 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 33.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 01 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.
14 484
المشتركون
+2324 ساعات
+1447 أيام
+53030 أيام
أرشيف المشاركات
በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነተ በሀገረ ስብከቱ ሥር ለሚገኙ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የ4ተኛ እና የ8ተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተሰጠ።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
ምዘናው በጭሮ በአራቱ አድባራት ተማሪዎች የፈተናውን አሰጣጥ ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከማደራጃው ኃላፊ መጋቤ ሥርዓት ዘነበ ብርሐኑ እንዲሁም የአንድነቱ ተቀዳሚ ሰብሳቢ መ/ር መኮንን አብዩ ሌሎቹችም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አማራር በመገኘት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ቡራኬና ጸሎት ሰጥተው ፈተናውን አስጀምረዋል።
ፈተናውም በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ እንዲሁም በአቡነ ጎርጎሪዎስ ትምህርት ቤት ተሰጥቷል። በተጨማሪም በወረዳ ላሉት የሰንበት ትምህርት ቤት ተፈተኞች
1. በጡሎ ዶባ ወረዳ በሂርና ሁለቱ አድባራት ና በዶባ ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን
2.በቦኬ ኦዳ ቡልቱም ወረዳ በበዴሳ ሁለቱ አድባራት ና በመካኒሳ ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን
3. በዳሮ ለቡ ወረዳ መቻራ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
4. በሀብሮ ወረዳ ገለምሶ ሁለቱ አድባራት እና በልበሊቲ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
5. በገመቺስ ወረዳ በቁኒ ሁለቱም አድባራት ፈተናው መስጠት ተችሏል።
ይህ የስርዓተ ትምህርት የምዘና ስራ አምና በአንድ ወረዳ ብቻ ተሰጥቶ ቢሆንም ዘንድሮ በ5 ወረዳ እና ከ16 ለሚበልጡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ፈተናው ተዘጋጅቶ መበተን ተችሏል። በርዕሰ ከተማው ለሚገኙ ተፈታኞችም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንጦንስ በፈተናው ማብቂያ ላይ በመገኘት ልጆቻቸውን ሲያበረቱ ምክር ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬን በመስጠ በጸሎት ማጠቃለያ ማድረግ ተችሏል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ ማደራጃ እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን በ9 ወረዳዎች ተዳራሽ ለማድረግ ስራዎችን ከወዲሁ እየሰራ ይገኛል። የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን።
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
+3
በምሥራቅ ሸዋ ሀ/ስብከት የ2018 ዓ.ም ሀገረ ስብከት አቀፍ የ4ኛ ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሞዴል ፈተናዎች ሰጠ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ስር የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም ሀገረ ስብከት አቀፍ የሞዴል ተሰጠ። በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ 6 ወረዳ ቤተ ክህነት መንበረ ጵጵስና ርዕሰ ከተማ አዳማ ፣ቢሾፍቱና አካባቢው፤ ሉሜ ፣አዳሚ ቱሉ፤ዱግዳ ፣እና በቦሰት ወርዳ ቤተ ክህነት በስሮቻቸው ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርቱን ሲከታተሉ ለቆዩት 3000 ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም ሞዴል ፈተና በቀን 07/09/2018 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡ የሞዴል ፈተናው ስድስት የትምህርት አይነቶችን ለየብቻቸው ተዘጋጅቶ ተሰጥቷል።
የተሰጠው ፈተና መሠረተ ሃይማኖት፤ ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ፤ልሳነ ግዕዝ ፤የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ለእያንዳንዱ ትምህርቶችን 50 ጥያቄዎችን ያከተተ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ አንድነት የሚዘጋጀው የ4ተኛ 8ተኛ እና 10ኛ ክፍል ሀገረ ስብከት አእቀፍ የሚኒስትሪ ፈተና በወጣይ ወር በሁሉም ወረዳዎች ባሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ይሰጣል።
