uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
914
Obunachilar
-324 soatlar
-177 kun
+5330 kun
Postlar arxiv
Repost from N/a
💎 بشرى لطلاب العلم: ستبدأ بعون الله تعالى دفعة جديدة من بعض البرامج العلمية بإشراف الشيخ عبد الرزاق البدر، وذلك يوم السبت ٢٩ / ٤ / ١٤٤٨ الموافق ١٠ / ١٠ / ٢٠٢٦م. 📍والبرامج هي: ١- برنامج فقه الصلاة، ومدته أربعة أشهر تقريبا، ورابطه في التليجرام: https://t.me/fiqhalhajj ٢- برنامج السيرة النبوية، ومدته ثمانية أشهر تقريبا، ورابطه في التليجرام: https://t.me/alsseerah ልዩ የኢልም ጥቆማ ሁለት ልዩ እና በፋኢዳ የተሞሉ ጥልቅ ማብራርያ ያካተቱ ልዩ የኢልም ደርሶች የመጀመሪያው ፊቂሁ ሰላት ለ4 ወራት የሚቆይ ሁለተኛው ደሞ ሲረቱ ነበዊያ አረበኛ የምትችሉ እና እነዚህን ሁለት ደማቅ የኢልም ኮርሶችን መካፈል የምትፈልጉ ከላይ ያሉትን የቴሌግራም ቻናሎችን ተቀላቀሉ እያንዳንዱ ደርሶች እራሳቸውን የቻሉ ፈተና አላቸው ፈተናዎቹን ለሚያልፉ የምስክር ወረቀት ይሰጣል:: ደርሶቹ የሚሰጡት በታላቁ ሸይኻችን አብዱረዛቅ አል-በድር ነው:: ❗️ሙሉ ለሙሉ ከክፍያ ነፃ ነው❗️ https://t.me/Abbu_Abdillah

የየመን ሑሢ ሺዐዎች ባበል መንደብን እና ዙባብን ለቀው ሸሽተዋል። በየቦታው እየተንጠባጠቡ ነው። በሑሢ መስፋፋት ሲቦርቁ የነበሩ ኢስላማዊ ዐቂዳ የማይገዳቸው የሺዐ ፈረሶች ዜናውን ላይነግሯችሁ ይችላሉ ብዬ ነው። = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

​بسم الله الرحمن الرحيم ​ ታላቅ የትምህርት ብስራት ከ«ኢብኑ ዐብባስ» Online መድረሳ! ​እውቀት የልብ ብርሃን፣ የሕይወት መመሪያ ነው። የዲንዎን እውቀት በጥራትና በስርዓት ለመቅሰም ካለዎት ፍላጎት በመነሳት «ኢብኑ ዐብባስ» የኦንላይን መድረሳ አዲስ ትምህርት ይዞላችሁ ቀርቧል። ​📌 የኮርሱ ዝርዝር መረጃ፦ ➠ ​የሚቀራው ኪታብ፦ «መሳኢሉል ጃሂልያ» (مسائل الجاهلية) — በሸይኽ ሙሐመድ ብን ዐብደልወሃብ (ረሒመሁልላህ) ◈ ​አስተማሪ፦ ኡስታዝኸድርአሕመድአል-ኬሚሴሀፊዘሁሏህ ​📲 የምዝገባ አድራሻዎች እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት ፦ ​🔹 ለወንዶች፦ 👉 @Hussein_cod018 👉 @Yufa4 ​በሴቶች  ለመመዝገብእናበቂመረጃዎችንለማግኘት ፦ 🔹 ለሴቶች፦ 👉 @bint_Adem15 👉 @Riiche1 ​📖 «እውቀትን መፈለግ በምእመናን ላይ ግዴታ ነው!» ​💡 ቦታ ሳይሞላ በፍጥነት ይመዝገቡ፤ ለሌሎችም በማጋራት የእውቀት ጥሪውን ያድርሱ!

አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም ፊትን ለወንድ መግለጥ ~ አንዳንዴ ፊታቸውን ከባዳ ወንዶች የሚሸፍኑ እህቶቻችን እንዲገልጡ የሚገፋ ጫና ይገጥማቸዋል። ለምሳሌ ጥጋበኛ እጅ ላይ ወድቀው ካልገለጡ ለከባድ ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ። በመሰል ሁኔታዎች ላይ መግለጥ ይችላሉ? ወይስ ችግሩ የፈለገ ቢከፋ እምቢ ማለት አለባቸው? አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም የማይፈቀድ ነገር ይፈቀዳል። الضرورات تبيح المحظورات የሚለው የፊቅህ መርህ ጠንካራ መነሻ ያለውና የታወቀ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦ { لَا یُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ } አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም።" [አልበቀረህ: 286] በአስገዳጅ ሁኔታ ህይወትን ለማትረፍ በክት መብላት ይቻላል። ተጨባጭ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ የክህደት ንግግር በመናገርም ራስን ማትረፍ ይቻላል። { مَن كَ.فَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ إِیمَـٰنِهِۦۤ إِلَّا مَنۡ أُكۡرِهَ وَقَلۡبُهُۥ مُطۡمَىِٕنُّۢ بِٱلۡإِیمَـٰنِ } "ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ሁኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር።" [አነሕል: 106] ሌሎችም ጉዳዮች እንዲሁ ይታያሉ። የሙስሊሟ ለባዳ ወንዶች ፊቷን መግለጥም በዚሁ አግባብ የሚታይ ይሆናል። ይህንን መርህ በመንተራስ አስገዳጅ ጉዳይ ሲገጥም ጊዜ ሴት ልጅ ፊቷን መግለጥ እንደምትችል ዓሊሞች ይገልፃሉ። በዚህ ላይ በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል:- 1ኛ፦ በማጨት ጊዜ :- ይሄ ሐዲሦች የመጡበት እንዲሁም ኢጅማዕ ያለበት በመሆኑ ለብዙ ሰውም የሚሰወር ስላልመሰለኝ ለማሳጠር ያክል በዚሁ ልለፈው። 2ኛ፦ ለህክምና፦ ጉዳቱ ያለበት ክፍል ፊትም ሆነ ሌላ ክፍል መግለጥ ይቻላል። ከተቻለ ባል ወይም ሌላ መሕረም (ቅርብ ቤተሰብ) አብሮ መኖር አለበት። ባይሆን ሴት ሃኪም ካለ ወደ ወንድ፣ ሙስሊም ካለ ወደ ሌላ መሄድ አይገባም ይላሉ ዓሊሞች። ለህክምና በሚያስፈልገው መጠን ሃኪሙ አካሏን መመልከት ይችላል ይላሉ ኢብኑ ቁዳማ። [አልሙግኒ፡ 7/459] በነገራችን ላይ ጦር ሜዳ ላይ ሴቶች ሶሐቢያት ወንዶችን ያክሙ ነበር። ኡሙ ዐጢያህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦ غَزَوْتُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَبْعَ غَزَوَاتٍ أَخْلُفُهُمْ فِي رِحَالِهِمْ، فَأَصْنَعُ لَهُمُ الطَّعَامَ، وَأُدَاوِي الْجَرْحَى وَأَقُومُ عَلَى الْمَرْضَى "ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ሰባት ዘመቻዎችን ዘምቻለሁ። እቃዎቻቸውን እጠብቅ፣ ምግባቸውን አዘጋጅ፣ ቁስለኞችን አክም እንዲሁም ህመምተኞችን እንከባከብ ነበር።" [ሙስሊም፡ 1812] የቡኻሪን باب هل يداوي الرجل المرأة، والمرأة الرجل እንዲሁም ዘርዘር ያለ ነገር የፈለገ ፈትሑል ባሪን መመልከትም ይቻላል። 3ኛ፦ ችሎት ላይ፦ በፍርድ ችሎት ላይ ፍርድ ለመስጠት ዳኛው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ፊቷን ይመለከታል። ካልሆነ ሐቅን ማስከበር አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል። ምስክር ሆና ስትቀርብ ወይም በሷ ላይ ምስክርነት ለመስጠትም እንዲሁ መገለጥ ግዴታ ሊሆን ይቻላል። ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ይላሉ፦ وللشاهد النظر إلى وجه المشهود عليها لتكون الشهادة واقعة على عينها، قال أحمد: لا يشهد على امرأة إلا أن يكون قد عرفها بعينها "መስካሪ ሰው ምስክርነቱ ቦታው ላይ ያረፈ ይሆን ዘንድ የሚመሰከርባትን ሴት ሊመለከት ይችላል። (ኢማሙ) አሕመድ 'በትክክል ለይቶ እስካላወቃት ድረስ አንዲት ሴት ላይ አይመሰክርም' ብለዋል።" [አልሙግኒ፡ 7/459] ይሄ የሳቸው ሃሳብ ብቻ አይደለም። ሌሎችም "ኒቃብ በለበሰች ሴት ላይ ፊቷን ሳትገለጥ መመስከር አይቻልም" ይላሉ። [አሸርሑል ከቢር፣ ደርዲር፡ 4194] 4ኛ፦ በግብይት ላይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሻጭ ወንድ ገዢዋን ሴት ሊመለከት እንደሚችል ዑለማኦች ይገልፃሉ። [አልሙግኒ፡ 7/459] ያለበለዚያ በግብይቱ ላይ ለተፈጠረ ክፍተት ማስተካከያ ለማድረግ ሊቸገር ይችላል። ለምሳሌ እቃ ሽጦላት ፊቷን ካላየ ኋላ ላይ እቃው ችግር ኖሮበት መመለስ ቢያስፈልግ በትክክል እሷ መሆኗን መለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። 5ኛ፦ አስገዳጅ ህግ ባለበት ሁኔታ፦ በአንዳንድ ሃገራት ህግ ወይም ኤርፖርት አካባቢ ወይም ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመም ፊቷን መግለጥ ትችላለች። ለምሳሌ በመጥፎ ሰዎች እጅ ላይ ወድቃ ራሷን አደጋ ላይ ከምትጥል ፊቷን በመግለጥ ራሷን ማትረፍ ትችላለች። "አስገዳጅ ሁኔታዎች የተከለከለን ነገር ያስፈቅዳሉ።" ስለዚህ ማንነቷን ለመለየት የሚጠይቅ አስገዳጅ ሁኔታ ቢገጥም ወይም ሌላ ተጨባጭ ምክንያት ከኖረ ፊቷን መግለጥ ትችላለች ማለት ነው። ይሄ እንግዲህ ከዑለማኦች አቋም ውስጥ ለደረሰች ሴት ልጅ ፊትን መሸፈን ግዴታ ነው የሚለውን ስንወስድ ነው። የሆነ ሆኖ ጫን ያለ ሁኔታ ካልገጠማት በስተቀር ለትንሽ ለትልቁ እጅ ልትሰጥ አይገባም። ፍተሻና መሰል ቦታዎች ላይ ሴቶችን መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ ካለ ወይም ደግሞ ጉዳዩ አንገብጋቢ ካልሆነ ባዳ ለሆኑ ወንዶች ፊትን መግለጥ አይገባም። አስገዳጅ ችግር ሲገጥም ደግሞ ጉዳዩን በችግሩ መጠን ብቻ ማስተናገድ ይገባል። "አስገዳጅ ሁኔታዎች በልካቸው ነው የሚስተናገዱት።" እንጂ ችግሩን ማመሀኛ አድርጎ አጉል መዘናጋት ውስጥ መግባት አይገባም። #ወላሁ_ አዕለም። = (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 01/2017) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ችግሮችን አትጥሉ፣ ተግዳሮቶችን አትፍሩ፡፡ ለዉድቀት ሁሉ አሉታዊ ትርጉም አትስጡ፡፡ከማይመቹ ነገሮች አዳዲስ ነገር ይወለዳሉ፡፡ ጨለማ ባይኖር ኖሮ መብራት ለመፍጠር ማን ይጥር ነበር?፡፡ ጎረቤቶቻችን
ችግሮችን አትጥሉ፣ ተግዳሮቶችን አትፍሩ፡፡ ለዉድቀት ሁሉ አሉታዊ ትርጉም አትስጡ፡፡ከማይመቹ ነገሮች አዳዲስ ነገር ይወለዳሉ፡፡ ጨለማ ባይኖር ኖሮ መብራት ለመፍጠር ማን ይጥር ነበር?፡፡ ጎረቤቶቻችን ዕቃ ባይከለክሉን ዕቃ አንገዛም ነበር፡፡ አከራዮች የቤት ኪራይ ባይጨምሩብን የራሣችን ቤት አንሠራም ነበር..፡፡ አዎ! ለችግራችን መፍትሄው ያለው ችግሩ አጠገብ ነውና ዙሪያችሁን ቃኙ፡፡

