ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Канал የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 16 797 подписчиков, занимая 4 943 место в категории Религия и духовность и 2 144 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 16 797 подписчиков.

Согласно последним данным от 03 ноября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 576, а за последние 24 часа — 7, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 60.01%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 13.20% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 10 080 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 218 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 47.

📝 Описание и контентная политика

Описание канала не предоставлено.

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 04 ноября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

16 797
Подписчики
+724 часа
+1327 дней
+57630 дней
Архив постов
የአርሲ ሰማእታት እና የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን አስመልክቶ ወቅታዊ መልእክት። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፤በአርሲ በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ሊገታ ያልቻለ እና ከልካይ የሌለው ተከታታይ ግድያ ምክንያት እጅግ አዝነናል ። በዚህም ለኦርቶዶክሳውያን ይልቁንም ለሰማእታት ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን። የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሞት ፣ መፈናቀልና ስደት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶ ይገኛል። በቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የወደቁትን፤ የሚታደጋቸው ሸተው በጭንቀት ያሉትን ቤት ይቁጠራቸው። ሃይማኖታቸው ምክንያት ሆኖ ግድያ ፣ ጥቃት ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ የሚደርሰባቸው ወገኖቻችን ጩኸት ተበራክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለውን የኦርቶዶክሳዊያን ሞት ፣ ስደት እና የአቢያተ ክርስቲያናት ቃጠሎን አስመልክቶ የወግዘትና የሐዘን መግለጫ ቢያወጣም መከራውን አልቆመውም ። ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣትም አልተቻለም። በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ይኸን ተከታታይ ማቆሚያ የሌለው ዕልቂት አስመልክቶ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሊቃውንት ፣ ምዕመናን እና ወጣቶች ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ በመሰየም በአርሲና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸሙትን ኢሰብዓዊና ሰይጣናዊ ድርጊቶችን በጥናት በመለየት ፤ ምክንያታቸውን በመተንተን የአደጋ መከላከልና የተጎዱትን የማበርታት ሥራ እንዲሁም የአንድን ዜጋ በነጻነት የመኖር እና የማምለክ ህገ መንግሥታዊ መብቱን ባላስጠበቁ የመንግስት አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ መንግስትን በመጠየቅ እና ኃላፊነትን ባለመወጣት ተጠያቂነት እንዲሰፍን በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ በትህትና በልጅነት መንፈስ እናሳስባለን ። ከዚህም በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ ሩፉኤልን የሚመሩት ኢህጉረ ስብከት አስመልከቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሰፊው መወያየቱንና በርካታ ማስራጃዎችን ጉባኤው ማዳመጡን ተረድተናል። በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተፈጸሙ የተባሉ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰቶች ለመስማት የሚዘገንኑ እንኳን አማንያኑን ኢአማንያንን የሚያስደነግጡ ፤ አንገትን የሚያሰደፉ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን በሚገባ ተገንዝበናል ። የተፈጸመውን አስተዳደራዊ እና ቀኖናዊ ጉዳዮች ጥሰት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ ያለ ልዩነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የማስጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል። ጥቂት የሀሳብ ልዩነቶች መፈጠራቸውን ታዝበናል። ይኸ የሀሳብ ልዩነት ቀኖና እና ህገ ቤተክርስትያንን ከመጠበቅ አንጻር የቀረበ እንዳይደለ ተረድተናል ። በተፈጸሙ አሳፉሪ ድርጊት አንገታችንን የደፋነው ሳያንሰን የአደባባይ ምስጢር በሆነው ጉዳይ ላይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ያለ ልዩነት አልመወሰን ራሱን የቻለ የቀኖና ጥሰት ነው ። ይህን ጉዳይ በሕገ ቤተክርስትያን መሠረት አድርጎ አለመወሰን ለነገም የሲኖዶስን ልዕልና ያሳጣል ሥርዓት አልበኝነትን ያነግሳል ። ስለሆነም ምልዐተ ጉባዔው ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የማስጠበቅ ፍጹም የማይሽራረፍ መንፈሳዊ ግዴታውን በምልዐት እንዲውጣ በትህትና እናሳስባለን ። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