መረጃው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫
እንኳን ለዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ ጉባኤ በአንድነት ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚመክሩበት፣ የትውልዱን መጻኢ ጉዞ የሚተልሙበት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለነገው ትውልድ ሊያሻግሩ የሚችሉ ዐውደ ሐሳቦች ለውይይት የሚቀርቡበት ታላቅ በዓል ነው። ይህ በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ተሰጥቶት በየዓመቱ እየተከናወነ የሚገኘው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ዘንድሮ በሀገራዊ ጉዳይ ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ደረጃ ጠቅላላ ጉባኤውን በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማከናወን ባይችልም በሁሉም አህጉረ ስብከት፣ በየወረዳው እና በየአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ዕለቱ በደማቅ ሁኔታ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫ በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ይውላል።
ቅዱስ ጳውሎስ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ብቻ አይደለም ያለን ይህንንም የመንፈስ አንድነት እንዴት መጠበቅ እንዳለብን በመንገርም ጭምር ነው እንጂ። ይኸውም በፍጹም የዋሕነት፤ ራሳችሁን ዝቅ አድርጋችሁ፣ እየታገሣችሁ፣ ለወንድሞቻችሁም እሺ እያላችሁ፣ በፍቅር እየተጋችሁና እየተባበራችሁ በማለት ነው። የአንድነታችንንም ዓላማ እንዳንዘነጋ ሲገልጽልን “ለአንዱ ተስፋችሁ እንደመጠራታችሁ” ይለናል። እኛም የ15ኛ ዓመት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ቀንን ስናከብር ከወትሮ በላቀ የመንፈስ አንድነታችንን ለመጠበቅ መትጋት እንዲገባን ይህን የቅዱስ ጳውሎስን ምክር መርሐችን አድርገናል። ከሁል ጊዜው በላይ ዓለምም ሆነ ሀገራችን እየተጓዘችበት ካለው አስፈሪ የጥፋት ጉዞ ትውልዱን መጠበቅ፣ ማዳንና ማሰማራት የሚቻለው የመንፈስ አንድነታችንን ለመጠበቅ ስንተጋ ብቻ ነው።
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ትውልዱን በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ለመጠብቅ የመንፈስን አንድነት መርሕ ይዞ የሚጓዝ መዋቅር ነው። ታዲያ ይህንን አንድነታችንን ከውስጥም ከውጭም ፈተናዎች ለመጠበቅ እየታየ ያለውን በጎ ፍሬ ለማስቀጠል ትጋትን ገንዘብ ልናደርግ ይገባናል እንላለን። ምን እንኳን በበዓለ ጰራቅሊጦስ የዘንድሮውን ዓለም አቀፋዊ ጠቅላላ ጉባኤያችንን ማከናወን ባንችልም በያለንበት መዋቅር ዕለቱን ልንዘክረው ይገባናል። በመጨረሻም የዘንድሮውን ዓለም ዓቀፍዊ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የሚከናወንበትን ዕለት በቅርቡ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን እንኳን ለዓመታዊው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ እንላለን።
የመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
+6
የ2018ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት የ12ኛ ክፍል የናሙና ምዘና ተሰጠ።
የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ግንቦት 17 2018ዓ.ም
በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አዘጋጅነት እየተተገበረ በሚገኘው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው ለሀገር አቀፍ ለሙከራ የናሙና ምዘና የደረሱ ተማሪዎችን ለ4ኛ ጊዜ አስፈተነ።
ለዚህ የናሙና ምዘና የደረሱ በአዲስ አበባና በሸገር ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አጥቢያዎች ሲሆኑ ምዘናውንም ግንቦት 16 ቀን ወስደዋል። በመቀጠልም በወርሐ ሰኔ መጨረሻ የማጠቃለያ ምዘና እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
ለሁሉም የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅር:- የሰንበት ትምህርት ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ማስፈጸሚያ ሰነድ በዚህ ሊንክ በተያያዘው ሰነድ መሠረት ተልኳል። https://eotc-gssu.org/a/የሰንበት-ት-ቤቶች-የሥራ-አመራር-ምርጫ-ማስ/