ምናልባት ከእናንተ የምርቅበት፣ ድምፄ ዝምታን የሚመርጥበትና ፅሁፎቼም እንደ ቀደመው ወደ እናንተ መድረስ የሚያቆሙበት ወቅት ቢመጣ… ከራሴ ነፍስና ከጊዜ እጥረት ጋር በብርቱ እየታገልኩ መሆኑን እወቁልኝ። አንድ ቀን ስሜ ቢጠፋችሁ፣ የፃፍኩት ሁሉ ቢረሳ እንኳ፤ እጆቻችሁን ወደ ሰማይ ዘርግታችሁ ከ አላህ ጋር በምትገናኙበት በዚያ የዱዓ ሰዓት፣ በልባችሁ ጥግ ላይ ይህንን ደካማና ወንጀለኛ ባሪያ ቅንጣት  ታክልም ብትሆን አስታውሱኝ። ያቺን ያበረከትኳትን ትንሽ ጥረቴን አላህ በራህመቱ እንዲቀበለኝ፣ ጉድለቴንና ወንጀሌን በይቅርታው ሸፍኖ ቀልቤን እንዲያበጅልኝ፣ በውስጤ የቋጠርኳቸውን መልካም ምኞቶች ሁሉ እንዲያሳካልኝ ከአንጀታችሁ ዱዓ አድርጉልኝ። በዚህች አላፊ ዓለም ውስጥ ለእኔ ከዚህ የላቀ ውድ ስንቅ የለምና… ሁሌም በኸይር አስቡኝ።