🕹 ለሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሙሉ በሥርዓተ ትምህርቱ አተገባበር ማሻሻያ መሠረት ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ድረስ የሥነ ጥበብ/ሕይወት ክህሎት እንደ 7ኛ ክፍለ ትምህርት ሆኖ እንደሚሰጥ ይታወቃል። ✍️ በመሆኑም ከ8ኛ እስከ 10ኛ ባሉት ክፍሎች ከመጽሐፉ ሕትመት ጋር አብሮ በምዕራፍ አንድ ብቻ ተካቶ የታተመ ሲሆን ቀሪዎቹን የመጻሕፍቱን ምዕራፍ ትምህርቶች ለመምህራን ማስተማርያ ይሆን ዘንድ በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የዌብሳይት ገጽ ላይ በመለቀቁ በማውረድ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ✍️ መልዕክት 👉 የትምህርት አሰጣጡን በተመለከተ ታትመው ለገበያ በቀረቡት መጻሕፍት መግቢያ ላይ የተጠቀሰ በመሆኑ አንብባችሁ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን። 👉 ሥነጥበብ ( ሥነ ጽሑፍ ስነ ሥዕል) ትምህርት 8ኛ ክፍል 👉 ሥነ ጥበብ (የሕይወት ክህሎት አንድ) 9ኛ ክፍል 👉 ሥነ ጥበብ (ብራና ሥራ፣ ድጉሰት፣ ኪነ ሕንጻ) 10ኛ ክፍል የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት https://eotc-gssu.org/a/የሥነ-ጥበብ-ትምህርት-መጻሕፍት/

🕹 ለሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሙሉ በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ድረስ መሠረት ከግዕዝ ትምህርት ጋር አብሮ የዜማና መዝሙር ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል። ✍️ በመ
🕹 ለሁሉም ሰንበት ትምህርት ቤቶች በሙሉ በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ድረስ መሠረት ከግዕዝ ትምህርት ጋር አብሮ የዜማና መዝሙር ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል። ✍️ በመሆኑም ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ባለው ከመጽሐፉ ጋር አብሮ ተካቶ የታተመ ሲሆን ከ5-7 ባለውም በሁለተኛው የማስተካከያ ሕትመት ተካቶ የሚታተም ይሆናል። ከ8-10ኛ ክፍል ባለው የግዕዝ ዜማ ወመዝሙር ትምህርቶች የመጽሐፍ ሕትመቱ ላይ በተወሰነ የተካተቱ ሲሆን ሙሉውን በመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የዌብሳይት ገጽ ላይ በመለቀቁ በማውረድ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የእያንዳንዳቸውን መጻሕፍት ሊንክ ለማግኘት ደግሞ 👉🏼 https://eotc-gssu.org/a/ዜማና_መዝሙር_8ኛ_ክፍል/ https://eotc-gssu.org/a/ዜማና_መዝሙር_9ኛ_ክፍል-2/ https://eotc-gssu.org/a/ዜማና_መዝሙር_10ኛ_ክፍል-2/ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም አዲስ በዓል! (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 Youtube 👉 Facebook
+7
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም አዲስ በዓል! (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