በውጭ ዓለም ለሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች መዋቅርና ተባባሪ አካላት የእንግሊዘኛ ትርጉም ተሳትፎ ጥሪ። በየሀገረ ስብከቱ ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት ለተጀመተው የሰንበት ትምህርት ቤቶች መጻሕፍት የእንግሊዘኛ ትርጉም ፕሮጀክት ሥራ ግብዓትና ተሳታፊዎችን ለመላክ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
https://eotc-gssu.org/a/የእንግሊዝኛ-ትርጉም-ሥራ-የተሳትፎ-ጥሪ/
+2
ሥርዓተ ትምህርቱን ለሚያስተገብሩ የአብነት መምህራንና ደቀመዛሙርት ሥልጠና ተሰጠ።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የካቲት 24/2018 ዓ.ም
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኘው የአሰላ ማኅደረ ስብሐት በዓታ ለማርያምና ቅዱስ ፋኑኤል ወቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ገዳም ለሚገኙ የአብነት መምህራንና ደቀ መዛሙርት ከየካቲት 21-22/2018 ዓ.ም ለኹለት ተከታታይ ቀናት ከመንበረ ፓትርያርክ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በተላኩ ልዑካን በመ/ሃ ቀሲስ ይታገሡ ደሴና በመ/ር ሚኪያስ ግዛቸው የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ፣ ልሳነ ግዝ የማስተማር ዘዴ፣ ትምህርተ ሃይማኖትና ብቁ መምህራን እንዴት ማፍራት ይቻላል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ሥልጠናው ተሰጥቶዋል።
በሥልጠናው የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች ክፍል ሓላፊ መ/ምሕረት ወልደ ሰንበት"፣ ክቡር የገዳሙ አስተዳዳሪና የሥልጠናው አዘጋጅ መልአከ ስብሐት ገረመው ሸዋዬ ተገኝተው ሥልጠናውን በማነቃቃት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል። ከሥልጠናው በኋላም የአብነት መምህራኑ በሥርዓተ ትምህርቱ የተካተተውን ልሳነ ግእዝና ትርጓሜ መጻሕፍት ለሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንደሚያስተምሩ ይጠበቃል።
(የሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
የመተከል ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር በቀን 14/06/2018 ዓ.ም. ለአድባራት አለቆች ለመምህራን እና ለሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሐላፊዎች ስልጠና ሰጠ።
በእለቱ ከየወረዳ ቤተ ክህነቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሐላፊ ከ39 አቢያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና መምህራን በተገኙበት ስለ ኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አደረጃጀት እና አወቃቀር እንድሁም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህት ምንነት እና ትግበራ ዙሪያ ከጧቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 11:00 ድረስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በተላከው መምህር ያሬድ ዮናስ አማካኝነት ሥልጠናው ከተሰጠ በኋላ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይትምተደርጓል።
በዕለቱ የመተከል ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መ/ም/ኅሩይ ብሩ እና የሰንበት ክፍል ሐላፊ ቀሲስ ንብረት እጅጉ የውይይት መርሐ ግብር ያደረጉ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ጥያቄ እና መልስ ከተደረገበት በኋላ ለሥልጠና መርሐ ግብሩ መሳካት አስተዋፅዖአቸው ለላቀ አካላት እና ለሥልጠናው ተሳታፊዎች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ሠልጣኞች ወደ አጥቢያቸው እንደተመለሱ ሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር ሥርዓተ ትምህርቱን እንዲያስቀጥሉ በወረዳ ደረጃ የሰንበት ትምህርት ቤትን በማቋቋም ደረጃ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አፅዕኖት በመስጠት አባታዊ መመሪያ ሰጥተው የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ተጠናቋል።
መረጃው የመተከል ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!
(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
👉 Youtube
👉 Facebook
👉 Telegram
👉 Tiktok
👉 Website
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