እውነት ለማናገር ደረስነት ማለት ቀላል ሂወትን አያስተናግድም እውቀትም ትንሽም ይሁን ብዙ በቀላል አይመጣም ይሄ የምታውት ቀልዲና ዝም ብሎም ለቲክቶክ  የተሰራ አይደለም ወላሂ ወቢላህ እኔ እራሴ በሰፈር ሂወቴ አሳልፌዋለሁ ተጠቅሜዋለሁ ሙሉ እንጀራው ደረቅ ሲሆን በርበሬ በመነስነስ በውሀ ተፈትፍቶ ነው የሚበላው በሰአቱ በጣም ይጣፍጣል ለእውቀት መሰዋትነት ከፈሉ መማር መታደል ነው በቦታው ያላችሁ ሙሳፊሯች ፅኑ እኔ ዛሬ እሚቆጨኝ ይሄን መብላቴ ሳይሆን ይሄን እየበላሁ በዛው ቆይቸ ተምሬ በሆን ብየነው። ከ7አመት በላይ ሰፈር ቆይቻለሁ ምናል በቀላሉ 7 ጨምሬ ቢሆን እላለሁ ለንጀራው አይደለም ለትምህርቱ!! https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf

(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። ራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም። "ራስን በሱስ በመጉዳትና ራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።" (13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል። "የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።" (14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ። "የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።" (15) የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ ሁን። የሶላትና የጥናት ጊዜህን የሚበላ፣ አሰተሳሰብህን የሚበክል፣ መጥፎ ምስሎችን ከመመልከት ሱስ የሚያጣብቅ እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። ማህበራዊ መገናኛዎችም ሱስ እንዳይሆኑብህ ተጠንቀቅ። ብትችል ቲክቶክ ከሚሉት ጥሩ ያልሆነ ሰፈር ከነጭራሹ ብትርቅ መልካም ነው። አጠቃላይ ከኢንተርኔት ጋር ያለህ ትስስር የሚያንፅህ እንጂ የሚያጠፋህ እንዳይሆን ደጋግመህ አስብበት። ሰላም! = (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor

ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች ~ ትምህርት እየተጀመረ ነው። ፈተና ሲደርስ መደናበር ወይም የአመቱ መጨረሻ ላይ ውጤትን ጭንቅ ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቁንም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከቀን አንድ ጀምረው በቁም ነገር መዘጋጀት ነው የሚያዋጣው። ከልቡ የተዘጋጀ ሰው በአላህ ፈቃድ የልፋቱን አያጣም። ጥሮ ግሮ ውጤት ባይመጣ እንኳ ሰበብ ያደረሰ ሰው የሚጠበቅበትን ተወጥቷል። ይህን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ለተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ስብእና እንዲኖራቸው ያግዛሉ ያልኳቸውን የተወሰኑ ነጥቦት እንደሚከተለው አስፍሬያለሁና በማሰራጨት ብታግዙኝ ደስ ይለኛል። ① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ። "አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።" "ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።" ② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚጎድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የኮፒ፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ። ③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ለዘር ተኮር ቀልዶች ጥርስህን አታሳይ። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው። "ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።" ④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው። "ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።" ⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ ራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ተረዳ። "Education is a better safeguard of liberty than a standing army." ⑥ ራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ። አንተ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም። "ራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።" ⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሃብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል። እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮችን ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው። "ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።" "አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ ራስህ እያለፍክ ነው።" ⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ ራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ። "ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።" ⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ። ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ። "ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።" (10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ ቴኳንዶ፣ የእጅ ሙያዎች፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ። "ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።" (11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን። "ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።" "ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"