እንኳን ለዘመነ ሉቃስ ፳፻፲፱ ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! "በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ" መዝ ፷፭ (፷፮) ፡ ፲፩ ዘመኑ የፍስሐ የስኬት የንስሐ እና የቅድስና ይሁንልን! መልካም አዲስ ዓመት! (የ
እንኳን ለዘመነ ሉቃስ ፳፻፲፱ ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! "በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ" መዝ ፷፭ (፷፮) ፡ ፲፩ ዘመኑ የፍስሐ የስኬት የንስሐ እና የቅድስና ይሁንልን! መልካም አዲስ ዓመት! (የሰ/ት/ቤቶች አንድነት) የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የተተኪ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሥልጠና ተጠናቀቀ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ በመንበረ ጵጵስና ደብረ ሣህል መድኃኔዓለም ካቴድራል ለ7 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የተተኪ ሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሥልጠና አጠናቀቀ። በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ  የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መ/ሰ መንበሩ ባሳዝነው:የሀገረ ስብከቱ የካህናት አስተዳደር ኅላፊ ቀሲስ እንዳለ ከበደ፣የስብከተ ወንጌል ኃላፊ መ/ር ታጋይ ሞላ፣የሰንበት ት|ቤቶች አንድነት አመራሮች መምህራንና ተመራቂዎች በተገኙበት አስመርቋል። ከነሐሴ 25 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው ይህ ሥልጠና ከ8 ወረዳዎች የተመረጡ ስሆን፤ ሥልጠናውንም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሀገረ ስብከቱ፣ የተላኩ 2 መምህራን ሰጥተውታል። የምርቃት መርሓ-ግብሩን ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊው መ/ሰ መንበሩ ባሳዝነው" ሁሉም በእግዚአብሔር ፍቃድ ሆኗል፤ የቤተክርስቲያንን ህልውና ለማስቀጥል በሰንበት ትምህርት ቤት ላይ ጠንክሮ መስራት ዋናው ተግባር ነው፤ከአብነት ትምህርት ቤት ቀጥሎ ለቤተክርስቲያን ህልውና ሰንበት ትምህርት ቤቶች ላይ ጠንክሮ ቀን ከሌሊት መስራት ለነገ የማይባል ሥራ ነው በርቱ ለማለት እንወዳለን በማለት እና ለዕለቱ ተመርቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት እና ለተማሪዎች መክሊታችሁን እንዳትቀብሩ ፤አግልግሎታችሁን በምትሄዱበት መንገድ ሁሉ በትዕግስት፤በብልሃት፤በጥበብ ማለፍ አለባችሁ በማለት አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል። በመርሐግብሩ ማጠቃለያም፣ ለ7 ቀናት ሥልጠናውን በብቃት ላጠናቀቁ 32 ተተኪ መምህራን እንዲሁም ሥልጠናው እንዲሳካ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትና የመምሪያ ኀላፊዎች ምስጋና አቅርበዋል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