👉#በዘርህ ከማንም በላይ ከማንም በታች አይደለህም። ኡስታዝ ሙሐመድ አህመድ ሙነወር(ኢብኑ ሙነወር) አላህ ይጠብቀው = የቴሌግራም ቻናል፦ @IbnuMunewor https://t.me/DeewaSelefyya1448 https://t.me/DeewaSelefyya1448.

👉#በዘርህ ከማንም በላይ ከማንም በታች አይደለህም። ኡስታዝ ሙሐመድ አህመድ ሙነወር(ኢብኑ ሙነወር) አላህ ይጠብቀው = የቴሌግራም ቻናል፦ @IbnuMunewor https://t.me/DeewaSeleffya1448 https://t.me/DeewaSeleffya1448.

🌿 النص العربي قالت أعرابية لرجل: مالك تعطي ولا تعد؟ قال: مالك والوعد؟ قالت: ينفسح به البصر، وينتشر فيه الأمل، وتطيب بذكره النفوس، ويرخى به العيش، وتكتسب به المودات، ويربح به المدح والوفاء. الخلق عيال الله، فأحبهم إليه أنفعهم لعياله. أولى الناس بالعفو أقدرهم على العقوبة. النساء حبائل الشيطان. عند الشدائد تعرف الإخوان. هون البلايا بالصبر. الخطايا تظلم القلب. القرى إكرام الضيف. الداعي إلى الخير كفاعله. الظلم ظلمات يوم القيامة. 🌿قالت أعرابية لرجل: مالك تعطي ولا تعد؟ አንዲት የበረሃ አረብ ሴት አንድን ሰው፦ «ለምን ትሰጣለህ እንጂ ቃል ኪዳን አትገባም?» ብላ ጠየቀችው። 🌿قال: مالك والوعد؟ እርሱም፦ «ቃል ኪዳን ምን ይጠቅማል?» አላት። 🌿قالت: ينفسح به البصر «ቃል ኪዳን ተስፋን ያሰፋል፤ ሰው ወደ ፊት በተስፋ እንዲመለከት ያደርገዋል።» 🌿وينتشر فيه الأمل «ተስፋም በልብ ውስጥ ይስፋፋል።» 🌿وتطيب بذكره النفوس «ቃል ኪዳን ሲታወስ ልቦች ይደሰታሉ።» 🌿ويرخى به العيش «ኑሮም ይቀላል፣ ሰውም እረፍት ያገኛል።» 🌿وتكتسب به المودات «በቃል ኪዳን ምክንያት ፍቅርና ወዳጅነት ይገኛል።» 🌿ويربح به المدح والوفاء «በእርሱም ምስጋናና ታማኝነት ይገኛል።» 🌿الخلق عيال الله، فأحبهم إليه أنفعهم لعياله. ሰዎች ሁሉ የአላህ ፍጥረቶች ናቸው፤ ከእነርሱም አላህ ዘንድ በጣም የሚወደው ለሌሎች ጥቅም የሚያደርስ ሰው ነው። 🌿أولى الناس بالعفو أقدرهم على العقوبة. ይቅርታን በጣም የሚገባው፣ ቅጣት ማድረግ የሚችል ሆኖ ይቅር የሚል ሰው ነው። 🌿النساء حبائل الشيطان. ሴቶች ለሰው ልጅ ፈተና ሊሆኑ ይችላሉ፤ ስለዚህ ከሐራም መንገድ መጠንቀቅ ይገባል። 🌿عند الشدائد تعرف الإخوان. ችግርና መከራ ሲመጣ እውነተኛ ወንድማማቾችና ጓደኞች ይታወቃሉ። 🌿هون البلايا بالصبر. መከራን በትዕግሥት መቀበል ክብደቱን ያቀልላል። 🌿الخطايا تظلم القلب. ኃጢአቶች ልብን ያጨልማሉ፣ ከአላህም ያርቃሉ። 🌿القرى إكرام الضيف.   እንግዳን መቀበልና ምግብ ማብላት  እንግዳን ማክበር ነው። 🌿الداعي إلى الخير كفاعله. ወደ መልካም ሥራ የሚጠራ ሰው፣ ያንን መልካም ሥራ እንደሠራው ምንዳ ያገኛል። 🌿الظلم ظلمات يوم القيامة. በዓለም ላይ የሚደረግ ግፍና በደል በትንሣኤ ቀን ለባለቤቱ ጨለማዎች ይሆናል። 🤲 اللهم علّمنا ما ينفعنا، وانفعنا بما علّمتنا، واجعلنا مفاتيح للخير، مغاليق للشر، وانفع بنا عبادك. አላህ ሆይ! የሚጠቅመንን እውቀት አስተምረን፤ ያስተማርከንንም እውቀት ጠቃሚ አድርግልን፤ ለመልካም መክፈቻዎች፣ ለክፉ መዝጊያዎች አድርገን፤ በእኛም ባሮችህን ጠቃሚ አድርግ። አሚን። 🌿 من كلام الحكماء: كلمةٌ طيبةٌ قد تفتح قلبًا، ووعدٌ صادقٌ قد يزرع أملًا، وعملٌ صالحٌ قد ينفع إنسانًا. https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

ተክፊሮችን ተጠንቀቋቸው! ከሸይኽ ፈውዛን በርካታ ንግግሮች፡ 👉 ከቢድዓ ስዎች የከፉ እነርሱ ተክፊሮች ናቸው። 👉 ከአላህ ውጭ ያለን ለእገዛ የሚጣራ (መደድ የሚል)  መረጃ ሳይብራራለት አይከፍርም። ኡዝር_ቢልጀህል_አለ። የሙስጤዎቹ አዲሶቹ ተክፊሮች ሙቀት ላይ ስለሆኑ በእርጋታ አይሰሙም እንጂ ጉዳዩ በብዙ ዑለማዎች ፍንትው ብሎ ተብራርቷል። ሙቀቱ ሲበርድላቸው ይሰሙት ይሆናል ኢንሻአላህ። https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

Repost from N/a
ሀራም መመገብ ጉዳቱ 🎙በኡስታዝ አረቡ ሰዒድ 🕌በደገር ከተማ መስጂድ ሰላም   ላይ የተደረገ_መሳጭ ነሲሀ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea

የባልን የሞት ዜና ለሚስት በብልሃት የማድረስ ምርጥ ዘዴ በአንዲት መንደር ውስጥ "ሙቅቢል" የሚባል ሰው ነበር የአላህ ውሳኔ ሆነና በድገት ሞተ። ጎረቤቶቹ መሞቱን ሲያረጋግጡ አጠቡት ከፈኑት ከዚያም ሬሳውን በሳጥን ተሸክመው ወደ ቤቱ ወሰዱት፤ ግን በሩ ላይ ቆመው እየፈሩና እየተጨነቁ፡ "የባሏን መሞት ለሚስቱ ሳናስደነግጣት እንዴት ብለን እንንገራት?" ተባባሉ። ድንገት ነው የሞተው እንደት ሳናስደነግጥ እናስረዳት በማለት ግራ ገብቷቸው እያለ ​አንዱ ቀረብ ብሎ በሙሉ እምነት፡ "ነገሩን ለእኔ ተዉልኝ፤ እኔ ከሴቶች ጋር እንዴት እንደሚወራ አውቃለሁ" አለ። ​ከዚያ "ሳጥኑን ይዛችሁ ከቤት በስተጀርባ ተሸሸጉ፤ እኔ ስጠራችሁ ወዲያው አምጡት" አላቸው። ​ሰውዬው ሄዶ በሩን አንኳኳ፤ ሚስቲቱም ማነው ብላ በሩን ከፈተች፡ "ሰላም ነው? ሰውየውም አንች የሙቅቢል ሚስት ነሽ ብሎ ጠየቃት ? እሷም አወ ምነው በባሌ ላይ የተፈጠረ ነገር አለእንዴ?" አለችው። ​ሰውዬው በተረጋጋ መንፈስ፡ "አይዞሽ፣ ምንም መጥፎ ነገር አልሆነም.. ግን ባልሽ ሙቅቢል ባንች ላይ ሌላ ሚስት አገባ!" አላት። ​ሚስቲቱም በቁጣ አብዳ መርገም ጀመረች፡ "በእኔ ላይ ሌላ አገባ?!⁉️ 1️⃣አምላክ ይበቀለው! 2️⃣እልም አላህ ያርገው 3️⃣በጁሱ መርዝ እምታጠጣ ይስጠው እያለች ተራገመች ​ከዚያም ሰውዬው ዞር ብሎ "እልል በይ! አላህ ዱአሽን ተቀብሎሻል ሰምቶሻል!.. አምጡት ወጣቶች!" ብሎ ጮኸ። ​ወጣቶቹ ሳጥኑን አምጥተው ፊቷ አስቀመጡት። ሚስቲቱም ሳጥኑን አይታ ረጋ ባለ ድምፅ፡ "አላህ ይማረው፣ ይህ የአላህ ውሳኔና ፍቃድ ነው.. ዋናው ነገር በእኔ ላይ ሌላ አለማግባቱ ነው!" አለች። ክክክ copy