#የባሕር_ዳር_ሀገረ_ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 778 የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በብፁዕ አቡነ አብርሃም አባታዊ ቡራኬ አስመረቀ 📍 ጳጕሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም. | ባሕር ዳ
+9
#የባሕር_ዳር_ሀገረ_ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 778 የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በብፁዕ አቡነ አብርሃም አባታዊ ቡራኬ አስመረቀ 📍 ጳጕሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም. | ባሕር ዳር የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፣ በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሲማሩ የነበሩ 778 ተማሪዎችን በብፁዕ አቡነ አብርሃም አባታዊ ቡራኬ አስመርቋል። የምረቃ መርሐ ግብሩ በደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተካሂዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመገኘት ለተመራቂዎቹ አባታዊ ቡራኬና መልዕክት ሰጥተዋል። በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ አቶ አየለ አዱኛ ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አንድነቱ በ102 አድባራትና ገዳማት የሚገኙ 83,625 አባላትን በማሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በተጨማሪም፣ በ59 አጥቢያዎች ለ27,542 ተማሪዎች ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል። 🎓 ምረቃ የመጨረሻ ሳይሆን፣ ለአዲስ የእውቀት፣ የእምነትና የአገልግሎት ምዕራፍ መነሻ ነው! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ፎቶ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሚዲያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የ2018ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የምረቃ መርሐ ግብር ተከናወነ። ነሐሴ 30/2018 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በሥርዓተ ትምህርቱ በቅድመ ትግበራ ሙከራ ሲከናወንባቸው ለነበሩ እና ለዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በዛሬው ቀን አስመረቀ። ለምርቃት የደረሱት ተማሪዎች ከሁለት ሀገረ ስብከት የተውጣጡ የ19ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ በምርቃት መርሐ ግብሩ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ ኀይለ እግዚ አሰፋ፣ የማደራጃ መምርያው ትምህርት ክፍል ሐላፊ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ይታገሱ ደሴ የሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ ዲያቆን ዶክተር ስንታየሁ ምስጋናው በመገኘት ለተማሪዎች መልዕክት አሰሰተላልፈዋል። በመርሐ ግብሩ ለተማሪዎች የሰርተፍኬት እና በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት እና በትምህርት ትግበራ እግቅስቃሴ የላቀ ውጤት ላስመዘገበው ደብር የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት የመርሀግብሩ ፍጻሜ ሆኗል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የተተኪ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን  ሥልጠና ተጠናቀቀ:: ነሐሴ  28 ቀን 2018 ዓ.ም የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ በአዳማ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ገዳም ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የደረጃ ሁለት የተተኪ ሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሥልጠና አጠናቀቀ። በምርቃት መርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የሀገረ ስብከቱ ም|ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ክፍለ ሓላፊች፣ የሰንበት ት|ቤቶች አንድነት አመራሮች መምህራንና ተመራቂዎች በተገኙበት አስመርቋል። ከነሐሴ 17 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው ይህ ሥልጠና ከየወረዳው የተመረጡ 40 ተተኪ መምህራንን ያቀፈ ነው። ሥልጠናውንም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሀገረ ስብከቱ፣ ከአዲስ አበባ እና ከልዩ ልዩ መዋቅሮች የተወጣጡ 10 ያህል የዘርፉ ባለሙያዎችና መምህራን ሰጥተውታል። የምርቃት መርሓ-ግብሩን በጸሎት የከፈቱት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር 1ን በማንሳት አምላካዊ ቃሉን አብራርተዋል። ሥራ አስኪያጁም፤ "ለጥበበኛ ሰው አንዲት ቃል ትበቃዋለች፤ እናንተ ተመርጣችሁ እግዚአብሔር ለዚህ ክብር በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራትና እናት አባትን ማክበር ነው፤ ቤተክርስቲያን የሰጠቻችሁን አደራ እንድትወጡ እኛም አደራ እንላለን። ራሳችሁን በጾም በጸሎት ጠብቁ፤ ከወንድሞቻችሁ ጋር በሰላም፣ በፍቅር፣ በመቻቻልና በመከባበር የተቀበላችሁትን አደራ በመወጣት እንድታስተምሩ ተመርቃችኋል" ሲሉ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል። በመርሓ-ግብሩ ማጠቃለያም፣ ለ10 ቀናት ሥልጠናውን በብቃት ላጠናቀቁ 40 ተተኪ መምህራን እንዲሁም ሥልጠናው እንዲሳካ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትና መምህራን የዕውቅናና የምስክር ወረቀት በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩል ተበርክቶላቸዋል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