የማለዳ መልእክት (51) ~ ቢድዐዎች መጠናቸው ይለያያል። 1. አንዳንዶቹ በመሰረታዊ ኢዕቲቃድ ላይ የተከሰቱ ከባባድ ቢድዐዎች (بدع اعتقادية كبرى) ናቸው። ለምሳሌ የጀህሚያ፣ የሙዕተዚላ፣ የአሻዒራ እና መሰል ቢድዐዎች። 2. ሌሎች ደግሞ በዒባዳዎች ውስጥ የሚከሰቱ (بدع عملية) ናቸው። ይሄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ነው። እንጂ መሀል ላይ ብዙ የተራራቁ የቢድዐ መጠኖች አሉ። በአንድ ምድብ ውስጥ ያሉ ቢድዐዎች ራሱ መጠናቸው በጣም ይራራቃል። ለምሳሌ የጀህሚያ ቢድዐ ከአሽዐሪያ በጣም የከፋ ነው። "አላህ ከፍጡሩ ጋር ተዋህዷል" ወይም "ሰፍሯል" የሚለው እንደነ ሐላጅ፣ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑል ፋሪድ፣ ዐፊፉ ቲልሚሳኒይ፣ ኢብኑ ሰብዒን፣ ... ያሉ ሱፍዮች ቢድዐ ክብደቱ እንግዳ ዒባዳዎችን ወይም የዒባዳ አፈፃፀሞችን ካመጡ አካላት ቢድዐ በጣም የከፋ ነው። የሁለተኞቹ ክፍሎች ቢድዐ ከመጀመሪያዎቹ በንፅፅር በጣም ያነሰ ነው። የመጀመሪያዎቹ ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ ነው። ይህንን መለየታችን 1ኛ፦ ጥፋቶችን የክብደታቸውን መጠን እንድንለይ ያግዘናል። 2ኛ፦ በዚሁ መሰረትም ለአጥፊዎቹ የሚኖረን አቋምና አያያዛችንም ይለያያል። መቼስ በሁሉም ላይ ያለን አቋም እንደ ሳሙና አንድ ቁርጥ ሊሆን አይችልም። 2 ኛ፦ ቢድዐ ከወንጀል የከፋ እንደሆነ የሚጠቁሙ የቀደምት ዑለማኦችን ንግግሮች ያላግባብ እንዳንረዳም ያግዘናል። እንደ ዝሙት፣ ነፍስ ማጥፋት፣ ወለድ (አራጣ) መብላት፣ ... ያሉ ከባባድ ወንጀሎች (کبائر الذنوب) ከተወሰኑት የቢድዐ አይነቶች (بدع عملية) ያነሱ አይደሉም፣ የከበዱ እንጂ። በመሰረታዊ ዐቂዳ ላይ የመጡ ከባባድ ቢድዐዎች ደግሞ ከተዘረዘሩት ከባባድ ወንጀሎች (کبائر الذنوب) በጣም የከፉ እንጂ ያነሱ ጥፋቶች አይደሉም። እና የቢድዐን አደጋ ለማጉላት የምናደርገው "ቢድዐ ከወንጀል የከፋ ነው" የሚለው ገለፃ ባላሰብነው አቅጣጫ እነዚህን ወንጀሎች አቅልሎ እንዳያሳይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ወላሁ አዕለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 24/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

የተጠናቀቀ የመንሀጁ ሳሊኪን ኪታብ ደርስ ~ ከክፍል 1 - 61 = ክፍል __ 1 t.me/IbnuMunewor/4756 ክፍል __ 2 t.me/IbnuMunewor/4833 ክፍል ___ 3 t.me/IbnuMunewor/4884 ክፍል __ 4 t.me/IbnuMunewor/4888 ክፍል __ 5 t.me/IbnuMunewor/4914 ክፍል __ 6 t.me/IbnuMunewor/4934 ክፍል __ 7 t.me/IbnuMunewor/4955 ክፍል __ 8 t.me/IbnuMunewor/4975 ክፍል __ 9 t.me/IbnuMunewor/4992 ክፍል __10 t.me/IbnuMunewor/5036 ክፍል __11 t.me/IbnuMunewor/5052 ክፍል __ 12 t.me/IbnuMunewor/5077 ክፍል __ 13 t.me/IbnuMunewor/5173 ክፍል __ 14 t.me/IbnuMunewor/5173 ክፍል __ 15 t.me/IbnuMunewor/5238 ክፍል __ 16 t.me/IbnuMunewor/5274 ክፍል __ 17 t.me/IbnuMunewor/5357 ክፍል __ 18 t.me/IbnuMunewor/5376 ክፍል __ 19 t.me/IbnuMunewor/5670 ክፍል __ 20 t.me/IbnuMunewor/5672 ክፍል __ 21 t.me/IbnuMunewor/5703 ክፍል __ 22 t.me/IbnuMunewor/5767 ክፍል __ 23 t.me/IbnuMunewor/5771 ክፍል __ 24 t.me/IbnuMunewor/5811 ክፍል __ 25 t.me/IbnuMunewor/5872 ክፍል __ 26 t.me/IbnuMunewor/5873 ክፍል __ 27 t.me/IbnuMunewor/5899 ክፍል __ 28 t.me/IbnuMunewor/5969 ክፍል __ 29 t.me/IbnuMunewor/6058 ክፍል __ 30 t.me/IbnuMunewor/6156 ክፍል __ 31 t.me/IbnuMunewor/6157 ክፍል __ 32 t.me/IbnuMunewor/6218 ክፍል __ 33 t.me/IbnuMunewor/6238 ክፍል __ 34 t.me/IbnuMunewor/6275 ክፍል __ 35 t.me/IbnuMunewor/6424 ክፍል __ 36 t.me/IbnuMunewor/6492 ክፍል __ 37 t.me/IbnuMunewor/6525 ክፍል __ 38 t.me/IbnuMunewor/6577 ክፍል __ 39 t.me/IbnuMunewor/6666 ክፍል __ 40 t.me/IbnuMunewor/6669 ክፍል __ 41 t.me/IbnuMunewor/6713 ክፍል __ 42 t.me/IbnuMunewor/6786 ክፍል __ 43 t.me/IbnuMunewor/6789 ክፍል __ 44 t.me/IbnuMunewor/6946 ክፍል __ 45 t.me/IbnuMunewor/6983 ክፍል __ 46 t.me/IbnuMunewor/7073 ክፍል __ 47 t.me/IbnuMunewor/7077 ክፍል __ 48 t.me/IbnuMunewor/7503 ክፍል __ 49 t.me/IbnuMunewor/7590 ክፍል __ 50 t.me/IbnuMunewor/7656 ክፍል __ 51 t.me/IbnuMunewor/9706 ክፍል __ 52 t.me/IbnuMunewor/9713 ክፍል __ 53 t.me/IbnuMunewor/9727 ክፍል __ 54 t.me/IbnuMunewor/9765 ክፍል __ 55 t.me/IbnuMunewor/9811 ክፍል __ 56 t.me/IbnuMunewor/9843 ክፍል __ 57 t.me/IbnuMunewor/9920 ክፍል __ 58 t.me/IbnuMunewor/10013 ክፍል __ 59 t.me/IbnuMunewor/10147 ክፍል __ 60 t.me/IbnuMunewor/10150 ክፍል __ 61 t.me/IbnuMunewor/10249