የተተኪ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን  ሥልጠና ተጠናቀቀ:: ነሐሴ  28 ቀን 2018 ዓ.ም የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፣ በአዳማ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ገዳም ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የደረጃ ሁለት የተተኪ ሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ሥልጠና አጠናቀቀ። በምርቃት መርሐ ግብሩ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የሀገረ ስብከቱ ም|ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ጌቱ ሞቲ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያው ክፍለ ሓላፊች፣ የሰንበት ት|ቤቶች አንድነት አመራሮች መምህራንና ተመራቂዎች በተገኙበት አስመርቋል። ከነሐሴ 17 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው ይህ ሥልጠና ከየወረዳው የተመረጡ 40 ተተኪ መምህራንን ያቀፈ ነው። ሥልጠናውንም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሀገረ ስብከቱ፣ ከአዲስ አበባ እና ከልዩ ልዩ መዋቅሮች የተወጣጡ 10 ያህል የዘርፉ ባለሙያዎችና መምህራን ሰጥተውታል። የምርቃት መርሓ-ግብሩን በጸሎት የከፈቱት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር 1ን በማንሳት አምላካዊ ቃሉን አብራርተዋል። ሥራ አስኪያጁም፤ "ለጥበበኛ ሰው አንዲት ቃል ትበቃዋለች፤ እናንተ ተመርጣችሁ እግዚአብሔር ለዚህ ክብር በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራትና እናት አባትን ማክበር ነው፤ ቤተክርስቲያን የሰጠቻችሁን አደራ እንድትወጡ እኛም አደራ እንላለን። ራሳችሁን በጾም በጸሎት ጠብቁ፤ ከወንድሞቻችሁ ጋር በሰላም፣ በፍቅር፣ በመቻቻልና በመከባበር የተቀበላችሁትን አደራ በመወጣት እንድታስተምሩ ተመርቃችኋል" ሲሉ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል። በመርሓ-ግብሩ ማጠቃለያም፣ ለ10 ቀናት ሥልጠናውን በብቃት ላጠናቀቁ 40 ተተኪ መምህራን እንዲሁም ሥልጠናው እንዲሳካ ድጋፍና አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትና መምህራን የዕውቅናና የምስክር ወረቀት በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩል ተበርክቶላቸዋል። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

Use the uploaded image as the exact visual reference and first frame. Keep the woman’s face, hairstyle, skin tone, Ethiopian traditional clothing, jewelry, body proportions, garden setting, flowers, chair, lighting, and overall appearance consistent throughout the entire video. Do not change her identity or outfit. Create a realistic cinematic talking-video of the beautiful Ethiopian woman sitting naturally in the garden. She looks directly into the camera with a warm, friendly smile. She gently moves her head and hands while speaking, with subtle natural blinking and realistic facial expressions. Her movements should be calm, elegant, and welcoming. The camera should remain mostly medium close-up / medium shot, with a very slow cinematic push-in toward her face. Natural sunlight filters through the trees, creating a warm festive atmosphere. The background remains softly blurred with realistic depth of field. Her Ethiopian traditional white dress and colorful embroidery should move naturally with her body. 🗣 Dialogue — spoken exactly in Amharic The woman says:
“እንኳን ለ2019 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቴ ይደረሳችሁ። መልካም በዓል!!”
Accurate Amharic pronunciation and natural Ethiopian accent. Perfect lip synchronization with every spoken word. Do not replace, translate, shorten, or alter the dialogue. 🎭 Acting / Expression Start with a gentle smile while looking directly at the camera. Speak warmly and naturally, as if giving a heartfelt New Year greeting to viewers. Slightly nod when saying “እንኳን ለ2019 አዲስ አመት…” Use a gentle hand gesture while saying the wishes for peace and love. Finish with a bigger, joyful smile on “መልካም በዓል!!” Maintain natural eye contact with the camera. Facial expressions should feel genuine, warm, elegant, and celebratory. No exaggerated movements or artificial facial animation. 🎥 Visual quality Photorealistic, cinematic, natural skin texture, realistic eyes and teeth, realistic hair movement, natural sunlight, shallow depth of field, subtle background bokeh, smooth camera motion, high-detail Ethiopian traditional clothing, professional cultural celebration video, warm and joyful atmosphere, stable composition, realistic human motion, clean audio, accurate lip sync. Avoid: changing her face, changing her hairstyle, changing the traditional clothing, extra fingers, distorted hands, warped jewelry, unnatural mouth movement, excessive body movement, camera shake, artificial-looking skin, subtitles, captions, text overlays, or background changes.

ለተከታታይ 6 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት አዘጋጅነት ለ 20 ወረዳዎች ከነሐሴ 18 እስከ 23  ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በርዕሰ አድባራት ደሴ ደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው ፣ የሃገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ኅሩያን ፍቅረ ኢየሱስ ተሰማ ፣ መልአከ ብርሃን ኪሮስ ፋሲል የደሴ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነት ዋና ስራአስኪያጅ ፣መምህር ተስፋማርያም ቢሰጠኝ የደቡብ ወሎ ሃ/ስብከት የስብከተ ወንጌል እና የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሐላፊ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣የሰበካ ጉባኤ አባላት የሰ/ት/ቤት አመራሮች እንዲሁም ስልጠናውን በደሴ ደብረ ቤቴል ቅድስት ሥላሴ እና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በሚገባ ሲከታተሉ የቆዩ ሰልጠኞች በተገኙበት እጅግ በደማቅ መርሃግብር ስልጠናው የተጠናቀቀ ተጠናቀቀ። በመርሃግብሩ ላይ ትምህርት፣የደቡብ ወሎ ዘሃገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አጠቃላይ ሪፖርት ፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በመጡት በ መምህር ያሬድ ስልጠና ፣ ቅኔ እንዲሁም በስልጠናው ላይ ለተሳተፉ እና ስልጠናው እንዲከናወን ድጋፍ ላዳረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት በመስጠት በመጨረሻም የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ በመምህር ቆሞስ አባ ለይኩን ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች እና መልእክቶች ተላልፈው መርሃግብሩ ተጠናቋል። በተያያዘም የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል። መረጃው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ነው። የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website

በደቡብ ኦሞ አሪ ዞን ሀገረ ስብከት በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የነበረው የተተኪ መምህራን ሥልጠና ተጠናቀቀ። ነሐሴ 24/ 2018 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በደቡብ ኦሞ አሪ ዞን ሀገረ ስብከት በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ 7 ወረዳ ቤተክህነት ለተውጣጡ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህራን ከነሐሴ 18-22 ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ስምረተ አብ እሸቴ እንዲሁ የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሓላፊ መጋቤ ሰናያት መምህር ፍሬው አሰፋ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና  በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የሰንበት ትምህርት  ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት አተገባበርና የማስተማር ሥነ ዘዴ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ሥልጠናውን የሰጡት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት አስተባባሪ መምህር ሚኪያስ ግዛቸው ገልጠዋል። የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍል ሓላፊ መጋቤ ሰናያት መምህር ፍሬው አሰፋ በበኩላቸው  ሀገረ ስብከቱ ባለው ርቀት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከናወነው የመምህራን ሥልጠና ሠልጣኞችን ልኮ ማሰልጠን ባይቻልም በሀገረ ስብከቱ የዚህ የሥልጠና መድረክ ዓላማ የመምህራንን ግንዛቤ እና አቅም መፍጠርያ እና ማጎልበቻ መሆኑን ገልጠዋል። አያይዘውም ከዚህ ሥልጠና ጎን ለጎን በከተማዋ ጂንካ ለሚገኙ የሥርዓተ ትምህርቱ ትግበራ ባለ ድርሻ አካላት የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የአብነት መምህራን፣ ሰበካ ጉባኤ ሓላፊዎችና ሰባኪያነ ወንጌል የሥልጠና መድረክ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል። በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ስምረተ አብ እሸቴ ሰልጣኝ መምህራን በሰለጠኑት ሥልጠና የእውቀትና የአመለካከት ለውጥ በሚያከናውኑት አገልግሎት ሁሉ እንዲያመጡ፣ መልዕክትን በማስተላለፍ ለሠልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል። በተያያዘ ነሔሴ 23 በከተማዋ ጂንካ ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የአብነት መምህራን እና ሰባኪያነ ወንጌል  ለሰንበት ትምህርት ቤት ያላቸውን ግንዛቤ  ማሳደጊያ ሥልጠና ተሰጥቷል። በመርሐ ግብሩ ፍጻሜም የሀገረ ስብከቱ ስራአኪያጅ መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ስምረተ አብ እሸቴ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ግንዛቤያችንን በማስተካከል፣ለሰንበት ትምህርት ቤት ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የነገውን ትውልድ ላይ እንስራ፣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጂንካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ! (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) 👉 Youtube 👉 Facebook 👉 Telegram 👉 Tiktok 👉  Website